Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

TEAM HUDA

Description
"أَفَلَا تَعْقِلُونَ"
"አታስተነትኑምን?"

አንብቡ! ራሳችሁን፣ በዙሪያችሁ ያሉትን ነገሮች፣ ሌሎች ሰዎችን፣ ፅሁፎችን.... አንብቡ! አስተንትኑ! ጠይቁ!

Big thanks for joining!

All team huda!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

5 days ago

ጥቋቁር ገፆች
(ከገሃዱ አለም ታሪክ-ለትውስታ)
.
"ህይወት ትውስታ ናት፤
ከተረሳህ ትሞታለህ
"
.
.
<< <ብዙ ቀን ተማሪዎቼን በደንብ ያላስተማርኳቸው ሲመስለኝ ህሊናዬ አያርፍም እንደምልሽ አስታወስሽ?.... በዛ ሁሉ ጨለማ ህይወትና አሁን የምኖረው ህይወት መሃል ያለው ብቸኛ ልዩነት.... ብቸኛ የደስታ ጭማሪ ህሊናዬ ማረፉ ስለሆነ ነው። እነሱ የሆነ ነገር ሲማሩ.... እንኳንም ያንን ሁሉ አለፍኩት፤ እንኳንም እዚ ጋር ለመቆም ታገልኩ እላለሁ። የመጀመሪያ ብዙ የምለውን ገንዘብ መቀበል የጀመርኩት እዚ ጊቢ ስገባ ነው.... ግን ከህሊናዬ ሰላም ውጪ የትኛውም ገንዘብ በየቀኑ ለማወጣው ጥረት የሚመጥን ሆኖ አይደለም የምቀጥለው። መምህር መሆን ቀላል አይደለም.... በየምሽቱ ለቀጣዩ ቀን መዘጋጀት ይጠይቃል። እኔን ስትሆኚ ደግሞ.... በየምሽቱ እንዴት ሰው ፊት እንደምትስቂ፣ እንዴት የራስሽን ችግር ለራስሽ ደብቀሽ ደስተኛና ባለ ተስፋ እንደምትመስዪ ማስመሰልንም ጭምር መለማመድ ይጠይቃል ምክኒያቱም ወትሮውን ደስተኛና ተግባቢ መሆን ቀርቶ የመኖር ተስፋ ያለው ሰው አይደለሁም።

.... የአእምሮ እጢ በሽተኛ ነኝ። አልጠበቅሽም አይደል? አንዳንዴ ክፉኛ ይነስረኛል.... ሀኪሞች በተኛህበት ደም አፍኖህ ልትሞት ትችላለህ እሰኪሉኝ ድረስ አደገኛ እጢ አለብኝ። ይድናል ወይ? አይድንም። እጢ እንዳለብኝ ያወኩት በ 14 አመቴ ነበር.... እሱም ነስር ሲበዛብኝ ሀኪም ቤት ራሴ ሄጄ በተመረመርኩ ጊዜ። የ 14 አመት ልጅ፣ መድሃኒት እንዴት እንደምገዛ.... ቀጠሮ እንዴት እንደምይዝ ምናምን ገና በወጉ ሳላውቀው ከፊቴ የተቀመጠው ዶክተር "ልትሞት ነው" ይለኛል። ለዚህኛው ግድ የለሽነታቸው ወላጆቼን መቼም ይቅር አልላቸውም። ተገደው ሊሆን ይችላል ለኔ ግድ ያልነበራቸው ግን.... እኔንጃ፤ ከዚ በኋላ ይቅር የሚል ልብ የለኝም። ዶክተሮች.... ወይ ደስተኛ በመሆን እድሜህን ታራዝማለህ፣ ወይ ራስህን በማስጨነቅና በመጠበብ ሞትህን ታፋጥናለህ ብለውኛል... ተፈልጎ የሚታዘን ይመስል። ብቸኛ ደስተኛ ቦታዬ ግን ይሄ ነው። በህይወቴ የፈለኩት አንድ ነገር.... "ጎበዝ!" መባል ነበር፤ ከወላጆቼ ለሰራሁት አንድ ነገር እንኳን ማበረታቻ ማየት.... ግን አልሆነም። እስካሁንም ካለኝ ነገር ላይ መስዋትነት በመክፈል ላይ ብቻ ነኝ። ግን እዚ መጥቼ ተማሪዎቼ "እንወድሃለን.... ገብቶናል" ሲሉኝ ለኔ ከዚ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ የቤተሰብነት ስሜት ይሰማኛል። ሁሌ "ደስተኛ ናቹ? ወዳቹኛል? ትንሽ ነገርም ቢሆን ገብቷቿል?" እያልኩ ማጨናንቃቸው ለዚ ነው። ተጨማሪ አንድ ቀን ለመኖር። ከንግዲህ ልሄድ ነው... ከ 1 ወር በኋላ.... ይሄን ሁሉ የማስረዳሽም ስለምሄድ ለውጥ አያመጣም በሚል ከጠቀመሽ ነው> >>

የንግግራችን ማብቂያ ባይሆንም ጭብጡ ነበር። ከዚ በኋላ እንደማልረሳውና.... ለራሱ ባይሆንም ለሌሎች ከተሞክሮው ትምህርት እንዲሆን መኖር እንዲቀጥል መነጋገራችንን አስታውሳለሁ-ከአመት በፊት። ከ800 በላይ መፅሀፎች አሉት.... "ረሀቤን ለማስታገስ ስል መፅሃፎቼን ሽጫለሁ" ሲል ከቀመሳቸው ክፉ ቀናቶች ሁሉ ይሄኛው እንደመረረው ፊቱ ላይ ይንፀባረቅ ነበር። ለዛም መሰለኝ ለኔ ለማስታወሻነት መፅሀፍ መስጠቱን የመረጠው። ውስጡ የተፃፈበት ትንሽ ማስታወሻ "በዚች ምድር ላይ ማንኛውም ጥቁረት፤ ነጩ ልብሽን እንዳያቆሽሸው ከመመኘት ጋር"... ከሚል ፅሁፍ ስር "ህይወት ትውስታ ናት፤ ከተረሳህ ትሞታለህ" የሚል ጥቅስ የታከለበት ነበር። የሚሞተው በእጢ የተመረዘ አካል ሲቀበር ሳይሆን ከትውስታ የተፋቀ ትዝታ ሲደመሰስ ነው ማለቱ ነው። እኔም ሁሌም በህይወት ይኖር ዘንድ ያካፈለኝን ቁምነገሮች ከወረቀት አሰፈርኩ...
.
.
ተፈፀመ

@Re_Ya_Zan

6 days ago

ጥቋቁር ገፆች
(ከገሃዱ አለም ታሪክ-ለትውስታ)
.
"ህይወት ትውስታ ናት፤
ከተረሳህ ትሞታለህ
"
.
.
< <ሆድህን በማትሞላበት ቦታ መራብህን ግልፅ አታድርግ> የሚል አባባል አለ። እኔም ስኖር የምከተለው ያንን መርህ ነበር። እቸገራለሁ.... ግን መቸገሬን ለማይረዱኝ ሰዎች ግልፅ አድርጌ አዘኔታቸውን ማየት አልፈልግም። መሰናዶ እየነበርን ለተማሪዎች የሚሰጥ ልዩ ክለብ ተጀመረ.... ግን በክፍያ ስለሆነ መሳተፍ አልችልም። ተማሪዎች በየቀኑ እየተማሩ እየመጡ ይሄን ያህል ጥያቄ ሰራን ይሄን ያህል ተሻሻልን ሲሉ እቀና ነበር። ለወራት ከተማሩ በኋላ አበቃና በቀጣዩ መንፈቅ ድጋሚ ተጀመረ.... ለቀጣዩ ግን ገንዘቤን አጠራቅሜ ተሳተፍኩ። በ 3 ሳምንት ውስጥ ቀድመውም ሲማሩ ከነበሩት የተሻለ ውጤት አመጣሁ። በመሰናዶው ማብቂያ ያንን ኮርስ ረዘም ላለ ጊዜ ብወስድ የህግ ት/ቤት መግባት እችል እንደነበር መምህራኖቼ ነገሩኝ። አማራጭ ስላልነበረኝ እና ሰልችቶኝ ስለነበር ገንዘብ ስላልነበረኝ እንደሆነ ነገርኳቸው። ቀደም ብዬ ብናገር ት/ቤቱ እርዳታ ያደርግልኝ እንደነበር ነገሩኝ.... ግን እንዳልኩሽ ነው.... ሰዎች ብትነግረን ኖሮ እንረዳሃለን ይበሉ እንጂ ህይወቴን የሚቀይር ለውጥ ሊያደርጉልኝ አይችሉም ነበር። ብዙ አዋቂ ባለባት ምድር ራሴን ራሴ እየሰራሁ ነው ያስተማርኩት.... ያልሰራሁት ስራ የለም። ጠዋት ጠዋት እና ከሰአት የከብቶችን አዛባ እየዛቅኩ አስከመማር ድረስ። ለመፅሀፍቶቼ ገንዘብ ለማጠራቀም ስል የትኬት ገንዘቤን ሰስቼ ባረጁ ጫማዎቼ ረጃጅም ጉዞዎችን እስከመመላለስ ድረስ። ከሁሉም የማልረሳው የሆነበት 2 ብር ይሰጣል ተብዬ በከንቱ ተሯሩጬ ሄጃለሁ። ግን እምልልሻለሁ.... ዛሬ ላይ ብዙ ሺ ገንዘብ ማግኘት ያኔ ከማገኛቸው ጥርቃሚ ሳንቲሞች የተሻለ ረፍት አላስገኘልኝም።> >>
.
.
የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል...

@Re_Ya_Zan

1 week ago

ጥቋቁር ገፆች
(ከገሃዱ አለም ታሪክ-ለትውስታ)
.
"ህይወት ትውስታ ናት፤
ከተረሳህ ትሞታለህ
"
.
.
<< <.....ትምህርት ቤት ስማር ምንም አልነበረኝም። ምንም.... ከምመገበውን ምግብ ጀምሮ እስከ መማሪያ ቁሳቁስ ድረስ። ከቤተሰብ በቀን 50 ሳንቲም ይሰጠኝ ነበር.... አልፈርድም፤ አልቀየምም። ከጠዋት እስከማታ ከሚሰራ ቤተሰብ ለኔ ሊሰጡኝ የሚችሉት ብቸኛው ነገር ነበር። በዛች ሳንቲም አንድ ዳቦ ጠዋት ላይ መግዛት እችላለሁ። ግን ደግሞ ለት/ቤት መፅሃፎቼንም መግዛት ስላለብኝ ነፍሴ ማጠራቀምንም ሹክ ይለኛል። በተለይ ደግሞ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት በምንዘጋጅባቸው ጊዜያት የማጠናበት ምንም መፅሃፍ አልነበረኝም። ሳይኮሎጂ
<ሰዎች ሲያድጉ ያለማቋረጥ ደጋግመው የሚገዙት ልጅ ሆነው የተከለከሉትን ነው> ይላል። የኔም የመፅሃፍ ፍቅሬ ከዚ የእጅ ማጠር ስሜት የተወለደ ይመስለኛል።

....አስታውሳለሁ... አንድ አዲስ የሚጠናበት መፅሃፍ ሲመጣ "ስሙን ልየው.... እስኪ ምን አይነት ነው" ብዬ እወስደውና ሌላ ክፍል ቶሎ ቶሎ ውስጡ ያሉ ጥያቄዎችን እሰራ ነበር። የመማር ፍቅሬ ያን ያህል ነው። ከማልረሳው .... አንድ ጓደኛ ነበረኝ፤ የቲም ነው። ከትምህርት ቤታችን የየቲሞች መርጃ ማዕከል ለቁርስ ሁለት ዳቦና አንድ ሻይ ይቀርብለት ነበር። ከለታት አንድ ቀን ወደኔ መጣና.... "####.... እኔ ከ ት/ቤት 2 ዳቦ ይሰጠኛል። አንዱ ያንተ ይሆናል፤ ሻይ በጋራ እንጠቀማለን። ገንዘብህን አጠራቅመህ መፅሃፉ ይገዛል.... ጊቢም ትገባለህ" አለኝ። እንደሱ አይነት ነጫጭ ልብ ያላቸው ሰዎችን ተደግፌ ነው ዛሬ ላይ የደረስኩት። ሰዎች ጥሩ መሆናቸውን የሚያምን የዋህ ማንነቴን የፈጠረው አንዱ ምክኒያት እሱ ይመስለኛል። መፅሃፉ በልጅ ካልኩሌሽናችን ባይገዛም ዛሬ ላይ ያለሁበት ቦታ ጊቢ እንድገባ ለረዱኝ መልካሞች መኖር አንዱ ምስክር ነው።> >>
.
.
ይቀጥላል...

@Re_Ya_Zan

2 months, 1 week ago

ረመዷን ነገ አንድ እንደሚል ሰማን፤

ትናንት በዙሪያችን የነበሩ ለዛሬዋ የረመዷን ለይል ያልበቁ እልፍ ሰዎች አሉንና አሏህን እናመስግን። በዱኣ አንርሳቸው። በመልካም ሁኔታ ፆመው ተጠቅመውበት ከሚያልፉ ባሮች የምንሆንበት ወር ይሁንልን።

ረመዷኑኩም_ሙባረክ!🤩

@Re_Ya_Zan
@Re_Ya_Zan

2 months, 3 weeks ago

....ከጎናችን ባለው ሰው አይን ውስጥ ቀጣዩ ረመዳን የመጨረሻው እንደሆነ ብንመለከት ምን እናደርግ ነበር? አልያም.... ቀጣዩ ረመዳን የመጨረሻችን እንደሆነ እያየ ምንም ባይለን ምን ይሰማን ይሆን?.... ብዬ አሰብኩ..

.....አለ አይደል?.... በሚለዋወጥ አላቂ አለም ውስጥ የማይለወጥ ተደጋጋሚ እኛነት። የመጣውን ስለመጣብን ብቻ መቀበል... የለመድነውን ዑደት መደጋገም... ሲሄድ በግድየለሽነት መሸኘት። ቆይ ከዚ በኋላ ባይመጣስ?.... ለአንዴ እንኳን "ረመዳን ስለደረሰ አውቄም ሆነ ሳላውቅ...." በሚል መልዕክት ፈንታ "....ያ አኺ ፊላህ... የፊታችን ረመዳን የመጨረሻችን ይሁን አይሁን ስለማላውቅ በህይወታችን አሳልፈነው የማናውቀው አይነት ልዩ የዒባዳ ወር እንድናሳልፍ ልጠይቅህ ወደድኩ። አድርገነው የማናውቀው አይነት ልዩ ቃል እንገባባ። አደራህን ባሁኑ ለለይል ካልተነሳሁ ቀስቅሰኝ... ተራዊህ ላይም ካልተያየን ተደዋወለን እንተዋወስ... ቁርዓንን ደጋግሞ ከማኽተሙ እንለፍና እንማማረው... የመጨረሻችንም አይደል?... በቀን ውስጥ አላህን ባስታወስናቸው ሰዎች ቁጥር እንፎካከር... መጥፎ ቃል የወጣንም እንደሆን አሁን በምንገባባው ቃል ታስረን ሰደቃ እንስጥበት... እንደውም የተመደበች የሆነች ሰደቃን ያልሰጠንበት ቀን እንዳያልፍ.... የመጨረሻችንም አይደል?... በቃ... ለአንድ ወር ጀነት የምትገባቸው ሰዎች እንሁን.... ምናልባት ከዚያ በላይ ረመዳኖችን እንድንኖር ተፅፎልን እንደሆንና ተኮራርፈን ቢሆን እንኳ... 'ያኔ ባሳልነፍነው 30 መልካም ቀናት ትዝታ' ስም ያለ ቴክስት አማላጅ አፉ እንባባላለን።" የሚል መልዕልት ቢደርሰኝ ተመኘሁ። ያ ኡመተል ሀቢብ.... አላፊ የሆኑ ወዳጆቻቹንና... መጪዎቹን የሚቆጠሩ ቀናት አደራ...

@Re_Ya_Zan

3 months, 2 weeks ago

....የሆነ ጊዜ ላይ.... በሰዎች ተከትቦ በሰዎች ተተውኖ ለሚቀርብልኝ ትርዒት ምላሽ፣ ንዴት አልያም እምባ ትንቅንቅ ውስጥ በገባሁ ጊዜ "እንዴ ምን ሆነሻል? ተራ ትወና እኮ ነው.... ሲቆይ የምር መሰለሽ እንዴ? አሁን ካሜራው ሲጠፋ የወዳደቁት ይነሳሉ እኮ... የተጣሉትም አብረው ራት ይገባበዛሉ" በሚል ራሴን ወደራሴ ለመመለስ እታገል ነበር.... ቀን ተቆጥሮ ከእድሜ ጋር በራሱ ጊዜ ጣእም አልባ መሆኑ ሊገለፅልኝ...

.....ዛሬ ዛሬ.... ነፍስ ሆይም፣.... መሰሎቿም በዙሪያዬ ለዚች ሁለት ቀን የዱንያ ተውኔት እርር፣ ቁጥት፣ ስበር፣ ቁጭት ሲሉ.... "ሲቆይ የምር መሰላቹ እንዴ?" በይ በይ ይለኛል.... ኧረ ጫን ሲል ያስቃልም... "የወደቅሽው ፈተና፣ የፈረሰብሽ ትዳር፣ የተባረረሽው ስራ... ሲቆዩ ዘላቂው እውነታ መስለው ታዩሽ እንዴ?...." አይነት ነገር... "ትናንት የቀበርሻት ነፍስ ሲቆይ የምር ካንቺ ጋር በዝምድና የተቆራኘች መሰለችሽ?.... ለዚህ ቆይታዋ ይሄን ሮል እንድትጫወት የተመደበች ተዋናይ እንጂ ሌላ አይደለችም እኮ.... ስራዋን ስትጨርስ በሰራችው ልክ የሚከፈላት ተራ ራሷን አሳቢ ነፍስ!..." አይነት ነገር.... "...ደግሞ ደግሞ የምር ከትርዒቱ ወጥታ የቀረች ነው እንዴ የመሰለሽ?.... ረዘመ እንጂኮ ሁሉም በየተራ እየወጣ የሚያልቅበት የህይወት ትወና ነው.... ነገ ደግሞ ሙሉ ድርሰቱ ሲያከትም እንደወጡ ያሰብሻቸው በሙሉ ከየከረሙበት ተጠርተው የሚሰበሰቡበት....".... አይነት ነገር...

....ነገሩ ከፊልም ሱሰኞች "መች ጠፋን እሱ" አይነት የብስጭት ምላሽ የተሻለ ጆሮ የሚሰጥ መች ሊገኝ። ይሄም ቀን ጠብቆ በራሱ እስኪገለጥ ከመጠበቅ ውጪ...

@Re_Ya_Zan

4 months ago

አንዳንዴ ህይወት እንዳሰብናት ረዥም አይደለችም.... አንዳንዴ ቀናችን ሲደርስ ሞትም ምክኒያት አይፈልግም.... መንገድ ላይ እየሄድን ድንገት ከጎናችን ተገንሶ ሲወድቅ ቀልድ እንደመሰለን እንደሱ.... ትናንት አብረናት ተሳስቀን ዛሬ ላትመለስ መሄዷን ሲነግሩን እንዳላመንነው እንደሷ....

ቆም ብዬ ሳስበው.... በሰአቱ ደንግጠው ይሆን እላለሁ። ከፊታቸው ስለተመለከቱት ለኛ ስለማይታየን እንግዳ ፍጡር የሆነ ነገር ሊሉን፣ ሊያስጠነቅቁን ፈልገው ይሆን? ሞት እንደሆነ እያለፉበት ያሉት ነገር ቶሎ ተረዱት ወይስ.... ገና ወጣት እኮ ነኝ፣ የምን ፍጡር ነው ይሄ ብለው ይሆን? ወይም ከደቂቃዎች በፊት እንኳን የሆነ ምልክት ነገር ፍንጭ ተሰቷቸው እንደኛው ልብ ሳይሉት ረፍዶባቸው ይሆን?.... ቆይ....ቆይ... እኛስ ረፍዶብን ይሆን?.... ይሄን ከተባባልነው ከኛ መሃል ቢያንስ አንዳችን.... አንዳችን ባንሆን እንኳን የአንዳችን ቤተሰብ በአዝራኢል የስም ሊስት ላይ ከቀጣዮቹ 1000 መሀል መሆኑ እርግጥ ቢሆን ስንታችን ባለንበት ሁነት ላይ እንቀጥል ነበር....?

ብቻ........  ያ ቃል የተገባልን ጉዞ ድሮ ይመስለን እንደነበረው ሩቅ አይለም....

@Re_Ya_Zan

5 months, 1 week ago

ልብ እንበል... ይሄ ከኔ የመጣ ሳይሆን ፀሀፊው የአለማት ጌታ ከሆነው ያ ብርቅዬ መፅሀፍ የመጣ ማስጠንቀቂያ ነው። ልብ እንበል... በዚህ ዲን ላይ የቻልነውን ሁሉ ማዋጣት ቀላል ሆኖ አያውቅም፣ ቀላልም አይሆንም... በአንድ ወር ተኩል ጩኸት የሚያከትምም አይደለም... ስለዚህ እስከ ሂሳብ ቀን ድረስ እንበርታ። ልብ እንበል.... አንቀፆቼ አልደረሷችሁም ነበርን? ከዚህ በፊት የነበሩት ህዝቦች ተምሳሌት አልመጣችሁም ነበር? በተባልን ጊዜ <ምነው ተራራውን ሆኜ ይሄን ቁርዓን ክብደቱን ተገንዝቤ ሳልቀበል በደቀቅኩ ኖሮ> ሳንል በፊት እንደ ሙእሚን አላህ ከኛ ምን እንደሚጠብቅ አስተንትነን እንስራበት። መተዋወሳችንን እዚህ ላይ አንዝጋው። ተኝተን ከነበረ እንንቃ፣ አውቀን የተኛን ከነበረም አላህን እንፍራ። አላሁመ ያለብኝን አድርሻለሁ፣ አላህ ሆይ መስክር። ወሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።

@Re_Ya_Zan

5 months, 1 week ago

አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ... በአላህ ስም በትእግስት ማንበባቹን እየጠየኩ አጠር ያለ መልዕክት ላስተላልፍ....

ከቢስሚላህ በኋላ.... ምሽቱን ስሰማው ውርር ካደረገኝና ከነበርኩበት እንቅልፍ ካባነነኝ የአንድ ዳዒ  ቃላት ልጀምርና፣ ንግግሩ <<ስንቶቻችን የድርሰት መፅሀፍቶችን ሽፋን አይተን <ኦ ይሄማ የእከሌ መፅሀፍ ነው! የእሱ ፅሁፎች ምንም አይወጣላቸው። ይሄን መፅሀፉን ለምናምነኛ ጊዜ ደግሜ አንብቤዋለሁ... ባሁኑስ ምን ያስተላልፍ ይሆን> ብለን እንደምናደንቀው፣ ቁርዓንን ስንመለከት... <ኦ ይሄኮ የአለማት ጌታ የፃፈው መፅሀፍ ነው... ምን ያህል ለኛ መድረስ ያለበት ወሳኝ ሀሳብ ቢኖር ነው ያ ሀያል ጌታ እኛን ለማናገር ያዘጋጀው?> የሚለው ሀሳብ የሚመጣልን?>> የሚል ነበር... በእርግጥም፣ ስለደበረው አልያም "ጥበብ ስለጠራችው" ብቻ የሚፅፍ ያልሆነው ግዙፍ ጌታ ያወረደውን ቁርዓን ተራሮች ሊሸከሙት ያልቻሉት በምክኒያት ነው። የራህማኑን ድምፅም ሆነ መልኩን ለማየት ያልታደልን ፍጡሮች ከመሆናችን ጋር... ቃላቱ በቀጥታ የሚስተጋቡበት ብቸኛው ቅሪት ማስተንተን እንዴት አያጓጓንም?

ወደጀመርኩበት ሃሳብ ስመለስ... ያ ኡመተል ሀቢብ፣ ራህማኑ ለኛ መገሰጫ ባስተማረን የቀደምቶቹ ታሪኮች ውስጥ አንዴ ቆም እንበል.... መሳጭ ባልናቸው ተካታታይ ልብወለዶች አልያም ፊልሞች ውስጥ በሙሉ ልቦናችን ተሳታፊ ሆነን "ገዳዩ ማን ይሆን?" ብለን የሚጠቅመውንም የማይጠቅመውንም ፍንጭ እንደምናገጣጥመው ሁሉ.... ባለፉት ህዝቦች ልምድ ውስጥ ምን ብልሃት እንደተደበቀ ለመረዳት አንዴ ቆም እንበል... እስከዛሬ ደጋግሜ ከማንበቤ ጋር ትናንት ምሽት ከዳዒው ትንታኔ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ልብ ካልኩት ቆምታ ልጀምር። አለማችን ላይ ግብረሰዶምን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመሩት የሉጥ ህዝቦች ታሪክ በብዙዎቻችን ዘንድ የታወቀ ነው። መላኢካዎች ሉጥ (ዐ.ሰ)ን ሊጠይቁት የመጡበት ምሽትና የሉጥ ህዝቦች አዲስ የመጡትን እንግዶች እንዲያስረክባቸው ከሉጥ የጠየቁበት ሁነት ብዙ ምዕራፎች ላይ ከመጠቀሱ ጋር፣ ግብረሰዶማዊ እስካልሆንን ድረስ እነሱን የነካቸው አይነካንም አይነት አናስተነትነውም። ቆምታችን የሚሆነው ታዲያ እዚ ጋር ነው። ለመሆኑ፣ ያን ምሽት የሉጥ ቤት ውስጥ መልከመልካም ወንዶች (መላኢካዎች) መግባታቸውን የሉጥ ህዝቦች በምን ሊያውቁ ቻሉ? ከጅምሩስ ማን ነገራቸው?... (ብለን ጠይቀን እናውቅ ይሆን?)

መልሱ ከፊሎቻችን ጋር የታወቀ ከመሆኑ ጋር ማስተንተኑ ላይ ግን አስፈሪ እውነታ አለው። በእርግጥም ገምታቹት ሊሆን እንደሚችለው ሚስጥሩን ያናፈሰችው  የሉጥ ሚስት እንጂ ሌላ አልነበረችም። በምላሹም የሉጥ ህዝቦችን የነካቸው በላእ ለሷም የተረፈ እንደነበር ቁርዓን ያስተምረናል። ነገርግን የሷ መቀጣት ማንም ተራ ሰው በማይጠቀስበት ውድ መፅሀፍ ላይ ለምን ተለይቶ ተጠቀሰልን? ከጅምሩስ ለምን የነሱን ያህል መቀጣቷ አስፈለገ? እሷ የሰራችው ያን ያህል የገዘፈ ወንጀል እንዳልነበር ልብ ብለናል? ማለት.... በዘመኗ ውስጥ ያለ ማንም ሰው ያደረገውን ነው ያደረገችው። በአሁኑ በኛ አማርኛ.... ሁሉም ቲክቶክ ስለሚጠቀም እሷም ተጠቀመች፣ እንደውም እንደሌሎቹ በዘፈን የተቀናበረ ቪድዮ አልለቀቀችም... ሌሎች ተቀርፀው ለለቀቁት ቪድዮ ትንሽዬ ማበረታቻ ላይክ ነው ያደረገችው። ወይም ደግሞ በዚ ሁሉም የሀራም ጓደኛ መያዝ ባበዛበት ዘመን የጓደኛዋን ስልክ ቁጥር ለሌላ ለምታውቀው ወንድ እንደመስጠት.... ካልሆነም ፎቶ መልቀቅ ለምትወደው ጓደኛዋ ስልክ ይዞ አቋቋሟን እየመምረጡ ፎቶ እንደማንሳት... አለ አይደል፣ ቀላል ነገር። ዞሮ ዞሮ እሷኮ አልሰራችውም ሀራሙን፣ ባለቤቷም ድረጊቱን እንዳይሰሩ ለህዝቦቹ ነግሯቸው እምቢ ብለዋል ስለዚ መካሪ ዘካሪ ብትሆንም ለውጥ አታመጣም... እሷ ባትተባበርም ደግሞ እነዚን ሀራም ተግባራት ሌላው መደገፉ አይቀርም። ስለዚህ.... አላህ ይምራታል (አይደል የምነለው?)። ካልሆነም ለቀላል ጥፋቷ ቀላል መቀጣጫ ይበቃት ነበር... የተወሰነ አመት ጀነት ሳትገባ ቆይታ ቅጣቷን ስትጨርስ እንደመግባት። (መዐዘ ላህ የአላህን ፍርድ እየተቸን እንዳልሆነ ልብ እያልን)።

ሆኖም ቅጣቷ ወንጀሉን ከሰሩት እኩል፣ ሳይቀናነስ እንደደረሳት ለኛ መታወሱ ወደ አንዲት መልካም ድርጊት ያቀጣጨ ሰው የራሱንም በሷ የሰራበት ሰውንም መልካም ምንዳ፣ ወደ መጥፎ ያቀጣጨም የራሱንም በመጥፎ ተግባር ላይ የዋለውንም ሰው ቅጣት የሚሸከም መሆኑን የሚያስታውሰን ነው።

በሌላ አንግል ደግሞ መላኢካዎች በኢብራሂም መኖሪያ ውስጥ በከተሙ ጊዜ ለኢብራሂም

إِنَّا مُهْلِكُوٓا۟ أَهْلِ هَٰذِهِ ٱلْقَرْيَةِ ۖ إِنَّ أَهْلَهَا كَانُوا۟ ظَٰلِمِينَ
«እኛ የዚህችን ከተማ ሰዎች አጥፊዎች ነን፡፡ ሰዎቿ በዳዮች ነበሩና»(28 : 31)

ማለታቸውን እንመልከት። ኢብራሂም (ዐ.ሰ)ም:-

إِنَّ فِيهَا لُوطًۭا ۚ
«በእርሷ ውስጥ ሉጥ አለ እኮ»

ሲል የሰጣቸው ምላሽ ይታወሳል። እየጠፋ ባለ ሙሉ ኡማ ውስጥ፣ "ሁሉም ተማሪ ካልመጣ አቴንዳንስ አይያዝም፣ አብረን እንቅር" አይነት ሁሉም ከጠመመ አላህ ሁሉንም አይቀጣም ብሎ እንደ ሉጥ ሚስት ከጠመሙት ጋር የመጥመም አልያም አላህ ከፈጠራቸው ደካማ ፍጡሮች የተብቃቃ፣ የሻውን ለይቶ በመቅጣት ለይ ቻይ መሆኑን ተገንዝቦ እንደ ሉጥ (ዐ.ሰ) በአላህ መንገድ ላይ መበርታት የኛ ምርጫ ነው። በምላሹም ከመላኢካዎቹ የመጣው አይነት

نَحْنُ أَعْلَمُ بِمَن فِيهَا ۖ لَنُنَجِّيَنَّهُۥ وَأَهْلَهُۥٓ
«እኛ በውስጧ ያለውን ይበልጥ ዐዋቂ ነን፡፡ (እርሱን) በእርግጥ እናድነዋለን፡፡ ቤተሰቦቹንም ጭምር፡፡» (28 : 32)

ምላሽ እንታደላለን። በእርግጥም ራህማኑ ማንንም አይበድልም።

ሳጠቃልልም.... ሰሞኑን እየኖርነው ባለነው፣ ገና ሳይበርድ መረሳት በጀመረው የፈለስጢን ወንድሞቻችን ሁኔታ ላይ "እኛ boycott አደረግን አላደረግን ምን ለውጥ አለው? ሁሉም እየገዛ አይደል.... ደግሞ እነሱ የት እኛ የት... እኛ አንድ ነገር ብንሆን እነሱ ምላሽ የሚሰጡልን ይመስል" የሚሉ ግድ የለሽነቶች ላይ ያ የሉጥን ሚስት ያጠፋትን ጀባር እና ተበቃይ ጌታ እንፍራ በሚል ላስታውሳቹ ወደድኩ። ዛሬ ባለንበት ዱንያ ላይ እንደ ሉጥ ህዝቦች በስም በስማችን የተስተካከለ ድንጋይ የሚወርድብን ቢሆን ኖሮ የድርጊቱ አስተዋፅኦ አበርካች ማን እንደሆነ በለየ ነበር፣ ግን የሀቢቡ ኡማ ቅጣታችንም ሽልማታችንም ተመዝግቦ አኼራ ላይ ስለሚጠብቀን እየሰራን ያለው ጥፋት ይሁን ልክ መገንዘብ ያዳግተናል። ልጃችንን ሊገል የሚሄድን ጦር መሳፈሪያ ወጪውን ሙሉ ዱንያ ተሰብስቦ እየከፈለለት ቢሆን እንኳን፣ ሁሉም ከከፈለለት አይቀር እኔም ልክፈልለት ብለን እንደማናዋጣው ሁሉ... እዚህ ጋርም እጃችንን ለመሰብሰብ የሚያስመነታ ነገር የለም። ለውጥ ስለሚያመጣ ስለማያመጣ ሳይሆን፣ ከላይ የሚመመለከተን አላህ ባመጣነው ውጤት ሳይሆን በጥረታችን ስለሚመነዳን...

وَأَن لَّيْسَ لِلْإِنسَٰنِ إِلَّا مَا سَعَىٰ (39) وَأَنَّ سَعْيَهُۥ سَوْفَ يُرَىٰ (40) ثُمَّ يُجْزَىٰهُ ٱلْجَزَآءَ ٱلْأَوْفَىٰ (41)
ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም። (39) ሥራውም ሁሉ ወደ ፊት ይታያል፡፡ (40) ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል፡፡
(52 : 41)

7 months ago
ከ'ህትነትሽ አትጉደይ ልቤን በክንድሽ ላኑራት፣

ከ'ህትነትሽ አትጉደይ ልቤን በክንድሽ ላኑራት፣
ከሕፀፅ ስሕተቴ መንገድ በምክርሽ በትር አቅኚያት።
እያፈርኩ እንዳልቀረብኩሽ ስወድቅ እንዳልከበድኩሽ፣
የፍቅርሽ ወንዙ አይድረቅ
መንገድ የሳትኹ ቀን ላይ 'ደህና ነኝ' ምልሽ ቢርቅሽ ።

@Re_ya_zan

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago