Ibnu Hashim(أمير هاشم)

Description
"ألا لستُ للفردوسِ أهلا ولا أقوى على نار الجحيم فهبْ لي توبة واغفر ذنوبي فإنك غافر الذنب الأغامي"!!
We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 Monate, 1 Woche her

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 11 Monate her

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 2 Wochen, 6 Tage her

1 month ago

ሐብትህን እወቀው‼️

ድል ባለ ቪላ ቤት ውስጥ የሚኖሩ አባትና ልጅ አንድ ቀን ልጅ ጓደኞቹ ድሃ ሲሉ ሰምቶ አባቱን “አባየ ድሃ ማለት ምን ማለት ነው?ብሎ ጠየቀው።አባትም ለልጁ በተግባር ለማስረዳት አሰበና ገጠር ካሉ ዘመዶቹ ጋር ይዞት ሄደ። እዛ ከገበሬዎች ቤት ለአንድ ቀን እንድቆይ አድርጎ  ዞር ዞር እያሉ አካባቢውን ሲያዩ ውለው ሲመሽ ከቤት ገቡ። ሻዋር ወስደው ትንሸ ካረፉ በኋላ ከዘመድ አዝማድ ጋር በረንዳ ተሰብስበው ሲጫወቱ አመሹና የራት ሰዓት ደርሶ ራት እየበሉ ሳለ  አባት ልጁን እንድህ ሲል ጠየቀው” ውድ ልጀ ከውሎህ ምን ተማርክ ፣አሁን ድህነት ማለት ምን ማለት እንደሆን ተረዳህ”በማለት  ጠየቀው።

ልጅም እንድህ ብሎ መለሰለት “አዎ አባየ እኛ አንድ ውሻ አለን እነሱ 4ውሻ አላቻው፣እኛ አንድ የመዋኛ ገንዳ አለን፣እነሱ ወራጅ እና ንፁህ ወንዝ አላቸው፣እኛ ቤታችን ውስጥ መብራት አለ ውጭ ስንወጣ ብዙ ኮኮብና የደመቀ ጨረቃ በበቂ ሁኔታ አናይም፣እኛ ቤታችን የታጠረ እና የተጨናነቀ ጊቢ ነው፣እንደነሱ ንፁህ አየር አናገኝም፣እኛ ከጎረቢቶቻችንም ጋር አንተዋወቅም!”

“እነሱ ግን ብዙ ጎረቢት እና ብዙ ጓደኛ አላቸው፣አብረውም ይመገባሉ፣እኛ የታሸገ ምግብ ከፍሪጅ ወይም ከሱቅ አምጥተን እመገባለን፣እነሱ የራሳቸውን ምግብ ያመርታሉ፣ ያለምንም ኬሚካል ንኪኪ ፍረሽ ምግብ ይመገባሉ፣እኛ ግን ብዙ ኬሚካል እና ኘሮሰስ የሆነ ምግብ እንጠቀማለን፣እነሱ ለቤተሰባቸው በቂ ጊዜ አላቸው፣እኔና አንተ ግን በሳምን 2 ቀን ብቻ ነው ጥሩ ጊዜ አብረን የምናሳልፈው። “

“አባየ እኛ በጣም ድሃ እንደሆን ስላስተማርከኝና ስላሳወከኝ በጣም አመሰግናለሁ።” በማለት አባቱን ያስደነገጠ መልስ መለሰለት።

ብዙዎቻችንም የሳትነው እውነት በዚህ ልክ ነው።ሃብት ማለት የገንዘብ ክምችት፣የእቃ ስብስብ ይመስለናል።ነገር ግን እውነተኛው ሃብት የጤና ሃብት ነው።ጤናማ የአኗኗር እና የአመጋገብ ስርዓት፣ከንፁህ ተፈጥሮ ጋር፣ከልብ ከሚወዱት ወዳጅ ጋር፣ከዘመድ አዝማድ ጋር እና ከሁሉም ሰዎች ጋር በፍቅር እና በሰላም መኖር ከሃብት ሁሉ ትልቅ ሃብት ነው።

t.me/IbnuHashm

1 month ago
1 month ago

የእድሜ ክልላችን አይሸውደን!

ሽ አመት የምንኖር እየመሰለን፣ነገ የሚነጋልን የሚመስለን አለመነሳትም እንዳለ አንርሳ።ማንም ሰው የቆመ ቢመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።አብዘሃኞቻችን ብዙ እድሜ ያለን እየመሰለን ዛሬን ከመልካም ስራ የምንቆጠብ ብዙ ነን።ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው እንደሚባለው ሸይጧንም ሲወስደን እያታለለን ነውና እንንቃ።አንድ ቀን አለመኖር እንዳለ አውቀን በተሰጠን እድል ያልሰራነውን ስህተት ለመስራት ከመሯሯጥ ያልሰራነዉን መልካም ስራ ለመስራት መሯሯጥ አለብን። ቅንነት ባህሪያችን መልካምነት ግብራችን ይሁን።

ስለ ሰው ብሎ በመሞት እንጅ ስለራስ ጥቅም ብሎ ሰውን በመግደል ፅድቅ አይኖርም።ሰው እንሁን፣ ስለ ሰው እናስብ፣ሰውን እናክብር።ከብሄራችን እና ከዘራችን በላይ ስለ ሰውነታችን እንጨነቅ።አካባቢያችን ፣ዘራችን፣ቀለማችን፣ቋንቋችን እና ሃይማኖታችን ማንነታችንን አይገድበው።ከሁሉም በላይ ሰው መሆን ይበልጣል። ቅን እንሁን፣ደግ እንሁን።መልካም ስራ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም!!!

t.me/IbnuHashm

3 months, 4 weeks ago

አሁን ያለሁበት ቦታ ሰዉ ተስፋ የሚቆርጥበት ቦታ ነዉ። ይህንን ፅፅፍ ከእራሴ ጋር እየታገልኩ ነዉ የፃፍኩት ም/ቱም እኔ private የሆነ ይህወት ነዉ ያለኝ እንደ አብዘሀኛዉ social media ባልተቤት Public የሆነ ይህወት የለኝም ግን ይህ ነገር እናንተ ትማሩበታላችሁ ብዬ ስላሰብኩ ነዉ ይህንን ነገር ላካፍላችሁ የወደድኩት።

በአሁኑ ሰዐት አይኔ ብዙ ነገር እያየ ነዉ። አንድ ነገር ታዘብኩ እኛ እቤታችን ስንሆን ሰዉ የሚታመም አይመስለንም። ሁሉም ሰዉ ደህና የሆነ ነዉ የሚመስለን። ይህ የአብዘሀኞቻችን አመለካከት ነዉ። ግን ይህ አመለካከት ከእዉነት የራቀ ነዉ። አሁን ባለሁበት ሰዓት አንዳንዶቹ ተስፋ ቆርጠዉ ይገኛሉ አንዳንዶቹ እግራቸዉ ሊቆረጥ ወደ ኦፕሬሽን እየገቡ የሚገኙ አይቻለሁ አንዳንዶቹ በቱቦ የሚሸኑ አሉ ወ.ዘ.ተ ዘርዝሬ አልጨርሰዉም ብቻ አላህ ሱብሀነ ወተዐላ ትልቅ ኒዕማ ነዉ የሰጠን ይህም ኒዕማ ጤና ነዉ። በዚህ ምድር ላይ የመጀመሪያዉ ነገር ጤና ነዉ❗️❗️ግን አላህ ሱ.ወ ይሄንን የመሰለ ትልቅ ኒዕማ ሰጦን አናመሰግነዉም እናማረዋለን!!

ወላሂ በዚች ዱንያ ላይ ከጤና የበለጠ ትልቅ ኒዕማ የለም!! ምስጋና ይገባዉ። አልሀምዱሊላህ።

t.me/IbnuHashm

3 months, 4 weeks ago
3 months, 4 weeks ago
4 months ago

በይቅርታ ከሰከነው ውቅያኖስ ዳርቻ ላይ ቆመው የቁርሾ ጠጠር የሚወረውሩ አካላት የሚያገኙት ውጤት ሰፌድ የምታህል ማዕበል ብቻ ነው። ውቅያኖሱ ላይናወጥ ረግቷል። ካዋጣ ፋይዳ ቢስ በሆነችው ማዕበል ይዝናኑ።

መልካም ቀን!

t.me/IbnuHashm

4 months ago

ባል ለሚስቱ የሆነ መረጃ እያነበበላት ነው። በሁለቱ መካከል የነበረው የሃሳብ ምልልስ ይህን ይመስላል: -

ባል ?  «ሴት ልጅ በቀን ውስጥ ከአንደበቷ የሚወጡት የቃላት ብዛት ሶስት ሺህ ሲጠጉ የወንድ ልጅ ግን አንድ ሺህ ብቻ አንደሆነ ታውቂያለሽን ??? 
.
.
ሚስት ? «በሚገባ አውቃለሁ፤ ምክኒያቱም እኛ ሴቶች ነገር ለማይገባቸው ደደቦች የተናገርነውን ቃል በደንብ እንዲረዱት ሁለት ጊዜ ደጋግመን ለመናገር ስለምንገደድ ነው» 
.
.
ባል ? «ምን ማለት ነው ??»
.
.
ሚስት ? «አየህ አይደል!  ያልኩትን ነገር መድገም አለብኝ» 

t.me/IbnuHashm

4 months ago

ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ የቻናሌ ቤተሰቦች በዚህ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ ? @a_m_i_r_he t.me/IbnuHashm

4 months, 1 week ago

▻ የቀልብህ ህያውነትነና መሞት ከኢልም ጋር የተያያዘ ነው

? በኢልም የታነፀች የአሊም ቀልብ ሁሌም በብርሀን እና በኑር ላይ ሲሆን
? ከእውቀት የራቀው የጃሂል ቀልብ ሁሌም በጨለማ ላይ ነው::

► ኢማም ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንለት) እንዲህ ይላል

►ኢልም (እውቀት) ማለት
--የቀልብ ምግብ
--የቀልብ መጠጥ
--የቀልብ መድሀኒት
--የቀልብ ህይወት ሲሆን
--በአጠቃላይ ቀልብ በእውቀት ላይ የቆመች ናት
♻️ነገር ግን ቀልብ እውቀትን ካጣች
--ሟች (የሞተ) ይሆናል

? مفتاح دار السعادة (1/344)

https://t.me/IbnuHashm

We recommend to visit

The first Telecom operator in Africa https://t.me/EthiotelecomChatBot

Last updated 2 Monate, 1 Woche her

◉ Welcome to the 433 Films

Best Place To Find All Movies..

🤞For Promo - @Abusheymc

☕️Buy ads: https://telega.io/c/Films_433

Last updated 11 Monate her

"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Last updated 2 Wochen, 6 Tage her