Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

ሳቅ ተራ - ስነፅሁፍ

Description
ነሐሴ 12 2014

👉 @Saq_Tera_Bot
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 month, 1 week ago

*💐*💐🌷 ሙግቱ አበቃ! 🌷💐💐

𝓶𝓾𝓰𝓮𝓽𝓾   𝓪𝓫𝓮𝓺𝓪

ምዕራፍ 8⃣     𝑠𝑒𝑎𝑠𝑜𝑛 8⃣

🔸 ክፍል 7⃣2⃣

ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**

አለማየሁ በሆስፒታል ውስጥ እየተራመደ፣ አንድ የቆመ የህክምና ባለሙያ አጠገብ ሄዶ ቆመ። "ዶክተር! ናትናኤል የሚባል ታካሚ እዚህ ገብቶ ነበር እና የት እንዳለ ማወቅ ፈልጌ ነበር" አለው። የህክምና ባለሙያው ትኩር ብሎ አይቶት "ገብቶ ነበር! ግን ዛሬ ወጥቷል" አለ። አለማየሁ "አመሰግናለሁ" ብሎ ወጣ።

ሔኖክ ከሁለት ወፋፍራም ወንዶች ፊት ለፊት ቆሞ እያናገራቸው ነው።
"ከጀርባዋ ማን እንዳለ በደምብ አጣሩ። በደምብ! በፍፁም እንቅስቃሴያችሁን ማንም ማወቅ የለበትም። ማንም ይሁን ማን በጥራጥሬ ዐይን ነው ምታዩት። ወንድሜ ናቲ ቢሆን እንኳ ይጠረጠራል። እያንዳንዱን እንቅስቃሴዋን ተከታተሉ" አለ።

ባምላኩ ወደ ዳዊት ስራ ቦታ ሄደ። እንደደረሰ የዳዊት ቢሮ ውስጥ ገባ። ዳዊት ተቀምጧል። ባምላኩ ግራ በመጋባት "ምንድነው እንደዚ አቻኩለህ የጠራኸኝ?" አለ። ዳዊት ረጋ ብሎ "ተቀመጥ!" አለው።  ባምላኩ ተቀመጠ። ዳዊት ተነሳና የቢሮውን በር ቆለፈውና ቁልፉን ነቀለ። ባምላኩ መደንገጥ ጀመረ።

ዳዊት ሽጉጥ አወጣ። ባምላኩ መንቀጥቀጥ ጀመረ።  ዳዊት ወደ ባምላኩ ደግኖ "የአባቴን ገዳይ ንገረኝ!" አለ። ባምላኩ" እእእ......እኮ ተረጋጋና  .. ሽጉጡን  አስቀምጠው" አለ። ዳዊት "ትነግረኛለህ ወይስ አትነግረኝም" አለ። ባምላኩ "እሺ........ አባትህን የገደለው........ ..............

.
.
.
.
.    . ....... 𝑐𝑜𝑛𝑡𝑖𝑛𝑢𝑒 ... ይቀጥላል

🔸🔸🔹 @saq_tera 🔹🔸🔸

1 month, 1 week ago

💐💐*🌷 ሙግቱ አበቃ! 🌷*💐💐

𝓶𝓾𝓰𝓮𝓽𝓾   𝓪𝓫𝓮𝓺𝓪

ምዕራፍ 8⃣     𝑠𝑒𝑎𝑠𝑜𝑛 8⃣

🔸 ክፍል 7⃣1⃣

ድርሰት እና ዝግጅት :- በይበልጣል ተሾመ**

የሰሎሞን ጓደኛ አለማየው በመንገድ እየሄደ ነው። "ማንም ምንም ቢል፣ አያስቆመኝም። መጋፈጤን መቼም አላቆምም፤ ያለኝ ተስፋ ከድቶኛል። እኔም እከዳዋለው"

ሆስፒታል ውስጥ 2 ፖሊሶች እና አንድ ዶክተር ቆመው ያወራሉ። "አሁን ልናናግረው እንችላለን?" አለ አንደኛው ፖሊስ። ዶክተሩ "መናገር እኮ ይችላል፣ ግን ስለተፈጠረው ነገር አንስታችሁ ስታወሩት የበለጠ ሊጨንቀው ይችላል" አለ። ሌላኛው ፖሊስ "አብሮት ሰው አለ እንዴ?" ብሎ ጠየቀ። ዶክተሩም "አዎ ጓደኛው አብሮት አለ" አለ።

የዳዊት ቢሮ ውስጥ ዳዊት ቁጭ ብሏል። ሜሮን በሩን ከፍታ ገባች። ዳዊት "አቶ ዳንኤል ወዴት ሄዱ" አለ። ሜሮን "አኔም አላየሁም ነበር" አለች። ዳዊት ወደመቀመጫው እየጠቆመ "ተቀመጭ እስኪ" አለ። ሜሮን ተቀመጠች።
"ያወሩት ነገር ገብቶሻል?"
"ያንተ መኖር በጣም ያሳስበኛል፣ ላንተ መሞት ከማይተኛ ሰው ጋር ልጋፈጥ ነው የመጣሁት አይደል ያሉት"
"እኮ! እቺን ብቻ ተናግረው ወጡ፤ ማነው ታዲያ ለኔ መሞት ማይተኛው?"
"እኔ እንጃ እኔም ግራ ገብቶኛል"
"ባምላኩ ስለዚህ ነገር ያውቃል"
"እና፣ እንዴት አልነገርህም?"
"ንገረኝ ስለው ረፍዷል ብሎኝ ሄደ። ምን ማለት ነው ረፍዷል?"
"ቆይ ግን፣ ይሄን ሰው ብታውቀው ምን ነበር ምታደርገው"
"እሱን ሲደርስ እናየዋለን"

ትርሲት ስፖርት ቤት ውስጥ መሮጫ ትራክ ላይ ሆና እየሰራች ነው። ሔኖክ በንዴት መጣ። መጥቶ ከመሮጫ ትራኩ ጎትቶ አወረዳት። ትርሲት ደንግጣ ጮኸች። "ማን ነው የላከሽ?" አለ። ትርሲት "ሰውዬ ያምሃል?" አለች ጮክ ብላ። "ኧረ ባክሽ፣ የወሰድሽብኝን ንብረት አንድ በአንድ ትተፊያታለሽ፤ እኔ ሔኖክ አይደለውም!" ብሎ ወጣ።

መንገድ ላይ እየሄደ እያለ ስልኩ ጠራ። "ሄለው እማ" አለ። እናቱ በስልክ መናገር ጀመረች።
"አዋረድከኝ ልጄ፣ አዋረድከኝ"
"እማ፣ እኔም አላወቅኩም ነበር"
"ኤዲያ! እሱን ተወውና፣ ናቲን አይተኸዋል?"
"አሁን ሄጄ አየዋለው"
"በል ልጄ አንድ ነገር እንዳይሆን፣ እሱ ንብረት የሚጠብቅ እንጂ፣ ንብረት የሚበትን አይደለም"  ብላ ዘጋች።

አለማየው በመንገድ እየሄደ ስልኩ ጠራ።  "አቤት" አለ። የታፈነ ድምፅ። "ልጁ ተርፏል፣ አሁን ሆስፒታል ነው ያለው። ስለዚህ እዛው ሄደህ ጨርሰው!" አለ።

.
.
.
.
.    . ....... 𝑐𝑜𝑛𝑡𝑖𝑛𝑢𝑒 ... ይቀጥላል

🔸🔸🔹 @saq_tera 🔹🔸🔸

1 month, 1 week ago

#ሙግቱ_አበቃ

ምዕራፍ ስምንት SEASON EIGHT

..... ማዳን ዋጋ ያስከፍላል

ዛሬ አመሻሹን። ይጀምራል።

ሳቅ ተራ ስነጽሑፍ

ማንበብ ሲፈልጉ - Click Here....

1 month, 2 weeks ago

ደረሰ! ደረሰ! ደረሰ! ደረሰ!

ስምንተኛው ምዕራፍ ሊጀምር ነው!

#ሙግቱ_አበቃ

ዘወትር ሰኞ ፣ ዕሮብ እና አርብ አመሻሽ 12:00 ላይ ይለቀቃል።

የፊታችን ሰኞ ይጀምራል።

ድንቅ እና ልብ አንጠልጣይ ታሪክ።

Share

........... @Saq_TerA

1 month, 2 weeks ago

......... ማዳን ዋጋ ያስከፍላል።

"ምዕራፍ 8" በቅርብ ቀን!

እርስ በእርስ ሲሟገቱ፣ ሲሟገቱ መጨረሻቸውን ማወቅ ሁላችንም ጓጉተናል።

የይበልጣል ተሾመ ተከታታይ ዝግጅት

#ሙግቱ_አበቃ
ስምንተኛው ምዕራፍ በቅርቡ ይቀጥላል።

ሀሳባችሁን አስቀምጡልን___

........ @Saq_Tera

3 months, 1 week ago

#ሙግቱ_አበቃ ክፍል 7⃣*0⃣*

Yibeltal Teshome

ምዕራፍ 7⃣ ክፍል 🔟**

ሔኖክ እና ትርሲት የቤቱ በረንዳ ላይ ቆመው እየተጨቃጨቁ ነው።
"ማነው? ከየት ነው የመጣው?"
"ኧረ ባክሽ"
"ይሄኮ የእነባምላኩ ስራ ነው። መጀመሪያም ጠርጥሬ ነበር"
"ዝም በይ! ከሀዲ! ውሸታም! አሁን ውጪ!"
"ወዴት ነው ምወጣው?"
"የፈለግሽበት ግቢ! እሱ የኔ ጉዳይ አይደለም"
"ኧረ ባክህ! እንዲሁ በቀላሉ ውጪ? እናያለን"

ብላ ወደ ውስጥ ገባች። ጥቂት ቆይታ ሻንጣ ይዛ ወጣች። ሔኖክ ፊት ለፊት ቆማ "እናያለን!" ብላ ከግቢው ወጣች።

ላዳ ውስጥ። ትርሲት ቁጭ ብላ እየሄደች ስልክ ታወራለች። "አዎ! ........ አንዳንዴ ጠላትም ወዳጅ ይሆናል ........... አሁን ሁሉም ነገር አብቅቷል ........ ተጣልተናል፣ የፍርድ ቤት ወረቀት አምጥቼ ንብረቱን እካፈላለሁ....... በቃ፣ .... ደህና ይዋሉ።"

ቹቹ ና ናቲ መንገድ ላይ እየሄዱ ያወራሉ።
"ማሚ ደህና ናት?"
"ደህና ናት፣ ምነው ጠፋህ ብላሀለች"
"አይ አዲስ ስራ ጀምሬ ነው። በሳምንት 2 ቀን ስለሚታይ ነው"
"ደግሞ ዳዊት ባምልዬን አስጨንቆታል"
"ለምን?"
"የአባቴን ገዳይ ንገረኝ ብሎ"

ናቲ ደነገጠ። "አንተ ታውቃለህ እንዴ?" ብሎ ጠየቀው። ቹቹ "አዎ!" አለ። ናቲ ይበልጥ ደነገጠ። "በቃ ቻው" ብሎ ተመለሰ።

ዳዊት ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብሏል። ሜሮን የቢሮውን በር ከፍታ ገባች።
"ምነው፤ ገንዘብሽን ፈልገሽ ነው?" አለ በንቀት። "የምን ገንዘብ" አለች ግራ ተጋብታ። ዳዊት "ለካ አላወጡትም፣ ስለዚህ ምን ትሰሪያለሽ" አለ።
"ምን ሆነህ ነው? ስለምንድነው ምታወራው?"
"ለራሴ ጉዳይ እራሴ አላንስም፣ እኔ መክፈል እችላለሁ። አሁን ውጪ!"
"ቆይ ስለምን ገንዘብ ነው ምታወራው?"
"ለነሰለሞን ስለሰጠሽው"

የቢሮው በር ተከፈተ። አቶ ዳንኤል ገቡ። ዳዊት ደነገጠ።

አቶ ዳንኤል "እኔ የሰጠዋቸው" አለ።

ናቲ እየሮጠ ሄዶ ቤቱ ደረሰ። ስልክ አንስቶ ደወለ። "ባምሌ የት ነህ?....... እሺ በቃ ልብስ ቀይሬ መጣው" አለ።

ሻወር ቤት ገባ። ሻወር ከወሰደ በኋላ ፎጣ ለብሶ ወደ መኝታ ክፍሉ ገባ።

እሪ ብሎ ጮኸ። አናቱ ላይ የሆነ ትልቅ ነገር ተከመረበት።

ምዕራፍ 7 አልቋል።
ምዕራፍ 8 ይቀጥላል።

Join 👉 @saq_tera

3 months, 2 weeks ago

#ሙግቱ_አበቃ ክፍል 6⃣*9⃣*

Yibeltal Teshome

ምዕራፍ 7⃣ ክፍል 9⃣**

"ምን ሆነሀል ዳዊት?" አለች ሜሮን ደንግጣ። ዳዊት "ማነሽ?" አለ። ሜሮን ግራ ተጋብታ "ምን ማለት ነው ማነሽ? የተፈጠረ ችግር አለ?" አለች። ዳዊት "አታቂኝም፣ ከተነሳብኝ በጣም ጨካኝና ክፉ ሰው ነኝ እሺ፣ ቆይ ማነው የላከሽ?" አላት።

ሜሮን ተረጋግታ "ኧረ ተው ዳዊት፣ አሁን ደግሞ ምን ሰማህ?" አለች። ዳዊት "ከዚህ በኋላ ላይሽ አልፈልግም፣ ውጪ!" አላት።

ከዳዊት ቢሮ ወጥታ ስትሄድ መንገድ ላይ አብርሀም ጋር ተገናኘች። አብራሀም ምንም ሳይላት "በጣም ይቅርታ አብራሀም" ብላ አልፋ ሄደች።

ባምላኩ ወደዳዊት ቢሮ ገባ። ዳዊት ከተቀመጠበት ተነስቶ የባምላኩ ፊት ለፊት ላይ ቆመ። "ማነው አባቴን የገደለው?" አለ ኮስተር ብሎ። ባምላኩ "ተረጋጋና ተቀምጠን እና......" ብሎ ሳይጨርስ ዳዊት "በቃ!" ብሎ አቋረጠው። "አባቴን የገደለው ማን ነው? የታል መረጃው?" አለ። ባምላኩ "ረፍዷል ዳዊት፤  ረፍዳል።" ብሎ ወጣ።

ዳዊት ተቀመጠ። ቁጭ ብሎ ማሰላሰል ጀመረ።

ሔኖክ ከቤት ሊወጣ መኪና ውስጥ እየገባ ነው። በሩ መንኳኳት ጀመረ። ሄዶ በሩን ከፈተው። ውጪ ላይ አቤኑ ቆሟል። የትርሲት ልጅ።

ሔኖክ "ቤቢ፣ ምን ፈልገህ ነው?" አለ። አቤኑ "አባቴ ነህ አደል?" አለ። ሔኖክ ደነገጠ። "የምን አባት?" አለ። አቤኑ "ሁለተኛ አባቴ" አለ። ሔኖክ ተንፈስ አለ። "ኡ...ፍ  እስደነግጠኝኮ፣ ማነው ግን ሁለተኛ አባትህ ነው ያለህ?" አለ።
"የቹቹ ወንድም ነው"
"ማነው የቹቹ ወንድም?"
"ባምላኩ ነዋ"
"እሱ በቃ ማያመጣብን ነገር የለም አደል"
"ያየሁት የሰርግ ፎቶ ግን ያንተ አልነበረም፤ ወንድሟ ነህ እንዴ?"
"እንዴ፣ የማን?"
"የእማዬ"

.......ይቀጥላል

Join 👉 @saq_tera

3 months, 3 weeks ago

#ሙግቱ_አበቃ ክፍል 6⃣*8⃣*

Yibeltal Teshome

ምዕራፍ 7⃣ ክፍል 8⃣**

ዳዊት እየተርበተበተ "......አቤት..... ማን ልበል" አለ። ሴትየዋ "ዳግመኛ ስህተት ውስጥ እንዳትገባ" ብላ ተመልሳ ወጣች። 

ልክ ስትወጣ ሰለሞን ሲገባ አጠገብ ለአጠገብ ተላለፉ። ሰለሞን ወደዳዊት ቢሮ ገባ። ዳዊት ደንግጦ ከመቀመጫው ተነሳ። ሰለሞን "ተረጋጋ ዳዊት፣ ተቀመጥ!" አለ። ዳዊት "ውጣልኝ!...... ፖሊስ ነው ምጠራው" አለ። ሰለሞን "ቼኩን ቀድጄዋለው" ሲል ዳዊት ግራ ተጋባ። "የምን ቼክ?" ብሎ ጠየቀ። "አንድ ቀን ሌሊት ቤትህን ልናቃጥል መጣን። ከዛ ሜሮን አቋረጠችንና ገንዘቡን ሰጠችን" አለ። ዳዊት ደነገጠ።

ሜሮን ቤት ውስጥ ቁጭ ብላለች።  ሀሳብ እያወጣች እያወረደች ቆየች። ስልኳ ሲጠራ አነሳችው። "አቤት" አለች። ዳዊት ነው የደወለው።
"የት ነሽ?"
"ቤት"
"ቢሮ ፈልጌሽ ነበር"
"አልችልም"
"ለብርቱ ጉዳይ ነው። አሁኑኑ ነይ" ብሎ ስልኩን ዘጋ።

ቹቹ የእነሔኖክ በር ላይ ቆሞ እያንኳኳ ነው። በሩን ሔኖክ ከፈተው። ቹቹ "ትርሲት አለች?" አለ። ትርሲት ከኋላ "አለው" ብላ መጣች።

ሜሮን ዳዊት ቢሮ ደረሰች። እንደገባች ኃይለኛ ጥፊ አረፈባት። እሪ ብላ ጮኸች።

.......ይቀጥላል

Join 👉 @saq_tera

3 months, 3 weeks ago

#ሙግቱ_አበቃ ክፍል 6⃣*7⃣*

Yibeltal Teshome

ምዕራፍ 7⃣ ክፍል 7⃣**

ዳዊት "ንገረኝ እንጂ ምን ያግደረድርሀል?" አለ። ባምላኩ "ዳዊት ያኔ....." ሲል በሩ ተከፈተ። አብራሃም ገባና ቶሎ ቶሎ እየተነፈሰ "ሜሮን ወደዚ መጥታለች?" ብሎ ጠየቃቸው። ባምላኩ "ምንድነው?" አለ። አብራሃም በፍጥነት እየተራመደ ከቢሮው ወጣ። ባምላኩም ተከትሎት ወጣ። ዳዊት በረጅሙ ተነፈሰ።

ባምላኩ በመንገድ እየሄደ ስልክ እየደወለ ነው። "የደወሉላቸው ደንበኛ ስልክ ለጊዜው ጥሪ አይቀበልም "
አሁንም ደግሞ ደወለ። ተመሳሳይ መልስ።

በመቀጠል ወደ አብራሃም ደወለ። መነጋገር ጀመሩ።
"አብራሃም የት ነህ?" አለ ባምላኩ። አብራሃም በፍጥነት "እባክህ ሜሮን የሆነ ነገር እንዳፈጥር ላገኛት ይገባል"ብሎ ስልኩን ዘጋ።

ባምላኩ በመንገድ ላይ እየሄደ ስልኩ ጠራ። አውጥቶ ሲያየው ደነገጠ። "አስጨነቀሽን እኮ ሜሪዬ የት ሄደሽ ነው?" አለ። ሜሮን ደነገጠች። "ማን አልከኝ?" አለች። ባምላኩ "የት ነሽ አሁን?" አለ። ሜሮን ምንም መልስ ሳትሰጥ ስልኩን ዘጋችው።

ዳዊት ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብሎ በሀሳብ ተውጧል። ከራሱ ጋር ብቻውን ያወራል። "ማን ሊሆን ይችላል?......... አባቴን ማን ሊገለው ይችላል....... እንዴት?"

ድንገት በሩ ተበረገደ። ሽጉጥ የደገነች ሴት። ዳዊት ደነገጠ።

.......ይቀጥላል

Join 👉 @saq_tera

3 months, 4 weeks ago

#ሙግቱ_አበቃ ክፍል 6⃣*6⃣*

Yibeltal Teshome

ምዕራፍ 7⃣ ክፍል 6⃣**

አብርሃም እና ሜሮን መንገድ ላይ አብረው እየሄዱ ነው።

"ይገርማል"
"አይ ሜሪ፣ እኔ ራሴ ግራ ገባኝኮ"
"ምኑ?"
" ሁሉ ነገር! አባት ሊያጠቃው የሚፈልገውውን ሰው ልጅ ደግሞ ሊያድነው ሲፈልግ"
"ከሱ በላይ ግን እኔን የገረመኝ የእናቱ ነገር ነው"
"ግን፣ ያንቺ እናት ከአረብ ሀገር መታለች እንዴ?"
"አዎ፤ ከአባቴም ጋ ታርቀዋል"
"ከነሱ ጋር ነው ምትኖሪው?"
"አዎ"
"እንዴ? አታገቢም እንዴ?"
"ምን? .... ቀልደኛ"

ባምላኩ እና ናቲ ሆቴል ውስጥ ቁጭ ብለው ምግብ እየበሉ ነው።

"ምን አለህ አብራሃም?"
"ኧረ የነሱን ነገር እኔ እንጃ! ስለነሱ የፍቅር ግንኙነት....
ባምላኩ አቋረጠው "የፍቅር ግንኙነት?  .. የምን ፍቅር ነው"

ናቲ ውሃ ጠጣና "እሱ ነው እወዳታለሁ ምናምን አለ። ከሳ ስትደውልለት ሜሪዬ ምናምን እያለ ወጣ"
ባምላኩ ፀጥ ብሎ ሆቴሉን ለቅቆ ወጣ።

አብራሃም እና ሜሮን ከሰዓታት በኋላ ወደሆቴሉ ገቡ። ቁጭ አሉ።
"እኔ ምልሽ ሜሪዬ"
"ወዬ አብርሽ"
"ይህን ማዕድ ከቆረስን በኋላ አንድ የምነግርሽ ነገር አለ"
" አይ አሁን ንገረኝ"
" ተይ በኋላ እነግርሻለሁ"
"አሁን ንገረኝ በኋላ አልሰማህም"
"እሺ ግን ሚስጥር ነው"

ዳዊት ቢሮ ውስጥ ከባምላኩ ጋር ቁጭ ብሎ  ያወራል።
"ባምላኩ፣ ውሸት አልፈልግም ሀቅ ሀቁን እናውራ"
"ስለምን"
"ስለአባቴ"

ባምላኩ ደነገጠ። "ስለአባትህ ምን?"

"ሲሞት በፍጥነት ወደቤት ሂድ ብለህ ቴክስት ፃፍክ...... ደግሞ ወደፖሊስ አትሂድ ትልቅ መረጃ አለኝ አልክ፣ የታል መረጃው?"

ባምላኩ መንተባተብ ጀመረ።

አብርሃም እና ሜሮን ዓይን ለዓይን ተፋጠዋል።
"ፍጠና፣ ንገረኛ!"
"ካየሁሽ ቀን ጀምሮ ልቤ ተሸንፏል። ወድጄሻለው"

.......ይቀጥላል

Join 👉 @saq_tera

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago