ወርቃማ ንግግሮች

Description
ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።

አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot

https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 4 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 11 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 day, 10 hours ago

2 weeks, 5 days ago
አብዛኛዉ ሰዉ ቁርዓን እየቀራ ሱጁድ ያለበት …

አብዛኛዉ ሰዉ ቁርዓን እየቀራ ሱጁድ ያለበት አንቀፅ ላይ ሲደርስ በሱጁድ ላይ ምን እንደሚባል አያዉቅም።

ይሀዉላችሁ የሱጁድ ዱዓዉ/ ዝክሩ

اللهم لك سجدت و بك آمنت ولك أسلمت سجد وجهي للذي خلقه وصوره وشق سمعه وبصره تبارك الله أحسن الخالقين
አለሁማ ለከ ሰጀድቱ ወቢከ ዓመንቱ ወለካ አስለምቱ ፣ ሰጀደ ወጅሂ ሊለዚ ኸለቀሁ ወሰወረሁ ወሸቀ ሰምዐሁ ወበሰረሁ ፣ ተባረከላሁ አህሰነል ኻሊቂን።

👌ቢሸመደድ ይወደዳል።

3 weeks, 6 days ago

ኑዛዜዬ ይህ ነው…! እስከሕይወቴ መጨረሻ የታመንኩለትን የፍልስጤም ውዴታ፣ በጫንቃዎቼ የተሸከምኩትን ታላቅ ሕልም ከዳር አድርሱ። እኔ ብወድቅ እናንተ አትውደቁ። ወደመሬት ያልጣልኩትን ሠንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋችሁ አውለውልቡ። መስዋዕትነቴን እንደድልድይ ተጠቅማችሁ ለተተኪው ክንደ ብርቱ ትውልድ መደላድሉን ፍጠሩ። እናት አገር በተግባር የሚኖሩት ተጨባጭ እንጂ የሚተርኩት ተረክ አይደለምና በሚሰዋው እያንዳንዱ ታጋይ እልፍ ተተኪዎች እንደሚፈጠሩ ጥርጣሬ አይግባችሁ።

የእኔ ተራ ደርሶ ከተለየኋችሁ የነፃነቱ ማዕበል የመጀመሪያ ጠብታ እንደነበርኩ፣ ሕይወቴንም ጉዟችሁን ስትፈጽሙ በማየት ጉጉት የገፋሁ መሆኔን አትዘንጉ። በጠላታችሁ ጉሮሮ ውስጥ የተሰካችሁ እሾህ ሁኑ። ዓለም ለሐቃችን መታገላችንን እስኪረዳ፣ ለዕለታዊ ዜና የቁጥር ግብዓት ብቻ እንዳልሆንን እስኪገነዘብ ድረስ ትግላችሁን ቀጥሉ።

የሕያ ኢብራሂም ሲንዋር | ጋዛ
----------

3 weeks, 6 days ago

~~ታሪካዊው የሸሂድ የሕያ ሲንዋር ኑዛዜ~~

አቡ ሊና የተባለ ድንቅ ብዕረኛ፣ በኻን ዩኒስ የዘካ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ዶ/ር ጀሚል አቡ ቢላል ይፋ የተደረገውን የሸሂድ የህያ ሲንዋር ኑዛዜ፣ "የጋዛው ሸሂድ የሕያ ሲንዋር ኑዛዜ" በሚል ርዕስ በጣም ግሩም በኾነ የቋንቋ ጥራት ወደ አማርኛ መልሶት በሳምንታዊው አዲስ አድማስ ጋዜጣ የዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 16፣ 2017 እትም ላይ አስነብቦናል።

የሸሂድ የሕያ ኑዛዜ እጅግ በጣም መሳጭ እና በፍሬም ተደርጎ ለታሪክ የሚቀመጥ የእውነተኛ ታጋይ ውብ ቃል ነው።
የሸሂድ የሕያ ኑዛዜ እጅግ ብዙ መስዋዕትነት እያስከፈለ የሚገኘው የፍልስጥኤማውያን የነጻነት ትግል የሚካሄድበትን ከብረት የጠነከሩ መንፈስ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ፣ ብዙ ሺህ የሕያ ሲንዋሮችን የሚወልድ፣ ትውልዶች የሚቀባበሉት የትግል ቃል-ኪዳን ችቦ ኾኖ ሲያበራ እንደሚኖር መጠራጠር የሚቻል አይመስኝም።

አቡ ሊና በሚሰኝ የብዕር ስም የሸሂድ የሕያ ሲንዋርን ኑዛዜ በሚጣፍጥ አማርኛ ተርጉሞ ላስነበበን ወንድም ልባዊ አድናቆቴንና የከበረ ምሥጋናዬን ለማቅረብ እወድዳለሁ።

--------

▪️ የጋዛው ሸሂድ የሕያ ሲንዋር ኑዛዜ!
➤ [የኻን ዩኑስ የዘካ ኮሚሽን ፕሬዚደንት ዶ/ር ጀሚል አቡ ቢላል እንዳስተላለፉት ]
———

እኔ ግዞትን ወደጊዜያዊ እናት አገር፣ ሕልሙንም ወደዳርቻ የለሽ ትግል መለወጥ የቻለ ስደተኛ ልጅ የሕያ (ሲንዋር) ነኝ። እኒህን ቃላት ስደረድር የሕይወቴን ቅፅበቶች በመላ እያስታወስኩ ነው። ያደግኩባቸውን ጠባብ ጎዳናዎች፣ ያሳለፍኩትን ረጅም የወህኒ ኑሮ፣ በፍልስጤም ምድር የፈሰሰችዋን እያንዳንዷን ደም አስታውሳለሁ።

ፍልስጤም አንዲት ቅዳጅ ትውስታ፣ በፖለቲከኞች ጠረጴዛ ላይ የተረሳች ቁራጭ ካርታ በሆነችበት ዘመን በኻን ዩኑስ የስደተኞች መጠለያ በ1962 ተወለድኩ። ሕይወቴ የተፈተለው በእሳት እና አመድ መካከል ነበር። በወረራ ሥር መኖር ዘላለማዊ ወህኒ መሆኑን ገና በልጅ ዕድሜዬ ተረዳሁ። በፍልስጤም ምድር ተርታ የሚባል ሕይወት እንደሌለ በአፍላነቴ ተገነዘብኩ። በዚህች ምድር እኖራለሁ ያለ ሰው ዝናሩ የማይነጥፍ መሣሪያ በልቦናው ይታጠቅ፣ ለረጅሙ የነፃነት ጉዞ መንፈሱን ያዘጋጅ ዘንድ ግድ ይለዋል።

ኑዛዜዬ ከዚህ ይጀምራል…! ወረራውን በመቃወም የመጀመሪያዋን ድንጋይ ከወረወረው ታዳጊ ግዙፍ እውነታን ተረድተናል። የምንወረውራት እያንዳንዷ ድንጋይ ቁስላችንን አይቶ ዝም ላለው ዓለም የምናሰማት ቃላችን ናት። የሰው ማንነት የሚለካው በዕድሜው ሳይሆን ለእናት አገሩ በከፈለው መስዋዕትነት መሆኑን የጋዛ ጎዳናዎች አስተምረውኛል። የእኔም ሕይወት ያለፈው በዚሁ መልክ ነበር… ተደጋጋሚ ወህኒ፣ በርካታ ውጊያ፣ የበዛ ሕመም እና እስከገደፉ በተስፋ የተሞላ ሙቅ ሕይወት…

በ1988 ነበር የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶብኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ወህኒ ቤት የገባሁት። ፍርኃትን ከነጭራሹ አላውቀውም። በጨለማ የእስር ቤት ክፍሎች ሆኜም በግድግዳው ገጽ ላይ ወደሰፊው አድማስ የሚከፈት መስኮት፣ በብረት ፍርግርጎቹ መካከልም የነፃነቱን ጉዞ የሚያበራ ፋኖስ ይታየኝ ነበር። በእስር ቤት ሶብር መልካም ባህሪ ብቻ አለመሆኑን፣ ይልቁንም ባህርን ጠብታ በጠብታ የመጭለፍ ያክል እንደብረት ጠንካራ መሣሪያ መሆኑን ተረዳሁ።

ኑዛዜዬን እንካችሁ…! ወህኒ ቤትን አትፍሩ። ወህኒ ቤት የነፃነት ጉዟችን አንድ ግብዓት ነው። ነፃነት ከተሰረቀ መብት ይልቅ ከህመም ተፀንሶ በትዕግስት የሚቀረጽ ሐሳብ መሆኑን የተማርኩበት መድረሳ ነው።

በ2011 በ"ወፋኡል አሕራር" የእስረኛ ልውውጥ ስምምነት ስፈታ ማንነቴ እጅጉን መቀየሩን ለማስተዋል በቃሁ። የወጣሁት እምነቴ ጠንክሮ ነበር። ትግላችንም ከትግልነት ባለፈ እስከ መጨረሻዋ የደም እንጥፍጣፌያችን ተሸክመነው የምንዘልቅ የአላህ ውሳኔ (ቀደር) መሆኑን ተገንዝቤ ነበር።

ኑዛዜዬን እንካችሁ…! ነፍጣችሁን፣ ለድርድር የማይቀርብ ክብራችሁን፣ መሞት የማያውቅ ሕልማችሁን አጥብቃችሁ ያዙ። ጠላት ትግላችንን ማስቆም ይሻል። ወኔያችንን በማለቂያ የለሽ የድርድር ተስፋ ጠፍሮ ለማኮላሸት ይደክማል። እኔ ግን እላችኋለሁ… በመብታችሁ አትደራደሩ። ትግላችን በተሸከምነው ነፍጥ ብቻ የሚሰፈር አለመሆኑን አትርሱ። ትግላችን ፍልስጤምን መውደዳችን፣ በከበባና በድብደባ የማይፈታ ወኔያችን መሆኑን አስታውሱ።

ኑዛዜዬን እንካችሁ…! ለሸሂዶቻችን ደም ታማኝ ሁኑ። እሾሃማውን መንገድ ያሳየን ትውልድ በደሙ መስዋዕትነት የነፃነትን መንገድ አስጀምሮናልና በፖለቲካ ጨዋታ፣ በዲፕሎማሲ ውስለታ ክብሩን ዝቅ ከማድረግ ተጠንቀቁ። የእኛ መኖር ዓላማ ቀደምቶቻችን የጀመሩትን ትግል ከዳር ማድረስ ነውና የፈለገው ቢሆን ከመንገድ ማፈንገጥ አይገባም። ጋዛ ምንጊዜም የትግሉ ዋና ከተማ፣ የፍልስጤማዊ ወኔ መቀመጫ ልቦና ሆና ኖራለች። ወደፊትም ትኖራለች።

በ2017 የሐማስን የጋዛ ክንፍ አመራር ኃላፊነት ስወስድ ለእኔ ጉዳዩ የአመራር መቀያየር ጉዳይ ብቻ አልነበረም። ይልቁንም ከወንጭፍ ጀምሮ ወደነፍጥ ያደገው ገናና ትግላችን ዕድሜ የቀጣይነት ሠንሠለት ነበር። በእያንዳንዷ ቀናት የሕዝባችንን ዘወትራዊ ፍዳ በዓይኔ በብረቱ ታዝቤያለሁ። የነፃነት ጉዟችን እያንዳንዷ እርምጃም ብዙ መስዋዕትነት የሚከፈልባት መሆኑን ተረድቻለሁ።

አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሆኜ እነግራችኋለሁ…! እጅ መስጠት የባሰ ዋጋ ያስከፍለናል። ግዴለም በጥንካሬያችን እንዝለቅ። ዛፍ በሥሮቹ አፈሩን አንቆ እንደሚረጋ ሁሉ የፍልስጤምን አፈር ሙጭጭ አድርገን እንያዝ። ለመኖር የወሰነን ሕዝብ የትኛውም ንፋስ ከመሬቱ ሊነቅለው ከቶ አይችልም።

የአቅሷ ማዕበል ዘመቻ መሪ መሆን ለእኔ ትልቅ ክብር ነበር። የአንድ ግሩፕ ወይም የአንድ ንቅናቄ መሪ ሳይሆን ነፃነትን የሚያልም ፍልስጤማዊ ሁሉ ድምጽ መሆን እንደቻልኩ ተሰምቶኛል። ትግል ኃላፊነት እንጂ ምርጫ እንዳልሆነ ሁሌም እረዳ ነበር። እናም ይህ ልዩ ዘመቻ በፍልስጤማውያን የትግል መዝገብ አዲስ ገጽ የሚገልጥ፣ የተለያዩ ታጋይ ቡድኖችን በጠላት ፊት በአንድነት የሚያሠልፍ ዘመቻ እንዲሆን ጥልቅ ፍላጎት ነበረኝ፤ ጠላታችን ሕፃን ከሽማግሌ፣ ድንጋይ ከዛፍ ሳይለይ ሁሉንም ያጠቃልና።

ኑዛዜዬ ግለሰባዊ አይደለም…! ይልቁንም ነፃነትን ለሚያልም እያንዳንዱ ፍልስጤማዊ ሁሉ፣ በትከሻዋ ሰማዕት ልጇን ለምትሸከም እናት ሁሉ፣ በዕኩያን ጥይት ልጁ ለተገደለችበት አባት ሁሉ የጋራ ስንቅ የሚሆን ውርስ ነው።

የመጨረሻ ኑዛዜዬን እንካችሁ…! ትግላችን መና እንደማይቀር አትርሱ። የምንከፍለውን ዋጋ ብቻ ሳይሆን በወኔ እና በክቡር ስብዕና ጌጠን የኖርነውን ሕይወት አስታውሱ። የጋዛ የከበባ ኑሮና የወህኒ ውጣ ውረድ ትግሉ ትከሻ የሚያጎብጥ፣ ጉዞውም ሰውነት የሚያዝል መሆኑን አስተምሮኛል። ግና እጅ አልሰጥም ባይ ሕዝብ ብዙ ተዓምር ይሠራል።

ከምድራዊ ሕይወት ፍትህ አትጠብቁ። የዓለም ሕዝብ ሕመማችንን ዓይቶ እንዳላየ መሆን መምረጡን ስረዳ ኖሬያለሁ። እናንተም መረዳታችሁ አይቀርምና ከሌሎች ፍትህ መጠበቁን ትታችሁ ራሳችሁ ፍትህ ሁኑ። የፍልስጤምን ሕልም በልቦናችሁ ያዙ። ከእያንዳንዱ ቁስለት ጥንካሬን፣ ከእያንዳንዷ ዘለላ እንባ ተስፋን መምዘዝ ተማሩ።

ይሃችሁ የእኔ ኑዛዜ ነው…! መሣሪያችሁን በፍጹም አትጣሉ። ወንጭፎቻችሁን አታስቀምጡ። ሸሂዶቻችሁን አትዘንጉ። ሕልማችሁን አትተዉ። እኛ በአፈራችን፣ በልቦናችን፣ በልጆቻችን የወደፊት ተስፋ ውስጥ እንደምንኖር አትዘንጉ።

3 weeks, 6 days ago

ታሞበት ይዞ የመጣ ባለ ሚኒባስ ወንድም እኔ በነፃ ላድርስላችሁ ብሎ አደረሰልን፣ አስክሬኑንም በቤቱ አሳረፍን😭 😭😭

በዕለተ ማክሰኞ ጥቅምት 05/2017 ዓ/ም መደበኛ ፍ/ቤቱን ከፍተን ሙሌን ወንድሜን ላይመለስ ደዌ ሜዳ መቃብር ቀበርነዉ አፈር አልብሰነዉ ተመለስን። ወጣቱን ህፃኑን ሙሌን በጨካኞች፣ በሆዳሞች ተጨከነበት እኛም ጨክነን አፈር አለበስነዉ። የሙሌ ነፍስ ግን አሁን ፍትህ በማለት ትጮኻለች፣ ገድለዉት ያልረኩ፣ ሞቶም የሚፈሩት ገዳዮቹ አሁንም የፍትህን ድምፅን ለማፈን እንቅልፍ አጥተዉ እየሰሩ ነዉ። እዉነት ብትመነምንም ስለማትቆረጥ ለሙሌ ነፍስ ቀን ወጥቶ ፍትህ ሰፍኖ በስልጣኑና በገንዘቡ ያበጠዉ ከርከሮም ተገንድሶ ወድቆ እናያለን።

📌 በጣም የሚያሳዝነውና የሚያበሳጨው ግን አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣን ሙቶ ምን ላግዛችሁ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ላድርግላችሁ ብሎ የሚጠይቀን የመንግስት አካል መጥፋቱ ነው። የደሴ ከተማ አስተዳደር የሚያሳየዉ ዳተኝነት ነገ በየቤታችሁ የሚያንኳኳ ግፍ ነዉ።

3 weeks, 6 days ago

ልብ የሚነካ የሙሉጌታ ከበዴ የግድያ ታሪክ😳😢
_______
በሬ ካራጁ ከመዋሉ በፊት፣ የገዳዮቹን ዱለታ ያልተረዳዉ ሟች የተደገሰለትን የዕለቱን የሞት ድግስ አያዉቅም፣ መንፈስ የተረዳ ይመስል ሰሞኑን ስለመኖር ከንቱነት የዚች ዓለም ኑሮ ኮንትራትነት ከሃይማኖታዊ አስተምሮ እያጣቀሰ ጓዴኞቹን ሲያወራ ሳምንቱን አሳልፏል። ቅዳሜና ዕሁድን ለቤተሰቡ የሰጠዉ ወጣቱ ዳኛ ሙሉጌታ ከበዴ የገዳዮችን ካራ እየተሳለበት መሆኑን አልተረዳም፣ በሱ ላይ የሚያሾከሽኩ፣ ጨለማን ተገን አድርገዉ የሚመክሩ ሰዉ በላዎች በመንገዳችን ላይ ሆነብን ብለዉ የሚያስቡ ሰዉ በላዎች በየሰርጣ ሰርጡ ሙሉጌታን ስለማስወገድ የሚመክሩ የተንኮል ድምፆችን አይሰማም፣ ሙሌ ልበ ብርሃን ቀና አሳቢ ነዉ፣ በሙሉጌታ ልብ የሚታሰቡት ፍቅር ፍትሃዊነት እንጂ ሰዉ በላዎች ሊጠረጥር ይቅርና ሰዎችን መበደል ልቡን የሚያሳዝነዉ ልጅ ነዉ። እንዲህ አይነት አረመኔነትን አይጠረጥርም፣ የሰዉ ጅቦች ድምጽን መስማት የሚችል ጆሮ የለዉም።

ዕለተ ሰኞ መደበኛ ፍ/ቤት የሚከፈትበት ዕለት ነዉ፣ በማያዉቀዉ መልኩም በሱ ላይ ካራ ሲስሉ የነበሩ ሴረኞችንም ያገናኜች ዕለት ነበረች። ሙሌ ጥቅምት 04/2017 መደበኛ ስራዉን ለመከወንና የዓመቱን የፍ/ቤት መደበኛ ስራ መከፈትን በማስመልከት ደመቅ ብሎ የወጣበት ዕለት ነዉ። ከቤት ከመዉጣቱ በፊት በእንግድነት የመጡ ቤተሰቦቹንና ጓዴኞቹን ሞቅ ባለ ጨዎታ ሸኝቷል። ቢሮዉ ሲገባ ከጥበቃ ሰራተኞችና ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ሰላምታ ሳይሆን የናፍቆት ቀልድን ጭምር የሚለዋዎጠዉ ሰብሳቢ ዳኛ ሙሉጌታ የእለት ስራ ዕቅዱን በሚኒ ማስታወሻ ላይ ከመዘገባ በኋላ ቡና ለመጠጣት በሽሚዝ ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ከቢሮ አቅራቢያ በምትገኝ የጀበና ቡና እየጠጣ የዚህ ዓመት ስራ ዕቅዳቸዉን ያወራሉ፣ በፍ/ቤቱ መዘጋት ምክናየት የፍትህ ጥያቄያቸዉ የዘገየባቸዉ ዜጎችን ግልጋሎት ለመስጠት ህልማቸዉን ይገላለፃሉ። ሙሌ ጥቅም አሳጣን መሬት አገደብን፣ የፍ/ቤት ስራን ተክተዉ ለመስራት የፈለጉ አስፈፃሚ አካላት እንደፈለጋቸዉ ለመጋለብ መሰናክል ሆነብን ብለዉ ያሰቡ ሴረኛ እባቦች ከጀርባዉ የሞት ድግሳቸዉን እንደሚያጋፍሩለት ግን ልቡ አልጠረጠረም ነበር።
ሙሌ ከዕለት ስራዎች ዉስጥ የፍትህ ተግባራትን ብቻ ሳይሆን የበጎ አድራጎት ስራዎችንም ጭምር የሚሰራ ልባም ሰዉ ነበር። በቢጫ ሚኒ ማስታወሻ ላይ የዕለት ተግባሮቹን የሰደረባቸዉን ገፅ ሳብ አድርጎ ተመለከተና “let’s go to our todays mission” አለኝ ይላል አንድ አብሮት የነበረ የስራ ባልደረባዉ፦

በአንድ ስፔሻሊቲ ሆስፒታል ተደፍራ የተኛችን ህፃን መጎብኘትና ፍትህ የምታገኝበትን መንገድ ማመቻቸት ……………
ችግር ላይ ያሉ ሁለት አቅመ ዳካሞችን ወደ ቤታቸዉ ዘልቆ መጠየቅ ……………
ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ስለ ስራ መወያየት፣ የተወሰኑ ያደሩ ስራዎችን መጎብኜትና የስራ መነቃቃትን መፍጠር
የሚሉ ተግባራቶች በዕለት ማስታሻ ደብተሩ ላይ የተመዘገቡ ዝርዝር ተግባራቶች ነበሩ።

ስራዎቹ የዚህ ዓመት የፍ/ቤት ተግባራትን ለማነቃቃትና ዓመቱን ከስራ ባልደረቦቹ ጋር ለመዝለቅ እንጂ በአራጅ እጅ ነፍሱ እንደምትነጠቅ የሚያዉቀዉ ነገር የለማ። ሰዉ ያስባል ጌታ ይፈፅማል እንደሚባለዉ ሙሌ ረጅም አቅዶ የሚሰራ ከጀርባዉ ደግሞ የማያያቸዉ ግን ሁሌም የሚጠረጥራቸዉ ስዉር ባለ ረጃጅም ጥርስ ቀፈተ-ሰፊ በልተዉ የማይጠረቁ ሰይጣን ገዳዮች በየርምጃዉ እየተከተሉት ነበር።

ወጣቱ ዳኛ ሙሉጌታ እስከ ሰዓት የሚከዉነዉን ከዉኖ ለምሳ በራሱ ቤት ግብዥ ስለተደረገለት ሾፌሩን ጨምሮ ከጓዴኞቹ ጋር ወደ መኖሪያ ቤቱ አምርተዉ በሚያምርና ደስታ በተሞላበት ቤተሰባዊ ግብዣ የምሳ ሰዓት ማሳለፋቸዉን ጓዴኛዉ ይገልፃል። ሙሌ ከህፃን ልጆቹ ጋር ያለዉ ቅርርብና መስተጋብር በህፃናት አይኖች ዉስጥ የአባታቸዉን ንጉስነት፣ አይቻሌነት፣ የሚያቅተዉም ሆነ የሚያጣዉ ነገር አይኖሬነትና ገዘፍ ያለ መተማመን ይታይባቸዉ ነበር። ህፃናት በአባታቸዉ ለመጫዎት ወደ ሰማይ ሲወረወሩ የሚያሳዩት ፍልቅልቅነት በአባታቸዉ ላይ የአይሳኔነት መተማመን ሲፍለቀለቁ ይታያሉ፣ በዚያ ደረጃ የሚቀራረቡ አባትና ልጆችን ተመልክተናል ይላል በዕለቱ አብሮት የነበረዉ ጓዴኛዉ፤

ከምሳ በኋላ ወላጅ አባቱን ለመጠየቅ መገናኛ ሰፈር አምርቶ የአባቱንና የቤተሰቡን የደህንነት ሁኔታ ከጠየቀ በኋላ ጊዜ ሳያባክን ወደ ቢሮ ነበር የተመለሰዉ፣ በዕለቱ ያቀዳቸዉን የቢሮ ተግባራቶች ከሸከፈ በኋላ የዕለቱ የስራ ቀን ሲጠናቀቅ መንፈሱን ወደሚድስበትና ስለስራ ወደሚወያይበት መናፈሻ አካባቢ ሂዶ በስራ፣ በቤተሰብ ጥየቃና በበጎ አድራጎት ተግባራቶች ሲዝል የዋለዉን ሰዉነቱን ሲያፍታታ አመሼ………

ይች ምሽት የማቅ ነበረች፣ ጀንበሯ ራሱ ስትገባ ሙሌን ስማዉ የገባች ይመስላል። ለሙሌ እየጠለቀች ያለችዉ ፀሃይ ተመልሳ አትመጣም (የምሯን ነዉ)፣ ሆዳምና ቀፈታም ገዳዮቹ ከጀርባዉ እያደቡ መሆኑን ታዉቃለች ግን አንደበት ስለሌላት አትናገርም። ሙሌን ሃቀኛዉን ፍትሃዊዉን ሰዉ ቻዉ ያለች ትመስል እገሯንም እጇንም ዘርግታ ነበር የጠለቀችው።

ምሽት አንድ ሰዓት ሲሆን ከሾፌሩ ጋር ወደ ቤቱ ጉዞ ሲጀምር የሞት መላዕክ የገዳዮች ሰይፍ የተጠጋዉ መሆኑን ያልተረዳዉ ሙሉጌታ ከበዴ በነፃነት ጉዞዉን ቀጥሏል፣ የተረገመች ሰኞ ምሽት ወንድሜን የበላች ጩኻ መናገር ያቃታት፣ ከኋላ የሚያደባው የሞት መላዕክ መከላከል ያቃታት ሰኞ ምሽት ይላታል ታሪክ ነጋሪያችን እንባዉን በሶፍት እየጠረገ …………… በላተኛዋ ሰኞ ምሽት ……… እያለ ከባድ ሃዘን.........
አንድ ሰዓት አካባቢ የተደወለልኝ ስልክ ሙሉጌታን እኮ መቱት የሚል ድምፅ ሰማሁ፣ ሟርተኛ ምን ታሟርታለህ አልኩት ወላሂ በቦንብ መቱት አለኝ። የምርህን ነዉ ተጎድቷል ፈነከቱት አልኩኝ ቀለል አድርጌ…….. እኔ ያለሁበት ሰፈር ሙሌ ከወደቀበት በጣም ሩቅ ነዉ።

ጨነቀኝ ለማን ልደዉል ፈራሁ ለማን ላዉራ
ሙሌ ከተመታ በሗላ ማንም የሚደርስለትም ሆነ አይዞህ ወንድሜን ብሎ ቀና የሚያደርገውና የሚፈሰውን ደሙን የሚያስቆምለት ጓደኛ፣ወንድም፣ ዘመድ አዝማድ፣ወዳጅና የቅርብ ረዳት የሚሆነው ሰው እንኳን አላገኘም ነበር። ከ40 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ፖሊስ ሲደርስ ሙሌ ከጌታዉ ጋር ተገናኝቷል (ሁሉም ተጠናቋል)😭😭😭😭😭ኡፍ፣ ገዳይ ሰይጣን አራጆቹ በሙሌ ነፍስ ላይ ጨክነዋል፣ ሌቦች ሆዳሞች ፈጣጦች ሳያፍሩ ሙሌን ፍትሁን ገደሉት፣ ፖሊስ አስክሬኑን አፋፍሶ ሆስፒታል ወስዶታል እኔም ስደርስ ሌሎች ወንድም ወዳጆቹ ነበሩ፣ ከፍተኛ ድንጋጤ ሞቱን ያለመቀበል በመካከል ተቃቅፎ መላቀስ በቁጭት ከንፈር መብላት የተወዛገበ ስሜት እያስተናገድን ነበር።

በዚህ መካከል አደጋዉን የሰሙት ሞቱን ያረጋገጡት የደሴ ከተማ አመራሮች ከንቲባዉን ጨምሮ ማንም ዝር ያለ አካል አልነበረም፣ ሙሌን ሙቶም ይፈሩት ይሆን አንጃ እኔ …… ከጉሬያቸዉ ሁነዉ መሞቱን በፌስቡክ ያሳወጁና ያስነገሩ አካላት የሙሌ አስክሬን ሆስፒታል ተኝቶ ለማስተባበርም ሆነ ለማፅናናት በድንጋጤ የመጣ አንድም የአመራር አካል አልነበረም። አስክሬኑን ወደ ቤት ለመዉሰድ ሆስፒታሉ አንቡላንስ እንዲተባበር ጠየቅን አሁን አይወጡም ነበር ምላሻቸዉ፣ ብዙ ያገለገለዉ ፍትሃዊው ልጅ ከርከሮ ጥርስ ጅቦች ጋር የተላተመዉ ወጣቱ ዳኛ ሙሉጌታ ያገለገላት፣ ለፍትህ ጅቦችን የተጋፈጠላት ደሴ አስክሬኑን ለማድረስ የሚሆን መኪና አጣችለት፣ የግል መኪኖችም እዚሁ ደሴ እስከ 20ሺ ብር ጠየቁን፣ በመካከል ሙሉጌታ መሆኑን ያወቀ አንድ ቤተሰብ

4 months ago

ከነፍሷ በላይ የምትወድህ አንዲት እንስት ትኖራለች። አንተ ዘንድ ከሁሉም እንስቶች ልዩ ሆና ትቀርባለች። ጉዳዮቿን በሙሉ አንተ ፊት ለመተረክ አታመነታም፣ አንተን ለማየት የምትከፍተው ዓይን እርሷ ጋር የተለመደው ዓይነት አይደለም። ልዩ ነው!

…እብድ ናት። ካንተ ጋር ስትሆን ብቻ… ቀልዱንም ቁምነገሩንም የምትቀላቅል እብድ ትሆናለች። እንዳሻት የምትሆነው ባንተ ስለምትሰክንና ባንተ ስለምትተማመን ነው። እቅፍህ ዘንድ የትኛውም ዓለም ላይ የማታገኘው እረፍት ይሰማታል። አንተ ዘንድ ሊያባብሏት እንደምትፈልግ ህፃን ናት።  ከሌሎች ጋር  ደግሞ የንግግሯን ጥንካሬ ታያለህ። ክብሯን ለማስጠበቅ ስትለፋ ትመለከታለህ። ካንተ ውጪ ያለው ዓለም ውስጥ አንተ ጋር እንደምታያት ዓይነት ለስላሳ አትሆንም።

…እና ይህች ልዕልት አንድ ጊዜ ብቻ ነው በህይወትህ የምትመጣው። ከርሷ ጋር አብሮ የሚመጣው እንክብካቤ፣ ፍቅር፣ እዝነት  አንድ ጊዜ ብቻ ነው እድሉን የሚሰጥህ። ወይ ጠብቀሃት ትቆያለህ አሊያም እርሷን በማጣትህ ትከስራለህ። የርሷን ዓይነት ስሜት 1% ያላትን እንስት ፍለጋ ትንከራተታለህ። አታገኛትም።

( በዚህ ልክ የሚወዷችሁን እመቤቶች ጠብቁ ነው መልዕክቱ)

?

4 months ago
4 months, 3 weeks ago

እውነተኛው ሩቃእ ክፍል 5️⃣

? (የሁለተኛ የህክምናው ደረጃ ህክምናው ሲጀመር የሚቀሩ የቁርአን ሱራዎችና አያዎቻቸው)

? መጀመሪያ እጃችን በታመመው አካል ማስቀመጥ ከዛ አያዎቹ እንደሚከተሉ እናውሳቸው

? ሱረቱል ፋቲሀ

? ሱረቱል በቀራ የመጀመሪያ አያዎች

? ሱረቱል በቀራ ከ163-164 ያለው አያ

? ሱረቱል በቀራ አያተል ኩርሲይ ከ255-257

? ሱረቱል በቀራ የመጨረሻ አያአመነ ረሱል 288-286 ያለው አያ

? ሱረቱል ኢምራን ከ18-19

? ሱረቱል አእሯፍ ከ54-56

? ሱረቱል ሙእሚኑን ከ115-118

? ሱረቱ ሷፋት ከመጀመሪያው - 10 ኛው አያ

? ሱረቱል አህቋፍ ከ29-32

? ሱረቱ ራህማን ከ33-35

? ሱረቱል ሀሸር ከ21-24

? ሱረቱል ጂኒ ከመጀመሪያው -9ኛው አያ

? ሱረቱል ኢህላስ ሙሉውን

? ሱረቱል ፈለቅ ሙሉውን

? ሱረቱ ናስ ሙሉውን

?? በነዚህ ማከም

የዚህን ጊዜ 3️⃣ ነገሮችን ልብ በል

ሀ) ምንም ሳያወራ ታባርረዋለህ ይህ ገሩ ነው መመኘትም ያለብህ ይህንኑ ነው ድካም ልፋት ዝባዝንኬ ይቀራል ማለት ነው የግድ ካላስለፈለፍኩት ፊት ለፊት ካልተጋፈጥኩት አትበል
ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ጠላትን ፊት ለፊት መግጠምን አትመኙ በሚለው ሀዲስ በመስራት

ለ) ለፍልፎ ጮሆ ኡኡ እናቴ ድረሺልኝ ሲል ወይም ወይኔ እኔ እከሌው ጀግናው አቃጠሉኝ ሊል ይችላል በቃ እሪ ይላል

ሐ) ከሁለቱም ውጪ እንደ ላብ እንደ መንቀጥቀጥ እንደ መደበቅ አይኖቹ እንደመጭፈን ሊያደርገው ይችላል ከፍ ያለ መንቀጥቀጥ መፈራገጥ ሊኖረው ይችላል ማለት ነው
እነዚህ ማግኘትህን መከታተል አለብህ

አላህ ከአመፀኞች አመፅ ይጠብቀን

??ሼር ሼር ሼር??

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 4 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 11 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 day, 10 hours ago