ቬኒሲያ

Description
" ኵሉ ጽድቅ ወኵሉ ጥበብ እምኀበ እግዚአብሔር ውእቱ"

ይህ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጣፋጭ ታሪኮች ሚቀርቡበት ቻናል ነው ። @Venisiya21 አዲሱ ቬኒሲያን በዚህ ተቀላቀሉን

ለአስተያየትዎ @Get_loza ላይ ያድርሱን
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

3 years, 2 months ago

ተጠንቀቁ እንጂ አትፍሩ!

አንድ ጊዜ አንድ ንጉስ ከጦር አጃቢዎቹ ጋር ሆኖ ወደ ሌላ ሃገር ጉዞ ሲደርግ አንድ እጅግ አጥፊ የሆነ አውሎ ነፋስ ወደ እሱ አገር አቅጣጫ በመገስገስ ላይ እንዳለ ተመለከተና ባለው የጦር ኃይል አውሎ ነፋሱን አስቁሞ፣ “ወደ እኔ ሃገር አቅጣጫ በመሄድ ላይ ነህ፡፡ ከእኔ ሃገር ሰው ማንንም እንዳማታጠፋ ቃል ካልገባህ አታልፍም አለው” አውሎ ነፋሱም፣ “በእርግጥ ነው ወደዚያ አቅጠጫ ነው የምሄደው፤ ነገር ግን የአንተን ሃገር ሕዝብ በፍጹም እንደማልነካ ቃል እገባልሃለሁ” አለው፡፡

ንጉሱ ከጉዞው ሲመለስ ከሃገሩ ሰዎች በርካታዎቹ እንደሞቱ ሰማ፡፡ በጣም በመቆጣት አውሎ ነፋሱን ተከታትሎ ደረሰበትና፣ “ማንንም እንደማትነካ ቃል ገብተህልኝ ለምንድን ነው ብዙ ሰው የገደልከው?” አለው፡፡ አውሎ ነፋሱም እዲህ ሲል መለሰ፣ “እኔ በሃገርህ አጠገብ አለፍኩኝ እንጂ የሃገርህን ህዝብ አንዱንም አልነካሁም፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ ግን ከባድ አውሎ ነፋስ መጣ የሚል ወሬ ተወርቶ በፍርሃትና በድንጋጤ አንዳንዱ በልብ ድካም፣ አንዳንዱ ሲሯሯጥ እርስ በርሱ ተረጋግጦ ነው የሞተው”፡፡

አንዳንዴ በሃገራችን ከሚከሰተው ችግር ይልቅ በችግሩ ላይ ያለን አመለካከት፣ የሚወርሰን ፍርሃት፣ የምንሰጠው ተገቢ ያልሆነ ምላሽና የፍርሃትና የድንጋጤ ስሜታችን ከማየሉ የተነሳ አዋቂዎቹ የሚነግሩንን መመሪያ በአአምሯችን አስበን አለመከተላችን ነው የሚያጠፋን፡፡

አንባቢዎቼ በወቅቱ በደረሰብን አስጊ ሁኔታ ስለራሳችንና ስለቤተሰቦቻችን የማሰባችን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በምክንያት የለሽ ፍርሃት ከመተራመስና ራስን ለከፋ ነገር ከማጋለጥ እንጠበቅ፡፡

በዚሁ አጋጣሚ ንስሐ ገብተን ፣ ቅዱስ ቁርባንን ተቀብለን እንዘጋጅ

ፈጣሪ እናንተንና የእናንተ የሆኑትን ሁሉ ይጠብቅላችሁ፡፡

╭══•:|★✧♡?♡✧★|: ══╮
@Venisiya21 @Venisiya21
╰══•:|★✧♡?♡✧★|: ══╯

3 years, 10 months ago

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን #አብይ ፆም

ዐቢይ ለምን ተባለ ቢሉ ‹‹ዐበየ›› ማለት ከፍ አለ ማለት ሲሆን ከዚህም ግስ አቢይ የሚለው ቅጽል ይገኛል፡፡ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፡-

ሀ. ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ
ለ. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ
ሐ. ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም 'ትዕቢት' 'ስስት' 'ፍቅረ ነዋይ' ድል የተመቱበት ስለሆነ ነው፡፡

በቤተክርስቲያን ስያሜ መሰረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፡-

  1. ዘወረደ
    የዐቢይ ጾም የመጀመሪያው ሰንበት ሲሆን ይህም ቅድመ ዓለም የነበረ ዓለምን ፈጥሮ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ ከሰማየ ሰማያት መውረዱንና ከእመቤታችን ከቅድስተ ቅዱሳን ከንጽሕተ ንጹሐን ከድንግል ማርያም መወለዱን የሚያመለክት ሥያሜ ነው፡፡

  2. ቅድስት
    ይህ የሁለተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን የተባለበትም ምክንያት ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና ስለሚያወሳ ነው፡፡ እንዲሁም ይህ ዕለት ዕለተ እግዚአብሔር የተባለች የሰንበት ክርስቲያን ቅድስናን ያመለክታል ምክንያቱም የዚች ዕለት ጌታ እርሱ ቅዱስ እግዚአብሔር ነውና ስለዚህም ዕለተ ሰንበት ቅድስት ተብላለች፡፡

  3. ምኩራብ
    ይህ የሦስተኛው ሰንበት ስያሜ ሲሆን በዚህ ሰንበት ጌታ በመዋዕለ ትምህርቱ በምኩራብ ገብቶ ማስተማሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም ይህች ዕለት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምኩራብ ገብቶ እንዳስተማረ የሚታሰብበት ዕለት ነው፡፡ ምኩራብ ማለት የቤተ አይሁዳውያን የጸሎት ቤት ነው፡፡

  4. መጻጉዕ
    ይህ የአራተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱ እውራንን ማብራቱ ለምጻምን ማንጻቱ ሽባዎችን መተርተሩ የሚያነሳ መዝሙር የሚዘመርበት እንዲሁም እነዚህ ሁሉ ድንቅ ገቢራተ ታምራቶች የሚዘከሩበት ዕለት ነው፡፡

  5. ደብረ ዘይት
    ይህ የአምስተኛው ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ነገረ ምጽአቱን እንዳስተማረ የሚወሳበት ሰንበት ነው፡፡ ደብረ ዘይት ማለት ወይራ የበዛበት ተራራ ማለት ነው፡፡

  6. ገብርኄር
    ይህ የስድስተኛው ሳምንት ሰንበት ስያሜ ሲሆን ይህም ዕለት ለጌታው ታማኝና በጎ የሆነው ባርያ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ ተብሎ እንደተመሰገነ የሚነገርበት ዕለት ነው፡፡

  7. ኒቆዲሞስ
    ይህ የሰባተኛው ሰንበት ስያሜ ነው፡፡ ይህም ዕለት ኒቆዲሞስ የተባለው የአይሁድ መምህር በሌሊት ወደ ጌታው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ እየመጣ ይማር እንደነበረ ይታሰብበታል በዚም ዕለት የኒቆዲሞስን ታሪክ የሚያስታውስ መዝሙር ይዘመርበታል፡፡

  8. ሆሳዕና
    ይህ የስምንተኛው ሳምንት ሰንበት መጠሪያ ሲሆን ይህም ዕለት በነቢዩ በዘካርያስ ላይ የተጻፈው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችም መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያይቷ እና በውርንጭላይቷ ላይ ተቀምጦ ሆሳዕና በአርያም ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ ተብ እየተመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ መግባቱ የሚተሰብበት ዕለት ነው፡፡ ሆሳዕና ማለት ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::
    ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን፡፡
    ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

4 years ago
4 years ago

ስደተኞች ክፍል 8
የቆርኔሌዎስ ሚት ኔርያ ንጭንጯ ብሶበታል፡፡ ሄለንን ቁም ስቅሏን ታሳየታለች፡፡ ለአንድ ሰሞን አዛዡ ባልዋ ለግዳጅ ከወጣ ጦሟን አውላ ታሳድራት ነበር፡፡ ሄለን ከጸሎት በቀር ውላ ስታነብ ታድራለች፡፡ አንደበትዋ ዝምታን እንጂ መናገርን አልለመደውም፡፡ በኋ ግን ቆርኔሌዎስ ሁኔታውን እየተረዳው በመምጣቱ ወደ ግዳጅ ሲጣ የሚበላ ነገር መኝታ ቤቷ ውስጥ ደብቆ ያስቀመጥላት ጀመር፡፡ ነገር ግን የኔርያን ጠባይ የሄለን ደግና የዋህ ልቡና ሊቋቋመው አልቻለም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ክርስቲያን መሆንዋ ምርር ያስብላታል፡፡ መልሳ ደግሞ የወንድምዋን ምክሮች ስታስባቸው ትጽጽናናለች፣ ትጸናለችም፡፡ አንድ ቀን ከዚህ አስከፊ ኑሮ ወጥታ ወደ ኢየሩሳሌም እንደምትጓዝ በዚያም ወንድሟን እንደምታገኘው ስታሰብ ደግሞ ብሩህ ተስፋ ይታያታል፡፡

መቼም በክርስትና ጉዞ ተስፋ ከሌለ የሚጣፍጥ ነገር ባልኖረም ነበር፡፡ ሕይወት የጨለመ ኑሮ የመረረ ሲመስል ፊት ለፊት የሚጠብቀንን የአባታችንን የእግዚአብሔርን በረከት ያዘጋጀልንን መንግሥተ ሰማያት ባናስብ ኖሮ ሁላችንም ራሳችንን ባጠፋን ነበር፡፡ ነገ የኛ በእግዚአብሔር እጅ መሆንዋን ባንረዳ እግዚአብሔር ሁሉን ለበጎ እንደሚያደርገው ባናምን ኖሮ መንፈሳችን ተሠብሮ ስብእናችን ይሞት ነበር፡፡ ነገር ግን ተስፋ አለን፡፡ ተስፋ ኑሮን የሚያለመልም የመንፈስ ውኃ ነው፡፡

ቆርኔሌዎስ ወደ ጎረቤት ሀገር ሰው ልኮ ማርቆስን አስፈልጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ቀናት ጀምሮ የት እንደሄደ አለመታወቁን ነገሩት፡፡ ይህን ለሄለን አልነገራትም፡፡ ተስፋ ትቆርጣለች ብሎ ፈራ፡፡ሄለንን ምን እንደሚደርጋት ዘወትር ያሥጨንቀዋል፡፡ በእንዲህ አይነት ኑሮ እርሷን ሆነች እርሱ እስከ መቼ ለመዝለቅ እንደሚችሉ ሲያስበው ዙርያው ገደል ይሆንበታል፡፡ እርስዋ ኢየሩሳሌም ሆይ የሚለውን መዝሙር መኝታ ቤቷ ውስጥ ሆና ዝቅ ባለ ድምጽ ስትዘመር በሰማ ቁጥር ልቡን ይበላዋል፡፡ ላይ ላዩን ሳይሆን ውስጥ ውስጡን ያነባል፡፡ በመጨረሻ የተደገሰልትን የሞት ድግስ ያላወቀው ቆርኔሌውስ ይህን ጭንቀቱን ጨዋ እየሆነ በመምጣቱ ለወደደው ለአኒባል ሊያየው ፈለገ፡፡ አኒባል ደግሞ መርዙን ጨብጦ ቆርኔሌዎስን ለውይይት ሳይሆን ለግድያ እየጠበቀው ነው፡፡

ለኔርያ የባልዋ ሄለንን መቅረብ፣ ወደ መኝታ ቤቷ ገብቶ “ኢየሩሳሌም የሚለውን መዝሙር መዘመርና ጸጉሯን እየደባበሰ ሲያወራት መመልከት ቅናቷ ያባብስባታል፡፡ በመጥረቢያ በያቸው በያቸው የሚል ስሜት ፈጥሮባታል፡፡ ባልዋን የተነጠቀች እየመሰላት፡፡ ቆርኔሌስ ደግሞ ደጋግሞ ይህን ክፉ ዐመሏን እንድትተው ቢነገራትም የምትሰማ አልሆነችም፡፡ እንዲያውም እየደለላት መሰላት፡፡ አንድ ቀን ኔርያ ቤቷን ስታጸዳዳ በጨርቅ የተጠቀለለ የሚሰነፍጥ ነገር አገኘች፡፡ እየፈራች በእንጨት ጎልጉላ ፈታችው፡፡ የተቀበረባት መተት ስለመሰላት ድንጋጤና ንዴት ወሯታል፡፡ በመጨረሻም በአጠገብዋ በሚገኘው መንደር ወዳለው መድኃኒት ዐዋቂ በምሽ ገስግሳ ወፈር ያለ ጉርሻ በማስታቀፍ ምንነቱን ጠየቀችው፡፡ ያን ጊዜ ነበር ገዳይ መርዝ መሆኑን የተረዳችው፡፡
“የነዚያ እባቦች መርዝ ነው! እኔን ኔርያን በመርዝ ሊገድሉ ከዚያ እነርሱ ሊምነሸንሹበት” ከት ብላ ሳቀች፡፡ “እኔ ልጅት ልኳን እሰጣታለሁ፡፡” እየተስፈነጠረች ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ ያን መርዝ የደበቀው ግን አኒባል ነበር፡፡ ካመጣው መካከል ግማሹን ቀንሶ ካዘጋጀ በኋላ የቀረውን ለመጠባበቂያ ደበቀው፡፡ ነገረኛ የማይጎለጉለው የለምና ኔርያ አገኘችው፡፡ ያ ቤት የሞት ጥላ አጠላበት፡፡ ኔርያ ለሄለን አኒባል ለቆርኔሌዎስ፡፡
አንድ ቀን ኔርያ በቤትዋ ግብዣ አደረገችና ቆርኔሌዎስን አኒባልንና ሌሎች ጓደኞቹን እንዲጋብዝ ነገረችው፡፡ ቆርኔሌዎስ ሄለን ከመጣች ጊዜ ጀምሮ የቀረ ግብዣ ዛሬ እንዴት ትዝ እንዳላት ገርሞት በደስታ ተቀበለው፡፡ አኒባል ደግሞ ይቺን መሰልዋን አጋጣሚ በጉጉት ይጠብቃት ነበር፡፡ ስለዚህም ሲመጣ ባዶውን አልነበረም፡፡ መርዙን ሰልቆ እንጂ፡፡ ኔርያ በጓዳዋ ጉድጉድ ስትል አኒባል ሊረዳት ገባ፡፡ የተጠሩት መኳንንት ስለነበሩ በማስተናገዱ ቢሳተፍ ጥያቄ ውስጥ እንደማይጥለው አውቋል፡፡ ኔርያም ለተንኮሏ መንገድ እንደሚከፍትላት ስለተረዳች ተቀብላዋላች፡፡

መጠጡን ከቀንድ ወደ ተሰሩት ዋንጫዎች እየቀዳች የማን እንደሆኑ ለይታ ሰጠችው በመጀመሪያዎቹ ዋንጫዎች ላይ ሁለቱም ምህረት አድርገዋል፡፡ ግን አልተነጋገሩበትም፡፡ ሁለተኞቹ ዋንጫዎች ጓዳውን ሲለቁ ግን አስቀድሞ የኔርያ መርዝ በሄለን ዋንጫ ላይ ተሞጅሮ ነበር፡፡ አኒባል ደግሞ ልቡ ዘዴ እያውጠነጠነ ነው፡፡
“እስቲ እርስዎ ብቅ ይበሉና ብሉ ጠጡ ይበሉ” አላት የተፈለገች አስመስሎ፡፡ “እንግዳ ጋብዘው ጓዳ ሲቀመጡ ዛሬ የመጀመሪያዎ እኮ ነው ኔርያ እውነቱን መሆኑ ገባት፡፡ ከዚህ በፊት ፈገግታ እየጋበዘች ታስተናግዳለች እንጂ ጓዳ ተቀብራ አታመሽም ነበር፡፡ “አንተ መጠጡን ይዘኸው ና!” አለችና ልብስዋን አስተካክላ ወደ እልፍኙ ብቅ ስትል አኒባል መርዙን በቆርኔሌዎስ ዋንጫ ላይ ዶለው፡፡

ይቀጥላል…..

ቬኒሲያ ?:
╭══•:|★✧♡?♡✧★|: ══╮
@Vensi @Vensi @Vensi
╰══•:|★✧♡?♡✧★|: ══╯

4 years ago

ወንድ የሆነ ይቀንሰው

አሁን ያለንበት ወቅት ጾመ ነቢያት ማለትም የገና ጾም ነው፡፡ ይህ ጾም ከገባ ሳምንታት ቢልፈውም አንገታቸው ላይ ማተብ ያሰሩ ሁለት ባልንጀራሞች ከአንድ ሥጋ ቤት በረንዳ ላይ ሆነው ይህን ጥሬ ሥጋ በወግ በወጉ እየቆረጡ ወደ ሆዳቸው ይልኩታል፡፡ በመሐል አንደኛው የፕቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጆች ጾም ይቀነስ እያሉ በየመንደሩ የሚያስወሩትን ወሬ ሰምቶ ኖሮ “ጾም ሊቀነስ መሆኑን ሰምተሃል እንዴ? ሲል ባልንጀራውን ይጠይቀዋል፡፡ ባልንጀራውም የጎረሰውን ጥሬ ሥጋ እያኘከ በእጁ በያዘው ቢላ ደግሞ በቀጣይ የሚጎርሰውን እየቆረጠ “ማነው እሱ ቀናሹ?” ሲል ይጠይቃል፡፡ ባልንጀራውም “እኔ ምን አውቄ ያው ቄሶቹ ይሆናሉ፤ ሌላማ ማን ሊሆን ይችላል” ሲል ይመልሳል፡፡ በዚህ ጊዜ ባልንጀራው በስጨት እንደማለት ካደረገው በኋላ በእጁ ላይ ያለውን ቁራጭ ሥጋ በእንጀራ ጠቅልሎ በአዋዜ እያጠቀሰ “ይህማ አይደረግም፤ እስኪ ወንድ የሆነ ይቀንሰውና እንተያያለን፡፡ አለ ይባላል፡፡

ይገርማል አንዳንድ ሰው ክርስትናውን የሚኖረው አምኖበት ሳይሆን በስሜት ነው፡፡ እሱ ራሱ የሚቀንሳቸውና የሚሽራቸው በርካታ የቤተክርስቲያን ሥርዓቶች እያሉ ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚከራከርን ሰው ምን ትሉታላችሁ?በዚህ ታሪክ መነጽርነት ሁላችንም ወደ ራሳችን እንመልከት፡፡ እውነት ለመናገር ከሰባቱ አጽዋማት በትክክል እየጾምን ያለነው ስንቱን ነው፡፡

እስኪ እውነት እንነጋገር ያለ ቤተክርስቲያን ውሳኔና ቀኖና ማንም ሳያሰናብተን በራሳችን ስልጣን የሻርናቸውና የማንጾማቸው ሌሎችም እንዳይጾሙአቸው የምናከላክላቸው አጽዋማት የሉምን ስለምን ይህንን እናደርጋለን?እኛ ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ ሆነን ሌላውን ወደ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ማምጣት እንዴት እንችላለን?

ቬኒሲያ ?:
╭══•:|★✧♡?♡✧★|: ══╮
@Vensi @Vensi @Vensi
╰══•:|★✧♡?♡✧★|: ══╯

4 years ago

[ጸበል የቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን መንፈሳዊ ሕክምና ነው፡፡ ቤተ-ክርስትያንን መንፈሳዊ ሆስፒታል ናት ።

‹‹ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፡፡ ስለዚህ ሄዶ ታጠበ/ተጠመቀ/ እያየም መጣ›› ዮሐ 9÷7](https://t.me/joinchat/AAAAAEvYcTPcvC4BF9NK4g)

4 years ago

??? ያጣ ለማኝ ???
???????

ቀበሮዋ አንድ የበሰለ የወይን ዛላ ተንጠልጥሎ ለመብላትም አስጎምጅቶ ታገኛለች፤ በመሆኑም በጣም ካልዘለለች በስተቀር እንደማታገኘው ስለታወቃት እንጣጥ እያለች ብዙ ሞከረች። ይሁን እንጂ ወይኑ እንዳሰበችው በቀላሉ የምትደርስበት አልሆነም። ወደኋላ ተንደርድራ በጣም ዘለለችና የመጨረሻ ሙከራ አደረገች። ይሁን እንጂ ፈጽሞ ልትደርስበት አልቻለችም። ወይኑ በአለባበሱ በጣም ልዩ ነው፤ ለዐይን የሚያምር ለመብላትም የሚያስጎመጅ ነው። ወይኑን ትታ እንዳትሄድ ያስጎመጃል እንዳትበላው ደግሞ ስትዝል ብትውልም አልደረሰችበትም። ስለዚህ ''እንደውም ይኼ ወይን አልበሰለም'' ብላ ትታው ሔደች።

?????????

"ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሔዳል'' የሚባለው ለእንደዚህ ዐይነቱ ነው። የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለመናፍቃን ያልተመቸችው አላዋቂ ወገኖቻችን እንደሚሉት የዶግማና የቀኖና ችግር ኖሮባት ሳይሆን ይህንን መኖርና መፈጸም ስላቃታቸው ብቻ ነው። መጾም ያቃታቸው ጾምን አያስፈልግም ሲሉ ንጽሕናቸውን ያጎደፉና ቆባቸውን የጣሉት ደግሞ ምንኩስና አያስፈልግም ይላሉ። ያቃተንንና ያልተደረሰበትን ነገር ሁሉ አያስፈልግም ብሎ መንቀፍ የቀበሮ ጠባይ ነው። የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሥጋዊ ዕውቀት የማትመረመር ብትሆንም ትምህርቷ ግልጽ፤ ተልኮዋም የታወቀ ነው "ወንጌላችን የተከደነ ቢሆንም እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉት ነው" እንዲል 1ኛቆሮ 4፥3

????????????

ቬኒሲያ ?:
╭══•:|★✧♡?♡✧★|: ══╮
@Vensi @Vensi @Vensi
╰══•:|★✧♡?♡✧★|: ══╯

4 years ago

የማይበድል ባርያ
የማይምር ጌታ የለም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እብሉይ የተባለ በግ ጠባቂ ነበር ከኃጥያት ስራ የቀረው የለም። ያመነዝራል፣ ይሰርቃል ይገድላል በዚህም የሰይጣንን ሥራ እየፈጸመ ፵(40) ዓመት ኖረ።

በአንዲት ዕለትም ከቀኑ እኩሌታ የመውለጃዋ ጊዜ የደረሰ እርጉዝ ሴትን አየ ሰይጣንም በልቡ ክፉ ሃሳብን ጨመረበት እንዲህም አለ ሆዷን ሰንጥቄ ህጻኑ እንዴት እንደሚተኛ ማየት አለብኝ ብሎ ጸጉሯንም ጎትቶ ከመሬት ጣላት ሆዷንም በቢላ ሰንጥቆ ልጁንም እናቱንም ገደላቸው።

በግ አርቢውም የሰራውንም ኃጥያት ተመልክቶ እጅግ አዘነ የማይበድል ባርያ የማይምር ጌታ የለም ብሎ አምርሮም እያለቀሰ ወደ በረሀ ሄዶ ፵(40) ዓመት ስለበደሉ አለቀሰ አጋንንትም ተገልጸው ከአንተ ዲያቢሎስ አባታችን ይሻላል እያሉ ያፌዙበት ነበር።እሱ ግን በተጋድሎ በረታ።

የእግአብሔር መልአክም ተገልጾ ስለ ሴቲቱ ደም ጌታ ይቅር ብሎሃል ስለ ልጁ ግን ይቅር አላለህም አለው አባ እብሉይም ተጨማሪ ፵(40) ዓመት ተጋደለ ጌታም ይቅር አለው።(ስንክሳር የካቲት ፭)
?????????
ክርስቲያን ሆይ እግዚአብሔር ይቅር ባይ መሐሪ አምላክ ነው እንደ ቸርነቱ ነው እንጅ እንደኛ በደልማ በጠፋን ነበር።ስለዚህ ንስሐ ከመግባት አንቦዝን
@Vensi @Vensi @Vensi

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago