Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago
ታሕሳስ 15 እንኳን ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ወርሐዊ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ የቅዱስ አባታችን ረድኤትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡ አሜን!
✧ሩፋኤል ብዬ ስጠራህ✧
ሩፋኤል ብዬ ስጠራህ
ሚስጥሬን ሁሉ ሣወራህ
ትላንት የረዳኝ ጸሎትህ
ዛሬም ይድረሰኝ ለልጅህ/2/
ሩፋኤል ብዬ አንደበቴ ለምዶት ስምህን
" " " " " " ልጅነቴ ቀምሶ ፍቅርህን
" " " " " " የህይወቴ ቅጥር ሲላላ
" " " " " " ነብሴ ትጮሀለች ሩፋኤል/2/ብላ
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ሩፋኤል ብዬ ካምላኬ ስትላክ ለምህረት
" " " " " " ስጠብቀኝ ቀንና ለሊት
" " " " " " ባስከፋህ በትዕግስት እለፈኝ
" " " " " " ምልጃህ ረድኤትህ ያግዘኝ እኔን ይደግፈኝ
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
ሩፋኤል ብዬ ህመሜ እንዳይጸና ክፋቱ
" " " " " " መድሐኒት እንዲሆን ሀሞቱ
" " " " " " ካጠገቤ እንዳትርቅ ከጎኔ
" " " " " " ትዳሬ እንዲጸና ሩፋኤል እንዲበራ አይኔ
✥•┈•●◉༒ ናሁ ሰማን-ዜማ ༒◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
✞ @Nahuseman256✞
✞ @Nahuseman256 ✞
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯
ታህሳስ 8/2017 #ፃድቁ_አባታችን_አቡነ_ኪሮስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፃድቁ ስም ለምናመሰግንበት ለፃድቁ አባታችን #አቡነ_ኪሮስ የልደት መታሠቢያ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን
👉 #አቡነ_ኪሮስ አባታቸው ንጉስ ዮናስ እናታቸው እንስራ
ይባላሉ እሊህም #እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው ሀገራቸው ሮም ሲሆን በታህሳስ 8 ቀን ተወለዱ የመጀመሪያ ስማቸው ዲላሶር ይባል ነበር
👉በኋላ አባታቸዉ ከሞቱ በኋላ ሀብት ንብረታቸዉን ተካፍለዉ ለድሆች ከመፀወቱ በሑዋላ ከአባ #በቡነዳ_ገዳም ገቡ
👉በ17 አመታቸው ስርአተ ምንኩስናን ተምረው ከአባ በቡነዳ እጅ ስርአተ #ምንኩስናን ተቀበሉ ከዚህ በሁዋላ በፆምና በፀሎት ተወስነው ኖሩ
👉ስለ አለም መከራ ለ 40 ዘመን ተኝተው ሲፀልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ #መላዕክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡርን ቃል ሰምቶ ወድቋልና ጌታም ድምፁን ያሰማኝ አሏቸው በኋላም #ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይቷቸው በመጨረሻም ጌታችን ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል
👉ቃል ኪዳናቸውም መካኖችን ልጅ የሌላቸው #ገድላቸውን
አቅፈው ቢያለቅሱ #ፀበሉን ቢጠጡ ስምሕን ቢጠሩ የመካኒቱን ማሕፀን እከፍታለሁ
👉ህፃናት የሚሞትባቸው #እንዳይሞትባቸው አደርጋለሁ በንፁህ ገንዘቡ ቂም እና በቀልን ሳይዝ በሕግ በስጋ ወደሙ ለፀና ሰው በስምህ በተሰራው #ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ እሰጠዋለሁ ብሎ ጌታችን ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል
👉ከዚህም በኋላ በተወለዱ በ 270 አመታቸው ሐምሌ 8 ቀን አርፈዋል #የፃድቁ_አቡነ_ኪሮስ ረድኤት በረከታቸዉ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️
👉ታህሣሥ 8/2017
✧ብፁእ ኤልያስ✧
ብፁእ ኤልያስ ሠረገላው እሳት
የሰላም ዝናብ የዘነበለት
ሞት ያልቀመሰ ነብዩ ኤልያስ
ልቤ በሀሳብ............. ኤልያስ
አዝኖ ሲጨነቅ
የኤልሳ መምህር
ልነግርህ ስማኝ
ከጭንቀቴ እንዳርፍ
ፀጋ በረከት ለእኔም አድለኝ
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
አካብና ኤልዛቤል............. ኤልያስ
ለጣኦት ሰግደው
ዝናብ እንዳይሰጥ
ሰማይን ለጎምክ
ህዝቡም ተራብ
በዛን ሰዓት ኤልያስ
ምህረት ለመንክ
በአንድ ቀን ዘርተህ
በአንድ ቀን በቅሎ ህዝቡንም መገብክ
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
በእሳት አምሳል............. ኤልያስ
መንፈስ ቅዱስን
የተቀበልከው
ምህረቱ ብዙ
ቁራ የመገብክ
ያንን ህብስት
ለፍሴ ስጣት በሠረገላህ
✥•┈┈•●◉አዝ◉●•┈┈•✥
በብሔረ ህያዋን............. ኤልያስ
የምትኖር ነህ
በዕለተ ምፅአት
እንደ ቅዱሳን
ስጋህን ለብሰህ
በምድር መጥተህ
ተጋድሎህን ትፈፅማለህ
✥•┈•●◉༒ ናሁ ሰማን-ዜማ ༒◉●•┈•✥
╭━─━─━─≪✠≫─━─━─━╮
✞ @Nahuseman256✞
✞ @Nahuseman256 ✞
╰━─━─━─≪✠≫─━─━─━╯
እንኳን አደረሰን
...ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም ኹለተኛም ጸለየ፥ሰማዩም ዝናብን ሰጠ ምድሪቱም ፍሬዋን አበቀለች። (ያዕ፭:፲፯)
<<ከቅዱስ ኤልያስ ነቢይ በረከት ያድለን።>>
✨እየጾማችሁ ነውን? (ሊቁ ቅዱስ ዮሃንስ አፈወርቅ)
🌿እንግዲያስ መጾማችሁን በተግባር አሳዩኝ? "እንዴት አድርገን እናሳይህ?" ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስላችኋለሁ፡- ድኻው እርዳታችሁን ፈልጎ እንደሆነ ቸርነትን አድርጉለት፤ የጠላችሁትን ሰው ካያችሁት ከእርሱ ጋር ፈጥናችሁ ታረቁ፤ ባልጀራችሁ ተሳክቶለት ስታዩት በእርሱ ላይ ቅናት አትያዙ፤ ቆነጃጅትን በመንገድ ሲያልፉ ስታዩ በዝሙት ዓይን አትመኙ፡፡ እንዲህ እንዲህ እያደረጋችሁ በትክክል መጾማችሁን አሳዩኝ።
በሌላ አገላለጽ አፋችሁ ብቻ ሳይሆን ዐይናችሁ፣ እግራችሁ፣ እጃችሁ፣ በአጠቃላይ የሰውነታችሁ ሕዋሳቶች በሙሉ መጾም አለባቸው፡፡
🖐️ እጆቻችሁ ከመስረቅና የእናንተ ያልሆነውን ከመውሰድ ይጹሙ፤
🦶 እግሮቻችሁ የኃጢአት ሥራን ለመፈፀም ከመፋጠን ይጹሙ፤
ዐይኖቻችሁ ውጫዊ በሆነ ውበት ምክንያት ከመቅበዝበዝ ይጹሙ፡፡
ጥሉላትን ፥ (የፍስክ ምግብ) እየበላችሁ አይደለም አይደል?
እንግዲያስ በዐይኖቻችሁም ክፉ ነገርን አትብሉ፡፡ የሚታዩ ነገሮች ለዐይን ምግቦች ናቸውና፡፡
👂 ጀሮዎቻችሁም ይጹሙ፡፡ የጀሮ ጾም ሐሰተኛ ወሬንና ሐሜትን አለመስማትና ይህን የመሳሰለ ነው አንደበታችሁም ከከንቱ ንግግር ይጹም፡፡
ዓሣንና ሌሎች ጥሉላትን ከመብላት ተከልክለን ሳለ ነገር ግን ወንድሞቻችንን በሐሜት የምናኝካቸውና የምንበላቸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ወንድሙን የሚያማና የሚነቅፍ ሰው እርሱ የወንድሙን አካል ያቆስላል ፤ ሥጋውንም ይበላል፡፡ለዚህም ነው ሐዋርያው ይህን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ተናገረ፡- "እርስ በእርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በእርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ" /ገላ.5፡15/።
➛ስታሙ በጥርሳችሁ የወንድማችሁን ሥጋ አትነክሱም፡፡ በክፉ ንግግራችሁ ግን የወንድማችሁን ነፍስ ትነክሳላችሁ ፤ ታቆስሉትማላችሁ፡፡ እንዲህ በማድረጋችሁ ራሳችሁን ፣ ወንድማችሁንና ሌሎች ብዙ ሰዎችን ትጎዳላችሁ፡፡
➢አንደበታችሁ ክፉ ነገርን ከመናገር ካልጦመ ጉዳቱ በዚህ ብቻ አያበቃም፡፡ በሐሜታችሁ እናንተን የሚሰማ ወንድማችሁም የሐሜታችሁ ተባባሪ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት እርሱንም በደለኛ ታደርጉታላችሁ ማለት ነው፡፡ እርሱም የራሱን ኃጢአት እንዳይመለከት ስላደረጋችሁት ሳያውቅ ከሐሜተኞች ጎራ ይቀላቀላል፡፡ በዚህም የሌሎች ወንድሞቹን ድካም እየተመለከተ እርሱ ግን በመጦሙ ትልቅ የጽድቅ ሥራን እንደፈጸመ ቆጥሮ ይኩራራል ስለዚህ አንደበታችሁም ክፉ ከመናገር ይጹም፡፡
ይቀላቀሉ ለሌሎችም ያጋሩ👇
የተመረጡ ገፆች
ለፍቅረኛው ብሎ ሃይማኖቱን የቀየረው ወጣት ታሪክ‼
"በሃይማኖት የማትመስለው ወጣቱ እወድሻለሁ የሚላት ሴት ሃይማኖትክን ካልቀየርክ እኔ ከአንተ ጋር መቀጠል አልችልም ከዛሬ ጀምሮ የእኔ እና የአንተ ግንኙነት መቋረጥ አለበት አለችው
👉ለጊዜው በሰይጣናዊ ፍቅር ልቡ የተነደፈው ወጣት አንቺን ከማጣ ሃይማኖቴ እቀይራለሁ ወይም እግዚአብሔርን በአጣ ይሻለኛል ብሎ እስዋን ላለማጣት ከእግዚአብሔር ለመለየት ወሰነ ከባድ ሞት
ይህን ትውልድ የገጠመው ይህ ነው ብዙ ወንዶች እንወዳችኋለን የሚሉአቸው ሴቶች ላለማጣት እግዚአብሔር አጥተዋል ብዙ ሴቶች እንወዳችኋለን የሚሉአቸውን ወንዶች ላለማጣት እግዚአብሔርን አጥተዋል
👉ከእነዚህ እንሻላለን የሚሉት አንዳንዶቹ ደግሞ አንቺም በሃይማኖትሽ እኔም በሃይማኖቴ ተባብለው አብረው ለመኖር እራሳቸውን ያታልላሉ ይህ ማለት እሳት እና ቅቤ አብረው ይኖራሉ እንደማለት ነው
🤔እንስሳት እንኳን ከማይመስላቸው ጋር አይራቡም በግ ከፍየል ፍየልም ከበግ ጋር ቁርኝነት የላቸውም ሁሉም ተፈጥሮአቸውን ጠብቀው ይኖራሉ የሰው ልጅ እንዴት ከፍየል መማር ያቅተዋል
እግዚአብሔርማ በኃጢአተኞች ምክር ተስማምቶ አያውቅም
"ድኅረ ልቡናሁ ፄወወ ፍቅረ አሐቲ ብእሲት፣ ለዘወጽአ ረድእ እምሃይማኖት፣ዘመሐርክምዎ በእስራ ዕለት፣መሐሩኒ ሥላሴ ነገሥት"
መልክአ ሕማማት
በመጨረሻም ወጣቱ ተጸጽቶ ንስሐ ቢገባ በሀያ ቀን እግዚአብሔር ይቅር አለው ይላል እንደበደላችን ያልተመለከተን የቅዱሳን አምላክ የተመሰገነ ይሁን 🙏🙏
ቴሌግራም ይቀላቀሉ
በመጋቤ ሐዲስ ወብሉይ አባ ገብረኪዳን
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago