Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
[ † ኅዳር ፳፬ [ 24 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. "፳፬ቱ" ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ [ሱራፌል]
፪. ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት
፫. "፵፰" ሰማዕታት [ማሕበሩ]
፬. አባ ዮሴፍ ዘሃገረ ጻን
፭. ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጥዑመ ዜና
፮. ቅዱስ ኪርያቅ ሰማዕት
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት [መምሕረ ትሩፋት]
፪. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
፫. አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
፬. ቅዱስ አጋቢጦስ [ጻድቅ ኤጲስቆጶስ]
፭. ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
፮. ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም [ኢትዮጵያዊ]
፯. ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
† " በዙፋኑ ዙሪያም ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ:: በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው: በራሳቸውም የወርቅ አክሊል ደፍተው ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር:: ከዙፋኑም መብረቅና ድምጽ: ነጐድጓድም ይወጣል:: በዙፋኑም ፊት ሰባት የእሳት መብራቶች ይበሩ ነበር:: እነርሱም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት ናቸው::" † [ራዕይ ፬፥፬]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
🕊
[ † እንኳን ለ፳፬ [ 24 ] ቱ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ እና ቅዱስ አዝቂር ሰማዕት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ † 🕊
† እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥራቸው በነገድ መቶ [፻] : በክፍለ ነገድ አሥር [፲] አድርጓቸዋል:: አቀማመጣቸውንም በሦስት ሰማያትና በ፲ ከተሞች [ዓለማት] አድርጓል::
† መላእክት ያሉባቸው ከተሞች ከታች ወደ ላይ "ኤረር: ራማና ኢዮር" ይባላሉ:: አሥሩ ክፍለ ነገድ ደግሞ ከነ አለቆቻቸው ይህንን ይመስላሉ :-
፩. "አጋእዝት" [የቀድሞ አለቃቸው ሳጥናኤል: አሁን የተረፉት በቅዱስ ሚካኤል ሥር ናቸው]
፪. "ኪሩቤል" [አለቃቸው ኪሩብ]
፫. "ሱራፌል" [አለቃቸው ሱራፊ]
፬. "ኃይላት" [አለቃቸው ሚካኤል]
፭. "አርባብ" [አለቃቸው ገብርኤል]
፮. "መናብርት" [አለቃቸው ሩፋኤል]
፯. "ስልጣናት" [አለቃቸው ሱርያል]
፰. "መኳንንት" [አለቃቸው ሰዳካኤል]
፱. "ሊቃናት" [አለቃቸው ሰላታኤል]
፲. "መላእክት" [አለቃቸው አናንኤል] ናቸው::
† ከእነዚህም :-
- አጋእዝት: - ኪሩቤል - ሱራፌልና - ኃይላት መኖሪያቸው በኢዮር [በ፫ኛው ሰማይ] ነው::
- አርባብ: - መናብርትና - ስልጣናት ቤታቸው ራማ [፪ኛው ሰማይ] ነው::
- መኳንንት: - ሊቃናትና - መላእክት ደግሞ የሚኖሩት በኤረር [በ፩ኛው] ሰማይ ነው::
መላእክት ተፈጥሯቸው እምኀበ አልቦ ኀበ ቦ ነው:: አይራቡም: አይጠሙም: አይዋለዱም: አይሞቱም:: ተፈጥሯቸውም ረቂቅ ነው:: ተግባራቸውም ዘወትር "ቅዱስ: ቅዱስ: ቅዱስ" እያሉ ፈጣሪያቸውን ማመስገን ነው:: ምግባቸውም ይሔው ነው::
ዕረፍት ብሎ ነገርን አያውቁም:: "አኮቴቶሙ ዕረፍቶሙ: ወዕረፍቶሙ አኮቴቶሙ" እንዲል:: በተጨማሪም መልአክ ማለት ተላላኪ [አገልጋይ] ነውና ከፈጣሪ ወደ ሰው ልጆች ለምሕረትም: ለመዓትም ይላካሉ::
ምሕረትን ያወርዳሉ:: ልመናን ያሳርጋሉ:: ቅጡ ሲባሉም ይቀጣሉ:: ስነ ፍጥረት [አራቱ ወቅቶች] እንዳይዛቡ ይጠብቃሉ::
- ዘወትርም ስለ ሰው ልጆች ያማልዳሉ:: [ዘካ.፩፥፲፪]
- ምሥጢርን ይገልጣሉ:: [ዳን.፱፥፳፩]
- ይረዳሉ:: [ኢያ.፭፥፲፫]
- እንዳንሰናከል ይጠብቃሉ:: [መዝ.፺፥፲፩]
- ያድናሉ:: [መዝ.፴፫፥፯]
- ስግደት ይገባቸዋል:: [መሳ.፲፫፥፳, ኢያ.፭፥፲፫ 5, ራዕ.፳፪፥፰]
- በፍርድ ቀንም ኃጥአንን ከጻድቃን ይለያሉ:: [ማቴ.፳፭፥፴፩]
- በአጠቃላይ ለሰው ልጆች ሕይወትና ድኅነት ሲባል ከፈጣሪያቸው የተሰጣቸውን ትዕዛዝ ሲጠብቁና ፈቃዱን ሲፈጽሙ ይኖራሉ::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህች ዕለት የሃያ አራቱን ቅዱሳን ካህናተ ሰማይን መታሰቢያ ታደርጋለች:: እኒህ ቅዱሳን መላእክት በነገድ ፲ ሲሆኑ መጠሪያቸው "ሱራፌል" : መኖሪያቸውም በኢዮር ነው:: ነገር ግን ሃያ አራቱ አለቆቻቸው ተመርጠው በመሪያቸው በቅዱስ ሱራፊ አለቅነት በጽርሐ አርያም ያገለግላሉ::
በቀናች ሃይማኖት ትምሕርት ሁሉም ቅዱሳን መላእክት ለእግዚአብሔር ቅርብ ቢሆኑም: በነጠላ የቅዱስ ሚካኤልን ያህል: በነገድ ደግሞ የኪሩቤል [አራቱ እንስሳ] እና የሱራፌልን (ሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ) ያህል ቅርብ የለም::
† ሃያ አራቱ ቅዱሳን ካህናት ሥራቸው :-
፩. እንደ ሞገድ ከአንደበታቸው ምስጋና እየወጣ: ጧት ማታ ፈጣሪያቸውን ይቀድሱታል:: [ኢሳ.፮፥፩, ራዕይ.፬፥፲፩, ፣ ፭፥፲፩]
፪. የሥላሴን መንበር ያለ ማቋረጥ ያጥናሉ:: [ራዕይ.፭፥፰]
፫. የሰው ልጆችን: በተለይም የቅዱሳንን ጸሎት በማዕጠንታቸው ያሳርጋሉ:: [ራዕይ.፰፥፫]
፬. የረከሱትን ይቀድሳሉ:: [ኢሳ.፮፥፮]
፭. ዘወትርም ለሰው ልጆች ምሕረትን ሲለምኑ ይኖራሉ:: [ዘካ.፩፥፲፪]
ስለ እነዚህ ቅዱሳን ካህናት [ሱራፌል] ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ብዙ ይላል:: ለምሳሌ :- ዐቢይ ነቢይ ወልዑለ ቃል ኢሳይያስ ፈጣሪው ተቀይሞት በነበረበትና ዖዝያን በሞተበት ወራት: ግሩማን ሆነው ሥላሴን "ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ" እያሉ ዙሪያውን ከበው ሲያመሰግኑ ሰምቷል::
ከእነርሱም አንዱ [ሱራፊ] መጥቶ በጉጠት እሳት ከንፈሩን ዳስሶ ከለምጹ አንጽቶታል:: [ኢሳ.፮፥፩] አቡቀለምሲስ የተባለ ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በግርማ: በአምሳለ አረጋዊ ተመልክቷቸዋል:: [ራዕይ.፬፥፬]
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን የመሰሉ ቅዱሳን ሊቃውንት ደግሞ በጣዕመ ምስጋናቸው ሲገልጿቸው :-
"ካህናተ ሰማይ ቅውማን በዐውዱ::
አክሊላቲሆሙ ያወርዱ::
ቅድመ መንበሩ እንዘ ይሰግዱ::
ይርዕዱ::
ከመ ኢይዝብጦሙ ሶበ ይበርቅ ነዱ::" ብለዋል:: [መጽሐፈ ሰዓታት]
ትርጉሙም "በፈጣሪ መንበር ዙሪያ የሚቆሙ የሰማይ ካህናት አክሊለ ክብራቸውን አውርደው በመንበሩ ፊት ይሰግዳሉ:: መብረቀ መለኮቱ በተገለጠ ጊዜም በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ::" ነው:: ግሩም ባሕርየ ሥላሴን ሊቋቋመው የሚችል ፍጡር የለምና::
ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ በምስጋናቸው: በማዕጠንታቸውና በምልጃቸው ክቡራን ናቸውና ዘወትር ልናከብራቸው ይገባናል:: የረከሰ ማንነታችንን ይቀድሱ ዘንድ: በምልጃቸውም ዘንድ እንድንታሰብ: ጸሎታችንንም ያሳርጉልን ዘንድ እንለምናቸው::
† ኅዳር ፳፬ [24] ቀን ዓመታዊ በዓላቸው ነው ማለት በየወሩ በ፳፬ [24] ወርኀዊ በዓላቸው መሆኑን ያሳያልና ዘወትር ልናስባቸው ይገባል::
በተለይ ያዘነን ልብ ደስ ያሰኛሉና እንደ ሊቃውንት እንዲህ ብለን እንጠራቸዋለን::
"ሰላም ለክሙ ካህናተ ሕጉ ወትዕዛዙ::
ለእግዚአብሔር ቃል ዘጶዴሬ ሥጋ አራዙ::
እምነቅዐ አፉክሙ ሐሴት ዘኢይነጽፍ ዉሒዙ::
ኪያየ ኅዙነ ወትኩዘ ልብ ናዝዙ::
ወበክንፍክሙ ብርሃናዊ ዐውድየ ሐውዙ::" [አርኬ ዘኅዳር ፳፬]
🕊 † ቅዱስ አዝቂር ካህን † 🕊
† ከዜና ካህናት ወደ ዜና ካህናት እንለፍ:: ቅዱስ አዝቂርን የመሰሉ ካህናት ምንም ሥጋ ለባሽ ቢሆኑም ሥልጣናቸውና ግብራቸው ሰማያዊ ነውና መላእክትን ይመስላሉ:: አንድም በስልጣናቸው ከመላእክት ይበልጣሉ::
"ካህናትየ ይቤሎሙ::
ወእምኩሉ ፈድፋደ አክበሮሙ::
ዘኢተገብረ ለመላእክት ተገብረ ለካህናት::"
ትርጉም "አገልጋዮቼ አላቸው::
ከሁሉ በላይ አከበራቸው::
ለመላእክት ያልተደረገ ለካህናት ተደረገ::" እንዳለ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ:: [መጽሐፈ ቅዳሴ]
ቅዱስ አዝቂርም የናግራን [አሁን የመን] ክርስቲያን ሲሆን በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን በንጹሕ የክህነት አገልግሎቱ ሰውንም: ክርስቶስንም ደስ ያሰኘ አባት ነው:: አሕዛብን: አረማውያንን ሁሉ ድል ነስቶ መንጋውን ጠብቋል:: በቁጥርም አብዝቷል::
ገርፈው ቢያስሩት በቃሉ ስልጣን የብረት በሮችን ከፍቶ አሕዛብን ሲያጠምቅ ተገኝቷል:: ሊገድሉት ሲወስዱት በየመንገዱ ይሰብክ ነበር:: ገዳዮቹ በርሃ ላይ ውኃ ጥም እንዳይገድላቸውም በአንዲት ገበታ ላይ ዝናም አዝንሞ ፯ መቶ ወታደሮች ከነ ፈረሶቻቸው አጥግቧል::
በመጨረሻም አይሁድ በድንጋይ ሲወግሩት ድንጋዮቹ እየተመለሱ አናት አናታቸውን ብሏቸዋል:: ያን ጊዜ በብስጭት አንገቱን ቆርጠውታል:: አብረውም ቅዱስ ኪርያቅ ወዳጁንና ፵፰ ተከታዮቹን ሰይፈዋል::
† አምላከ ቅዱሳን ካህናተ ሰማይ ከምስጋናቸው ሐሴትን: ከማዕጠንታቸው በጐ መዓዛን ያውርድልን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
🕊
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ደቅስዮስ [የእመቤታችን ወዳጅ]
፫. አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት
፬. አባ ጳውሊ የዋህ
፭. ቅዱስ ዮልዮስ ሰማዕት
፮. ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ ሐዋርያ
† " ልጆች ሆይ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ:: አሸንፋችሁአቸውማል:: በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና:: እነርሱ ከዓለም ናቸው:: ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ:: ዓለሙም ይሰማቸዋል:: እኛ ከእግዚአብሔር ነን:: እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል:: ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም::" † [፩ዮሐ. ፬፥፬]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን:: ✞✞✞
† ስንክሳር ዘወርኀ መስከረም ፱ †
=> # ቅዱሳት_መጻሕፍት እንደሚነግሩን የመላእክት ሁሉ
አለቃቸው በፈጣሪው ኃይል ብዙ ድንቆችን ሠርቷል::
ከመጀመሪያው ሰው #አዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ: አምነው
ለሚጠሩት ረዳት ነው:: ዘወትርም ያድናቸው ዘንድ በሚፈሩት
ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል:: (መዝ. 33:7)
¤እግራችን እንዳይሰናከል ዘወትር ይጠብቀናል:: (መዝ.
90:11)
¤የቅዱስ ሚካኤል ስሙ ድንቅ ነው:: (መሳ. 13:18)
¤ከእርሱ በቀርስ የሚያጸና ማን አለና! (ዳን. 10:21)
¤ለሕዝቡም የሚቆም ታዳጊ መልአክ ነው:: (ዳን. 12:1)
¤በፊቱ ሲቆምም ስለ ክብሩ ጫማ አውልቆ: ባጭር ታጥቆ
ነው:: (ኢያ. 5:13)
+ይህ ድንቅ መልአክ ከሺህ ዓመታት በፊት በሮም ከተማ ይህንን
ድንቅ ተአምር በዚህች ዕለት መሥራቱን ቤተ ክርስቲያን
ትመሰክራለች:: በድሮው የሮም ግዛት ' # ሩፍምያ ' የምትባል
ከተማ ነበረች:: ይህች ከተማ ክርስቲያኖችም: ኢአማንያንም
ተቀላቅለው የሚኖሩባት ናት::
+በከተማዋ የክርስቲያኖች ቁጥር ትንሽ ቢሆንም በእምነት ግን
ጠንካሮች ነበሩ:: በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያኗ መጋቢ ባለ
ፍጹም እምነት ሰው ነበር:: በቦታው የቅዱስ ሚካኤል ቤተ
ክርስቲያን በመኖሩም ብዙ ተአምራት ይደረጉ ነበር:: ተበለጥን
የሚል ስሜት የተሰማቸው አሕዛብ (ዮናናውያን) ግን ይሕንን
ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት ተማማሉ::
+በቀጥታ ሔደው ቢያፈርሱት ወይም ቢያቃጥሉት በሕግ
እንደሚጠየቁ ያውቃሉና በሥጋዊ ጭንቅላታቸው ዘዴ ያሉትን
መከሩና ወሰኑ:: በከተማዋ ዳር የሚያልፍ አንድ ትልቅ ወንዝ
አለ:: በሞላ ጊዜ ያገኘውን ሁሉ ጠርጐ የሚወስድም ነበር::
+ታዲያ ክፋተኞቹ ሌሊት ሌሊት እየተነሱ የሚሔድበትን መንገድ
ዘግተው: ወደ ቤተ ክርስቲያኑ አቅጣጫ መንገድ ከፈቱለት::
ከቀናት በሁዋላ ከባድ ዝናብ በዚህች ቀን ጣለ:: ወንዙ ትልቅ
ነውና ያገኘውን ሁሉ እያገላበጠ ደረሰ::
+በወቅቱ በቅዱሱ መልአክ መቅደስ ውስጥ ከመጋቢው በቀር
ሰው አልነበረምና አስፈሪ ድምጽ ሰምቶ ቢወጣ ወንዙ እየደነፋ
ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እየመጣ ነው:: አሰበው: ከደቂቃዎች
በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳልነበረ ሊሆን ነው::
+እርሱ አንድ ተስፋ ነበረውና ወደ ውስጥ ገብቶ ቅዱስ
ሚካኤልን ተማጸነ:: ከዚያ ላለመውጣትም ወሰነ:: ትንሽ ቆይቶ
በታላቅ ኃይል ወንዙ ደረሰ:: በዚህ ጊዜ ግን ቅዱስ ሚካኤል
በግርማ ከሰማይ ወርዶ በወንዙ ፊት ቆመ::
+መጋቢውንም "ጽና: አትፍራ" ብሎት በያዘው የብርሃን በትረ-
መስቀል መሬትን አንድ ጊዜ መታት:: በዚያች ቅጽበትም ትልቅ
ሸለቆ ተፈጠረ:: ወንዙም በሸለቆው ውስጥ አልፎ ሔደ::
+የሚገርመው ሸለቆው የተፈጠረው በቤተ ክርስቲያኑ በታች
ነው:: ቅዱስ ሚካኤል ግን መጋቢውን ባርኮት በክብር ዐረገ::
በማግስቱ ክርስቲያኖቹ ይህንን አይተው ደስ አላቸው::
መልአኩንም አከበሩት:: አሕዛብ ግን አፈሩ::
+"+ # ቅዱስ_ቢሶራ_ሰማዕት +"+
=>በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያን መሆን የሚያስከፍለው ዋጋ ብዙ
ነበር:: ከምንም በላይ መከራው የጸናባቸው ግን የቤተ
ክርስቲያን መሪዎች ነበሩ:: ክደው ያስክዳሉ በማለት አብዝተው
ያሰቃዩአቸው ነበር:: ቶሎም አይገድሏቸውም:: መከራውን
ከማራዘም በቀር::
+ከእነዚህም አንዱ አባ ቢሶራ ነው:: እርሱ በምድረ ግብፅ
'መጺል' ለምትባል ሃገር ኤዺስ ቆዾስ ነበረ:: በእድሜው
አረጋዊ: በትምሕርቱ ምሑር: በምግባሩ ቅዱስና በእረኝነቱም
የተመሠከረለት በመሆኑ በምዕመናን ዘንድ ተወዳጅ ነበር::
+መከራው እየገፋ ሲመጣ ግን ቅዱሱ በመፍራት ፈንታ
የሰማዕትነት ፍቅር አደረበት:: ስለ ሃይማኖት መሞትን እና ቶሎ
ወደ #ክርስቶስ መሔድን ናፈቀ:: ነገር ግን መልካም እረኛ ነውና
በጐቹን (ምዕመናንን) እንዲሁ ሊተዋቸው አልወደደም:: ሰብስቦ
ምን እንዳሰበ አማከራቸው:: የሰሙት ነገር ክርስቲያኖችን
አስለቀሳቸው::
+"አቡነ ለመኑ ተኀድገነ-አባታችን ለማን ትተኸን ትሔዳለህ?"
ሲሉም ከእግሩ ወደቁ:: እርሱ ግን አስረድቷቸው: አጽናንቷቸውም
በእንባ ተሰናበታቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ "አብረንህ እንሞታለን"
ብለው ተከተሉት:: ቅዱስ አባ ቢሶራን ከብዙ ስቃይ በሁዋላ
አረማውያን ከነ ተከታዮቹ በዚህ ቀን ገድለውታል::
+"+ # ቅዱስ_ያሳይ_ንጉሥ +"+
=>በቀደመው ዘመን መንግስታቸውን ትተው ከመነኑ ነገሥታት
አንዱ ቅዱስ ያሳይ ነው:: ምናኔ በቁሙ ከባድ ነው::
መንግስትን: ዙፋንን: ክብርን ትቶ መመነንን ደግሞ ከማድነቅ
በቀር እንዲህ ብለው ሊገልጹት ይከብዳል::
+ቅዱስ ያሳይም መንግስቱን ትቶ ልምላሜ ወደሌለበት ደረቅ
በርሃ ሔደ:: በዚያም ከአንዲት ዛፍ በቀር ምንም ነገር
አላገኘም:: በዚያች ደረቅ ዛፍ ላይ ወጥቶ ለዓመታት በጾምና
በጸሎት ተጋደለ::
+በዘመነ ተጋድሎው ከዛፏ አልወረደም: ሰውም አይቶ
አያውቅም:: በመጨረሻም ስለ ቅድስናው ዛፏ ለምልማለች::
እርሱም በዚህች ቀን ዐርፏል::
=>አምላከ ቅዱሳን ተራዳኢ መልአክን ይዘዝልን:: ከወዳጆቹ
በረከትም አይለየን::
=>መስከረም 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ቢሶራ ሰማዕት
3.ቅዱስ ያሳይ ንጉሥ
4.ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት (ልደቱ)
5."14,730" ሰማዕታት (የቅዱስ ፋሲለደስ ማሕበር)
=>ወርሐዊ በዓላት
1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)
2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮዽያዊ)
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ)
4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮዽያዊ)
6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት)
=>+"+ የፋርስ መንግስት አለቃ ግን ሀያ አንድ ቀን
ተቁዋቁዋመኝ:: እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ #ሚካኤል
ሊረዳኝ መጣ:: እኔም ከፋርስ ነገሥታት ጋር በዚያ ተውሁት::
+"+ (ዳን. 10:13)
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
✞ ወለወላዲቱ ድንግል ✞
✞ ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ✞
✞✝✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✝✞
❖ መስከረም ፰ (8) ❖
✞✞✞ እንኩዋን ለሊቀ ነቢያት #ቅዱስ_ሙሴ እና
ለቅዱሳን ካህናት #ዘካርያስና_አሮን ዓመታዊ በዓል
በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+" ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት "+
=>ቅዱሳን ነቢያት እጅግ ብዙ ናቸው:: ከፈጣሪያቸው
የተቀበሉት ጸጋም ብዙና ልዩ ልዩ ነው:: ያም ሆኖ
ከሁሉም ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ይበልጣል:: መጽሐፍ
እንደሚል ከእርሱም በፊት ቢሆን ከእርሱ በሁዋላ እንደ
እርሱ ያለ ነቢይ አልተነሳምና:: ይህስ እንደ ምን ነው
ቢሉ:-
¤ዓለም በተፈጠረ በ3,600 ዓመት እሥራኤል በረሃብ
ምክንያት 75 ራሱን ወደ ምድረ ግብፅ ወረደ:: በዚያም
ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ለ215 ዓመታት ተከብረው: ለ215
ዓመታት ደግሞ በባርነት: በድምሩ ለ430 ዓመታት
በምድረ ግብፅ ኑረዋል::
¤በባርነት ዘመናቸውም 'ራምሴና ጋምሴ' የሚባሉ 2
ከተሞችን (ዛሬ ፒራሚዶች የምንላቸውን) ገንብተዋል::
ግፋቸው እየበዛ ሲሔድ ግን ጩኸታቸው ቅድመ
እግዚአብሔር ደረሰ:: ያድናቸውም ዘንድ አንድ ቅዱስ
ሰው እንዲወለድ አደረገ:: ይኽም ሰው ሙሴ ይባላል::
¤ወላጆቹ መታመናቸውን በፈጣሪያቸው ያደረጉ
'እንበረም'ና 'ዮካብድ' ሲሆኑ ከሌዊ ነገድ ናቸው::
ከሙሴ ውጪም አሮንና ማርያምን ወልደዋል:: ቅዱስ
ሙሴ በተወለደበት ወራት ወንድ የእሥራኤል ሕጻናት
ይፈጁ ነበር:: ጌታ ግን በገዳዮቹ ልቡና ርሕራሔን
አምጥቶ አትርፎታል::
¤በሁዋላም በ3 ወሩ ዓባይ ወንዝ ላይ ጥለውት ተርሙት
(የፈርኦን ልጅ ናት) ወስዳ በቤተ መንግስት
አሳድጋዋለች:: 'ሙሴ' ያለችውም እርሷ ናት:: 'ዕጉዋለ
ማይ / እማይ ዘረከብክዎ' (ከውሃ የተገኘ) ለማለት
ነው:: ወላጆቹ ያወጡለት ስም ግን 'ምልክአም'
ይባላል:: ሲወለድ ፊቱ እንደ መልአክ ያበራ ነበርና::
¤ቅዱስ ሙሴ 5 ዓመት በሆነው ጊዜ ፈርኦንን በጥፊ
በመማታቱ ለፍርድ ቀርቦ እሳትን በመብላቱ አንደበቱ ኮልታፋ ሆኖ ቀርቷል:: እናቱ
ዮካብድ ሞግዚት ሆና ስላሳደገችው 40 ዓመት በሆነው
ጊዜ የፈርኦንን ቤት ምቾትና የንጉሥ ልጅ መባልን ናቀ::
ቅዱስ ዻውሎስ እንደሚለው በአሕዛብ ቤት ካለ ምቾት
ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን ሊቀበል ወዷልና::
(ዕብ. 11:24)
¤አንድ ቀንም ለዕብራዊ ወገኑ ተበቅሎ ግብጻዊውን
ገድሎት ወደ ምድያም ሸሸ:: በዚያም ለ40 ዓመታት
የካህኑን ዮቶርን በጐች እየጠበቀ: ኢትዮዽያዊቱን
ሲፓራን አግብቶ ኖረ:: 2 ልጆንም አፈራ:: 80 ዓመት
በሞላው ጊዜ እግዚአብሔር በደብረ ሲና ተናገረው::
ሕዝቡንም ከባርነት ቀንበር እንዲታደግ ላከው::
¤ቅዱስ ሙሴም ከወንድሙ አሮንና ከአውሴ (ኢያሱ) ጋር
ግብጻውያንን በ9 መቅሰፍት: በ10ኛ ሞተ በኩር መታ::
እሥራኤልንም ነጻ አወጣ:: ሊቀ ነቢያት የሠራቸው
ሥራዎች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም::
¤እርሱ ባሕረ ኤርትራን ከፍሎ ሕዝቡን በደረቅ
አሻግሯል::
¤ግብጻውያንን ከነሠረገሎቻቸው በባሕር ውስጥ
አስጥሟል::
¤ለሕዝቡ መና ከደመና አውርዷል::
¤ውሃን ከጨንጫ (ከዓለት) ላይ አፍልቁዋል::
¤በብርሃን ምሰሶ መርቷቸዋል::
¤በ7 ደመና ጋርዷቸዋል::
¤ጠላቶቻቸውን ሁሉ ድል ነስቶላቸዋል::
¤ስለዚህ ፈንታ ግን ወገኖቹ ብዙ አሰቃይተውታል:: እርሱ
ግን ደግ: ቅንና የዋህ ሰው ነውና ብዙ ጊዜ ራሱን ለእነሱ
አሳልፎ ሰጥቷል:: "ሙሴሰ የዋህ እምኩሎሙ ደቂቀ
እሥራኤል" እንዲል:: (ዘኁ. 12:3) ቅዱስ ሙሴ ለ40
ዓመታት ሕዝቡን ሲመራ ከእግዚአብሔር ጋር ለ570 ጊዜ ተነጋግሯል::
¤ከጸጋው ብዛትም ፊቱ ብርሃን ስለ ነበር ሰዎች እርሱን
ማየት አይችሉም ነበር:: ታቦተ ጽዮንንና 10ሩ ቃላትን
ተቀብሎ ጽላቱ ቢሰበሩ ራሱ ሠርቶ በጌታ እጅ ቃላቱ
ተጽፈውለታል:: "የቀረው የቅዱሱ ሕይወት በመጻሕፍተ #ኦሪት (በብሔረ ኦሪት) ውስጥ የተጻፉ
አይደሉምን?"
¤እኔ ግን ደካማ ነኝና ይህቺ ትብቃኝ:: ቅዱስ: ክቡር:
ታላቅ: ጻድቅ: ነቢይና ደግ ሰው ቅዱስ ሙሴ በ120
ዓመቱ ዐርፎ በደብረ ናባው ሊቃነ መላእክት ቅዱሳን
#ሚካኤል: #ገብርኤል እና #ሳቁኤል ቀብረውታል::
መቃብሩንም ሠውረዋል:: (ይሁዳ. 1:9)
+"+ #ቅዱስ_ዘካርያስ_ካህን +"+
=>ስም አጠራሩ የከበረ: ሽምግልናው ያማረ ቅዱስ
ዘካርያስ የቅድስት ኤልሳቤጥ ባል: የመጥምቁ ዮሐንስም
አባት ነው:: በእሥራኤል ታሪክ የመጨረሻው ደግ ሊቀ
ካህናት ነው:: ይህ ቅዱስ ሰው ከአሮን ወገን ተወልዶ:
በሥርዓተ ኦሪት አድጐ: በወጣትነቱ መጻሕፍተ ብሉያትን
ተምሮ ሊቀ ካህንነቱን እጅ አድርጉዋል::
¤በጐልማሳነቱም ቅድስት ኤልሳቤጥን አግብቶ
በደግነትና በምጽዋት አብሯት ኑሯል:: ከኢያቄምና ከሐና
ጋር ቅርብ ወዳጆች ነበሩና አልተለያዩም:: ቅዱሱ ዘወትር
ለማስተማር: ለመስዋዕትና ለማዕጠንት ይተጋ ነበር::
ጸሎቱና እጣኑም ወደ ቅድመ እግዚአብሔር ይደርስለት
ነበር::
¤እስኪያረጅ ድረስ ባይወልድም አላማረረም:: ደስ
የሚለው ደግሞ እመ ብርሃን ድንግል ማርያምን
ከወላጆቿ ተቀብሎ ለ12 ዓመታት ያሳደጋት እርሱ ነው::
ዘወትር መላእክት ከበው ሲያገለግሏት እየተመለከተ
ይመሰጥ ነበረ::
¤የልጅ አምሮቱን የሚረሳው ከእርሷ ጋር ሲሆን ነው::
እንደ አባት አሳደጋት: እንደ እመቤትም ጸጋ ክብር
አሰጥታዋለች:: እድሜው መቶ ዓመት በሆነ ጊዜ
በቅዱስ ገብርኤል ተበስሮ ዮሐንስን አገኘ:: ለ9 ወራት
የተዘጋ አንደበቱ ሲከፈት "ይትባረክ እግዚአብሔር
አምላከ እሥራኤል" ብሎ ትንቢትን ተናገረ::
¤ሔሮድስ ሕጻኑን ሊገድለው በፈለገ ጊዜም ሕጻኑን
ቅዱስ ዮሐንስን ወስዶ በክንፈ ኪሩብ ላይ አስቀመጠውና
መልአክ ወደ በርሃ ወሰደው::
ቅዱስ ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደሱ መካከል (70: 80
ዓመት በንጽሕና ባገለገለበት ቦታ ላይ) ገደሉት::
¤ሥጋውን አምላክ ሰውሮት የፈሰሰ ደሙ እንደ ድንጋይ
ረግቶ ሲጮህ ተገኝቷል:: ለ68 ዓመታትም ደሙ ሲፈላ
ኑሯል:: በ70 ዘመን ጥጦስ ቄሣር አይሁድን ሲያጠፋቸው
ደሙ ዝም ብሏል:: ይህ ቅዱስ: ጻድቅ: ነቢይና ካህን
ስሙ በተጠራ ጊዜ ሲዖል ደንግጣ ነፍሳትን እንደምትሰጥ
ሊቃውንት ነግረውናል:: (ማቴ. 23:35)
+"+ #ቅዱስ_አሮን_ካህን +"+
=>በቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት የቅዱሱ ካህን
የአሮን በትር ሳይተክሏትና ውሃ ሳያጠጧት ለምልማ:
አብባ: አፍርታ የተገኘችው በዚህ ቀን ነው:: ዳታን:
አቤሮንና ቆሬ ከተከታዮቻቸው ጋር በፈጠሩት ሁከት
ምድር ተከፍታ ከዋጠቻቸው በሁዋላ እግዚአብሔር
የ12ቱን ነገደ እሥራኤል በትር ሰብስቦ ሲጸልይበት
እንዲያድር ሙሴን አዞት: እንዲሁ ሆነ::
+በነጋም ጊዜ ይህቺ ደረቅ የነበረች በትረ አሮን 12 ፍሬ
(ለውዝ: ገውዝ: በኩረ ሎሚ) አፍርታ ተገኘች:: (ዘኁ. 17:1-11) ለጊዜው ክህነት ከቤተ አሮን እንዳይወጣ
ምልክት ሆናለች:: ለፍጻሜው ግን ምሳሌነቷ ለድንግል
ማርያም ነው:: #እመ_ብርሃን የወንድ ዘር ምክንያት
ሳይሆናት አምላክን ወልዳ ተገኝታለችና::
"ጸናጽል ዘውስተ ልብሱ ለአሮን ካህን: ወዓዲ በትር እንተ
ሠረጸት: ወጸገየት: ወፈረየት" እንዳለ #አባ_ሕርያቆስ::
(#ቅዳሴ_ማርያም)
=>የእነዚህ ቅዱሳን ነቢያትና ካህናት አምላክ
ደግነታቸውን አስቦ: ከግራ ቁመት: ከገሃነመ እሳትም
ይሰውረን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::
=>መስከረም 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን
በዓላት=
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ቅዱስ ዘካርያስ ካህን (ጻድቅ ነቢይ)
3.ቅዱስ አሮን ካህን
4.ቅዱስ ዲማድዮስ ሰማዕት
✝"✝ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን
ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ በአንቺ የተደረገው ነገር ድንቅ
ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል:: በውስጥዋም
ሰው ተወለደ:: እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት:: ✝"✝
(መዝ. 86:1)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
? ጉባኤ አቅሌሲያ ⛪️
''በእንተ ስማ ለማርያም ለእኔ ተማሪ'' አኩፋዳው ቢጓደል የማይጎድል ጥበብ የያዘ ፣ እልፍኝ ቢዘጋበት የዕውቀት ገጿ ያልጠፋው የዛሬ የየኔታ እሸት የነገ የቤተክርስቲያን ፍሬ የአብነት ተማሪ!
የጥበብ ምንጯ እግዚአብሔር ፤ ሐገሯ ከየኔታ ብራና ሆና ሚስጥራትን በመጋረጃዋ ጋርዳ ለዘመናት ለሚፈልጓት ብቻ እየተገለጠች ፍሬ አፍርታ ጥበበኞችን አፍልቃለች።
''በእንተ ስማ ለማርያም'' ስንል ጉባኤ ዘርግተን የየኔታን ደጅ በጥቂት ልናሳይ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ሰባኪያነ ወንጌል ፣ ካህናት ዘማሪያን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በተገኙበት መንፈሳዊ ኦርቶዶክሳዊ የወንጌልን ገበታ ዘርግተን ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ/ም ከቀኑ 7:00) ጀምሮ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ 4ተኛ ፎቅ የሚገኘው አዳራሽ እንጠብቃችኋለን።
መግቢያ ፦ በነጻ ነው!
ለበለጠ መረጃ:- በነጻ አጭር የስልክ መስመር 9066 ወይም 0938944444
አዘጋጅ:- ማህበረ ቁስቋም
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад