Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
የአንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ልብ → ልክ እንደ bluetooth ነው፤ ያገኘውን ኮኔክት ያደርጋል። የጀግና ወንድና የጥብቅ ሴት ልጅ ልብ ግን → በምንም መልኩ ሐክ የማይደረግና እንደ WiFi password የሚጠይቅ ነው። ፓስወርዱም ትክክለኛ ኒካሕ ነው!
ልጄ ሆይ ዱንያ እንደ ጥልቅ ባህር ነች።በሷም ውስጥ ከሰዎች ብዙዎች ሰጥመዋል። ስለዚህ በሷ ላይ ለመንሳፈፍ ከፈለግክ ጀልባህን የአላህ ፍራቻ፤ መቅዘፊያህን ኢማን፤ መንገድህን ደግሞ በአላህ ላይ መመካት አድርግ።
➯ጥበበኛው ሉቅማን ለልጃቸው ከመከሩት
«ዝምድና በአርሽ ላይ ተንጠልጥላለች። እኔን የቀጠለ አላህ ይቀጥለው እኔን የቆረጠኝን አላህ ይቁረጠው ትላለች።»
ረሱል (ﷺ)
መውሊድን ከማላከብርበት ምክንያቶች፦
1) ረሱል ﷺ የተወለዱት አመል ፊል በተባለው አመት ነበር ፤ አብረሃ ካዕባን ለማፍረስ የሞከረበት አመት ማለት ነው። እንዲሁም የተወለዱት ሰኞ ቀን እንደሆነና ቀኑን እንደሚፆሙት ነግረውናል፤ ሆኖም የቱኛው ሰኞ እንደሆነ ግን የተገለፀ ነገር የለም። እርግጠኛ ሆኖ መናገር የሚቻለው የተወለዱት በዓመል ፊል ሰኞ ቀን መሆኑን ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ያለው ሁሉ ስምምነት የለበትም።
2) ነብዩ ﷺ በዱንያ ላይ 63 አመታትን ቆይተዋል ፤ በዚህ ረጅም ቆይታቸው በፍፁም አንድም ቀን አመት ጠብቀው ይህ የተወለድኩበት ቀን ነው ብለው አላከበሩም አልተናገሩምም። ሰኞ ቀን መወለዳቸውን ከመግለፅ ውጭ።
3) ከዚህ ውጭ የረሱል ﷺ ባልደረቦች ፤ ታቢኢዮችም ይሁኑ አራቱ አኢማዎች ማለትም ኢማሙ አቡ ሀኒፋ ፣ ኢማሙ ማሊክ ፣ ኢማሙ ሻፊዕይ ኢማሙ አህመድና እንደ እነ ኢማሙ ዙህሪ ሱፍያኑ ሰውሪ ኢማሙል አውዛኢይ እና ሌሎችም ይህንን ቀን ነብዩ የተወለዱበት ቀን ብለው አላከበሩም። ቀን ቆርጦ ማክበሩ መልካም ቢሆን በቀደሙን ነበር።
4) እንዲሁም ረሱል ﷺ ኸይር ነገር የተባለን ነገር ሁሉ እንደጠቆሙንና እንዳመላከቱን መጥፎን ነገር ደግሞ እንደከለከሉንና እንዳስጠነቀቁን ግልፅ አድርገው ነግረውናል። ሆኖም መውሊድን አክብሩልኝ ብለው የተናገሩት ነገር ግን በፍፁም የለም።
5) ረሱል ﷺ ተወለዱበት ተብሎ የሚከበረው ረቢዐል አወል 12 ኡለሞች ዘንድ ያለ ልዩነት አሽረፈል ኸልቅ የሞቱበት ቀን እንደሆነ ተስማምተዋል። የተወለዱበት ቀን መች እንደሆነ እርግጠኛ ሳይሆኑ የሞቱበት ቀን መሆኑን ግን ስምምነት እያለ በምን መልኩ ይህን ቀን አቅል ያለው ሰው በዓል አድርጎ ያከብረዋል።
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ፦ 『ረሱል ﷺ የሞቱበት የመሰለ አስከፊና ጨለማ ቀን አልገጠመኝም።』ሚሽካቱል መሳቢህ
6) ነብዪ ﷺ ሰኞ ቀን የተወለዱበት ቀን መሆኑን ሲናገሩ ቀኑን በፆም እንደሚያሳልፉት ተናግረዋል። ቀኑ እንደ ዒድ በአል ተደርጎ ቢቆጠር ኖሮ አይፆሙትም ነበር ምክንያቱም በኢድ ቀን መፆም የተከለከለ ነውና። እርሳቸው የተወለዱበትን ሰኞ ቀን በመፆማቸው ውስጥ ለአዕምሮ ባለቤቶች ጥቆማ አለ። ይህም የተወዱበትን ቀን ኢድ አድርጎ መያዝ አለመቻሉን ነው።
ጌታዬ ሆይ! ያንተንም የመልዕክተኛህንና የናንተን ወዳጆች የሚወድ ልብ ለግሰኝ! አቡ ቁዳማ
?ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናትና
መልካም ስራ ላይ መበርታት
بسم الله الرحمن الرحيم
فضل عشر ذي الحجة ووصايا لمن أدركها
ምስጋናና ውዳሴ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን ሰላትና ሰላም የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድ ላይ ይስፈን አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ የተለያዩ ወደርሱ የሚያቃርቡ ልዩ የመልካም ስራ እድሎችን ፈጥሯል በዚህም ተፎካካሪዎች እንዲፎካከሩ፣ ተሽቀዳዳሚዎችም እንዲሽቀዳደሙ ገፋፍቷል የስው ልጅ ነፍስ ሁሌ አንድ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን ትሰለቻለች አዲስ ነገር ስታገኝም ትነቃቃለች ይህንም ባህሪይ ሽሪዓችን ለነፍሲያ በሚገባ ጠብቆላታል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው የሚከተለውን ብለዋል
" ነፍስ፥ አንዳንዴ ለመልካም ስራ ትነቃቃለች አንዳንዴም ትሰለቻለች ንቃትና ከፍተኛ ፍላጎት ባላት ጊዜ ኸይርን ስራ በሚገባ አሰሯት በታከተችና በሰለቸች ጊዜ ግዴታ ለሆኑ ነገሮች እንጂ አትጫኗት" ብለዋል
?ይህ በጌታው በሚገባ የሚያምንና ስሜቱንም የማይከተልን ሰው ነፍስ ለማለት እንጂ በመሰረቱ ስሜቱን የሚከተልና የጌታውን ህግ የሚጥስን ሰው ነፍስ አይመለከትም!
?መንፈስን ለማደስና ነፍስንም መልካም ነገር ላይ ለማነቃቃት አላህ በየጊዜው በመጠነኛ ልፋትና ጥረት ከፍተኛ ምንዳ የሚያስገኙ እድሎችን አስገኝቷል ይህንንም እድል ፈጥነን እንድንጠቀም ትሩፋቱን ገልጿል
☄ከነዚህም እድሎች መካከል አንዱ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ 10 ቀናቶች ናቸው ቡኻሪይና ሌሎችም ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል
[ما من أيام العمل الصالح فيها أحب إلى الله من هذه الأيام يعني أيام العشر .... الحديث]
"ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበለጠ መልካም ስራ ከመቼውም በላይ አሏህ ዘንድ ውድ የሚሆንበት ቀን የለም"
?እነሆ አዱኒያ አጭር ናት እድሜያችንም አጭር ነው ከአጭሯ ዱኒያ የቀረውም በጣም አጭር ከአጭሯ ዱኒያ የአንተ ድርሻ ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ነው ይህም እውነታ ቀደም ሲል በቁርኣን ተነግኖራል
[قُل متاعُ الحياةِ الدنيا قَليل والآخِرةُ خَيرٌ لِمَن اتَقى....] النساء 77
" ነቢዩ ሙሐመድ ሆይ ንገራቸው፥ የዱኒያ ህይወትና መጠቃቀሚያዋ አጭርና ጥቂት ነው የአኼራ ህይወትም (አሏህን ለሚፈሩ) ከዱኒያ የተሻለ ነው" "ሱረቱንኒሳእ 77"
አጭርና ጥቂት ከሆነችዋ የዱኒያ ህይወት የቀረው ጥቂቱ መሆኑንም ሲነግረንም አሏህ እንዲህ ብሏል
(اقتَرَبَت الساعةُ وانشَقَّ القَمَر)
" ቂያማ ተቃረበች ጨረቃም ለሁለት ተከፈለች “ ሱረቱልቀመር 1
(اقتَرَبَ للنَّاسِ حِسابُهم)
“ የሰው ልጆች መተሳሰቢያና መመርመሪያ ጊዜያቸው ተቃረበ እነሱ ግን ቸልታና መዘናጋት ላይ ናቸው
” ሱረቱል አንቢያ 1
▪️አጭሩ እድሜያችን መች እንደሚቋጭ አናውቅምና ሁሌም ራስን ለሞት ማዘጋጀት ብልህነት ነው
ለሞት መዘጋጃትም፥ መልካምን ስራ ተሽቀዳድሞ በመስራት ከወንጀል በመራቅ አኼራን በመናፈቅ ነው
▪️ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም የውርደትም ይሁን የስኬት ሰበቡ የጊዜ አጠቃቀም ነው፣በዱኒያም በአኼራ በማይጠቅም ነገር ጊዜና ገንዘባችንን የምናባክን ሰዎች:-
☄ቀጣይ ምርጥ 10 የዙልሒጃ ቀናትን በአግባቡና ወደ አላህ በሚያቃርብ ስራ ለማሳለፍ ከወዲሁ ነፍሲያችሁን አሸንፉ!
ሌት-ከቀን በኔት ጊዜ፣ ገንዘብና አይናችሁን የምታቃጥሉ፥ አሏህን ፍሩ እራሳችሁንም ፈትሹ ከማይጠቅም ወሬና ተግባርም ራቁ መለከል_መውት ከመምጣቱ በፊትም ከእንቅልፋችሁ ንቁ! የአኼራው ድልድይ/ ሲራጥ ላይ እንዳትወድቁ አላህ ከሚጠላው ስራ በሙሉ በመራቅ ቁርኣን ቅሩ ዘክሩ የኔትና የወሬን ፍቅር በአላህ ውዴታ ቀይሩ!
? ውድ የአሏህ ባሮች
አላህ ዘንድ ውድ የሆኑ 10 ቀናትን:-
▪️አምስት ወቅት ሰላቶችን በወቅታቸው፣ ከፊትና ከኋላ የሚሰገዱ ሱናችን ከመጠበቅ ጋር፣ ወንዶች በጀማዓ በመስገድ፣
▪️ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር፣ ዱዓ እንዲሁም ተክቢራ በማብዛት፣
▪️የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና የታመሙን በመጠየቅ፣
▪️ከዙልሂጃ 1 ጀምሮ እስከ 9ኛው ቀን በመጾምና የጾሙ ሰዎችንም በማስፈጠር ወዘተ አሏህ የሚወዳቸው መልካም ስራዎችን በመስራት እናሳልፋቸው
☄ከላይ እንደተጠቀሰው የሰው ልጅ እድሜ በጣም አጭር ነው አሏህ ኸይርን የሻለት ሰው ግን በአጭር ጊዜ ብዙ ቁም ነገር መስራት ይችላል::
በነዚህ ውድ ቀናት ለአኼራችን ስንቅ እንሸምት በጣም ድንቅና የተከበሩ ቀናት ናቸው አሏህ በተከበረው ቁርኣኑ በነዚህ ቀናት ምሏል አሏህ ትልቅ ነው በትልቅና ጠቃሚ ነገር እንጂ አይምልም! ነቢያችንም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ቀናት መልካም ስራ ላይ እንደንበረታ ገፋፍተውናል
እራሳቸውም ቀናቱን በመልካም ስራዎች ያሳልፏቸው እንደነበረ ተዘግቧል
☄እነሆ ኢማሙ አሕመድና ሌሎችም ዘግበውት አልባኒይ ሰሒህ ባሉት ሐዲስ የምእምናን እናት ሐፍሳ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብለዋል "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዓሹራ፣ የዙልሒጃ 10 ቀናትና በየወሩ 3ቀን መጾምን አይተውም ነበር" ብላለች
▪️እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ነጥብ ቢኖር እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ " ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዙልሒጃ10 ቀናትን ጾመው አያውቁም" ብላ የተናገረችበት አጋጣሚ አለ ይህ ማለት እሷ እስከ ምታውቀው ድረስ ለማለት ነው ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘጠኝ ሚስቶች ነበር ያሏቸው እሷ ቤት በሚያድሩበት እለት ጾመው አለማየቷን ነው የሚያሳየው እንጂ በጭራሽ አይጾሙም ነበረ ማለት አይደለም።ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር አመላክተው እራሳቸው ወደ ኋላ አይቀሩም!
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኡሱል ትምህርት ዘርፍ ዑለሞች እንደጠቀሱት አንድን ጉዳይ በተመለከተ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አድርገዉታል ወይስ አላደረጉትም የሚል ውዝግብ ከተነሳ ማድረጋቸው የተጠቀሰው በትክክለኛ ሰነድ መሆኑ ከተረጋገጠ ቅድሚያ የሚሰጠውና ተቀባይነት የሚያገኘው እሱ ነው ምክንያቱም አላደረጉም ያለው አካል የማያውቀውን ነገር እርሱ በማወቁ ጉዳዩ ላይ ይበልጥ አዋቂው ቅድሚያ ይሰጠዋል:: በመሆኑም ከነቢዩ ባለቤቶች መሀል አንደኛዋ ጾመዋል ስትል ሌላኛዋ ደግሞ አልጾሙም ካለች ተቀባይነትና ቅድሚያ የሚያገኘው ጾመዋል ያለችዋ ሃሳብ ይሆናል ማለት ነው።
ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም ፈለጋቸውን ይከተሉ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች ትልቁ ጭንቃቸውና የህይወት ዓላማቸው "ዒባዳ" ወይም መልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ነበር ለዚህም ነው ከነሱ መካከል አንዱ እንዲህ ያሉት
☄" በዱኒያ ጉዳይ አንድ ሰው ሊቀድምህ ቢፈልግ መንገዱን አስፋለት በአኼራ ጉዳይ ግን ማንም እንዳይቀድምህ! "
አሁን አሁን እየዘነጋን ኖሮ እንጂ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል መክሮን ነበር
(سابقوا إلى مغفرة من ربكم وجنة)
" ተሽቀዳደሙ……..ወደ ጌታህቹ ምህረትና ወደ ጀነት" ሱረቱልሀዲድ 21 አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸው እርሱ ከሚጠላው ነገር በሙሉ ከጠበቃቸው ባሮቹ ያድርገን!
✍ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
@ዛዱልመዓድ
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад