Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

ኦርቶዶክሳዊ ወጣት

Description
ኦርቶዶክሳዊ ወጣት አንተ ነህ! አንቺ ነሽ! እኛ ነን! ይህ ለኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች የተዘጋጀ ቤት ነው እዚህ ና Join አድርግ ቤተክርስቲያን ትፈልግሀለች ና አብረን እንሰራለን። የተማርነው እናስተምራለን ያልተማርነው እንማራለን። ቤተክርስቲያንህን ትወዳለህ? አናግረን ምንም አይኑርህ ግድ የለም በምን ላገልግል በለን።
እንወያይ @Eorthodoxbot
@ethiopianorthodoxyouth
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 week, 1 day ago

ጌታዬ አምላኬ እልሃለሁ
ያመነ ሁን እንጂ ያላመነ አትሁን
ያልከኝን ሰምቼ
አምኛለሁና ቁስልህን አይቼ

ጎንህን ዳስሼ
እውነት ነው ትንሣኤህ
እውነት ነው
ለማያምኑት ኀዘን ለእኛ ግን ሕይወት ነው
እውነት ነው

እውነተኛ ፍቅርህን ቀምሻለሁ
የቆሰሉ እጆችህን አይቻለሁ
የተወጋ ጎንህንም ዳስሻለሁ
.
.
ዘማሪት አዳነች አስፋው

1 week, 1 day ago

በእኛም ልብ ተነሣ

#በስደተኞቹ

በሕይወት አጋጣሚ ሥጋዊ ኃይላችንን አሳጥተው ፣ ስለ እምነታችን ጽናት ሊፈትኑን ብቻ ክፉዎች እውነታችንን ሲሰቅሉብን ፣ ተስፋችንን አብረን ከመቃብር ላወረድን ፥ 'አሁንስ ተስፋዬ ማነው እግዚአብሔር አይደለምን!?' ያለውን ዘንግተን ሞትን ብቻ በምናብ እያሰላሰልን ፣ ለወትሮው ጠንካራ የነበሩ አርአያ ምግባሮቻችን መንፈሳዊ ወንድም እህቶቻችን በተመሳሳይ ጭንቀትና ሀፍረት መሆናቸውን እንጂ ወድቆ የመነሳትን ነገር እንደ አንስት ርህሩኃን የሆኑ አባቶቻችን ኖረው ያስተማሩንን ችላ ላልን ፤ የትንሣኤ ብርሃንን በልባችን አደግዘን በሁለት ሀሳብ ነፍሳችን እያነከሰች ከሰላም ግምጃ ፥ ከበረከተ ነፍስ ፣ ከእንጀራ ቤት በብዙ ምዕራፍ ርቃ ወደ ታናሽ ሥጋ መንደር እየተሰደደችብን ላለች ፤ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ሕማምና መጎስቆል እንደ ስንዴ ከአፈር የጣልነው ቃልህ በምግባራችን ፍሬ ከማጣት የወደቀ ሲመስለን ከደጅህ በፍርሃት ወደ ዓለም ለተመምን. .

#በመንገድ ነፍሳችን ለተራበች

የቱን ያህል ብንርቅ ልትመልሰን እንዲቻልህ የጠፋን ቢመስለን በመዳፎችህ እንደተያዝን ፣ የቱን ያህል በኃጢአት ብንቆሽሽ ፣ በበደል ርቀን ብንጓዝ ፣ እጅጉን ብንጎሰቁል የትንሳኤህ ብርሃን እኛን ከዚያ ለማውጣት እንዳይሳነው!ለመአት የዘገየህ ለምሕረት የቀረብክ አንተ የቸርነትህጥግ በዝለታችን እና በውድቀታችን ርቀት የሚመዘን አይደለም ፥ እጅግ የጠለቀ የሰፋ ነው እንጂ!

በደጅ ቆሞ የሚያንኳኳ ፥ በሩንም ሊከፍትለት ለሚወድ ሁሉ ደግሞ እራት ሊበላ በማዕዱ አብሮ የሚቀመጥ እርሱን ፣ ፊቱን በመፈለግ 'ከእኔ ዘንድ እደር ህይወቴ ጨልሟልና ቅረበኝ ፣ እተጋበት የነበረ ቀን ጽልመት ጋርዶታልና በክፋት በከረፋ ሰውነቴ በቸርነትህ ታድር ዘንድ ፈቃድህ ይሁን' እስክንለው ይጠብቀናል። ምን ልናቀርብለት? የምናቀርበው የላመ የጣመ ምግባር ባይኖረን በእምነት ከጠራነው ፣ እራት ይሆነን ዘንድ እርሱ የህይወት እንጀራችን ነው! ዛሬም ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ባርኮ ይሰጠናልና ፥ ስለ ባዶነታችን ምክንያት አንስፈር!

በዓለም ስደት ስለ አምላካችን ፍቅር ልቡ የተቃጠለበት በእኛ ዘንድ እንዲያደር ፣ ሥጋውን እንብላ ደሙን እንጠጣ ዘንድ ግድ እያለ የሚያተጋ እንዴት ያለ የተመረጠ ወዳጅ ስደተኛ አብሮን አለ ይሆን! ከእንጀራ ቤት ሸሽተን ስንሄድ ብሉኝ ብሎ የሚከተልስ እንደምን ያለ እንጀራ ነው! በመንገድ ያገኘነው የትርጓሜና የምስጢር እንግዳ እንደምን ያለ የሕይወት መንገድ ነው! የዓለም አንጻራዊ እውነታዎቻችንን ክፉዎች ሰቅለውብን ብለን ስናዝን ፡ በጨለማ ያለምንም ምስክር አንጻር ሳያስፈልገው ለልባቸን የሚያበራልን እንዴት ያለ እውነት ብርሃንም ነው!

#ዝግ ልቡናችን ሰላምህን ለሚጠባበቅ

ጨለማ ለከደናት ዓለም ብርሃን የሆናት ቅዱስ ሥጋና ደምህ ጨለማ ለነገሠባቸው የልቡናችን ዓይኖችማ እንደምን አያበሩ! ከልቡናችን ደጅ ቆመህ ስታንኳኳ ባንሰማህ እንኳ አቤቱ በቅዱስ ሥጋና ደምህ ዐይኖቻችንን ክፈትልን ፡ በዝግ ልቡናችን ፣ በደካማ ማንነታችን በረድኤትና በረከት ለመገለጥ ከእኛ መሻትን ብቻ እንድትፈልግ የቸርነት ጥግ ኃያል ምስክር ነውና!

#በጥርጥር ወደ ቀደመ ግብራችን ላማተርን

ስለ ፍቅር በተቀበልካቸው ችንካሮችህ በፍቅርህ ሕመም እጆቻችንን ተኩሰሃቸው ለእኩይ ምግባራት የተኮማተሩ ይሁኑ ፣ ለምጽዋትስ ተዘርግተው በሰማይ አጸድህ ሕንፃን የሚገነቡ የአንተ መሐንዲሶች እንዲሆኑ እናምናለን። እንኪያስ ከሆነ 'ጌታዬ! አምላኬም' ብለን በፍጹም ማመን የክፋት ቆዳችንን የምንገፍለት ፍቅርህ በልባችን እንዲሳል ፣ የችንካርህ ምስጢራት ይረዱን ዘንድ እሳት ቃልህን በኑሮአችን እንድንዳስሰው ይሁን።

አንድነታችንን ለቅዱስ መንፈስህ አስገዝተን በፍጹማዊ ሰላምህ እስክንጎበኝ ፥ በሰማያዊው ኃይል እስክንኖር ለምግባር የምንቀናበት በእምነት የምንተጋበት እንዲሆን አቤቱ በእኛም ልቡና ዳግም ተነሣ!

#የትንሣኤ ሳምንት
#ዳግም ትንሣኤ
#እሁድ

1 week, 2 days ago

ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ
ክርስቶስ ተነሳ እሰይ እሰይ
እኛንም ከሞት ሊያስነሳ
ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ

ሰላም ሰላም
ለሰው ልጆች በምድር ኾነ ሰላም
.
.
ዘማሪት ማርታ ኃ/ሥላሴ

1 week, 6 days ago

👆ጥርጥር_እና_እምነት
[#Orthodox_perspective]

♧ጥርጥሮች በተለያየ መልክ ሊመጡ ይችላሉ ፥ አብዛኛዎቹ ቀድመን የያዝናቸው እውቀቶች ወይም አቅጣጫዎችን ሊመሠረቱ ይችላሉ፡፡ እነዚህ እውቀቶች አመጣጣቸው መነሻ ሊኖረው ይችላል ፤ አከባቢያችን ያሉ ሰዎች፣ የቀደመ ጉዳት፣ የምናነባቸው መጻሕፍት፣ የምናያቸው ቪዶዎች ...ወዘተ በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል ። እነዚህን እውቀቶች ይዘን የተቀረውን ነገር ሁሉ በእነዚህ መነጽርነት ለመመልከት እንሞክራለን፡፡ እምነት ደግሞ በተቃራኒው፤ ከእነዚህ አቅጣጫዎች ውጪ ወይም በላይ ሆኖ መመልከትን መጓዝ ይጠይቃል፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ቃላት ተቃራኒ ቢመስሉም መገናኛ ቦታ አላቸው፡፡
.
.
✞ጥርጥር ወደ እምነት ስንጓዝ መሸጋገርያ ምዕራፍ ነው፡፡ በዳግም ትንሣኤ በቤተክርስቲያን የሚነበበው ወንጌል (ዮሐ 20፡19-ፍጻሜ) ይህንን እንመለከት ዘንድ ይጋብዘናል :- በፋሲካው ዕለት ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ በመጣ ጊዜ ቶማስ ከእነሱ ጋር አልነበረም፡፡ ሌሎቹ ደቀመዛሙርት ጌታችንን አየነው ብለው ሲነግሩት አለመናቸውም ይልቅም ይህን አለ "የችንካሩን ምልክት በእጆቹ ካላየሁ ጣቴንም በችንካሩ ምልክት ካላገባሁ እጄንም በጎኑ ካላገባሁ አላምንም" (ዮሐ 20፡25)፡፡
.
.
ይህንን ስንሰማ "ክርስቶስ ስለ ትንሣኤው አስተምሮት የለም እንዴ ?..ጌታ አላዓዛርን ከሞት ሲያስነሳ በእዛ አልነበረም እንዴ? .. ሌሎቹን ደቀመዛሙርት ለምን አላመናቸውም?.. ለምንስ ሊዋሹኝ ይችላሉ ብሎ ገመተ? " ልንል እንችላለን፡፡ እውነታው ግን ሁላችንም በሕይወታችን እንደዚህ አይነት አጋጣሚዎች አሉን፤ በውስጣችን ከምናውቀው እውነት ይልቅ ጥርጥራችን በልጦብን ያውቃል፡፡ የቶማስ ጥርጥር የቀደመ እውቀቱን/አስተሳሰቡን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ቶማስ በክርስቶስ ከመጠራቱ በፊት ሰዱቃዊ ነበር ፤ ሰዱቃውያን ደግሞ በትንሣኤ አያምኑም ነበር (ሐዋ 23፡8)፡፡ የጌታችንን ትንሣኤ የተጠራጠረው የቀደመ የሰዱቃዊ አስተሳሰቡ መሰረት ሆኖት ነው፡፡
.
.
በተመሳሳይ ሁኔታም የእኛ ጥርጥሮች በብዛት አጥብቀን ከያዝናቸው አቅጣጫዎች የሚመጡ ናቸው፡፡ በስምንተኛው ቀን (በዳግም ትንሣኤ ዕለት) ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ በተገለጠላቸው ጊዜ ክርስቶስ ቶማስን ለምን አላመንክብኝም ብሎ አለጠየቀውም ይልቅም እንዲህ አለው "ጣትህን ወደዚህ አምጣና እጆቼን እይ እጅህንም አምጣና በጎኔ አግባው ያመንህ እንጂ ያላመንህ አትሁን" (ዮሐ 20፡27)፡፡ ጌታችንን ቶማስን እውቀቱን/አቅጣጫውን ይፈትን ዘንድ ጋበዘው፣ ከዛ ተሻግሮ ወደሚበልጠው ይጓዝ ዘንድ፡፡ የቶማስ ጥርጥር የቀደመ እውቀቱን ትቶ ወደሚበልጠው እምነት እንዲጓዝ ረዳው፤ ጥርጥር ብቻውን ሳይሆን ጥርጥሩን በጌታ ፊት ማቅረቡ ጭምር እንጂ፡፡
.
.
ቶማስም ወዲያው አመነ ክርስቶስም እንዲህ አለው "ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው" (ዮሐ 20፡29)፡፡ የዚህ ቃል አንደኛው አረዳድ የክርስቶስን ትንሣኤ በአይናቸው ሳያዩ የሚያምኑ (ክርስቲያኖች) ብፁዓናቸው የሚል ነው፡፡ ይህ ቃል ግን ከዚህ በላይ ነው፤ ካስቀመጡት አቅጣጫ ውጪ የሚመለከቱ፣ ከቀደመ እውቀታቸው በላይ የሚያዩ ማለት ነው፡፡ የቶማስ ጥርጥር ካስቀመጠው እውቀት በላይ እንዲያስብ፣ ከሚመለከተው አቅጣጫ ውጪ እንዲያይ ረድቶታል፤ በዚህም እምነት ትገኛለች፡፡
.
.

♡ሁላችንም ጥርጥር በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ያጋጥመናል፤ የሚጠበቅብን ጥርጥራችን በተለያዩ ነገሮች አብዝተነው (በንባብ፣ በመስማት፣ በመጠየቅ) ወዴት እንደሚያመራን ማየት ሳይሆን፤ እንደ ቶማስ ጥርጥራችንን ወደ ጌታ ይዘን መቅረብ ነው፡፡ ጌታም በሕይወታችን ውስጥ የሚገኙትን መጠራጠሮች ወደ እምነት መሻገሪያ መንገድ ያደርጋቸዋል፡፡ እምነታችን ጥርጥር ባለማስተናገዳችን አይለካም ይልቅም እነዚህን ጥርጥሮች ወደ እግዚአብሔር በማቅረባችን እንጂ፡፡ የእምነት ሙሉ የለም፤ ሁላችንም ከዛሬ የተሻለ እምነት ይኖረን ዘንድ ተጓዦች ነን፤ ጥርጥር ደግሞ ወደዛ መሻገሪያ ድልድይ ነው፡፡ እግዚአብሔር እምነት ይሰጠን ዘንድ ስንለምነው ጥርጥር እንደሚመጣ ጠብቁ፤ የእምነት መንገድ መሻገሪያ ድልድይ ነውና፡፡ የጌታችን የትንሣኤው ብርሃን በእኛ ላይ ያብራልን፡፡ የቅድስት ማርያም እና የቅዱሳኑ ሁሉ በረከታቸው በእኛ ላይ ይደር፡፡ አሜን።

ተወዳጅ ስለሺ

#የትንሣኤ ሣምንት
#ቶማስ
#ማክሰኞ

2 weeks, 2 days ago

እርሱ ጻድቅ ሲሆን ፍጹም ቡሩክ አምላክ
በመስቀል ተሰቅሎ ወደደን ያለ ልክ
ስለ በደላችን ለእኛ ተሰቀለ
በሥጋው ታመመ ግፍን ተቀበለ

በሲዖል እሥራት ለተጎሳቆሉት
ሰላምን አወጀ ሆናቸው ድኅነት
ወኅኒ የነበሩ የታሠሩት ነፍሳት
በመስቀል ተሠብሯል የእጃቸው ሠንሰለት
.
.
ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

2 weeks, 3 days ago

ስለ ፍቅር

"የማይታመም የርሱን ሕማሙን እንናገራለን ፣ የማይሞት የርሱን ሞቱን እንናገራለን ፣ የፍቁር የጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ሕሊናም ይመታል!"

እጅን ወደኋላ መታሰር ➻ ሰው እጁን ወደ ኋላ ቢታሰር ልቀቁኝ፣ ምን አደረኩ ፣ አለቃችሁም እያለ ይዝታል ፣ ለመፈታትም ይታገላል። ክርስቶስ ግን ይህን አላደረገም በቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት ”እንደ ሌባ የኋሊት አሰሩት ፣ እንደ የዋህ በግ በፍቅር ተከተላቸው፣ ሊፈርዱበት በአደባባይ ተቀመጡ። ”ሲል እንደተጻፈ ሁሉን በሥልጣኑ ማድረግ የሚችል ጌታ ዝም ብሎ በፍቅር ተጎተተላቸው።

በገመድ መጎተት ➻ መጎተት ድካምን ያበረታል ፣ ሰውነትን እየከረከረ ከባድ ስቃይን ያደርሳል ፣ ያቈስላል ፣ አካልን ይልጣል ፣ እንኳን ለሰው ልጅ ለእንስሳት እንኳን ምን ያህል ከባድ ነው?ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ይህን ስለ ፍቅር ታገሠ።

ምድር ላይ መውደቅ ➻ ከምድር ላይ መውደቅ ለእሾህ እና ለጠጠር ያጋልጣል። በሰዎች ዘንድም መሳለቂያ ያደርጋል። ምንም ባልቀመሰ፣ ውኃን እንኳን ባልቀመሰ ሆድ ሲሆን ደግሞ ስቃይ ይበረታል።ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ይህን ስለ ፍቅር ታገሠ።

ልብስን መገፈፍ ➻ ሰው እርቃኑን በልብሱ ይሸፍናል ፣ ማዕረጉንም በልብሱ ይገልፃል። ለከዋክብት የብርሃን ልብስ ያለበሳቸው እርሱ ግን በዕለተ ዓርብ እርቃኑን በቀራንዮ አደባባይ አቆሙት። ይህንንም ስለ ፍቅር ታገሠ።

ምራቅ ሲተፉበት መታገስ ➻ ምራቅ መትፋት ሰውን ያስቀይማል ፣ ጥላቻንና ንቀትን ያሳያል። የዕወሩን ዓይን ያበራ እርሱ በፊቱ ላይ ተተፋበት። ቅዱስ ኤፍሬም “ለእኛ ፊት ክብርን የሰጠ እንዳንተ ያለማን አለ? የዕውሩን አይን ስታበራ እንኳን አርአያችንን አክብረህ ወደ መሬት ተፋህ እንጂ በፊቱ ላይ አልተፋህበትም” ሲል ገለጸ።እነርሱ ግን ይህን ድንቅ የሚያደርግ ጌታ ተፉበት እርሱም ስለፍቅር ታገሣቸው።

በጥፊ መመታት ➻በጥፊ መመታት ንዴትን እልህን ፣ብሶትን ቀስቅሶ ለድብድብ ይጋብዛል፣ ትዕግሥትን ይፈታተናል።እርሱ ግን ስለወደዳቸው ፈንታ በጥፊ ሲመቱት ምንም አልመለሰም።

ጀርባን መገረፍ ➻ በጅራፍ መገረፍ ይለበልባል ፣ሰውነትን ያቆስላል።ጅራፉ ጫፍ ላይ ስለት ሲኖረው ደግሞ ስቃዩን ማሰብ ይከብዳል። ስጋው አልቆ አጥንቱ እስኪታይ ቢገርፉትም እርሱግን ይህንንም ስለፍቅር ታገሠ።

ራስን በዱላ መመታት

የእሾህ አክሊል መድፋት ➻ አንዲት እሾህ ስትወጋን እንኳን ሰውነታችን ላይ ታላቅ ህመም ይፈጥርብናል ፡ እሾሆችን ሰብስቦ አክሊል ሠርቶ በራሱ ሲያደርጉበት ስቃዩ እንዴት የከፋ ይሆን?ለሱራፌል የብርሃን ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የእሾህ አክሊል አቀዳጁት።ይህንንም ስለፍቅር ታገሠ።

መስቀል መሸከም

በችንካር መቸንከር

በመስቀል ላይ መሰቀል

መራራ ሐሞትን መጠጣት ➻ ሐሞት መራራ ጣዕም ያለው ሲሆን ተጠማሁ ባላቸው ጊዜ መራራ ሐሞትን ሰጡት።

በቸርነቱ ይቅር ይበለን!

#ሰሙነ ሕማማት
#ስቅለት
#ዓርብ

2 months, 3 weeks ago

🎲 Quiz 'ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 4'
*🖊 5 questions · 5 min*

2 months, 3 weeks ago

🎲 Quiz 'ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 2 እና 3'
*🖊 5 questions · 5 min*

2 months, 3 weeks ago

🎲 Quiz 'ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ 1'
*🖊 6 questions · 5 min*

2 months, 3 weeks ago

☝️ነቢዩ ዮናስ_'ነቢየ አሕዛብ'

ነቢዩ ዮናስ የእስራኤል ነቢይ ሲሆን የስሙ ትርጒም 'ርግብ''የዋህ' ማለት ነው። ትውልዱ ከነገደ ይሳኮር ወገን ሲሆን አባቱ አማቴ እናቱ ደግሞ ሶና ይባላሉ። በአይሁድ ትውፊት እንደሚነገረው ነቢዩ ኤልያስ ከሞት ያስነሳው የሠራፕታዋ መበለት ልጅ እርሱ ነው። ከራሱ መጽሐፍ ውጪ በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት የተጠቀሰም ነቢይ ነው። በ825-784 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በዳግማዊ ኢዮርብአም ዘመነ መንግሥት የነበረ ሲሆን ከነቢዩ አሞጽ ጋርም በዘመን ይገናኛሉ። በብሉይ ኪዳን ስለ አሕዛብ የሚናገሩት ሁለት መጻሕፍት አንደኛው ነው። ስለ ኤዶማውያን የሚናገረው ትንቢተ አብድዩ ሲሆን ነቢዩ ዮናስ ደግሞ ስለ ነነዌ ሰዎች ይናገራል። በዘመኑም ያስተምር የነበረው ከምድረ እስራኤል ውጪ በነነዌ ስለነበረ 'ነቢየ አሕዛብ' ይባላል። በዚህም ኤዶማዊ የደም አፍሳሽነት ጠባይዕ  በጽዮናዊ መንፈሳዊ ማንነት የተካ አዲስ ሰው እንዲመጣ እንዲሁም አሕዛብ አምነው በንስሐ እንዲመላለሱ እግዚአብሔርም ቤተክርስቲያንን በአሕዛብ መካከልም ስንኳ እንደሚያቆም በምሳሌያዊነት የቀረቡ ምስክሮችና አመልካቾች የነበሩ ናቸው።

የነቢዩ ዮናስ የትንቢት መጽሐፍ በዕብራይስጡ ቀኖና መጽሐፍት ከደቂቅ ነቢያት አምስተኛ ሲሆን በግእዝ እና በሰባ ሊቃናት ስድስተኛ ነው። አይሁድ ነቢያትን ሲያሳድዱና ሲገድሉ እሊህ የነነዌ ሰዎች ግን አሕዛብ ሲሆኑ የነቢዩ ዮናስን ትምህርት በአንድ ቀን ተቀብለው በእውነተኛ ንስሐ ተመልሰዋል። ነቢዩ ዮናስ አስቀድሞ ወደ ነነዌ መሄድ ለማስተማር ያለመፈለጉንም ነገር በትንቢት መነጽር የወገኖቹን ጥፋት ስለማየቱ እንጂ አሕዛብን በመጥላት እንዳልሆነ የጥንት ሊቃውንት ይናገራሉ። ሙሴ ስለ ሕዝቡ ከሕይወት መጽሐፍ ይደመሰስ ዘንድ እንደለመነ ነቢዩ ዮናስም እንዲሁ ስለ ወገኖቹ ጥፋት በማዘን ያለው እነደሆነም ይናገራሉ።  በአራት ምእራፍ የተጠቀለለው የትንቢት መጽሐፉ ይህን የእርሱን ሐሳብና መልእክት በእምነት ገንዘብ ያደረጉ የነነዌ ሰዎች አሕዛብ ሳሉ በጠማማ መንገዳቸው በራሳቸው ፍርድን ከጨመሩ አይሁድ ይልቅ በፍጹም ንስሐ ስለመመለሳቸው መዳናቸውን ያስረዳል። በታሪኩ ሰንሰለት ዉስጥ ስለ እግዚአብሔር መሐሪነትና ጥልቅ ፍቅር ፣ የሰዎችን ድካም በመኮታዊ ጥበቡም ስለመቃኘቱ እንዲሁም ፍጥረቱን ለመገሰፅ ግእዛኑን ሳይቀር እንዲጠቀም ፣ የዮናስንም የዉሀትና የነነዌ ሰዎችን መታዘዝና እምነት እንረዳለን።  የዮናስ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በከርሠ አንበሪ መቆየት ለጌታችን ሞትና ትንሣኤ በምሳሌያዊ ማስረጃነት በራሱ በጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠቅሶአል። (ማቴ 12÷39: ሉቃ11÷29)

‹ 'እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይጸጸት እንደ ሆነ ፥ ከጽኑ ቍጣውም ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?' እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸው እንደተመለሱ ሥራቸውን አየ ፤ እግዚአብሔርም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጽቶ አላደረገውም። ›

📖— ዮናስ 3፥9

እነሆም ከዚህ ጽሑፍ በመቀጠል ሙሉውን መጽሐፍ ታነብቡ ዘንድ ጋበዝን!

#ኦርቶዶክሳዊ_ወጣት

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago