AASTU Muslims union

Description
ይህ የቴሌግራም ቻናል ሁሉንም የ አአሳቴዩ ሙስሊም ተማሪዎች የሚመለከት ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ኢስላማዊ ትምህርቶች፣ የተለያዩ ዳእዋና ሙሃደራዎች እንዲሁም ጀመዓውን የሚመለከቱ መልእክቶች ይለቀቁበታል። ከዚህ ውጪ ሌላ ቻናል የሌለን መሆኑን እና የትኛውም ከዚህ ቻናል ውጪ የሚለቀቅ ነገር እኛን እንደማይወክል እናሳስባለን።

ለማንኛውም አስተያየት

@ab097ab097
@abduw99
Advertising
We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 1 week ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot

For Advertisement👇🏿
@atcads

Last updated 22 hours ago

NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ

ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 2 months, 3 weeks ago

2 дня, 5 часов назад

Today's Tajweed program is as scheduled.

2 дня, 14 часов назад

ከዱንያ ይልቅ ዲናዊ ጉዳዮች ያሳስቡህ። ድክመትህን እመን፣ ክፍተትህን አርም ... ለመሻሻልና ለመለወጥ ሁሌም ዝግጁ ሁን።

ኢማኔ ደከመ፣ቀልቤ ደረቀ፣ከአላህ ራቅኩኝ፣
የቂኔ ከዳኝ፣ተወኩሌ ጠፋ፣ከዱዓ ተሳነፍኩኝ፣ለዚክር ምላሴ ከዳኝ፣
ቁርአንን ዘነጋሁ፣አዘኔታ አጣሁኝ፣
ጥሩ ሶላት ከሰገድኩ ቆየሁ፣ሱና መስገድ ተውኩኝ፣ከዋጂቡ ችላ አልኩኝ፣…

አላህ ምስክሬ ነው በነኚህ ነገሮች በእጅጉ ከተቆጨህና ለማስተካከልም አብዝተህ  ከደከምክ ሌላውን ዱንያዊ ጉዳይ የኑሮውን፣ የልጁን፣ የትዳሩን፣ የሀብቱን ጉዳይ ለአላህ ተው። አላህ ይበቃሃል፣ ያሳካልሃል አትጠራጠር።

منقول

3 дня, 4 часа назад

Today after megrib we will have tajweed program

4 месяца, 1 неделя назад

ከሰኞ እስከ ሰኞ

ተከታታይ ወርቃማ ቀናት ከፊታችን፦

√ ሰኞ: የሙሐረም 9ኛ ቀን፣
√ ማክሰኞ: የሙሐረም 10ኛ ቀን → የዐሹራእ ጾም፣
√ ረቡዕ : የዐሹራእ ቀጣይ ቀን፣
√ ሐሙስ: ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን፣
√ ጁሙዓህ: የአያሙልቢዽ የመጀመሪያ ቀን (ሙሐረም 13)
√ ቅዳሜ: አያሙልቢዽ፣
√ እሁድ: አያሙልቢዽ፣
√ ሰኞ: ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን

አላህ አላህ!

እንኳን ተጨማሪ ሰበብ ኖሮት ሙሐረምን ሙሉውን መፆም ይወደዳል።

የቻልን እንጹም፣ ሌላውንም እናመላክት። አላህ ያግራልን።

منقول

4 месяца, 1 неделя назад

ـــــــــــــــــ

ከዐሹራ ጋር የነበረው የቀደምቶች መንገድ

✍?ሸይኸ አል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ رحمه الله: ‏

"መልክተኛውም ሆነ አራቱ የሙስሊም መሪ የነበሩት ኹለፋኦች በዐሹራ ቀን

➡️የሀዘንና የትከዜ ቀን (እንደ ሺዐዎቸ)
➡️የደስታና የመዝናኛ ቀን (እንደ አህባሽ+ሱፍዮች) ሱና አላደረጉትም ይላሉ

?"الفتاوى الكبرى" (١/٢٠٢)?ምንጭ

አዎ የዐሹራ ቀን ቀኑን አስቦ ከፆም ውጪ በምንም የተለየ ዒባዳህ ወደ አላህ ለመቃረብ መሞከር ኢስላም አላዘዘበትም።

4 месяца, 1 неделя назад

ሙሐረም እና ዓሹራ-

~በቁርኣን ዉስጥ እንደተጠቀሰው የዓመቱ ወራት 12 ናቸው፡፡ ከነርሱ ዉስጥም አራቱ የተከበሩ ናቸው፡፡ ሦስቱ ተከታታይ ወራት ናቸው፡፡ ዙልቂዕዳ፣ ዙልሒጃ፣ ሙሐረም፡፡ ረጀብ ተነጥሎ ነው የሚገኘው፡፡ አሁን የተከበረው ሙሐረም ዉስጥ ነው ያለነው፡፡ ከተከበሩ እና ልቅና ከተሠጣቸው የዓመቱ ወራት ዉስጥ አንዱ ነው፡፡ በኢስላማዊው ጨረቃ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወርም ነው፡፡ 1446 ዓመተ ሂጅራ ከገባ ዛሬ ሰኞ 2ኛ ቀናችን ይዘናል፡፡

የአላህ መልዕክተኛ (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) «ከረመዷን ቀጥሎ ምርጡ ፆም የአላህ ወር ሙሐረም ወር ፆም ነው፡፡ ከግዴታ ሶላት ቀጥሎ ምርጡ ሶላት የሌሊት ሶላት ነው፡፡» ብለዋል፡፡ ሙሐረም የአላህ ወር ነው መባሉ በራሱ ልቅናውን ከፍ ያደርገዋል፡፡

ሙሐረምን ጨምሮ በአራቱ የተከበሩ ወራት ዉስጥ ራሣችሁን አትበድሉ ተብለናል፡፡ በደል ሲባል ብዙን ጊዜ ለኃጢኣት ነው፡፡ አላህ ልቅና በሠጠው ወር ዉስጥ ወንጀል መፈፀም በትልቁ ራስን መበደል ነው፡፡ በርግጥ ወንጀል ሁሌም ክልክል ቢሆንም፤ በነኚህ ወራት ዉስጥ ክልክነቱ ጠብቋል፡፡ አላህ ይጠብቀን፡፡

የሙሐረም ወር አሥረኛው ቀን ዓሹራ ይባላል፡፡ በዚህ ቀን ዉስጥ ትልቅ ክስተት ተከስቷል፡፡ ትልቅ ድልም ተበስሯል፡፡ እውነት በዉሸት ነግሷል፡፡ ነቢያችን (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ከመካ ተሰደው መዲና ሲደርሱ የመዲና አይሁዶች የዓሹራን ቀን ሲፆሙ አገኟቸው፡፡ «ምንድነው ይህ የምትፆሙት ቀን?» በማለትም ጠየቋቸው፡፡ «ይህ ቀን አላህ ሙሳን እና ህዝቦቹን ነጃ ያወጣበት ፈርዖንና ሠራዊቱን በዉሃ ያሠጠመበት ቀን ነው፡፡ ሙሳ አላህን ለማመስገን ብለው ፆሙት፡፡ እኛም ለዚያ ብለን ነው የምንፆመው፡፡» አሉ፡፡ የአላህ መልዕክተኛም «ከናንተ ይልቅ እኛ ነን ለሙሳ የምንቀርበው፡፡» አሉና ፆሙት፤ ተከታዮቻቸዉም እንዲፆሙት አዘዙ፡፡» አሉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሙስሊሞች ይፆሙታል፤ ልጆቻቸዉንም ያስፆማሉ፡፡

በዚህ ወር ዉስጥ መልካም ሥራ የተባለን ሁሉ ማብዛት ይወደዳል፣ ፆም ከሥራዎች ሁሉ ምርጡ ሥራ ነው፡፡ ሰደቃ፣ ዱዓእ፣ ሶላት፣ አላህን ማውሳት ማብዛት እና ሌሎችም ብዙዎችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

በአሥረኛው ቀን መፆም የተወደደ ነው፡፡ ሳያስበው አፍጥሮ ያነጋ ሰው እንኳን የተቀረዉን ቀኑን በፆም ቢያሳልፍ ይመረጣል፡፡ ነቢያችን ቀኑን ፆመውታል፤ ግና በሚመጣው ዓመት አላህ ካኖረኝ ዘጠነኘዉንም ቀን ጨምሬበት እፆማለሁ ብለው ነበር፡፡ በሌላም ሐዲሥ ዓሹራን አንድ ቀን ከፊቱ አሊያም ከኋላው ፁሙ ብለው ነበር፡፡

•አላህ ሆይ ወሩንና ዓመቱን ሁሉ መልካም አድርግልን፡፡ በረከትህንና ችሮታህንም ለግሰን፡፡ አላህ ሆይ ሙስሊም አድርገህ አኑረን፣ በእስልምና ላይም ግደለን፡፡

منقول

5 месяцев, 2 недели назад

‏{فمن عفا وأصْلح فأجره على الله}
??????
      ትርጉም ?( ይቅር ያለና ያሳመረ
                         አጅሩ ከአላህ ነው።)

ይህ አያ ላይ ? (وأصلح) ማለት አፉ ሚባለው  ሰው አፉ በመባሉ ጥቅም
ሲኖረው ብቻ ነው።

?አፉ በመባሉ ይባስ ለሚያጠፋማ
        ወይም አፉ መባሉ በድጋሚ ሌላ
        ጥፋት ላይ እንዲገኝ ሰበብ
        ሚሆነው ከሆነ ይህ ማለት   

ምሳሌ:ለአመፀኛ
         አፉ ማለት ይህ በአመፀኝነቱ ላይ
         እንዲቀጥል ሰበብ ስለሚሆነው
          ለእንደዚህ አይነቱ ሰው አፉ
           አለማለቱ በላጭ ነው።

? እንደው ምናልባትም አመፁ ታይቶ አፉ አለማለቱም ዋጂብ ሊሆን ይችላል።

?شرح الواسطية?ምንጭ
ابن عثيمين-رحمه الله-:?ምንጭ

5 месяцев, 2 недели назад
5 месяцев, 3 недели назад

ለፈገግታ

የስስታም ሀጅ

አንድ ስስታም ሰው ሀጅ አደረገ ከሀጁም ሲመለስ ጓደኞቹ ተሰብስበው ቤቱ መጡና ከሀጅ መልስ አዘጋጃለሁኝ ብሎ ቃል ገብቶላቸው የነበረውን የድግስ ፕሮግራም እንዲያዘጋጅ ጠየቁት እሱም

"በእርግጥም ከሀጅ በፊት ተናግረነው
     የነበረውን ሁሉ አላህ ይቅር ብሎናልኮ
     ብሏቸው"እርፍ።

[ أخبار الحمقى والمغفلين ] ?ምንጭ

5 месяцев, 4 недели назад

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

?በአላህ ፈቃድ ዛሬ ሀሙስ 15/09/2016  ከአስር  ሰላት በኋላ  የ (الآجرومية (في النحو  ኪታብ እና ከመግሪብ ሰላት በኋላ የ
أصول السنه
ኪታብ ቂርአት ኘሮግራም ይኖረናል።

አሏህ ይወፍቀን

We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 1 week ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot

For Advertisement👇🏿
@atcads

Last updated 22 hours ago

NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ

ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 2 months, 3 weeks ago