Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ATC NEWS

Description
#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot

For Advertisement👇🏿
@atcads
Advertising
We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 4 weeks, 1 day ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot

For Advertisement👇🏿
@atcads

Last updated 1 week ago

💫💫💫NGOjobs💫💫💫
🆕ማንኛውንም ስራ ከ 0 አመት ጀምሮ በየቀኑ እና በየሰአቱ
🆓 ነፃ የትምህርት እድሎች
✔️ስልጠናዎች
🌏 ለማስታወቂያ ወይንም ስራ ለማስነገር @promoter14 ላይ ያናግሩን !
Promotion የምትሰሩ አናግሩን @promoter14
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 5 days, 17 hours ago

1 Woche her
ATC NEWS
1 Woche her
ATC NEWS
1 Woche her
ATC NEWS
2 Wochen her
ATC NEWS
2 Wochen her
ለመጨረሻ ግዜ የወጣ ማስታወቂያ ***‼️***

ለመጨረሻ ግዜ የወጣ ማስታወቂያ ‼️
#WachamoUniversity

መጋቢት 06/2016 ዓ/ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተፈጠረው የሲስተም ችግር ምክንያት የባንኩን ገንዘብ በማጭበርበር ገንዘብ ያወጣችሁ ወይንም ያዛወራችሁ ተማሪዎች እስከ 04/08/2016 ዓ/ም እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ገንዘቡን ለባንኩ እንድትመልሱ እና የመለሳችሁበትን ማረጋገጫ /ደረሰኝ/ ከባንኩ እንድታመጡ በቀን 03/08/2016 ዓ/ም ጥብቅ ማስታወቂያ ማውጣታችን ይታወቃል፡፡

ስለሆነም በማስታወቂያው መሠረት ገንዘቡን የመለሳችሁ ተማሪዎችን እያመሰገንን፤ እስከ አሁን ገንዘቡን ለባንኩ ያልመለሳችሁ ከዚህ በታች ከ1 እስከ 55 ድረስ ስም ዝርዝራችሁ የተገለጠው ተማሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ እስከ 11/08/2016 ዓ/ም ድረስ እንድትመልሱ እያሳሰብን ፤ ገንዘቡን የማትመልሱ ተማሪዎች እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን በጥብቅ እናስታውቃለን። (ዩንቨርስቲው )

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

2 Wochen, 1 Tag her
ATC NEWS
3 Wochen her
ATC NEWS
3 Wochen her
[#KotebeUniversityofEducation](?q=%23KotebeUniversityofEducation)

#KotebeUniversityofEducation

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በዲፕሎማ በቀን መርሐ ግብር ተመላላሽ ተማሪዎችን በክፍያ ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ ስለሆነም ከታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ከሚያዝያ 04 እስከ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በዋናው ሬጅስትራር በመቅረብ ማመልከት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርትና መረጃዎች

👉ለዲፕሎማ

፨በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለተፈተኑ

📌የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች
➢ ለወንድ 245ና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው፤ ➢ ለሴት 224ና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው፤

📌የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች

➢ለወንድ 208 ና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው፡ ➢ለሴት 190 ና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው፡

[ተጨማሪ መስፈርቶችን ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ]

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

3 Wochen, 1 Tag her
ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር …

ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ሕንጻዎችን እያስገነባ ነው።

ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የሕንጻዎችና መሠረተ ልማቶች ግንባታ እያካሄደ መሆኑን የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግንባታ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋሁን ገብሩ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ግንባታዎች እያከናወነ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜም 25 የተለያዩ ሕንፃዎችና መሠረተ ልማቶች እየተገነቡ ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተያዘው በጀት ዓመት ከሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተለያዩ ሕንጻዎችንና መሠረተ ልማቶችን እየገነባ እንደሚገኝ ጠቅሰው፤ የሕንጻ ግንባታዎቹ በተለይም የመማር ማስተማሩን ሂደት ምቹ ለማድረግ፣ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና የተማሪ ቅበላ አቅምን ለመጨመር የሚረዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ግንባታው የአስተዳደር፣ የተማሪዎች አገልግሎት ሕንጻዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተማሪዎች ዶርሚተሪዎች፣ ቤተሙከራዎች (ላቦራቶሪዎችን) ጨምሮ አይሲቲ ታወሮች እና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ያካተተ ነው።

ሙሉውን የኢፕድ ዘገባ ለማንበብ 👇
https://press.et/?p=125521

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

4 Wochen her

‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም!! ረ/ፕ ወይም ተባባሪ ፕሮፌሰር ነን የሚሉትን ሰዎች ዩንቨርሲቲው “አቶ”ነው የሚላቸው"ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ  ‘‘የክብር ዶክትሬት ሽልማት እና የዶክትሬት ትምህርት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ አቅራቢነት በፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ አወያይነት መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም በዚሁ ርዕሰ ላይ የገለጻና የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር::

በዚህ የገለፃና የውይይት መድረክ ላይ  የክብር ዶክትሬት ሽልማትን በተመለከተ በፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ባቀረቡት ሰፊ የጥናት ፅሑፍ እንደገለፁት  የክብር ዶ/ር ሽልማት እንጂ ለመጠሪያነት አይውልም:: እንዲሁም ረዳት/ፕሮፌሰር ወይም ተባባሪ/ፕሮፌሰር የሚለውም ስያሜም በጋዜጠኞች ብቻ የሚሰጥ ቅፅል እንጂ ለመጠሪያነት እይውልም በማለት ተናግረዋል:: በኢትዮጵያ የክብር ሽልማት አሰጣጡ በዩንቨርስቲዎች ላይ ያለውን ችግርም በዝርዝር አንስተው ሊያስተካክሉ የሚገባቸውን ጉዳዮችንም በዝርዝር ገልጸዋል::

በተለይ ፕሮፌሰር ማስረሻ የክብር ዶክትሬትን በተመለከተ በፁሁፋቸው ላይ እንደገለፁት ከሆነ
" በየትኛውም አለም "ክቡር ዶ/ር እገሌ" ተብሎ ሲጠራ አይታወቁም :: የክብር ዶ/ር ይህ በእኛ ሐገር ብቻ በጋዜጠኞችና ከአካዳሚያዊ ክበብ ራቅ ባሉ ሰዎች  የሚጠራ ሲሆን ለዚህ ክፍተት ደግሞ የክብር ዶ/ር የሚሸልሙ ዩንቨርሲቲዎቹ የክብር ዶ/ር ለመጠሪያነት እንደማይውል ለተሸላሚዎቹና ለህዝቡ አለመግለፃቸውን እንደችግር አንስተዋል:: አያይዘውም ለነገሩ ረ/ፕ እና ተባባሪ ፕሮፌሰር የሚል መጠሪያ የሚሰማው በእኛ ሐገር ጋዜጠኞች ብቻ ነው::አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ እነዚህን ሰዎች ረ/ፕ /ተባባሪ ፕሮፌሰር( እገሌ) ብሎደብዳቤ አይፅፍላቸውም:: ዩንቨርስቲዮቹ ለእነዚህ ሰዎች አቶ (እገሌ) ብሎ ነው ደብዳቤ የሚፅፍላቸው:: ጋዜጠኞች ይህን ስያሜ የሚሰጡት ዶክተር ላልሆነ ሰው ከፍ ማድረጊያ እየመሰላቸው የሚጠሩበት ስያሜ ነው:: ለነገሩ  ባይገርማችሁ አሁን ደግሞ እጩ ዶክተር" እየተባለ መጠራት ትጀምሯል:: በማለት ተሰብሳቢውን ፈገግ አድርገውታል::" በማልት የገለፁ ሲሆን አያይዘውም

የክብር ዶክትሬትን በተመለከተ ብቸኛዋና በጥሩ አርአያነት የምትጠቀሰው ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ናት:: ከባህርዳር ዩንቨርስቲ የክብር ዶክተር ሽልማትን ስትቀበል "በለመደ አፋችሁ ዶክተር ብላችሁ  እንዳትጠሩኝ" ብላ የተናገረችውን አድንቀው ተናግረዋል:: እኔም ለፕሮፌሰር ማስረሻ ፕሮግራሙ ካለቀ በኃላ አንድ ጥያቄ አነሳሁላቸው "የዩንቨርሲቲው ሰዎች እኮ ናቸው ጋዜጠኞቹን በረዳት ፕሮፌሰር / በተባባሪ ፕሮፌሰር ስም ጥሩኝ የሚሉት እነሱ እንጂ ጋዜጠኛው አይደለም" ስላቸው በትህትና ወንድሜ "እነዚህ ሰዎች በራሳቸውና ባገኙት እውቀት የማይተማመኑ ሰዎች ናቸው:: እንዲህ የሚሉ ካሉ ያሳዝናሉ" ብለውኛል::

በዚህ ፕሮግራም ላይ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ  የኢትዮጵያ በርካታ ምሁራን ተገኝተው ነበር::

(ይትባረክ ዋለልኝ)

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 4 weeks, 1 day ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot

For Advertisement👇🏿
@atcads

Last updated 1 week ago

💫💫💫NGOjobs💫💫💫
🆕ማንኛውንም ስራ ከ 0 አመት ጀምሮ በየቀኑ እና በየሰአቱ
🆓 ነፃ የትምህርት እድሎች
✔️ስልጠናዎች
🌏 ለማስታወቂያ ወይንም ስራ ለማስነገር @promoter14 ላይ ያናግሩን !
Promotion የምትሰሩ አናግሩን @promoter14
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 5 days, 17 hours ago