Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
ከቅዱስ ገብርኤልና ከቅድስት ኤልሳቤጥ ጋር እንዲሁም ቀድሞ ከነበሩ ሰዎች ጋር የድንግልን ክብር እንናገራለን።
የድንግል ክብር እንደምንድነው? ቢሉ በድንግልና ጸንሶ በድንግልና መውለድ ነው። ወይንም ደግሞ በቃል ኪዳኗ ለሚታመኑ፣ በተስፋዋ ለሚማጸኑ ሁሉ ምሕረት ይቅርታ ማሰጠት ነው።
[ዛሬም ካሉ ቅዱሳን አባቶቻችን ጋር ሆነን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናከብራታለን፣ እናገናታለን፣ በፍጹም ምስጋና እናመሰግናታለን።
አሁን እመቤታችንን የምናገናት ሆኖ አይደለም! ገናንነቷን እንናገራለን ስንል ነው እንጂ።
ኃይለ ልዑል ወልድ ከሦስቱ ግብራት ከለከላት። ከዘርእ፣ከሩካቤ፣ከሰስሎተ ድንግልና። "ውእቱሰ ንጹሕ እምነ ሠለስቱ ግብራት ዘውእቶሙ ዘርእ ወሩካቤ ወሰስሎተ ድንግልና እለ ሥሩዓን በእጓለ እመሕያው ወእሙራን ቦሙ" ብሎ ሊቁ እነሰደተናገረው](https://t.me/dn_mez)።
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለው ከሚመሰገኑት ከሦስቱ ቅዱስ አንዱን ቅዱስ ከሦስቱ አካላት አንዱን አካል ወለድሽው።
ይኸውም የዓለም መድኃኒት ነው። ተወልዶም ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ አዳነን።
መልካም ቀን ተመኘሁላችሁ!!!
ዲ/ን መዝሙር ንጉሴ
28-02-17 ዓ.ም
ታላቁ አባ መቃርስ
ከ፹ ዓመት በላይ በበረሃ የተጋደሉ፣
በአስቄጥስ ገዳም ፭፼ መነኮሳትን በመመገብ የመሩ፣
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ ወደሙን ተቀብለው ስለ ሥጋ ወደሙ ክብር ሲሉ ለ፷ ዓመት ምራቃቸውን ሳይተፉ የኖሩት ታላቁ አባት ናቸው።
አባ መቃርስ በነሐሴ ፲፱ ፍልሰተ አጽማቸው ሳስዊር ከሚባል ሀገር ወደ አስቄጥስ የተፈጸመበት የከበረ በዓል ነው፡፡
ታላቁ አባ መቃርስ እጅግ ሩህሩህ አባት ነበሩ፡፡ በአንድ ወቅት አንዲት ዘመሚት ነክሳቸው ገደሏት፡፡ ነገር ግን ወዲያው ተጸጽተው ስለ ትንኟ ነፍስ ወደ በረሃ ወንዝ ወርደው ሥጋቸውን ለዘመሚቶች ሰጥተው ዘመሚቶቹ እየነከሷቸው ስድስት ወር ኖረዋል፡፡ ከስድስት ወር በኋላም ወደ ገዳማቸው ሲመለሱ ምን እንደሆኑና የት እንደነበሩ ማንም አላወቀም ነበር፡፡
አንድ ቀንም በበዓታቸው ሳሉ አንዲት ሴት ጅብ መጥታ የአባታችንን ቀሚስ ይዛ እየጎተተች ወስዳ ዋሻዋ ውስጥ አደረሰቻቸው፡፡ ሦስት ልጆቿንም አወጣችላቸው፡፡ እርሳቸውም ቀርበው ቢመለከቷቸው ዕውሮች ናቸው፡፡ እናቲቱንም ጅብ እያደነቁ ግልገሎቿን ይዘው በዐይኖቻቸው ውስጥ ምራቃቸውን ተፍተው አዳኝ በሆነ በክርስቶስ መስቀል ምልክት አማተቡባቸው፡፡ ወዲያውም ድነው ይፈነድቁ ከእናታቸውም ጋር ይጫወቱ ጀመር፡፡ መቃርስም እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ወደ በዓታቸው ተመለሱ፡፡ እናቲቱ ጅብም የበግ አጎዛ አምጥታ ሰጣቻቸውና አባ መቃርስም አጎዛውን የመኝታቸው ምንጣፍ አደረጉት፡፡
በግብፅ ሀገር ታላቅ ረኃሀብ ተከሥቶ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ ጢሞቴዎስ መልእክተኛ ወደ እርሳቸው በመላክ አብረው ጸሎት እንዲያደርጉ ጠየቋቸው፡፡ አባ መቃርስም ሄደው በጋራ ቢጸልዩ ዕለቱን ሕዝቡ ‹‹በቃን በጎርፍ እንዳናልቅ…›› እስኪል ድረስ ዝናብን አዝንበውላቸዋል፡፡
ታላቁ አባ መቃርስ ከእስክንድርያው መቃርስ ጋር ያሳለፉት ታሪክም እንዳለ ቅድሳት መጻሕፍት ይጠቅሳሉ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ለሁለቱም በአካል ተገልጦላቸው ታቦቱንና ንዋየ ቅዱሳቱን አክብሮታል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስና ወንጌላዊ ቅዱስ ማርቆስም በአካል ተገልጠውላቸው በቅዳሴ ጊዜ ተራድተዋቸዋል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ዮሐንስም የየራሳቸውን መልእክት አንብበውላቸዋል፡፡ ቅዱስ ዳዊትም መዝሙሩን ዘምሮላቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶላቸዋል፡፡
ቅዱሳን መላእክትም ይራዱአቸው ነበር፡፡ አባ መቃርስና የእስክንድርያው መቃርስ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ቀድሰው ለሕዝቡ ሥጋ ወደሙን አቀበሉ፡፡ ጌታችንም ለአባ መቃርስና ለእስክንድርያው መቃርዮስ ተገልጦላቸው ታላቅ ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም ለዚያች ደሴት ሕዝቦች ሌላ ጳጳስ ከሾሙላቸው በኋላ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ባሰቡ ጊዜ መልአክ መጥቶ ነጥቆ ወስዶ የእስክንድርያ ጳጳስ አባ ጢሞቴዎስ ፊት አቆማቸው፡፡ እርሱም ሁለቱን ባያቸው ጊዜ እጅግ ተደሰተ፤ ከዚያም መልአኩ ወደ ገዳመ ሲሐት ወሰዳቸው፡፡ በመጨረሻም ግንቦት ስድስት በሽምግልና ሆነው በታላቅ ክብር ዐርፈዋል፡፡
ታላቁ አባ መቃርስ ከዕረፍታቸው በኋላ ከሀገሩ ከሳስዊር ሰዎች መጥተው ሥጋቸውን በድብቅ ወስደው ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ከዚያ አኑረዋቸዋል፡፡ ሆኖም በዚያን ጊዜ እስላሞች በመንገሣቸው ክርስቲያኖች ለመሰደድ ተገደዱ፡፡ በዚህም የተነሣ የአባ መቃርስን ሥጋ ወስደው በድጋሚ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በዚያ አኖሩት፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱም ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የአባ መቃርስን ሥጋ እንዲሰጠው እያለቀሰ ወደ እግዚአብሔርን ልመና ካቀረበ በኋላ የአስቄጥስ ገዳም አረጋዊ መነኮሳትንም አስከትሎ የአባ መቃርስ አጽም ወዳለበት ሄደ፡፡
ሕዝበ ሳስዊር ግን በመከንኑ መሪነት ሰይፋቸውን ይዘው የአባ መቃርስን አጽም ከለከሏቸው፡፡ ሊቀ ጳጳሳቱና መነኮሳቱም እጅግ አዝነው ተመለሱ፡፡ ይህን ጊዜ አባ መቃርስ በዚያች ሌሊት ለመኮንኑ በራእይ ተገለጠለትና ‹‹ከልጆቼ ጋር መሄድን ለምን ትከለክለኛለህ? እንግዲህስ ከልጆቼ ጋር ወደ ቦታዬ ልሄድ›› አለው፡፡ መኮንኑም በጠዋት ተነሥቶ እየፈራና እየተንቀጠቀጠ አረጋውያን መነኮሳቱን ጠርቶ የከበረ የአባ መቃርስን ሥጋ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም እጅግ ደስ ተሰኝተው የአባ መቃርስን ሥጋ ይዘው በመርከብ በመሳፈር ተርኑጥ የምትባል ሀገር ሲደርሱ ስለመሸባቸው በዚያው አደሩ፡፡ በማግሥቱም ወደ አስቄጥስ ገዳም ለመድረስ በረሃውን ሲያቋርጡ ጥቂት ድካም ስለተሰማቸው ሊያርፉ ቢወዱም አባ ሚካኤል ግን ‹‹የቅዱስ አባታችንን ሥጋ የምናሳርፍብን ቦታ እግዚአብሔር ካልገለጠልን በቀር አናርፍም›› በሚል ሐሳብ አቀረቡ፡፡ ከመቅጽበትም የአባ መቃርስን ሥጋ የተሸከመው ግመል ወደ አንድ ቦታ ደርሶ በዚያ በርከክ በማለት የአባ መቃርስ ሥጋ ያለበትን ሣጥን ራሱ ይጥል ዘንድ ወዲያና ወዲህ ሲዟዟር ተመለከቱ፡፡ መነኮሳቱም እግዚአብሔር የፈቀደው ቦታ መሆኑን አውቀው ድስ ተሰኙ፡፡ ያም ቦታ እስከዛሬም ድረስ እንደታወቀ አለ፡፡ ከዚህም በኋላ መነኮሳቱ የአባ መቃርስን ሥጋ ይዘው ወደ አስቄጥስ ገዳም በደረሱ ጊዜ የገዳሙ መነኮሳት ሁሉም ወጥተው ወንጌልና መስቀሎችን ይዘው እየዘመሩና እያመሰገኑ ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገቡት፡፡ ከአባ መቃርስም ሥጋ ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተገልጠዋል፡፡
የታላቁ አባት የአባ መቃርስ ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከታቸው ይደርብን፤ አሜን፡፡
ምንጭ፡– የግንቦትና የነሐሴ ወራት መጽሐፈ ስንክሳር
https://t.me/dn_mezmur
. ወዮ! ስለ አንቺ ድንቅ ኾኖ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? ቅድመ ዓለም ያለ እናት ተወልዶ፣ ድኅረ ዓለም ያለ አባት እንደምን እንደወለደሽው መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? የአካላዊ ቃል እናቱ ንጽሕት ደንግል ሆይ! ኪሩቤል ለሚሸከሙት ለንጉሥ ማደሪያ ኾንሽ፡፡ ንዕድ ክብርት ሆይ! እኛም ክብርሽን ገናንነትሽን ዕፁብ ዕፁብ እያልን እናመሰግንሻለን /ሉቃ.፩፡፵፰/፡፡ የአካላዊ ቃል እናቱ መልካሟ ርግብ (ርግበ ኖኅ) ማርያም ሆይ! ስምሽን በትውልደ ሴም፣ በትውልደ ካም፣ በትውልደ ያፌት እንጠራለን፡፡ ሊቁ እመ አምላክን “መልካሟ ርግብ” አላት፡፡ ይኸውም የኖኅ ርግብ “የጥፋት ውሃ ጐደለ፤ የጥፋት ውሃ ተገታ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሰላም ነው” ስትል የምሥራቹን የዘይት ቅጠል ይዛ እንደታየች ኹሉ /ዘፍ.፰፡፲፩/ እመቤታችንም “የኀጢአት ውሃ ጐደለ፤ የመርገም ውሃ ተገታ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ዘመነ ሰላም ነው” ስትል ዓመተ ፍዳ ዓመተ ኩነኔን ኣሳልፎ ዓመተ ምሕረትን የተካ፣ ለዓለሙ ኹሉ ታላቅ የምሥራች የኾነ፣ የዓለም መድኃኒት ክርስቶስን ወልዳልናለችና፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡
https://t.me/dn_mezmur
ስኬት በአንድ ጀንበር የሚከሰት ነገር አይደለም።
ስኬት የብዙ ቀናት ልፋትና ጥረት ውጤት ነው !
?☞ወር በገባ በ18 ከሚታሰቡት መካከል ክብሯ ቅድስት ፀበለ ማርያም ይቺውም በፀሎቷ ብዛት በወገቧ በታጠቀችው ሰንሰለት በስግደቷም ስጋዋ ከአካሏ ተቆራርጦ እስኪወድቅ ድረስ የጌታዋን መከራ እያሰበች ትሰግድ ነበር
☞ማንም ከቶ እንዳያውቅባት ከአካሏ የወደቀውን ስጋዋን መሬት ቆፍራ ትቀብረው ነበር በዚህም የተነሳ የገዳሟ መሬት ሁለተኛ አካሏ ሆነ ከእንባዋም ብዛት የተነሳ ዝናብ የጣለ መሬት ይመስል መሬቱ በእንባዋ ይረሰርስ ነበር እርሷ ግን ሰው እንዳያውቅባት በደረቅ አፈር ትለውሰው ነበር።
♨የዓለም መዳኒት ኢየሱስ ክርስቶስ በደሀ ሰው ተመስሎ ምግብ ለመናት እርሷም
ጌታዋን መገበችው ደክሞኛል እዘይኝ ባላት ጊዜ እርሷ አዛኝ ናትና በጀርባዋ አዝላ
የዲንጋይ መወርወሪያ ያህል ተሸክማ ወሰደችው በዚህ ክብርት የምትሆን
እናታችን ፀበለ ማርያም ስለንፅህናዋ ፀበል አፈለቀላት እመቤታችንም ከሰማይ
ወርዳ ስሜን የተሸከምሽ ፀበለ ማርያም ሆይ ነይ ብላ አቅፋ ሳመቻት።
☞የክርስቲያን ወገኖች ስሙኝ የገዳሟን አፈር የወሰደ የስጋዋን ቁራሽ
ለመዳኒትነት
እንደወሰደ ይወቅ ይረዳ የእምነት አፈሩ ክርስቶስን ተሸክሟልና የእንባዋን ፀበል
የወሰደ ፍፁም ፈውስ ያገኛልና ከቶ እናቴ ፀበለ ማርያም እያላችው ተማፀኗት።
☞ገና ዓለም ሁሉ ገዳሟ እንደሚጎርፉ ዝናዋ የዓለም ጫፍ እንደሚደርስ የማታ
የማታ የከተማ ልጆች ቤቴን ይሰሩታል የተባለው ትንቢት መድረሱን የገዳሙ
አባቶች ይናገራሉ።
የገዳሟ አድራሻ ፦ በደቡብ ወሎ ጃማ ዳጎሎ አህያ ፈጂ የሚባል ቦታ ልዩ ስሙ
ንህበት የሚባል ቦታ ነው ።
☞የጻድቋ እናታችን የጸበለ ማርያም የጸሎቷ በረከት አይለየን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
#ማኅሌት እና #ምሥጢሩ
በሕጻንነቴ ቤተ ክርስቲያን የሚሄድበት ምክንያት ምን ነበር ብትሉኝ?
አባቶች መቋሚያውን ከጸናጽኑ አስማምተው ሲያወዛውዙት ማየት ምን አይነት ምሥጢር ነው ያሰኘኝ ነበር።
ለዚያ ነበር ሁሌም ሌሊት ሌሊት ቤተ ክርስቲያን ከእናቴ ጋር የምንሄደው።
አንዳንዴማ መዘምራኑ በቅኔ ማኅሌቱ መቋሚያውን ከግራ ወደ ቀኝ ሲያሽከረክሩት እርስ በእርሳቸው ተጣልተው ሊደባደቡ ይመስለኝ ነበር።
በተለይ አንድ ቀን ጥቅምት መድኃኔዓለም ማኅሌቱ ደምቋን መዘምራኑ በተመስጦ ላይ ናቸው። አሁን ከአሁን ተደባደቡ እያልሁ ስጠብቅ ማኅሌቱ ተፈጸመ።
? እናንተስ የመቋሚያው መወዛወዝ ምሥጢሩ ምን ይመስላችሁ ነበር? መቼም በሕጻንነት እናውቀዋለን አትሁኝም!!! በኮሜንት ጻፉልኝ
? #ምሥጢሩ#ግን#እንዲህ#ነው።
? መቋሚያ ቤተ ክርስቲያን ከምትገለገልባቸው ከዜማ መሳሪያ መካከል አንዱ ነው።
?#መቋሚያ ምሳሌነቱ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሸከመው እና የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ምሳሌ ነው።
#በሥርዓተ#ማኅሌት#ጊዜ#መዘምራን
1. #መጀመሪያ ከላይ ወደ ታች ያደርጉታል።ይህም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከሰፍሷ ነፍስ ነስቶ መወለዱን ያመለክታል።
2. #ከዚያም ዓለምን ዞሮ ማስተማሩን ለማጠየቅ መቋሚያውን ከግራ ወደ ቀኝ ፣ከቀኝ ወደ ግራ ያሽከረክሩታል።
#አንድም ከሐና ወደ ቀያፋ ፣ከጲላጦስ ወደ ሄሮድስ መመላለሱን መከራ መቀበሉን ለመሰብ ነው።
3. #መቋሚያውን ወደ መሬት የሚደስቁት የማይሞት ጌታ ወደ መቃብር ወረደ ሲሉ ነው።
4. #ወደ መሬት የደሰቁትን ተመልሰው ወደ ላይ ማንሳታቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሣ ለመመስከር ነው።
5. #በተመሳሳይ ሁኔታ ከቀድሞ ከፍ አድርገው ከዚያም ረጋ ብለው የሚመልሱት ዕርገቱን እና ዳግም ምጻቱን ለማዘከር ነው።ሞቶ የተነሳው ፣ተነስቶም ያረገው፣ዳግመኛም የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ሲሉ ነው።
#ቤተ ክርስቲያን ፊደልን ከወርድ፣ ወርድን ከዓረፍተ ነገር ፣ዓረፍተ ነገርን ከንባብ፣ ንባብን ከትርጓሜ፣ ትርጓሜን ከምሥጢር፣ምሥጢርን ከሕይወት አመሳጥራ የምትይዝ ስንዱ እመቤት ነች።
በዚህ መልኩ ነው ክርስቶስን የምትሰብከው ቤተ ክርስቲያን።
በመሠረቱ ቤተ ክርስቲያን እያንዳንዱ የምታረጋቸው ነገሮች ባንረዳው እንጂ ምሥጢራዊ ነው።
ይህን ምሥጢር ለማየት ለማወቅ ማኅሌት መቆም አባቶችን ማየት መጠየቅ ያስፈልጋል።
አሁን ጊዜውም ፍልሰታ ለማርያም ስለሆነም ንሐሴ 16 ይህን ምሥጢር ሁላችንም ቤተ ክርስቲያን ማኅሌት ቆመን ማየት አለብን።
መልካም ጊዜ !!!
#ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ዝጉ #መንገድ #ሚዲያ
#ይህ_ትምህርት_ለሁሉም_ይዳረስ_ዘንድ_ሸር_ላይክ_እናድርግ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እንድርገው
#ዲ/ን_ #መዝሙር_ንጉሴ
#ወልቂጤ_ኢትዮጵያ
#09_12_16 ዓ.ም
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад