Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
https://www.facebook.com/187991754570725/posts/4988530944516758/?sfnsn=mo
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
"ፍሥሐ ለኩሉ ዓለም ተወልደ ለነ ክርስቶስ"
(ቅዱስ ያሬድ)
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!
የመስቀል በዓልን ከአደባባይ በዓልነት ለማውረድ የሚደረጉ ሴራዎች የሺሕ ዓመታት ትውፊትን አያዳፍኑም!
የአዳማ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ ጀልዱ የመስቀል በዓል በአዳማ ከተማ እንዳይከበር ከልክዋል። በምክክር መድረኩ ከተወሰነው በተቃራኒ በግላቸው የወሰዱት ውሳኔ እንደሆነ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
የ፳፻፲ወ፫ ዓ.ም. የመስል በዓልን አከባበር በተመለከተ ለመወያየት የአዳማ ከተማ አስተዳደር በጠየቀው መሠረት መስከረም ፲፩ ቀን ፳፻፲ወ፫ ዓ.ም. ነበር ቀጠሮ የተያዘው። በጥያቄው መሠረት የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ፣ የከተማው አብያተ ክርስቲያናት ካህናትና ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች በቀጠሯቸው መሠረት በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ ተሰብስበው ጠበቁ። ከንቲባው በወኪላቸው አቶ ጋረደው በኩል በዕለቱ መገኘት እንደማይችሉ ገልጸው ራሳቸው የጠሩትን ስብሰባ በተኑ። ለ፲፫/፩/፳፻፲ወ፫ ዓ.ም. በሪፍት ቫሊ ሆቴል ሌላ ቀጠሮ ተያዘ። በውይይቱ ቦታ ግን የተገኙት የቤተ ክርስቲያኗ ተወካዮች ብቻ ሳይሆኑ የሙስሊም ማኅበረሰብ ተወካዮችና አባ ገዳዎችም ነበሩ።
በዕለቱ በከንቲባው መሪነት ውይይት ከተደረገባቸው ጉዳዮች አንዱ የመስቀልና ኢሬቻ በዓል አከባበርን የተመለከተ ነበር።
የመስቀል እና ኢሬቻ አከባበር ላይ ውይይት ተደረገ። በዓሉን ወቅቱን ባገናዘበና አገልጋዮች ለኮሮና ቫይረስ ሥርጭት በማይጋለጡበት መልኩ ማክበር እንደሚገባ ሐሳብ ቀርቦ ቤቱ ተስማምቶበታል። የመስቀልን በዓል በመስቀል አደባባይ ተገኝቶ ማክበር ያለበቸውን አገልጋዮች ቁጥር የቤተ ክርስቲያን አባቶች ወስነው እንዲያሳውቁ፣ የከተማ አስተዳደሩ በፌደራል እና በክልሉ ስንደቅ አላማ የበዓሉን ማክበርያ ሥፍራ እንደሚያስጌጥ በስምምነት ላይ በመድረስ ስብሰባው ተቋጨ።
ከስብስባው በኋላም በብፁዕ አቡነ ጎርጎራዮስ ሰብሳቢነት በአዳራሹ በመቅረት የሰውን ቁጥር ለመወሰን ከንቲባው በተገኘበት ለመነጋገር ተሞከረ። ከንቲባው አቶ ኃይሉ ጀልዱ ቀደም ሲል በዋናው ውይይት ከተደረሰበት ስምምነት በተቃራኒ በመቆም በዓሉ በየአጥቢያው ውስን በሆነ ሰው ብቻ መከበር እንዳለበት ተናገረ። በወቅቱ እርሱ ያቀረበው ሐሳብ እንደማይሆን ሊቀ ጳጳሱ መልስ ሰጡት። በብፁዕ አባታችን መሪነት ተደጋጋሚ ውይይት በማድረግ ለመግባባት ቢሞከርም ከንቲባው ግን የያዙትን አቋም ማለሳለስ አልፈለጉም። ይባስ ብለው «በየአጥብያችሁ አክብሩ ከፈለጋችሁ የመስቀል አደባባዩን መግቢያ በር እዘጋዋለሁ፤» በማለት ማስፈራራታቸው ተነግሯል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ብቻ ሳይሆን ለመላው ኢትዮጵያውያን ብሎም ለሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነት የምትጨነቅ፣ የምትጸልይና የምትሠራ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ናት። አገልግሎቷን በሓላፊነት መንፈስ የምትከውን እመቤት ናት። ኮቪድ 19 ከበድ ባለ ሁኔታ እንደተስፋፋ በሚነገርበት አዲስ አበባ የተወሰኑ አገልጋዮችን በሚያሳትፍ መልኩ የመስቀልን በዓል ለማክበር እየተዘጋጀች ነው። በዚህ ወቅት ሥርጭቱ አስጊ ባልሆነባቸው አዳማ፣ ቢሾፍቱና ሞጆ ከተሞች የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣው የጥንቃቄ ደረጃ ባሟላ ሁኔታ በዓሉን ለማክበር የምትከለከልበት ምክንያት አሳማኝ አይደለም።
መንግሥት ለሕዝቡ ጤንነት ማሰብ ሥራው ነው። ነገር ግን እጅግ ለኮሮና አጋላጭ በሆነና በተፋፈገ ሁኔታ ዕለት ዕለት ዳንኪራ ሲረገጥባቸው የሚያድሩ ሆቴሎች በበዙበት ከተማ ውስን አገልጋዮች አካላዊ ርቀትን በጠበቀ መልኩ የሚያከናውኑት መንፈሳዊ ሥርዐት ለምን የጭቅጭቅ ማዕከል እንዲሆን እንደተፈለገ ግልጽ አይደለም።
ነገሩ ተሞክሮን ማስፋት ይመስላል። አምና በቢሾፍቱ መስቀል እንዳይከበር የተሳካ ሴራ የፈጸሙት የቢሾፍቱ ከተማ መስተዳድርና የጸጥታ አካላት ተሞክሮ ዐድጎና ሰፍቶ እየተተገበረ እንዳይሆን ያሰጋል።
ን በመቆጣጠር ገንዘብ ማበደር ÷ የገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤቱን በመቆጣጠር ለራስ ወገን
የግብር ጫና ሲቀነስ ለሌላው የመጫንና የማማረር ስራዎች ተገቢ ጆሮ ያጡ ስልቶች ናቸው። ገንዘብ ያላቸውና የሚሰጣቸው ሰዎች በከተማዋ ለሽያጭ የሚቀርቡ ቤቶችን እንዲገዙ ማድረግ ፥በተለይ ከሪል-ስቴት አልሚዎች ጋር በተያያዘ የተለያዩ አልሚዎች የዚህ አላማ
ተሳታፊ እንዲሆኑ ከዱባይም ጭምር እንዲሳተፉ እየተደረገ ነው።
8- ብሔር አልባን ከብሔር ድምር ማውጣትም አንዱ ስልት ነው። ቀጣዩን የህዝብና ቤት ቆጠራ መሠረት በማድረግ በተለይ የከተማዋ ነዋሪ የብሔር ማንነትን ለመቀበል የማይፈልግ መሆኑን በማየት አንድም የጥምር ብሔር አማራጭና ብሔር የማይገለፅበት የመታወቂያ
አማራጭ በማንሳት ከዚህ ቀደም ሳይወዱም ወደተለያዩ ብሔሮች የሚመዘገቡትን የመቀነስ አማራጭ ታስቧል።
እንደዚያ ሲሆን በከተማዋ ከፍተኛው ብሔር ማንነው ሲባል ራሱን ያልመደበውን ስለሚቀንስ የቁጥር ጨዋታውን ያሳድጋል።
9- የሌላ ህዝብ መግቢያ አማራጮችን መዝጋት
ይህ በተለይ በኢኮኖሚ ስደት ወደከተማዋ ገብተው የሚኖሩና በሒደት ወደቋሚ ነዋሪነት የሚለወጡበት መንገድ እንዲዘጋ የታሰበ ይመስላል። የጎዳና ልጆች ማንሳት ÷ የምሽት መጠጥ ቤቶች (clubs) ንግድ ስራ እንግልትና ክልከላዎች በዚህ በኩል ይጠቀሳሉ።
10- አዲስአበባ ተኮር ንቅናቄን መድፈቅ በፊንፊኔ መተካት
ይህንን አላማ ሊያደናቅፉ የሚችሉ እንደባልደራስ ያሉ ንቅናቄዎች ላይ ጨካኝ እርምጃና ዛቻ ማድረግ የአላማውን ተፈፃሚነት የሚያግዝ ነው ። ይህ በተለይ የከተማዋን ወጣት
የሚያንቀሳቅስ ተግባር በኦሮሞዎች የተጀመረውን እንቅስቃሴ የሚያስተጓጉል እርምጃ በመሆኑ ከጅምሩ የከተማዋን ወጣት ሰብስቦ የማሠር ፥ ለኦነግና መሰሎች የሚፈቀዱ ጉዳዮች በተለይ የመሰብሰብ ፥ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ፥ ጋዜጣዊ መግለጫ የመስጠት
እና መሰል እንቅስቃሴዎችን መከልከልና ማስፈራራት ትልቅ ሥራ ተደርጎ ጠቅላይሚኒስትሩ ድረስ ማስፈራሪያ የተሰጠበት ነው። አገር ከሚገረምበት የእነ እስክንድር መንታ የመንግስት መርህ በተጨማሪ የአማራ ወጣት ማህበራት ስብሰባዎችን የማወክ ተግባርም የዚሁ አካል ነው።
"አሁን እንኳ ለሳምንታት ከተደረገው የኦሮሚያ ጭፍጨፋ ይልቅ በመጀመሪያዋ ቀን ቄሮ ከተማ ውስጥ ገብቶ የፈፀመውን ቀውስ የአዲስአበባ አድርጎ ማጉላት ይቀላቸዋል።"
11- በአዲስአበባ ወንዝ ልማት የከተማዋን መስራች ህዝብ ከይዞታው ማንሳት ይህ 29 ቢሊዮን ብር በጀት ÷ 54 ኪሜ ርዝመት ÷ የ30ሺህ ህዝብ (ቤተሰብ?) መፈናቀል
የሚጠብቀው መርሃግብር በዚህች የአርሶአደርና ድሃ ከተሜ አገር ቅድሚያ ያገኘበት ጥበብ እንቆቅልሽ መሆኑ አያነጋግርም። "something that has nothing to do with the people stomach " አይነት ለአይንና ጆሮ እንጂ ለሆድ የሚሆን ማባበያ ነው።
ሆኖም የከተማ ልምላሜና የስነውበት ጉዳዮች በጥቅሉ ደስ የሚያሰኙ ቢሆኑም የአጠቃላይ ምጣኔ ሀብት ለውጥ ተዛማጅ ተፅዕኖ ውጤት (spillover effect ) እንጂ ከመሠረታዊው የልማት ስራ የሚቀድሙ ሆነው ታቅዶ ተጀምሯል። የአዲስአበባ ህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ
የሆነው ቤት ችላ ተብሎ ይህ ቅድሚያ ያዘ ? ለምን? ካልን የከተማዋ መስራች ህዝብ ቀድሞ የከተመው የወንዝ ዳርቻዎችን ተከትሎ የእንጦጦ ቤተመንግስትን ይዞ ነው።
ይህ ሲወርድ ሲዋረድ የተላለፈና በትውልድ የተያዘ አካባቢ ስነልቦናዊ ትስስሩና የከተማ ባለቤትነት ስሜቱ ከፍተኛ ነው። ለስራ ጉዳይ ባለፉት 20 ዓመታት መጥቶ ኮንዶሚንየም ላይ
ከሚኖረው በላይ ለመቶ አመታት በትውልድ ተዋረድ ተወልዶ ያደጉበት ይዞታ ትልቅ ትርጉም አለው።
ይህንን ባለቤትና መስራች ነይ የሚል ህዝብ "ከሌሎቹ እንደአንዱ" ማድረግ ጠቃሚው መንገድ ተደርጓል። ከልማት ስራው ጎን ይህን ማድረግ ጥቅም አለው። ባለቤትና መጤ ÷
መስራችና ባይታወርነት በመኖሪያ መንደር መገለፁ ይቀራል።
12- ከተማ ዙሪያ ማፅዳት - ለገጣፎ ÷ ቡራዩ ÷ ወዘተ - ይህ አሁንም ዙሪያዋ በአንድ ብሔር ግልፅ ባለቤትነት የተከበበች
አዲስአበባ ከተማ የመፍጠርና የኋላውን እሰጥአገባ ለመጫን የሚያግዝ ስልት ነው።
ሌሎች ብሔሮችን በማስወጣት በግልፅ በኦሮሞ የተከበበች ደሴት ከሆነች የባለቤትነት ጥያቄው ላይ አስተዋፅኦ ያደርጋል። የከተማዋን ህዝብ በመከበብ ስነልቦና ለማጠር ይመቻል።
--
እነዚህ ሁሉ አንድ በአንድ ባለፈው ሁለት ዓመት እየተተገበሩ ያሉ ናቸው። የከተማውን ወጣትና ህዝብ በምላስ እየሸነገሉና እያባበሉ ዓላማን የማሳካት ሒደቱ
ተጠናክሯል።
➨ ይህ ከአዲስአበባ ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ሁለት አማራጭ ይፈጥራል።
1) የመጀመሪያው ይህ የስነህዝብ ስሌታዊ ሒደትና እሴታዊ ቁጥጥር ከኢኮኖሚና የፖለቲካ
የበላይነት ጋር ሲዳመር ሌላው ከባለቤትነትና የብልጫ ስነልቦና ወርዶ ተፈቅዶለት የሚኖር መሆኑን ተቀብሎ እንዲኖር ያደርጋል። በዚህም በእኛ ስር በእኛ ፈቃድ ኑር የሚል መደምደሚያ ላይ ያደርሳል።
2) የተረጋገጠ የህዝብ ብልጫ ሲመጣ : አጨቃጫቂውን የባለቤትነት ጉዳይ በሪፍረንፈደም እንቋጨው የሚል አጀንዳ አንስቶ ማስወሰን ነው። "ሳይንሳዊ" ያስባለው አሁኑኑ ዝም ብሎ "የእኛ ነች" ÷ "ልዩ ጥቅም" ከሚል የፊትለፊት
ልፊያና አቀራረብ ይልቅ ቀስ ብሎ ህዝብን በማስገባት ነዋሪ ይወስን የሚል ፖለቲካዊ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ነው።
አዳራሽህ ገብተህ መላውን አጢነው!!
ለሌሎችም ሼር በማድረግ ሕዝቡን አንቁት ።
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад