Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
በዚህ ዕለት ለምለም ቄጤማ ይታደላል ፡፡ ቄጤማ የሚታደልበት ምክንያት ምሳሌያዊና ምስጢራዊ ትርጉም ስላለው ነው ምሳሌያዊ ትርጉም በኖኅ ዘመን የዘነበው ማየ አይኀ መድረቁን ለማረጋገጥ፣ ኖኅ ርግብን በመስኮት አውጥቶ ላከ በመጀመሪያው ዝም ብላ ተመልሳለች በሁለተኛው ስትላክ ‹‹ነትገ ማየ አይኀ ሐፀ ማየ ኃጢዓት›› እያለች ቄጤማ በአፏ ይዛ ስትመለስ ኖኅ እጁን ዘርግቶ ተቀብሏታል፡፡ የርግቢቱ ድርጊት የጥፋት ውሃ ደረቀ፣ የኃጢዓት ውሃ ደረቀ የሚል የምስራች አጉልቶ የሚያሳይ ነው፡፡ (ዘፍ 8፡6-11)
ምስጢራዊ ትርጉሙ ደግሞ ርግብ የተባለችው አማናዊት ርግብ እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት፣ ለምለም ቄጠማ በአፏ ይዛ እንደመታየት፣ አምላክ ወልደ አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷን የሚያመለክት ነው፡፡ ከእርሷ የተወለደው ክርስቶስ በመልዕልተ መስቀል ተሰቅሎ በሞቱ ሞትን እንዳጠፋልን "ማየ አይኀ" የተባለ ሞተ ነፍስን እንዳስቀረልን ለማመልከት የምስራች ሲሉ ካህናት ቄጤማ ያድላሉ፣ ምዕመናንም እስከ ትንሳኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያሥሩታል፡፡
#13ቱ_ሕማማተ_መስቀል?
1. አክሊለ ሦክ (ወደ 70 የሚደርስ ራስ ቅሉ ላይ የተተከለ የብረት እሾኽ የያዘ ዘውድ ወይም አክሊል)
2. ተኰርዖተ ርእስ (ራሱን በዘንግ ወይም በዱላ መመታቱ/መቀጥቀጡ)
3. ተጸፍኦ መልታሕት (ጉንጩን ወይም ፊቱን በጥፊና በቦክስ መመታቱ)
4. ሰትየ ሐሞት (ተጠማሁ ብሎ ስለ ውሃ ፋንታ መራራ ሐሞትን መጠጣቱ)
5. ወሪቀ ምራቅ (በፊቱ በአካሉ ላይ በንቀትና በጥላቻ በመሳለቅ በመዘባበት ፊቱ ላይ ምራቅ መትፋታቸው)
6. ተቀስፎ ዘባን (6,666 ጊዜ የሾለ አጥንትና ብረት በታሰረበት ጅራፍ መገረፉ)
7. ተአስሮ ድኅሪት (የፍጥኝ ወደኋላ መታሰሩ ...በአፍ ጢሙ መደፋቱ)
8. ፀዊረ ጒንደ ዕፀ መስቀል (የሚሰቀልበትን የእንጨት መስቀል መሸከሙ)
9. ሳዶር (ቀኝ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር)
10. አላዶር (ግራ እጁ ከመስቀሉ ጋር የተጣበቀበት ችንካር)
11. ዳናት (ቀኝ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር)
12. አዴራ (ግራ እግሩ መስቀሉ ከቆመበት ፍልፍል ግንድ ጋር የተጣበቀበት ችንካር)
13. ሮዳስ (ደረቱ ከመስቀሉ ጋር እንዲጣበቅ ከታሰረበት ሽቦ ጋር ልቡ ላይ የተቸነከረ...)
አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት እሊህ ናቸው
ብዙውን አንድ ብዙውን አንድ እያሉ በመቁጠር መናገር ነው እንጂ የመከራው ብዛት የስቃዩ ጽናት በቁጥር የሚገለጽ ሆኖ አይደለም!!!
ጌታ ሆይ! ሕማምህ ይፈውሰን ዘንድ
ቁስልህ እንዲሰማን ማስተዋልን ስጠን ???
እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ፃማ ወድካም
ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሓ ወበሰላም
አሜን!
በግብረ ሕማማት ውስጥ የሚገኙ የውጭ ጥሬ ቃላት ትርጉም፡-
ከመ/ር ሸዋንዳኝ አበራ
በሰሙነ ሕማማት በቤተ ክርስትያን ውስጥ የምንገለገልበት መጽሐፍ ግብረ ሕማማት ይባላል፤ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከሌሎች ልሳናት ወደ ግእዝም ሆነ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ጥሬ ቃላት ስለሚገኙ ትርጉማቸውን እንመልከት፦
፩፦ ኪርያ ላይሶን፥ ቃሉ የግሪክ (ጽርዕ) ሲሆን አጠራሩ (Κίρι Έλισον) «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፤ ኪርዬ - ማለት እግዚኦ -አቤቱ ማለት ሲሆን ኤሌሶን ማለት ደግሞ ተሣሀለነ - ማረን ማለት ሲሆን በአንድ ላይ «ኪርዬ ኤሌይሶን» እግዚኦ ተሣሀለነ - አቤቱ ማረን ማለት ነው፡፡ ነገር ግን በተለምዶ ኪርያ ላይሶን ማለትን እናዘወትራለን ምንም እንኳን ቃሉ የጽርእ ቢሆንም እኛ እስከ ተጠቀምንበት ድረስ በቃላት ላይ ጥንቃቄ ማድረጉ እጅግ ተገቢ ይሆናል ምክንያቱም ለተባእት የተነገረውን ለእንስት መጠቀሙ የቃላት ግድፈት ብቻ ሳይሆን የዶግማም መፋለስ ያስከትላልና መታረም ይኖርበታል፡፡
በእኛ ዘንድ ልምድ ሆኖ ኪርያላይሶን ነው የምንለው፤ ይህም በድምጾች መሳሳብ ቢሆንም ሌላ ትርጉም የሚያስከትል በመሆኑ ትክክለኛውን ድምጽ መያዝ ይኖርብናል፤ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን ኪርያ ላይሶን ማለት ደግሞ እግዚእትነ መሐረነ - አቤቱ ማሪን ማለት ነው፤ በዘልማድ ኪርያ ላይሶን የምንለው ኪርዬ ከሚለው የ(ዬ)፤ ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ የ(ኤ) ድምፆች በመሳሳባቸው የ(ያ)ን ድምፅ በመተካት እኛው ያመጣነው ድምፅ እንጂ ትክክለኛ ድምፅ ካለመሆኑም በተጨማሪ ትርጉሙም ዶግማ ያፋልሳልና ትክክለኛውን ድምፅ (Κίρι Έλισον) «ኪርዬ ኤሌይሶን» የሚለውን መከተል ግድ ይለናል፡፡
፪፦ ናይናን፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን ትርጉሙም «መሐረነ» ማረን ማለት ስለሆነ ይህ ቃል ከሌሎች ቃላት ጋር በመሆን ዓረፍተ ነገር ይፈጥራል ወይም ኃይለ ቃል ይሰጣል ይኸውም፦ እብኖዲ ናይናን፥ ታዖስ ናይናን፥ ማስያስ ናይናን፥ ኢየሱስ ናይናን፥ ክርስቶስ ናይናን፥ አማኑኤል ናይናን፥ ትስቡጣ ናይናን ይባላል፡፡
፫፦ እብኖዲ፥ የቅብጥ (የግብጽ) ቃል ሲሆን ትርጉሙም «አምላክ» ማለት ነው፤ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «ኦ አምላክ መሐረነ» አምላክ ሆይ ማረን ማለት ነው።
፬፦ ታኦስ፥ የግሪክ (ጽርዕ) ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ጌታ አምላክ» ማለት ነው፤ «ታኦስ ናይናን» ማለትም ጌታ አምላክ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡
፭፦ ማስያስ፥ መሲሕ ማለት ሲሆን ቃሉ የዕብራይስጥ ነው ትርጉሙም በጽርዕ ክርስቶስ ማለት ነው፤ «ማስያስ ናይናን» ማለትም «ኦ መሲሕ መሐረነ» መሲህ ሆይ ማረን፥ ክርስቶስ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡
፮፦ ትስቡጣ፥ የግሪክ (ጽርእ) ቃል ሲሆነ «ድስቡጣ - ዴስፓታ» ከሚለው ስርወ ቃል የወጣ ነው፤ ትርጉሙም «ደግ አመላክ ወይም ደግ ገዢ» ማለት ሲሆን ትስቡጣ ናይናን ጌታችን ሆይ ማረን ማለት ነው።
፯፦ ሙኪርያ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን «ኦ እግዚኦ» አቤቱ ሆይ ጌታ ሆይ ማለት ሲሆን ሙኪርያ ናይናን ማለት አቤቱ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡
፰፦ ሙአግያ፦ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን «ኦ ቅዱስ» ቅዱስ ሆይ ማለት ሲሆን ሙአግያ ናይናን ማለት ቅዱስ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡
፱፦ ሙዳሱጣ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን «ከሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ» ማለት ሲሆን መዳሱጣ ናይናን ማለት ከሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ ማረን ማለት ነው፡፡
፲፦ አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን ጌታ ሆይ በመንግሥትህ አስበን ማለት ነው፡፡
፲፩፦ አምንስቲቲ ሙአግያ አንቲ ፋሲልያሱ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን ማለት ነው፡፡
፲፪፦ አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልይዝሱ፥ የቅብጥ (ግብጽ) ቃል ሲሆን ከሁሉ በላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን ማለት ነው፡፡
እንበለ ደዌ ወሕማም፥
እንበለ ጻማ ወድካም፥ ለብርሃነ ትንሣኤሁ ያብጽሐነ፥ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም፡፡ (ያለ ደዌና ያለ ሕመም፥ ያለ ጣርና ያለ ድካም፥ እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤው በደሰታና በሰላም ያድርሰን፤ ያድርሳችሁ፡፡
ኅዳር ስድስት በዚህች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቁስቋም ገባ፤ በመንገድ ጉዞ ካገኛቸውም ድካም አረፉ።
መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር
''ሱላማጢስ ሆይ ተመለሽ፤ተመለሽ፤እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፤ተመለሽ ''እንዳለ የአባቷ የዳዊት ልጅ ጠቢቡ ሰሎሞን [መኃ ፯÷፩] ''የጌታ መልአክ(ም) ...ለዮሴፍ:-
የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑን እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለ '' ማቴ ፪÷፲፱-፳
እንኳን ከምድረ ግብፅ ስደት እመቤታችን ከተወደደ ልጇ ጋር ለተመለሰችበት ዓመታዊ በዓል አደረሰን፤ አደረሳችሁ !!!
ሕዳር 2016 ዓ/ም
በማህበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል መዝሙርና ኪነጥበባት ዜማ መሳሪያ ክፍል የህፃናትና ታዳጊያን ክፍል በሰፊው በመዝሙር(ቸብቸቦ) ና በበገና ክፍል ተጀምሯል።
ይህም በኛ በበገና የህፃናትና ታዳጊያን የዋና ማዕከል የዜማ መሳሪያ በገና መዘምራን (Head Office of MK for Children & Teengers Melody Begena Device Group) ብለን በቋሚነት ልጆቹን በተለያዩ አገልግሎቶች ከሚኖሩን (በቤተክርስትያን ከሚቀርቡልን ዓመታዊ እንዲሁም ወርሀዊ በዓላት ሰርክ ጉባኤያት ፣ በሰርግ ፣ በሀዘን) እንዲሁም በተለያዩ እገልግሎቶች በማሰማራት እግዚአብሔር በፈቀደው መልኩ በጥሩ ሁኔታ አንድ ዓመት አሳልፈናል።
አሁንም አዳዲስ የማገልገል ፍላጎት ያላቸው ልጆችን ያልሰሙ ካሉ ታሰሙልን ዘንድ አንዱ ማሰራጫችንን መንገድ እናንተን አድርገናል።
ስለሆነም ፍላጎት ኖሯቸው መረጃ ሳይሰሙ
በገናን በአግባቡ ተምረው የጨረሱ ልጆችን
ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ውስጥ ያሉ ካሉ እንድታሳውቁልን እናሳስባለን።
የማጥኛ ጊዜ ፣ ሰዓትና ቦታ
ጊዜ: በየሳምንቱ ቅዳሜ
ሰዓት: 9:00 - 11:00
ቦታ: 5ኪሎ በሚገኘው ቅድስተማርያም ቤተክርስትያን ፊት ማህበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ።
ለሚኖራችሁ ጥያቄዎች እንዲሁም ሀሳቦች
፩- ያድኤል - 0901963727 ፪- እየሩሳሌም - 0912488634 ፫- ሀብታሙ - 0911771539 ፬- ፍሬህይወት - 0934153962
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад