Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

Description
كناشة ابن منور
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 2 days, 7 hours ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 month ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 days, 6 hours ago

1 month, 2 weeks ago

""ሙሓደራ ክፍል 190 ""

አዲስ ሙሓደራ ክፍል 02

ረድ በ ወሰን ተላላፊዎች ላይ

የ ሚዳሰሱ ነጥቦች ለ አብነት 👇

““የ አቡዘር (አቡ ጦልሓ) ስህተቶች እና ግጭጭቶች…““
🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሐቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed

1 month, 2 weeks ago

ጥንቃቄ
~
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ብዙ ወጣት ሴቶች በሚዝናኑባቸው ቦታዎች ትላልቅ ከተማዎች ላይ GHB የሚባል ኬሚካል ተበራክቷል። "ጋባዦች" አንድ መጠጥ ውስጥ የGHB ጠብታ ሲጨምሩበት ተጠቂዎች (አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች) በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ያሉበት፣ አብረዋቸው የነበሩበትን እና የተወሰዱበትን ቦታ አያስታውሱም። ገንዘብ ተከፍሏቸው የደነዘዙ ሴቶችን ለማስደፈር የሚያቀርቡ ውጣት ወንዶችም ሴቶችም ይሄንን እየሰሩ የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። በተለይ "የቤት ልጅ" አይነት የሚባሉ (ተማሪዎች) እና ሌሎች ወጣት ሴቶች የዚህ ወንጀል ተጠቂ እየሆኑ ነው። GHB ከሰውነታቸው ወጥቶ ሲነቁ በማይታወቅ ቦታ ብዙ ጉዳት ደርሶባቸው ራሳቸውን ያገኛሉ። ምን እንደተፈጠረ አያውቁም። GHB የሰው ሕይወት ሊያጠፋ ይችላል። በከተሞች መዝናናት እና መገባበዝ ደግሞ የተለመደ ስለሆነ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል። እንዲህ አይነት ወንጀሎች በቅርብ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ውጪ ከኖሩ ኢትዮጵያውያን ነው።

ኮፒ
"ሼር" ቢደረግ ለወገን ይጠቅማል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

1 month, 2 weeks ago

አንድ ነጥብ
~
የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት የሚታወቅ ነው። ሰሞኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ሰዎች ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው እርዳታ ማድረጋቸው ጥሩ የድጋፍ ስራ መሆኑን አውስቼ "አላህ ጀዛቸውን ይክፈላቸው" ብል ይሄ ስሜት ያሰከረው መንጋ ሲንጫጫ ነበር። ከዚህ በፊት የመስጂድ ቦታ ለሰጡን አካላት ምስጋና ስገልፅ ምንም ያላሉት እነዚያ ሙስሊሞች ስላልሆኑ ነው። አንዳንድ ሰዎች ዘንድ "እናመሰግናለን፣ አላህ ይስጥልን" ማለት ለሙስሊሞች ሲሆን የቢድዐን አካል ማወደስ፣ የመንሀጅ መንሸራተት ሲሆን ለካፊሮች ሲሆን ግን ችግር የለውም። እንዲያውም እንደ ንቃት ነው የሚቆጠረው። ነገሮች እንዴት እየተያዙ እንደሆነ ቆም ብለን እናስተውል።
በተረፈ የመጅሊስ ሰዎች አካሄድ እንከን የለሽ ነው የሚል አቋም የለኝም። ባደባባይ ከሚታዩ ችግሮቻቸው ውስጥ በአንድ ሁለቱ ላይ ከዚህ ቀደም በግልፅ ፅፌያለሁ።
ለማንኛውም አንድ አካል ችግር ቢኖርበት እንኳ በመልካም ስራው ላይ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ማለት አቧራ የሚያስነሳ አይደለም።
1- ኢብኑ ባዝ - ረሒመሁላህ - ከሙሐመድ አልገዛሊ "መዐ'ላህ" ኪታብ በረጅሙ ከወሰዱ በኋላ መጨረሻ ላይ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ነቅዱል ቀውሚየቲል ዐረቢያ] [መጅሙዑ ፈታዋ፡1/317]
2- ሸይኹል አልባኒይም - ረሒመሁላህ - አሕመድ ዲዳትን ትልቅ ጂሃድ ላይ እንዳሉ በመግለፅ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር]
3- ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ ኣደምም እንዲሁ ከዩሱፍ አልቀርዳዊ "ፊቅሁ ዘካ" ኪታቡ ረዘም ያለ ክፍል ከወሰዱ በኋላ "ጀዛሁላሁ ኸይራ" ይላሉ። [ዘኺራ፡ 22/168] አለፍ ብለውም እንዲህ ሲሉ ስራውን ከማድነቅ ጋር ዱዓእ ያደርጋሉ:- انتهى ما كتبه الدكتور القرضاويّ شكر اللَّه سعيه، وهو بحثٌ نفيسٌ جدًا.
የቀርዷዊ ማንነት የሚታወቅ ነው።
አሁንም ሸይኹል አልባኒይ ለሙሐመድ አልገዛሊይ እና ዩሱፍ አልቀርዷዊይ አድናቆታቸውን ከገለፁ በኋላ ለቀርዷዊ "አላህ ይጠብቀው። ሙስሊሞችንም ይጥቀምበት" ብለዋል። [ጋየቱል መራም፡ 7]
አልባኒይ የነዚህን አካላት ብልሹ አካሄድ በመተቸት የታወቁ ናቸው። ከመሆኑም ጋር "በመልካም ስራቸው" ላይ አላህ እንዲመነዳቸው ዱዓእ ሲያደርጉ እናያለን። መሰል አካሄድ ብንፈልግ ሌሎችም ጋር እናገኛለን። "ሙብተዲዕን ማድነቅ ይቻላል" እያልኩ አይደለም። ይልቁንም ነገሮችን መለየትና በልክ መያዝ እንልመድ እያልኩ ነው።
ያያያዝኩት በሕሩ ተካ በጉራጌ ዞን ጉንችሬ ላይ የነበረን ሁከት ተከትሎ የነበረውን ሂደት አስመልክቶ ርስቱ ይርዳውን፣ የፍትህ ሚኒስቴርን፣ አስተዋይና ሚዛናዊ ብሎ የገለፃቸውን ክርስቲያኖችን፣ የጉንችሬና የእነሞር አመራሮችን ያደነቀበትና ያመሰገነበት ነው። ለሽፋን ከሚቀርቡ ሰሞንኛ ግርግር ውጭ እነዚህ የተጠቀሱት አካላት ለአካባቢው ችግር ወይ ጠንሳሽ ናቸው። ወይ አፍራሽ ሚና የነበራቸው ናቸው። ወይ ደግሞ ኃላፊነታቸውን ባለመወጣት ችግሩ እንዲቀጥል ያደረጉ ናቸው።
(የተነሳውን ነጥብ ጥለው በማስቀየስ ላይ እንደሚጠመዱ እጠብቃለሁ።)
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

5 months, 1 week ago

ደርስ
~
መንሀጁ ሳሊኪን
ክፍል:- 0️⃣0️⃣7️⃣
* የደርሹ መነሻ፦ والفرض من هذا
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

5 months, 1 week ago

ደርስ
~
ሪያዱ ሷሊሒን
ክፍል:- 9️⃣9️⃣
የለቱ ደርስ መነሻ ገፅ 251፣ باب فضل الغني الشاكر
የኪታቡን ሶፍት ኮፒ በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ
https://t.me/IbnuMunewor/3505
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

5 months, 1 week ago

ከደቂቃዎች በኋላ በዚሁ ቻናል የሪያዱ ሷሊሒን ደርስ ይኖራል፤ ኢንሻአላህ።

6 months, 2 weeks ago

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

📜መውሊድን በተመለከተ በኡስታዝ ኢብኑ ሙነውር የተዘጋጁ ከፊል ፅሁፎችን በቀላሉ እንዚህን ሊንኮች በመጫን ማንበብ ትችላላችሁ።

1, ነብዩ ﷺ መቼ ተወለዱ?
https://t.me/IbnuMunewor/893

2, መውሊድን ማን ጀመረው? በመረጃ ለሚያምኑ ብቻ
https://t.me/IbnuMunewor/869

3, መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ?
https://t.me/IbnuMunewor/876

4, መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!}
https://t.me/IbnuMunewor/884

5, “በአላህ እዝነት ይደሰቱ...” - ትልቁ የመውሊድ አጋፋሪዎች ምርኩዝ
https://t.me/IbnuMunewor/2227

6, የሰኞ ፆም እና መውሊድ
https://t.me/IbnuMunewor/2214

7, ዐቂቃ ሌላ መውሊድ ሌላ!
https://t.me/IbnuMunewor/2261

8, ዓሹራን ለመውሊድ?
https://t.me/IbnuMunewor/2269

9, መውሊድ ውስጥ እነዚህ አደጋዎች አሉ!
https://t.me/IbnuMunewor/2294

10, በመውሊድ ላይ ስለሚፈፀመው ጭፈራ ዑለማዎች ምን እንዳሉ ታውቃለህ?
https://t.me/IbnuMunewor/882

11, መውሊድን የሚፈቅዱትም አይፈቅዱትም!
https://t.me/IbnuMunewor/2298

12, መውሊድ የማያከብር ሰው የሙሐመድ ﷺ ጠላት ከሆነ፣ ገና የማያከብር ሰው የዒሳ ጠላት ነው!
https://t.me/IbnuMunewor/886

13, እውን የሡወይባ ታሪክ ለመውሊድ ማስረጃ ይሆናል?
https://t.me/IbnuMunewor/2234

14, ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት)
https://t.me/IbnuMunewor/898

15, ሲዩጢ፣ የመውሊድ ደጋፊዎች ሌላኛው ምርኩዝ
https://t.me/IbnuMunewor/2277

16, እውን ኢብኑ ተይሚያ መውሊድን ፈቅደዋል?
https://t.me/IbnuMunewor/878

17, በሸይኹል አልባኒ እና “መውሊድ ይፈቀዳል” በሚል ሰው መካከል የተደረገ ድንቅ ቃለ-ምልልስ
https://t.me/IbnuMunewor/34

18, ከ“ወሃብዮች” በፊት የነበሩ የመውሊድ ተቃዋሚዎች
https://t.me/IbnuMunewor/1624

19, መውሊድ ተከሽኖ
https://t.me/IbnuMunewor/2309

20, ለምንድን ነው የመውሊድ ተቃውሞ ኢኽዋኖችን ምቾት የሚነሳቸው?
https://t.me/IbnuMunewor/918

21, መሷሊሐል ሙርሰላ፣ የመውሊድ አክባሪዎች የመጨረሻው ምሽግ
https://t.me/IbnuMunewor/2302

6 months, 3 weeks ago

ይህንን ድምፅ የሰማ ሰው ግር ሊለው ይችላል። ድምፁ የኢብኑ ባዝ ድምፅ አይደለም ወይ? ሊል ይችላል። የያዘው መልእክት ግን የሳቸው እንዳልሆነ ይገልፃል። ምናልባት የተነሳው ጉዳይ በኢብኑ ባዝ ዘመን ስለነበረ ጉዳይ ቢሆን ኖሮ ሰው ሳያቅማማ የሳቸው ድምፅ እንደሆነ ይደመድም ነበር።
ለማንኛውም ድምፁ አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ በመጠቀም በኢብኑ ባዝ ድምፅ ቅላፄ የተዘጋጀ ማሳሰቢያ ነው።
ያለንበት ጊዜ በጣም ከባድ ነው። የሃይማኖት አስተማሪዎችን፣ ፖለቲከኞችን፣ ሌሎችም ታዋቂ ሰዎችን ድምፃቸውን በመጠቀም በስማቸው አደገኛ መልእክቶች ሊሰራጩ እንደሚችሉ መረዳት እንችላለን።
ከዚህ በኋላ በቀረበው ድምፅ ላይ እንደተገለፀው በታማኝነታቸው ከሚታወቁ ምንጮች የተወሰደ ካልሆነ በስተቀር ድምፅ ስለገጠመልን ብቻ "እከሌ እንዲህ እያሉ ነው" በማለት ድምፅ ማቅረብ በቂ አይደለም።
እንዲያውም ተፅእኖው ስለሚያይል ስለ ታዋቂዎች አነሳን እንጂ በግለሰቦች ላይ ጭምር ፈጠራ መሆናቸውን ለመለየት በሚከብድ መልኩ የድምፅ፣ የምስልና የቪዲዮ ቅንብር በማዘጋጀት ከባባድ ፈተናዎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ መገንዘብ ይቻላል።

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

6 months, 3 weeks ago

ማስታወቂያ
~
የፊታችን እሁድ በሑዘይፋ መስጂድ የሴቶች ፕሮግራም እንዳለ ስለተነገረን ሳምንታዊ ደርስ አይኖርም።

6 months, 3 weeks ago

ስለዚህ መውሊድ ላይ የተለመዱት ጥፋቶች ባይኖሩ እንኳን አፈፃፀሙ በራሱ እንደትንሽ ቢድዐ የሚያስቆጥረው አይደለም።
አንዳንድ ከኢኽዋን አካባቢ የሚመጣ ፍርፋሪ እንዳይቋረጥባቸው የሚሰጉ ፈሪዎች ደግሞ የመውሊድን ቢድዐነት እያወቁ የዚህን ሰሞን ጁሙዐ ሆን ብለው አመት ጠብቀው በነብዩ ﷺ ልደትና ሲራ ዙሪያ ኹጥባ ያደርጋሉ። የተግባራቸውን አንድምታ በውል ያላጤኑ አንዳንድ የዋሆችም በተመሳሳይ በያመቱ እዚህ ጥፋት ላይ ሲወድቁ ያጋጥማል። ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ይህንን ጊዜ ከሌሎች ጊዜያት በሙሐዶራ ወይም በኹጥባ መለየት እንደማይገባ ይጠቁማሉ። https://www.youtube.com/watch?v=ylzwYXq2k84
የሰዑዲያ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴም የተከበሩትን ነብይ ልደት በማስመልከት ትምህርት ቤቶችንና መስሪያ ቤቶችን ስለመዝጋት ወይም ኹጥባዎችን፣ ሙሓዶራትና ድስኩሮችን ስለማዘጋጀት ተጠይቀው ልደቶችን ማክበር፣ ለዚህ ሲሉም ስራ መዝጋት ቢድዐ ነው። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እና ሶሐቦቻቸው ረዲየላሁ ዐንሁም አልሰሩትምና በማለት ነው የመለሱት። በሌላ ፈትዋቸውም ላይ እንዲሁ ቢድዐነቱን አስረግጠው ከተናገሩ በኋላ እንዲህ ብለዋል፦
“እነዚህን በአላት በማክበር ላይ ማገዝ አይፈቀድም። ስጦታዎች በመስጠትና የሻይ ብርጭቆዎችን በማቀበልም ቢሆን። እነዚህን በአላት ለማሰብ ኹጥባዎችንና ሙሃዶራዎችን ማድረግም አይቻልም። ምክንያቱም ይሄ እውቅናና ሞራል መስጠት ነውና። ይልቁንም መቃወምና አለመሳተፍ ግዴታ ነው።”
እንዚህን ፈትዋዎች የማቀርበው በጥላቻ ለተደፈኑ ሰዎች አይደለም። ይልቁንም በየዋህነት በተዘዋዋሪ ለመውሊድ ድጋፍ እየሰጡ ያሉ ሰዎች እንዲነቁ ነው። በጥላቻ የተደፈኑና በቢድዐ ፍቅር የናወዙ ወገኖቻችንንም አላህ ከሰመመናቸው ያንቃቸው።
=
ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/IbnuMunewor

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 2 days, 7 hours ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 1 month ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 2 days, 6 hours ago