መድ🪶

Description
ከህልው ሜዳ ስንቃርም...


ከልብ መድ ስናጣቅስ...እንደዚህ!
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago

3 months, 3 weeks ago

ለመተዋወስ....

==============*============

فَهَلْ يَنظُرُونَ إِلَّا ٱلسَّاعَةَ أَن تَأْتِيَهُم بَغْتَةًۭ ۖ فَقَدْ جَآءَ أَشْرَاطُهَا ۚ فَأَنَّىٰ لَهُمْ إِذَا جَآءَتْهُمْ ذِكْرَىٰهُمْ

ሰዓቲቱንም ድንገት የምትመጣባቸው መኾንዋን እንጅ ይጠባበቃሉን? ምልክቶችዋም በእርግጥ መጥተወል፡፡ በመጣቻቸውም ጊዜ ማስታወሳቸው ለእነርሱ እንዴት ይጠቅማቸዋል?
(47 : 18)

==============*============

@yeruh_weg

3 months, 3 weeks ago

"እኔ ምልህ…" "እእ… " " እስኪ ልብህን ሳልልኝ?" " አሁን ከምር የልብ ቅርፅ ጠፍቶህ ነው? ♡ ያው ሳልኩልህ!" "እንዲህ ነው ልብህ?" " አዎ ምነው? ያንተ ይለያል እንዴ ሃሃ..." " ታድለህ ጥርት ያለ ነው። የኔን ለመሳል ጥቁር ቀለም ያስፈልጋል።" " እእ ማለት?" " ኧረ ስቀልድ ነው ሃሃሃ…"

@yeruh_weg

4 months, 2 weeks ago

".....አንድ ነብር... 3 እርግቦችን ሊያድን እንደመጣ አስብ። ሁለቱ ነብሩን እንዳዩት ለመብረር ወሰኑ፣ አንዷ ግን ለመብረር አሰበች እንጂ አልወሰነችም። ነብሩ በዚ ቅፅበት ከደረሰ ስንት እርግብ የሚበላ ይመስልሃል?
.
.
.
.
.....1 ካልክ ተሳስተሃል፣ ነብሩ 3ቱንም ነው የሚበላቸው። ምክኒያቱም ሌሎቹ ሁለቱም ወሰኑ እንጂ አልበረሩም። በማሰብና በመወሰን መሃል ያን ያህል ልዩነት የለም። ልዩነት ያለው ተግባር ሲኖር ነው። ብዙ ሰዎች ይመኛሉ፣ ይወስናሉ፣ ይመዘገባሉ.... ግን ተግብረው የሚያሳኩ ጥቂቶች ናቸው።"

-ኡስታዝ ያሲር አልሁዘይሚ

@yeruh_weg

4 months, 2 weeks ago

....አንድ ጊዜ አልሃጃጅ ኢብን ዩሱፍ ወደ ጌታው የሚማፀን አይነስውር ያያል ይባላል። ምን ሆኖ ነው ሲልም ይጠይቃል። አላህ "አይኑን እንዲያበራለት እየጠየቀ ነው" ሲሉ ይመልሱለታል። አይነስውሩ አንዴ ልብሱን እየነካካ አንዴ ፀጉሩን እያሻሸ ዱዐ የሚያደርግበት ሁኔታ ያን ያህል ያመረረ እንዳልሆነ ያስታውቅ ነበር። አልሃጃጅ በዘመኑ ጨካኝ ከሚባሉ መሪዎች አንዱ ከመሆኑ ጋር በሁኔታው ተበሳጭቶ ወደ ሰውየው ይጠጋና "እኔን አውቀኸኛል?" ሲል ይጠይቀዋል። አይነስውሩም በመርበትበት "አዎ፣ እንዴታ! እርሶን የማያውቅ ማን አለ" ሲል ይመልሳል። አልሃጃጅም... "እስከ ፈጅር ጊዜ ሰጥቼሃለው። ፈጅር ላይ አይንህ በርቶ ባላገኘው በአላህ እምላለሁ አንገትህን ህዝብ ፊት ነው የምቀላው" ብሎት ይሄዳል። አይነስውሩ ከፍርሃቱ ሌሊቱን ሙሉ እያለቀሰ ጌታውን ከዚ ጉድ እንዲያወጣው ሲማፀንና ሲዋደቅ ያድራል። በነጋታው ጠዋትም አይኑ በርቶ ያገኘዋል። አልሃጃጅም... "ዱዐ ማለት እንዲ ነው" አለው ይባላል።

.....ጀባሩ በዱዐቸው ላይ ለነፍሱ እንደሰጋው አይነሰውር ችክ ብለው በሰጪነቱ ላይ ተስፋ የማይቆርጡትን ይወዳል። ፊርደውስ በሳምንት አንዴ በሚሰገድ ጁምዐ፣ በአመት አንድ ወር በሚቆምበት የረመዳን ዱዐ ብቻ አትገኝም። የሙስሊም ወንድምና እህቶቻችንም ፈረጅ ፖስት ባየን ቁጥር በሚመጠጥ ከንፈር አይደረስም። ዱዐችን ላይ ችክ እንበል.... አላህም ኸልቁ ሙሉ ተሰብስቦ ቢጠይቀው ለእያንዳንዳችን አንዳንድ ዱንያ በመስጠት ላይ ከሱ ቅንጣት የማያጎልበት ከመሆኑ ጋር ቻይ ነው።

@yeruh_weg

4 months, 2 weeks ago

....ወዳጆቻችሁ በህይወታቸው ውስጥ ያሉ ትንሽና ትልቅ ችግሮችን በሙሉ ቆጥረው መበደላቸውን ሲነግሯቹ... አላህን እንዲያመሰግኑ አስታውሷቸው። ምክኒያቱም እነዚህን ተቆጥረው የሚያልቁ ችግሮችን የቀደረባቸው ጌታ፣ ራሱ ተቆጥረው የማያልቁ ፀጋዎችን ያወረደባቸው ራህማን ጌታ ነው። አላህም ችግሮቻቸውን ሁሉ በቅፅበት ውስጥ ፀጋ፣ ፀጋዎቻቸውን ሁሉ በቅፅበት ውስጥ ወደ ችግር በመለወጥ ላይ ቻይ ነው። ፈልሃምዱሊላህ ተቆጥረው ለሚያልቁ ችግሮቻችን፣ ወልሃምዱሊላህ ዐላ ኩሊ ሃል?

@yeruh_weg

4 months, 3 weeks ago

...."ባንወድቅ ኖሮ.... እጃችንን እንዳልያዙት በምን እናውቅ ነበር?".... የሚል ነገር አነበብኩ...

ፈልሃምዱሊላህ በመንገዳችን ላይ ላጋጠሙን ትናንሽ እንቅፋቶች....

@yeruh_weg

7 months, 1 week ago

በሶሻል ሚዲያ ውሎውን ጀምሮ በዛው ላይ ከሚያድርበት ይልቅ… በሶላትና ቁርአን ጀምሮ በሶላት ና ዚክር የሚጨርስ የተሻለና የተረጋጋ ጊዜን ያሳልፋል… ረሱሉና ዐለይሂመሰላም ከኢሻ በኋላ ወሬን አይወዱም ነበር…

መድ?
@yeruh_weg

7 months, 2 weeks ago

እድሜ

ልጅነት የተለየ አለም አለው። ደስታ፣ ጨዋታ፣ መቦረቅ፣ መደባደብ… ከኛ ከትልቆቹ አለም እጅግ ይለያል። በጣም ጣፋጭ የማይገኝ የሚናፍቅ ጊዜ ነው "ኧረ ልጆች ልጆች እንጫወት በጣም፣ ከእንግዲህ ልጅነት ተመልሶ አይመጣም…" እያልን ትርጉሙን ሳናውቀው እየዘመርን ቦረቅንበት። ትልቅ መሆን እንደተመኘን ነፃነት ያለው እየመሰለን እየጓጓንለትም አደግን። ነገር ግን ስናድግ ትልቅነት እንዳሰብነው የሚናፈቅ አለም ሁኖ አላገኘነውም። ልጅ ሁነን እጃችን ላይ ትንሽ ነገር ከቧጨረን ሳምንቱን እንደ ህመምተኛ እጄን ነካብኝ፣ አያስበላኝም፣ አያስተኛኝም ብለን እንዳልቀበጥን ሁሉ፣ አሁን መች እንደቆሰለ ራሱ የማናውቀው ብዙ ቁስል ሰውነታችንን ሞልቶታል። መች እንደቆረጥነው ሳናውቅ ረጥቦን ስንመለከተው እየደማ እንደሆነ የምናውቅባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት አይደሉም። በማደግ ውስጥ አለመታመም ኑሮ ወይስ የውስጣችን ህመም በዝቶ ይሆን ሲቆስል የማትታወቀን ባይገባኝም ትልቅነት ግን የሚያጓጓ ጊዜ አልነበረም።

በትልቅነት ውስጥ አዕምሯችን ይበሰልም አይብሰልም ሀላፊነቶችን የመወጣት ግዴታ ይኖርብናል። አሁን ላይ እያንዳንዱ ጥቃቅን ስህተት "ልጅ ናት አታውቅም" ተብሎ አይታለፍልንም። "ትልቅ አልደለች እንዴ?!" ብሎ ተቆጪው ወቃሹ ብዙ ነው። የስኬት መንገዶች ላይ ድሮ ልጅ እያለን የማናውቀውን "ምቀኛ" የሚባል ቃል እንማራለን። በየምንገዱ ማልቀስ ላገኙት ሁሉ መዘርገፍ የማያዋጣ ነገር ይሆናል። ድሮ ልጅ ስለሆንን "እንዳያስቡ!" ተብለን የተደብቅናቸውን ችግርና ፈተና የሚባሉ ነገሮችን በተግባር እንማራለን። ከዛም ትልቅነት ያስጠላናል፣ የምንነፋረቅበት እቅፍ ይናፍቀናል። ወደ ልጅነት መመለስን ብንሻም በምኞት ውስጥ ስንዋልል ቁሞ የሚጠብቅ እድሜ የለንም። ከኋላችን እርጅና ያሳድደናል አሁን ከምንኖረው የባሰ የሆነ እድሜ። ቁጭ ብሎ ወጣትነትን እያስታወሱ ራሳችንን የምንወቅስበት እድሜ። መለስ ብለን ስናስበው ብንመለስበት ብዙ ማሳካት የምንችልበት እንደሆነ እንዲሰማን የሚያደርግ፣ አሁን ብዙ ያደከመንን ፈተና "ለዚህ ነው?" ብሎ የሚያስንቅ እድሜ ወደፊት ይጠብቀናል። ምኞት ብቻ ሁነን መስሪያ ጉልበቱን የምናጣበት፣ ለነገ ብለን የገፋነው ሁሉ ተጠራቅሞ የሚጠብቅብን፣ አንገፋው ወደፊት የለን…አንሰራው አቅሙ የለን… እንዲሁ ሁነን እንባክናለን። ከዛም ለምን ወጣትነት ላይ ፈተና እና ችግር እንደሚበዛ ይገለጥልናል። የተሻለ የእርጅና ዘመን ላይ መኖር እንችል ነበር። ነገር ግን ነጋችንን ሳናቅድ ኑረነዋልና ያተረፍነው ነገር ምን እንደሆነ አይገባንም። ከዛም ዳግም ለምን ወጣትነቴን ሳልጠቀምበት የሚል ቁጭት እናስከትላለን። ይህን የሚያውቁ አዛውንቶችም በቻሉት መጠን ሊመክሩን ይጥራሉ። ሁሉም ባለፈበት እንድናልፍ አይመኝልንም። ትንሽ የሚንቀሳቀስ ወጣት ሲያዩ ይደሰታሉ። ሁሉም ወጣቱን ህዝብ ይፈልገዋል፣ ለስኬት አስፈላጊ እንደሁነ ስለሚያውቅ ያለፈውን እድል ወጣቱን ተጠቅሞ እንዲሳካለት ይለፋል። ምክንያቱም አስቦበትም ይሁን ሳያስብበት ሀላፊነትን የተሸከመው ወጣት እሱ ብቻ እንደሚያሳካው የሚያውቁት እድሜውን ያለፉት ብቻ ናቸውና። እናማ… ህመሙ፣ ችግሩ፣ ሀላፉነቱ ቢበዛም ሁሉን ችሎ ትልቅ ቦታ የሚደርሰው የወጣትነት ሀይል ያለው ብቻ ነውና ችለን ነጋችንን መገንባት ትልቁ ስኬታችን ነው። የእድሜያችን ፈተና ይህ ስለሆነ!

@Re_Ya_Zan

7 months, 2 weeks ago

በምድር ላይ ባለህ ቆይታም ከመልካሞች ጋር ተወዳጅ...እነርሱ ከመካከላቸዉ በጠፋህ ጊዜ ፈላጊዎችህ ናቸዉ፣ መንገድ ስተህ ባዩህ ጊዜም ይመልሱሃል፣ በተዘናጋህ ጊዜ ያነቁሃል፣ በራቅካቸዉ ልክም ይናፍቃሉ፣ ከጌታቸዉ ጋር በተንሾካሾኩም ቁጥር ስምህን አይረሱም...?

@Re_Ya_zan
@Yeruh_weg

10 months ago

ረመዷን ወጣ ብለህ ከመሳጅድ ብትርቅ ሌሎች ወደ መሳጂድ ይሄዳሉ… ቁርዓንን ብትተወው ብትረሳው ሌሎች ይሃፍዙታል… አላህን ብትርቀው ሌሎች ይቀርቡታል… በስተመጨረሻም አንተ እንጂ ሌላ የከሰረ እንደሌለ ታስታውላለህ

ይህን የአላህ ቃል አስተንትን

{ وَاللَّهُ الْغَنِيُّ وَأَنْتُمُ الْفُقَرَاءُ وَإِنْ تَتَوَلَّوْا يَسْتَبْدِلْ قَوْمًا غَيْرَكُمْ ثُمَّ لَا يَكُونُوا أَمْثَالَكُمْ }

አላህም ከበርቴ ነው፡፡ እናንተም ድኾች ናችሁ፡፡ ብትሸሹም ሌሎችን ሕዝቦች ይለውጣል፡፡ ከዚያም (ባለመታዘዝ) ብጤዎቻችሁ አይኾኑም፡፡
መድ?

@yeruh_weg

We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 8 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 3 weeks, 1 day ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 months, 2 weeks ago