ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ

Description
ስለ ስምህ እንሞታለን
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 9 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 months ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 3 months, 3 weeks ago

6 months, 2 weeks ago

ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው

መዝ 60፥4 ላይ ልበ አምላክ ዳዊት “ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው" በማለት የተናገረው በምሥጢር ክርስቶስ የሚሰጠንን የሐዲስ ኪዳን ልዩ ምልክት ሲያመላክት ነው። እግዚአብሔር የሚሰጠንን ልዩ ምልክት ገንዘብ ለማድረግ አስቀድመን ሊኖረን የሚገባው “ፈሪሐ እግዚአብሔር" ነው። ፈሪሐ እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ መግቢያ በር ስለ ኾነ ልዩ ምልክትን ከእግዚአብሔር ለማግኘት የግድ የፈሪሐ እግዚአብሔርን ልብስ ውስጣችንን ማልበስ አለብን። ያ ልዩ ምልክት ቅዱስ መስቀሉ ነውና! መስቀል ዓለምን በሙሉ አምላካችን ክርስቶስ ወደ ራሱ የሳበበት የሰላም ዓርማ ነው። ይህ ምልክት ክርስቶሳውያን የመኾናችን ዋና መለያ ነው።

እግዚአብሔርን የማንፈራ በፊቱ ቆመን የምንተቻች፣ እርስ በእርሳችን የምንናናቅ እንዴት ምልክቱን ልናገኝ እንችላለን? በፈሪሐ እግዚአብሔር ውስጥ እስካልኖርን ድረስ ምልክቱን ማግኘት አንችልም። ለሚሳለቁበት፣ መቅደሱን የሳቅና የስላቅ ስፍራ ለማስመሰል ለሚጥሩ፣ ትሕትና ለሌላቸው፣ ቅዱሳን መላእክት በመንቀጥቀጥ የሚያመልኩትን አምላክ በመቅደሱ ተገኝተው የሚተኙበት ሰዎች ምልክቱን አያገኙትም። “ለሚፈሩት" ሲል ለሚያመልኩት ማለት ነው። እናመልክሃለን ብለው በተግባር ግን ፈጽሞ የራቁ ሳይኾን በእውነት የሚያምኑበት ናቸው ልዩ ምልክትን የሚያገኙት። ወደዚህ ምልክት ውስጥ በፍቅር እስካልገባን ድረስ ፍቅርንና ሰላምን ገንዘብ ማድረግ አንችልም። በተግባራዊ ሕይወታችን ውስጥ የቀበርነውን መስቀል በንጹሐን መምህራን በኩል ቆሻሻውን አስነሥተን መስቀሉን እስካላወጣነው ድረስ መስቀል የሕይወት ምልክት ነው ብለን የምንፈክር እንጂ በእርግጥም መኾኑን በሕይወት መግለጥ ያቃተን ግብዞች መኾናችንን እናረጋግጣለን።

ምልክት (Banner) የሚያመለክተው አምላካችን ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን አንድ ጊዜ የገባበት መቅደስ የተባለውን ቅዱስ መስቀልን ነው። መስቀል ለክርስትናችን መለያ ምልክት ነው። ክርስትናን ከመስቀል ነጥሎ ለማየት መሞከር ማለት ቤተክርስቲያንን ከክርስቶስ ነጥሎ ለማየት እንደ መፈለግ ነው። መስቀል የቤተክርስቲያን ሙሽራ ክርስቶስ ቅድስት ቤተክርስቲያንን በደሙ ሲያጭ ፥መታጨቷን ለመግለጽ ያኖረላት ምልክት ነው። ቤተ ክርስቲያን ጉዞዋ በሙሉ ወደ ድኅነት የሚመራ ነው። በምድር ላይ በምእመናን ልብ ውስጥ መስቀል እየሳለች ሰማያዊቷን መንግሥት ታጓጓናለች።

መስቀልን በአንገታችን ላይ ማድረጋችን የክርስቶስ ሙሽሪቶች መኾናችን ይታወቅ ዘንድ ነው። አንዲት ሴት ከታጨች በኋላ ሌላ ወንድ መፈለግ የለባትም፤ ሌላም ወንድ እንዲፈልጋት የሚያደርግ ሥራ መሥራት የለባትም። ቤተክርስቲያን መስቀሉን ከክርስቶስ በምልክትነት ከተቀበለች በኋላ ሌላ ነገር አትፈልግም። መስቀል የሕይወቷ ዓርማ አድርጋ ስትታወቅበት ትኖራለች እንጂ። መስቀል በምድር ያለችው ቤተ ክርስቲያን የሚደርስባትን መከራ የሚያመለክት ነው። መከራ ደግሞ የክርስትና ሕይወት መልክ ነው። ብዙዎቻችን የዚህ መሠረታዊ ሐሳብ ተቃራኒ የኾነ ሕይወት ነው ያለን። ከክርስቶስ መከራ ይልቅ የዘፋኞች ዘፈን ልባችንን የማረከብን፤ ከክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ይልቅ የዚህ ዓለም ተራ መብልና መጠጥ የሚያረካን ከክርስትናው እውነተኛ መንገድ እጅግ የራቅን ነን። ስለዚህ ምልክቱን ስንተው አጋንንትም መጥተው አደሩብንና ከሙሽራው ፈቃድ ለዩን።

ምልክት የተባለው በቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ “የክርስቶስ ደም" ነው ይላል። በእርግጥ ይህን ደም ምልክት አድርገን የምንኖር ከኾነ ጠላት ድል ያደርገን ዘንድ አይችልም። መስቀል ደግሞ በዚህ ትርጒም የምልክት ምልክት ነው። የክርስቶስ ደም የፈሰሰበት የሕይወት ዕፀ ነውና። በመስቀል ላይ የተቆረሰውን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ የፈሰሰውን ክቡር ደም እናይበታለን። መስቀሉን ስንስም የምንስመው ዕፅነቱን ብቻ አይደለም ይልቅስ በዚያ ላይ ከሞት የሚያድነን ንጹሕ የክርስቶስን ደም ነው። ስለዚህ በመስቀል ዐይንነት ክርስቶስን እናየዋለን። በምልክቱ በኩል ምልክቱን የሰጠንን አምላክ ደሙን ሲያፈስልን ተመልክተን ፍቅሩን እናደንቃለን።

“ለሚፈሩት ምልክትን ሰጠሃቸው" የተባለውን ብዙ ሊቃውንት የእስራኤላውያን በኲር በግብጽ ምድር የተረፈበትን የፋሲካውን በግ ደም ነው ይላሉ። ያ ምንም የማያውቀው በግ ደሙ በቤቱ ጉበን ላይ በመቀባቱ ምክንያት የእስራኤል በኩራት ከዳኑ ሕያው በግ ክርስቶስ ቤት አድርጎ በቀራኒዮ በገባበት መስቀል ላይ ባፈሰሰው የሚናገር ደም'ማ እንዴት የበለጠ ድኅነት ይገኝ ይኾን? በኩራችን ክርስቶስን ከልባችን ውስጥ ለማጥፋት የሚተጉትን ክፉ አስተሳሰቦች በሙሉ እንዋጋቸው። ኹል ጊዜም ነገረ መስቀሉን ምልክት አድርገን የአጋንንትን ሐሳብ እናርቅ፤ በእግዚአብሔር ቃልም መሠረት ሳንሠቀቅ መከራ መስቀሉን ለመሸከም እንትጋ። የእውነት መኖር ከጀመርን ሕይወታችን በራሱ የመስቀል ሕይወት ይኾናል፤ ብዙ ግራ የተጋቡ ሰዎችንም የመሰቀል ሕይወትን ጣዕም አቅምሰን ከስሕተታቸው መመለስ እንችላለን። በመኾኑም ምልክታችንን ከጥልቅ ውስጣችን ሕያው አጥር አበጅተን መጠበቅ አለብን።

?ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

6 months, 3 weeks ago

#ያልተሞረደ_አእምሮ_አስቸገረን
ቢላው ሲደነዘዝ ሥጋ አይቆርጥም ስለዚህ በድንጋይ ይሞርዱታል።
ከግንዛቤ እና ከመረዳት የተለየ አእምሮም በመምህር ይሞርዱታል።
ከአንድ ሊቀ ጳጳስ ጋር ሆነን የቢሮ መኪናዬን እየነዳሁ ጀሞ ስደርስ የመኪናው ፍሰት አላስኬድ ብሎኝ ቀስ እያልኩኝ የመኪና ዳዴ እያረኩ ሳለ አንዲት ነጭ በነጭ የባሕል ልብስ የለበሰች ድምጸ ሸካራ ሰውነተ ቀላል ሴት "#መነኩሴ_መኪና_አይነዳም_ንስሐ_ግባ" አለችኝ።

እ................ሺ አልኳትና ፈገግ አልኩኝ በዚህ ጊዜ አቡኑ "ከእሷ ንግግር ይልቅ የአንተ ፈገግታ ዘይገርም ነው" አሉኝ።

የክርስቶስ የማያቋርጥ ፍቅሩን እና ወዳጅነቱን እያሰባችሁ ፈገግ እያላችሁ አገልግሉ እንጂ የሰነፎች አሉባልታና ነቀፌታ ወደ አእምሯችሁ አታስገቡ!

ምክንያቱም የመርዛማ ሰዎች ንግግር ልቡናችሁን መርዞ ይገላችኋልና።

#ፓንዋማንጦን

6 months, 3 weeks ago

ትዳር እንደ አያያዙ ነው
ትዳር ማረፊያ ወደብም የመርከብ አደጋ የሚያጋጥምበት ሰርጥም ሊሆን ይችላል።

6 months, 3 weeks ago

“በአባ ቢሾይ ገዳም ከአባቶች መነኰሳት ጋር ተገናኘሁ። በዚያም የቦታውን መንፈሳዊነትም ሆነ የእንግዳ ተቀባይነታቸውን ነገር፣ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የሆነውን ተግባራቸውንና ትምህርታቸውን ተመለከትሁ፤ ሆኖም ግን ካየሁት ሁሉ አንዱንም እንኳ እንደሚገባ አድርጌ አሟልቼ ልገልጸው አልችልም። ሆኖም የክርስትና ገዳማዊ ሕይወት በታሪካችን ውስጥ የነበረውን ሚና መዘንጋት ለእያንዳንዱ ዐረብ ታላቅ ኪሳራ የመሆኑ ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ማስተዋል ተገቢ መሆኑን ለራሴ ተረድቻለሁ። በእ*ስልምና ሃይማኖት ውስጥ ምንኲስናና ገዳማዊ ሕይወት የሚባል ነገር አለመኖሩን ማሰብ ውስጥን የሚረብሽና የሚያሳዝን ነገር ነው።”

መናንያን በሥራ የሻከሩ እጆች ያሏቸው ብቻ ሳይሆኑ ከርኩሰትና ከነውር ንጹሕ የሆነች ነፍስ ትኖራቸው ዘንድ የሚጋደሉ እውነተኛ ጀግናዎችና ትክክለኛ ፈላስፋዎች ናቸው። ከመብላትና መጠጣት፣ ከማግባትና ከመጋባት ባሻገር ወዳለው ሰማያዊ ሕይወት የሚያመለክቱ አቅጣጫ ጠቋሚዎችና ዐዋጅ ነጋሪዎች ናቸው።

ስለሆነም ሰው ያልደረሰበትን ነገር በመሰላል ወጥቼ ልንቀፍ ማለት ተገቢ አይደለም! ሊታገሡት የሚገባም አይደለም! በዕድሜያቸውም ሆነ በእውቀታቸው ታዳጊ የነበሩት የ1950ዎቹና 60ዎቹ ትውልዶች በኦርቶዶክስ-ጠል መምህራን የተሞሉት ጥላቻ ዛሬ ያፈራውን መራራ ፍሬ እያየን፣ የእነዚያ የመንፈስ ልጆች የሆኑ በዕድሜ እንኳ ባይሆን በአእምሮ ሕፃናት የሆኑ ኦርቶዶክስ-ጠሎች ተገቢ ያልሆኑ ነገሮችን ሲናገሩና ሲጽፉ እያዩ ኦርቶዶክሳውያን ዝም ማለት አይችሉም።

ኦርቶዶክሳውያን፣ ገና ለገና ያሻንን ብንላቸው ለክፉ አይሰጡንም የሚሉ የፈሪዎችና የአጎብዳጆች የብዕር መፈተኛና የአፍ ማሟሻ መሆንን መቀበል ከማይችሉበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሰዋል። ስለዚህ ወደ ላይ አያዳልጣችሁ! የሚታየውን ብቻ ሳይሆን የማይታየውን መፍራትም ብልህነት ነው!

✍️ዲ/ን ያረጋል አበጋዝ

6 months, 3 weeks ago

የኔታዎች "#ወፈነዎሙ_በበክልኤ" ያለው ትርጓሜ አወራረዱ ስንት ነው?
አንድ ቀን አንድ ትንሽ ልጅ ከመንገድ ዳር በትናንሽ እጆቹ ዐይኖቹን እያሻሸ ስቅስቅ ብሎ ያለቅሳል᎓᎓ አንዱ ሆደ ቡቡ መንገደኛ ወደ ሕፃኑ ጠጋ ብሎ "ማሙሽዬ ለምንድነው የምታለቅስው ምንስ ሆነህ ነው"? ሲለው "እኚህ የኔታ «ሀ» በል ይሉኛል" ሲል ይመልሳል፡፡ በሁኔታው የተገረመው መንገደኛውም ነገሩን ቀለል አድርጎ "ታዲያ ምናለበት "ሀ" አትልም እንዴ"? ቢለው "እሳቸው መቼ ይተዉኛል? ሀ ስል ሁ በል ይሉኛል ሁ ስል ሂ በል ይሉኛል… እያለ Baby ብሶቱን ዘከዘከው አሉ።
አንዳንድ ሰው ሊሠራ የሚገባውን ሳይሠራ በሀሳብ ብቻ ይደክማል፡፡ የማያስፈራውም ደርሶ ያስፈራዋል።

"ሀ" ላለማለት ከመሬት ደርሶ "ው ው ው"! ብሎ ይጮሀል።

Baby እንግዲህ መልካም ጩኽት ይሁንልህ!

ሐተታው ከቀደመው ይገባል።
#ፓንዋማንጦን
መስከረም 18/01/2017 ዓ/ም

6 months, 3 weeks ago
7 months, 2 weeks ago

አበው ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ !

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው " ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት" ቅዱስ አውግስጢኖስ

"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??" ቅዱስ ኤፍሬም

7 months, 2 weeks ago

ራስን መንቀፍ

ራሱን የማይነቅፍ ሰው እርሱ ትክክል እንደሆነና እንዳልተሳሳተ አድርጎ ስለ ሚያስብ ምንም አይነት ስህተች ቢሰራ እንኮን ይቅርታ አይጠይቅም ።
ከወንድሙ ጋ ሲጋጭ ከእርሱ ጋር ለመታረቅ ራሱን አያነሳሳም ። እርቁ እንዲመጣ የሚፈልገው ከሌላ ወገን ነውና ።

ግን ለምን? ይህን የሚያመጣው ማንነት ነው! ሌላው ቢቀር እኔነቱ ምንም አይነት ስህተት እንዳልሠራ አድር  ስለ ሚያሳምነው ስህተቱንም በእግዚአብሔር ፊት እንኳን አይናዘዝም ።

ራስን መንቀፋ የሚመጣው ከትህትና ሲሆን ትህትና ደግሞ ራስን ወደ መካድ ይመራል ። ትኁት ያልሆነ ሰው ራሱን አይነቅፋም አይኮንንም ። ሁልጊዜ የሚነቅፈው ሆነ የሚኮንነው ሌሎችን ነው እንዲ አይነቱን ሰው ለምንድነው ሌሎችን የምትነቅፈው ብለህ ብጠይቀው እንዲ ብላችሁ በመጠየቃችሁ ብቻ ይቀየማል ይገስፃችሀል።

ራሱን በዚህ ዓለም ሳለ የሚወቅስ ሰው በወዲያኛው አለም ከመወቀስ ይድናል ።
ሰው ራሱን ከሚወቅስበት ምክንያት አንዱ ወደ ንሰሀ ለመቅረብ ነው ። ንሰሐ ከገባ ደግሞ እግዚብሔር ኃጢአተኛ ይቅር ይለዋል ። ራሱን ከማክበር አንፃር ራሱን የማይወቅስ ሰው ግን ሳይሻሻል በኃጢአት ውስጥ በመውቀስ ይኖራል ።
ቅዱስ እንጦስ << እኛ ራሳችን ከወቀስን ዳኛው በእኛ ይደሰታል ።>> ብሎ የተናገረው ምንኛ እውነት ነው። ከዚ በመቀጠልም << እኛ ኃጢአታችን የምናስታውሳቸው ከሆነ እግዚአብሔር በንሰሐ ይረሳልናል : እኛ ኃጢአታችን የማናስብና ንሰሀ የማንገባ ከሆነ እግዚአብሔር ያሰበዋል >> በማለት ተናግሮአል ።

ይህን አስመልክቶ ቅዱስ መቃርስ የተናገረው አባባል ምነኛ ድንቅ ነው!
<<ወንድሜ ሆይ! ሌሎች ሳይወቅሱህ አንተ ራስህን ውቀስ!>>

አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ
መንፈሳዊ ውጊያወች  መፅሀፍ ገፅ 41-42 የተወሰደ

7 months, 2 weeks ago

በዚህ ግራ በተጋባ አገር ውስጥ በክርስትናህ ፀንተህ መኖር አለመኖርህን ለመመዘን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለራስህ መልስ፡-
(1)  በቋሚነት ማታና ጠዋትን ጨምሮ  ተጸልያለህ?
(2)  ሳታቋርጥ በቤተክርስቲያን ቀኖና መሠረት፣ በመምሕረ ንሥሐ ምሪት ሥር  ሆነህ በቤተክርስቲያን የጋራ ጸሎት፣ በሌሎች የቤተክርቲያን ምሥጢራትና በቅዱስ ቁርባን ትሳተፋለህ?
(3)  በየዓመቱ የቤተክርስቲያን ግፃዌ ዑደት (ካሌንደር) መሠረት መጾም፣ በዓላቱን በተሠራው ቀኖና መሠረት ማክበር፣ በአጥቢያ ዓመታዊ የአገልግሎት ውሳኔዎች በመታዘዝ ትሳተፋለህ?
(4)  እኔ ኃጢአተኛው እገሌ ብለህ ራስህን በመርመር ለጸሎት በቆምክበትና በሁሉ ቦታ የአምላክን ምህረት ትጠብቃለህ?  በዚህም በሌሎች ከመፍረድ ራስህን ትገታለህ?
(5)   ዘመኑ ካመጣው ሩጫ፣ የተጨናነቀ ሥራ፣ አልጠግብ ባይነት፣ ያጡትን እያሰቡ ባገኙት ባለማመስገን በጭንቀት ውስጥ ከሚኖሩት ኢአማኒያን የሚለይህ እርጋታ አለህ?
(6)  በእጅህ ላይ ባለውና እግዚአበሔርን በሚያስደስተው ሥራህ ላይ ታተኩራለህ ወይንስ ሩቅና ምኞታዊ በሆነ ዐሳብ ትዋልላለህ?
(7)  በተፈጥሮ ከተሰጡን ፍላጎች ለምሳሌ መብላት፣ የተቃራኒ ፆታ ፍላጎት፣ ፍቅር ማግኘት፣ ክብር መፈለግ፣ መጠለያ ማግኘት፣ ወዘተ በተጨማሪ በሰብአዊ ትምህርትና መገናኛ ብዙሀን ጫና የሚመጡ በአካላዊ ገፅታ                መደነቅ፣ ዝሙት፣ ውዳሴ ከንቱ፣ አሸናፊነት (የበላይነት) መሻት የመሳሰሉ ፍተወታትን   --- በቃለ እግዚአበሔርና በቅዱሳን ሕይወት ምሳሌነት መግራትና ራስን መግዛት ወይስ ፍተወታትን እያዳመጡ ለማርካት መሥራት ላይ ትጠመዳለህ?
(8)    ከራስህ በማስቀደም ሌሎችን በመርዳት ትደሰታለህ? ወይስ በራስ ወዳድነት ለመብለጥ በምታደርገው ሩጫ አሸናፊና የበለጥክ ሆነህ መታየት ያስደስትሀል?
(9)  ከሌሎች ኦርቶዶሳዊያን ጋር በመሆን መንፈሳዊ ትምህርት በመማማር እምነትህን ታጸናለህ?፣ የግብረ ሠናይና መልካም ስነምግባር አርአያነት እንዲሁም በመረዳዳት ውስጥ  ትሳተፋለህ? ወይስ ከዓለማዊያን ጋር ሳምንቱን በጭፈራና በዋዛ ፈዛዛ በማሳለፍ ነገረ-እግዚአበሔርን በሰንበት ዕለት ብቻ ታስታውሳለህ?
(10)  መጽሐፍ ቅዱስን፣ ስንክሳርና የአባቶች ሕይወትን ለማንበብ ቋሚ ጊዜ  አለህ ወይስ በወቅታዊ መረጃ ንባብ ብቻ ትጠመዳለህ?
(11)  ከዘረኝነት ደዌ አምልጠህ የሰው ልጅን ሁሉ ባለማበላለጥ እኩል የመውድ ልብ አለህ ወይንስ በአራዊት አምሳል በጎራ ተስልፈው ከሚናከሱት ጋር አንዱን ጥግ መርጠህ ትተራመሳለህ?
(12)  የሕግ ሁሉ ፍጻሜ ሰውንና እግዚአብሔርን መውደድ ነውና በዚህ ፍቅር ውስጥ ትኖራለህ? ወይስ ለአንተ የሚስማማ የግል አምላክ ፈጥረህና ከሚመስሉህ ጋር የሀሰት እምነት መሥርተህ ከአንዲት ቤተክርስቲያን ተለይተህ ይሆን?
(13)  የክርስቲያን መሠረታዊ የሕይወት ትርጉሙ ምንጭ የሆነውን ፍቅር፣ ተስፋ፣ እምነት መያዝ አለመያዝህን ጠይቅ? በአእምሮህ የሰው ጠላት፣ ተስፋቢስነት፣ ኑፋቄና ክህደት ወርሰውህ በቁሳዊ ሀብትና የቡድን ዋስትና የምትተማመን ከሆንህ ፈትነህ ወደ ቤተክርስቲያን መምህራን ካህናት መጥተህ ሕክምና አግኝ፡፡

መምህር ፋንታሁን ዋቄ

7 months, 2 weeks ago

+++የሰማነው ግን ያልተማርነው ትምህርት+++

አባ በምዋ (Abba Bemwa) ዓለምን ትቶ ወደ በረሃ በሄደ ጊዜ፣ ለዚህ አዲስ ሕይወቱ የሚጠቅመውን ምክር ይሰጡት ዘንድ ወደ አንድ ቅዱስ አረጋዊ ቀርቦ "ምን ላድርግ" ሲል ጠየቃቸው። እኒህም አረጋዊ ንግግራቸውን የጀመሩት "በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ" በሚለው በቅዱስ ዳዊት የመዝሙር ቃል ነበር። (መዝ 39፥1) አባ በምዋም ይህንን የመጽሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ "ይበቃል አባቴ፣ ይህን ተምሬ እስክፈጽም ድረስ ሌላ ምንም አዲስ ትምህርት አይንገሩኝ" በማለት ወደ በዓቱ ሄደ።

ከዚያም ቀን ጀምሮ ለብዙ ጊዜያት ወደ አረጋዊው አልተመለሰም ነበር። ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋዊው ጻድቅ አባ በምዋን አግኝተው ለምን ለሌላ ተጨማሪ ትምህርት መልሶ ወደ እርሳቸው እንዳልመጣ ጠየቁት። እርሱም "እመኑኝ አባቴ፣ ገና የመጀመሪያውን ትምህርት በሚገባ አልተማርኹትም" ሲል መለሰላቸው። ከረጅም ዓመታትም በኋላ ወዳጁ የሆነ አንድ መነኩሴ የሰማውን የነቢዩ የዳዊትን ቃል እስከ አሁን አጥንቶ ጨርሶ እንደሆነ አባ በምዋን ጠየቀው። ቅዱሱም "በዚህ የነቢዩ ቃል ላይ ለማሰላሰል እና በሚገባ ወደ ተግባር ለመቀየር አርባ አምስት ዓመታት ወስዶብኛል" ሲል በትሕትና መለሰለት። የአባ በምዋን ታሪክ የጻፈልን ቅዱስ ጰላድዮስ እንደሚናገረው አባ በምዋ በሕይወቱ ሁሉ ፍጽምት የሆነች የዝምታን ሕይወት የመራ ሲሆን፣ በሞቱም ጊዜ "ምነው ይህን ባልተናገርኩ" የሚል አንድም የሕሊና ወቀሳ ሳያገኘው በሰላም አርፏል።

ቅዱስ እንጦንስም በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ሲል መክሯቸው ነበር ፦ "ዝም በሉ፤ ዝምተኛን ሰው እግዚአብሔር በፊቱ ካሉት ሠራዊተ መላእክት እንደ አንዱ ይቆጠረዋልና"

ስለዚህ ከመላእክት ጋር እንቆጠር ዘንድ አብረን ዝም እንበል!

We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 9 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 months ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 3 months, 3 weeks ago