قَناَۃُ اُمُ ذَكَرِيَا اَلْحَبَشِيِّ

Description
◁النساء السلفية اغلى من الذهب الأحمر
Advertising
We recommend to visit

- القناة الرسمية على التيليجرام استمتعو بالمشاهده ? ♥️ .

•┊اقتباسات ? •
•┊رمزيات ?
•┊فيديوهات ?

- @xxzbot // ? بوت تنزيل ستوريات انستا -

- @zzxzz // ? لـ التمويل -

Last updated 1 Jahr, 8 Monate her

- القناة الرسمية على التيليجرام استمتعو بالمشاهده ? ♥️ .

•┊فيديوهات ? •
•┊رمزيات ?
•┊اختصارات ?

- @zezbot // ?بوت زخرفه -

- @zzxzz // ? لـ التمويل -

Last updated 1 Jahr, 8 Monate her

- بوت تحميل من الأنستا ومن جميع مواقع التواصل الإجتماعي: ✅ .

- بوت التحميل من التيك توك: @EEEBOT

- بوت التحميل من الأنستا: @xxzbot

- بوت التحميل من اليوتيوب: @EMEBOT

- ? ? .

- للتمويل: @NNEEN

Last updated 1 Jahr, 8 Monate her

1 year, 1 month ago

ይምረናል በሚል ምኞት ወንጀልን መዳፈር መድሀኒት እንጠቀምበታለን ብሎ በማሰብ መርዝን እንደመጠጣት ነው።

ሸይኽ ሱለይማን ቢን ሰሊሙሏህ አልሩሀይሊይ

t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

1 year, 1 month ago

العلاقة بين الزوج والزوجة مثل العلاقة بين اليد والعين إذا جرحت اليد بكت العين وإذ بكت العين مسحت اليد العين.

በባልና በሚስት መካከል ያለው ግንኙነት እንደ እጅ እና ዓይን ግንኙነት ነው፡ እጅ ከቆሰለ አይን ያለቅሳል!! ዓይን ሲያለቅስ እጅ የዓይንን እንባ ያብሳል!!

https://t.me/deawa_selefiya

1 year, 1 month ago

*ዛሬ ሴት ልጅ ባልየው ከሚያገኛትና ከሚደውልላት በላይ የሚደውልሏት አሉ !!

?በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ* t.me/Darutewhide

1 year, 2 months ago

#አለቆቻችን

? የጀነት እንስቶች አለቃ - ፋጢማ ቢንት  ሙሐመድ
? የጀነት ወጣቶች አለቃ - ሐሰን ኢብኑ ዐሊ ኢብኑ አቡ ጧሊብ
   እና ሑሴን ኢብኑ ዐሊ ኢብኑ አቡ ጧሊብ
? የሰማእታት ሁሉ አለቃ - ሐምዛ ኢብኑ ዐብዱልሙጠሊብ
? የመላኢኮች ሁሉ አለቃ - ጅብሪል አለይሂ ሠላም
? የቃሪኦች/የቁርዓን አንባቢዎች/ አለቃ - ኡበይ ኢብኑ ከዕብ
? የሰው ልጆች ሁሉ አለቃ - ነብዩ ሙሐመድ ስለላሁ አለይሂ ወሠለም

https://t.me/Umu_zekeriyah_al_hebesh

1 year, 2 months ago

*ነሲሀ ለራሴ እና ለእህቶቼ

እህቴ ተመከሪ ሰዎች ወደ ገደል እየገቡ ባለበት ሁኔታ መካሪ ካገኘሽ ተመከሪ

ካልሆነ ግን

ምከረው ምከረው እምቢ ካለ.....  ነው የሚሆነው ነገሩ

እናማ እህቴ ምን ልልሽ ፈልጌ ነው
እኛ ሴቶች ልባችን በትንሽ ነገር ትታለላለች ሰውን (ወንድን) የማመን ባህሪያችንም በጣም የጎላ ነው።
በተለይ በዲን ስም ከመጣ በሚዲያ ተውሂድ ሱና እያለ የሚያወራ ከሆነ በቃ ልባችን ትሸነፋለች ግን መሆን የለበትም።
አዎ ተውሂድን በማሰራጨቱ ልናደንቀው እንችላለን ግና ይህችን ልምዱን ብቻ ይዘን ሙሉዕ ነው ብለን ማሰብን መተው አለብን ይህ የብዙዎቻችን ችግር ነው።
አዎ በዚች ምድር ላይ ሰው ሆኖ ሙሉዕ የሆነ የለም ነብዩ ﷺ ሲቀሩ

እናማ እህቴ በሚዲያ ለጮኸ ሁሉ አትሸንገይ ወሏሂ ወቢላሂ ወተሏሂ የምነግርሽ ነገር ቢኖር አሏህ ካዘነላቸው ውጭ ብዙዎቹ የሚዲያ ጀግኖች ቤታቸው ውስጥ ቁርዓን እንኳን አንስተው የማይቀሩ ባዶ ናቸው።

እየዋሸሁ አይደለም በአይኔ ካየሁት እና ከሰማሁት እንጂ

እህቴ ማንን ማግባት እንዳለብሽ በደንብ ልታስቢበት ይገባሻል ብዙ እየሰማን እና እያየን ነው በሚዲያ ታዋቂ ስለሆነ ብቻ ማንንም ስለሱ ምንም ሳትጠይቅ ሀታ ቢነግሯት እንኳን ምቀኝነት እየመሰላት "ተውኝ እሱ እናንተ እንደምታስቡት እና እንደምትለሉት አይደለም" እያለች ባህሪው ምንድን ነው እንኳን ብላ ሳታጣራ እየገባች መጨረሻዋ ለቅሶ ይሆናል።  ይሄ አያዋጣም መጀመሪያ ነው ማሰብ

አዎ አሏህ የወሰነው በእርግጥ አይቀርም ግን ሰበቡን ማድረስ አለብን በዲኑ ስለተማረክሽ ብቻ "ካላገባሁህ" ብለሽ መቀመጪያ አታሳጪው እሱም ደግሞ "ጠይቃኝ እምቢ ብያት" እያለ እና እየተኮፈሰ ለሌሎች እንዲወራብሽ አትሁኚ

ሲጀመር እህቴ መጠየቅሽ አደብ አይደለም አዎ መረጃ ብለሽ "ኸዲጃ እንዲሁም ሌሎች ሰሀቢቶች ረሱልን ﷺ ጠይቀው የለ እንዴ!? " ልትይኝ ትችያለሽ

አዎ ይህንን አልክድም ግን እኮ እህቴ አስተውለሽ ከሆነ ሰሀቢቶች የጠየቁት ነብይን ከአሏህ ወህየሰ የሚወርድለትን እንጂ ዛሬ አንቺ የጠየቅሽውን የሚዲያ ጀግና አይነት ሰው አልነበረም ነብይን አይደለም ጥቂት ሴቶች ሁሉም ቢጠይቁ አይገርምም ምክንያቱም ነቢይ ስለሆነ ግን ዛሬ አንቺ ያበድሽለትን አይነት ወንድ ውጭ ባህሪውን ሳታውቂ በዲኑ ላይ ያለውን ጥንካሬ (ቤት እና ኢባዳዎች ላይ) ሳታውቂ በሚዲያ ስለጮሀ ብቻ መጠየቅሽ ገርሞ የሚገርም ነገር ነው።

ሀቂቃ እህቴ ስለማዝንልሽ ነው ይህን የምልሽ ይሄ አሳፋሪ ተግባር ነው ለወንዶችም የልብ ልብ መስጠት ነው። እናም ይህን አይነት ባህሪን አትላበሺ ሀያዕ ይኑርሽ አሏህ ላንቺ የፃፈው አለ ማንም አይወስድብሽ አንቺ ግን ሰብር አድርጊ አሏህ ካላለው ስለጠየቅሽውም ላታገቢው ትችያለሽ

እናማ ውዷ እህቴ "ትዳር ጌም አይደለም" እና በደንብ አስቢበት

ማነው?   ባህሪውስ ምንድነው?  ለኔስ ይሆነኛል? እኔ በዲኔ ስዳከም የሚያጠናክረኝ ነው ወይስ?
እነዚህን ጥያቄዎች አስምሪባቸው።

እህት ተመከሪ ያየ እና ያወቀ ይምከርሽ

ለናሙና ያክል ይህን ካልን በቂ ነው ብልጥ ሴት ጥቆማ ይበቃታል!!

➾* https://t.me/deawa_selefiya

1 year, 2 months ago

ሁሉንም እድሎች እንጠቀምበት
      ምክንያቱም አንዳንድ እድሎች
       የሚመጡት አንዴ ብቻ ነው፡፡
           -----❀------

https://t.me/Umu_zekeriyah_al_hebesh

1 year, 2 months ago
1 year, 2 months ago

በየቀኑ አንድ ሀድስ ብንሐፍዝ በወር ሰላሳ ማለት ነው ለዛም እስኪ ከአጫጭር ሀድሶች በመጀመር እንበርታ ይጠቅመናል

1 year, 2 months ago
1 year, 3 months ago

*አስገራሚ ታሪክ ሡበሀንአላህ
ሂጃብ ላስወልቅ ተልኬ ኒቃብ ለብሼ ተመለስኩ! ዶ/ር ሸሪፋ

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ ሳለሁ ነበር የተለየ አጀንዳ ያላቸውን ሰዎች ቡድን ትኩረት ያገኘሁት። በመንግስት ሃላፊነት የሚሰሩ ነገር ግን ልዩ አጀንዳ ያላቸው ሲሆን የእስልምናን እሴት ለማጥፋት የሚሰሩ ግለሰቦች ማህበር ነበር
ምናልባትም አሁንም እንደዛ ናቸው።

እኔ እስከማውቀው መንግሥታዊ ቡድን አይደሉም፣ ነገርግን በአሜሪካ መንግሥት ስልጣን ውስጥ ያላቸውን ቦታ ተጠቅመው ዓላማቸውን ለማራመድ ይጠቀሙበታል።

በሴቶች የመብት ትግል ላይ ተሳትፎ እና ድጋፍ እንዳለኝ ስለሚያውቁ ነበር ወደ እኔ የቀረቡት። በአሜሪካ እና በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ አፅንዖት በመስጠት ሙስሊም ሴቶችን ወደ 21ኛው ክፍለ ዘመን የነጻነት ብርሃን ልመራቸው ከቻልኩ በግብፅ የአሜሪካ ኤምባሲ ስራ እንደማገኝ ዋስትና እንደሚሰጡኝ ነገሩኝ።

ይህ በጣም ጥሩ ሀሳብ ነው ብዬ ተቀበልኩ። ለዚህ አላማ ይረዳኝ ዘንድ ኮሌጅ ገብቼ ትምህርቴን ጀመርኩ ቁርአንን፣ ሀዲስን እና ኢስላማዊ ታሪክን ማጥናት ጀመርኩ ለማጥመድ እና በምንም መንገድ መጠቀም እንደምችል ጠቃሚ መሳሪያ እንደሚሆን ገምቻለሁ

መማር እና ማጥናት ከጀመርኩ በኃላ ግን ነገሮች እየተቀየሩ መጡ በማነባቸው ነገሮች እየተማረኩኝ እና ትርጉም እየሰጡኝ ሄደ፣ መልእክቱ የሚማርክ እና ሎጂካል ትርጉም ነበረው።
ቢሆንም ሙስሊም የመሆን ፍላጎት ግን አላደረብኝም

አባቴ በአሜሪካን መንግስት ትልቅ ስልጣን ኖሮት በጀርመን ሀገር በስራ ላይ ይገኛል። መላው ቤተሰቤ ስለ እስልምና መጥፎ አመለካከት ነው ያላቸው። በመሆኑም እስልምናን መቀበል የማይታሰብ ሆኖ ተሰማኝ።

ለሦስት አመት ምርመራዬን ቀጠልኩ

በአንድ ወቅት ከአንድ ፓኪስታናዊ አዛውንት በክርስትና እምነት ዙሪያ በጣም እውቀት ካለው ግለሰብ ጋር ምሽት ኢሻ ላይ ተገናኝተን በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እና በቁርኣን ዙሪያ ላይ ተወያይተን እስከ ፈጅር ድረስ ተከራከርን።

ንጋት ላይ ይህ ጠቢብ ሰው ማንም ያላደረገውን ጠየቀኝ። ሙስሊም እንድሆን ጋበዘኝ።በሶስት አመታት ውስጥ ፍለጋና ምርምር በቆየሁበት ማንም ሰው አልጠራኝም ተምሬ፣ ተከራክሬ ነበር፣ አልፎ ተርፎም ተሰድቤያለሁ ነገርግን አልተጋበዝኩም።

እናም እኝህ አዛውንት ሲጋብዙኝ የሆነ ነገር ተሰማኝ ጊዜው አሁን እንደሆነ ተረዳሁ እውነት መሆኑን አውቄ ነበር እና ውሳኔ ማድረግ ነበረብኝ። አልሀምዱሊላህ (አላህ ምስጋና ይገባው) አላህ ልቤን ከፈተልኝ እኔም "አዎ ሙስሊም መሆን እፈልጋለሁ በማለት ።

በዚህም ሰውዬው ሸሃዳ (የእምነት ምስክርነት) - በእንግሊዝኛ እና በአረብኛ ተቀበልኩ በአላህ እምላለሁ ሸሃዳውን ስወስድ በጣም የሚገርም ስሜት ተሰማኝ።

አንድ ትልቅ አካላዊ ክብደት ከደረቴ ላይ የተነሳ ያህል ተሰማኝ በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነፈስኩ ያህል ትንፋሼን
ተነፈስኩ። አልሀምዱሊላህ አላህ ለእኔ አዲስ ህይወት ንፁህ ልብ እንዲሁም ለጀነት እድል ሰጠኝ። እኔ ዘመናዊ አሜሪካዊ ሴት ነበርኩ። ሙስሊሟን ሴት ከጨለማ ወደ 21 ኛው ክፍለ ዘመን ብርሃን የማውጣት እቅድ ያላት ሴት ነበርኩ።

ነገርግን በጨለማ ውስጥ የነበርኩ እኔ መሆኔን እና ብርሃንን ማግኘት ያለብኝ እኔ መሆኔን አወቅኩ አልሀምዱሊላህ አላህ በብርሀን እና በመመሪያው ያዘኝ።

ሙስሊም ሴቶችን ለማሳሳት፣ስለሴቶች መብት፣የግል ነፃነት የሂጃብ ጭቆና እና የእስልምና ኋላቀርነት ለማስተማር የቁርዓን እና የሐዲስ ጥናቴ የእስልምና ውብ መልእክት ስረዳና ሳውቅ መዳኛ ሆነልኝ።

ሙሉ ሂጃብ መልበስ ስጀምር ነበር ችግሮች መከሰት የጀመሩት። አባቴ ዜናውን ሲሰማ ወደ ጀርመን በአስቸኳይ እንድበር የአውሮፕላን ትኬት ላከልኝ። አባዬ እውነተኛውን መንገድ ይዣለሁ ከእንግዲህ ምንም የሚቀይረኝ ነገር የለም እናም ወደ ጀርመን መምጣቴ ምንም ፋይዳ የለውም አልኩት

እሱም ትኬቱን ተጠቅመሽ የማትመጪ ከሆነ እኔ ሴት ልጅ የለኝም ነበር መልሱ። ትኬቱን ወርውሬ ላለመሄድ ወሰንኩ።
ለወራት አባቴ እንዲሁም መላው ቤተሰቦቼ ከእኔ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት አቆሙ።

ከቆይታ በኃላ ችግርም ናፍቆትም ያስተምራታል ብሎ በማሰብ አባቴ ደውሎ ልጄ ቅንጡ መኪና ፌራሪ እገዛልሻለሁ ብቻ እስልምናን ተይ፣ ይህንን ሂጃብሽን አውልቂ አለኝ "መኪና እንደምወድ ያውቃል"አባዬ ከፈጣሪ እና ከዕቃ እኮ ነው ምርጫ የሰጠኸኝ አልኩት።

ደስተኛ አልነበረም ዳግም ግንኙነት ተቋረጠ። በትምህርት ቤትም ችግር ነበረብኝ። ሂጃብ ማውለቅ እንዳለብኝ ከፍተኛ ግፊት ተፈጠረብኝ። አንዱ ፕሮፌሰር በግልፅ" ይህንን ፍትሽ ላይ የተሸፋፈንሽውን ጨርቅ ካላወለቅሽ ምንም ብትሰሪ የመጨረሻ ውጤትሽ F ነው ብሎኝ ነበር።

ምንም ይሁን እውነተኛ መሆኑን አምኜ የተቀበልኩት እስልምና በምንም ነገር የምቀይረው አልነበረም።ከዩንቨርስቲ ሳልጨርስ ወጣሁ ፣ ቤተሰቦቼ የሚልኩልኝ ገንዘብም ተቋርጦ ስለነበር እጅጉን ተቸገርኩ።

ስራ ለመቀጠር በምለብሰው ኒቃብ ምክንያት አልቻልኩም፣ ያለችኝን አሮጌ መኪና ሸጬ ለአንድ አመት ለምግብ አደረግኳት። ቸግሮኛል ብዬ ለማንም አልነገርኩም መቸገሬን እንዲያውቁም አላደረግኩም ነበር።ብቻ በአንድ ወቅት ፖስታ ሳጥኔን ስከፍት ረብጣ ብር ተቀምጧል የላኪ ስም የለም የእኔ ስም ብቻ ነው።

ሙስሊም ማህበረሰብ አሰባስቦ የላከልኝ ሊሆን እንደሚችል ገመትኩ፣ አሁንም ድረስ ያ ገንዘብ ከየት እንደተላከልኝ አላውቅም። ብቻ ብዙ ጉዳይ ሸፈነልኝ። ከቤተሰብ ለረጅም ጊዜ ተለያይቻለሁ፣ ምንም አይነት ግንኙነት የለንም፣አባቴ ወደ ደቡብ አሜሪካ ኮስታሪካ ተቀይሮ ስራ ላይ እንደሆነ አውቃለሁ

በአንድ ወቅት የተደራጁ ወንበዴዎች በአባቴ እና በቤተሰቦቹ ላይ ግድያ ሊፈፅሙ ዕቅድ እንዳላቸው መልእክት ለአባቴ አደረሱ። ቤተሰቦቼ በአሜሪካ መንግስት ጥበቃ ታዘዘላቸው በዚህ ሰአት አባቴ ደወለልኝ፣ ልጄ ጠልቼሽ አይደለም፣ ክፉሽን ተመኝቼ አይደለም፣ ስትቸገሪ፣ ሲርብሽ ሃሳብሽን ቀይረሽ ሂጃብሽን አውልቀሽ ትመጫለሽ ብዬ አስቤ ነበር፣ ሁሌም አስብሻለሁ፣ ስፀልይልሽ ኖሬያለሁ፣ አንቺም የቤተሰብ አካል ነሽ፣

ወንበዴዎች አንቺ ላይም ጥቃት ሊፈፅሙ ይችላሉ እናም እንደ ተሸፋፈንሽ እምነትሽን እንደያዝሽ ወደ ቤትሽ ተመለሽ በማለት በልዩ አውሮፕላን እቤቴ ተመለስኩኝ። ነገሮች ሁሉ ተስተካከሉ
ትምህርቴንም በዶክትሬት አጠናቀቅኩ።

ሴትነት በዋጋ የማይተመን ተፈጥሮዬ ሲሆን፣ሊጠበቅ ሊከበር ሊነሳም የሚገባው እንጂ ሚዋረድ ወይም የሚሸጥ አይደለም
እኔ አሁን ኩሩ ሙስሊም ሴት ነኝ፡ አስተማሪ፣ ተማሪ፣ ተከታይ፣ እና የእስልምና አፍቃሪ። አልሀምዱሊላህ!*https://t.me/Umu_zekeriyah_al_hebesh

Telegram

قَناَۃُ اُمُ ذَكَرِيَا اَلْحَبَشِيِّ

◁النساء السلفية اغلى من الذهب الأحمر

*አስገራሚ ታሪክ ሡበሀንአላህ
We recommend to visit

- القناة الرسمية على التيليجرام استمتعو بالمشاهده ? ♥️ .

•┊اقتباسات ? •
•┊رمزيات ?
•┊فيديوهات ?

- @xxzbot // ? بوت تنزيل ستوريات انستا -

- @zzxzz // ? لـ التمويل -

Last updated 1 Jahr, 8 Monate her

- القناة الرسمية على التيليجرام استمتعو بالمشاهده ? ♥️ .

•┊فيديوهات ? •
•┊رمزيات ?
•┊اختصارات ?

- @zezbot // ?بوت زخرفه -

- @zzxzz // ? لـ التمويل -

Last updated 1 Jahr, 8 Monate her

- بوت تحميل من الأنستا ومن جميع مواقع التواصل الإجتماعي: ✅ .

- بوت التحميل من التيك توك: @EEEBOT

- بوت التحميل من الأنستا: @xxzbot

- بوت التحميل من اليوتيوب: @EMEBOT

- ? ? .

- للتمويل: @NNEEN

Last updated 1 Jahr, 8 Monate her