Reslan Ibnu Neja(asselefy)

Description
እቺን ኡማ ምንም ነገር አያስተካክላትም የመጀመሪያዎቹን ያስተካከላቸው ነገር ቢሆን እንጂ (እነሱ ያስተካከላቸው ቁርአን ሀዲስን 'አልላህ ባዘዘበት ና መልእክተኛው ባስተማሩበት ተረድተው ስለተገበሩ ነው) ስለዚህ እኛ እንስተካከል ዘንድ ቁርአን ሀዲስን አልላህ ባዘዘበት መልእክተኛው ባስተማሩበት (ሰለፉነ ሷሊሆች) መልካም ቀደምቶች ተረድተው በተገበሩበት ተረድተው መተግበር ነው::አልላህ ያግራልን
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

hace 3 semanas, 5 días

🔷  ሰበር የምስራች

በኡሑዱ የጉንችሬ ማዞሪያ ዑመር መስጂድ ፕሮግራም ላይ ወንድማችን ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ ( አቡ ሐመዊያ ) የሚገኝ መሆኑን ስናስታውቃችሁ በደስታ ነው ። በመሆኑም በፕሮግራሙ ላይ የሚገኙ እንግዶቻችን
1– ሸይኽ ዐ/ሐሚድ
2 – ኡስታዝ ሸምሱ ጉልታ ( አቡ ሐመዊያ)
3 – ወንድማችሁ ባሕሩ ተካ ይሆናሉ ።

https://t.me/bahruteka

hace 4 semanas
***🔹*** **ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት

🔹 ታላቅ የሙሃዶራ ዝግጅት
በዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

በአላህ ፈቃድ የፊታችን እሁድ ታህሳስ 6/2017 በአይነቱ ልዩ የሆነ የሙሃዶራ ዝግጅት ተሰናድቷል

🕰 ሰዓት:- ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:30 (በጊዜ ይገኙ)

ተጋባዥ እንግዶች:-
ሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
ኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን (ሀፊዘሁላህ)
ኡስታዝ ሻኪር ሱልጧን (ሀፊዘሁላህ)
በተለያየ ርእስ ይቀርባል

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል

አድራሻ:- አዲስ አበባ ኮ/ቀ ክ/ከተማ አለምባንክ ከኦርዶፎ ህንፃ ፊት ለፊት ባለው ቂያስ ወደ ቤተል በሚወስደው ኮብልስቶን መንገድ ከድልዲዩ በስተ ቀኝ ባለው ቂያስ እንገኛለን።
ለተጨማሪ መረጃ:- +251920908031

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://t.me/DarASSunnah1444
https://t.me/DarASSunnah1444

hace 4 semanas
***👉*** ወንድማዊ ምክር ለእህቶችና ወንድሞች

👉 ወንድማዊ ምክር ለእህቶችና ወንድሞች

መለኮታዊ የህይወት መመሪያን መሰረት ያደረገው ኢስላም ለሴት ልጅ ያጎናፀፈውን ክብርና የሰጣት ቦታ የሚታወቅ ነው ። ሴት ልጅ በኢስላም የተከበረች የእናት ፣ የልጅ ፣ የእህትና ሚስትነት ቦታ የያዘች የህብረተ ሰብ አካል ነች ። ይህ ክብሯ ተጠብቆ የሚቆየው አላህ ባዘዛት ቦታ ስትገኝና ከከለከላት ቦታ ስትርቅ ነው ። ከተከለከለችው ነገር ውስጥ አንዱ ከባዳ ወንድ ጋር መቀላቀልን ነው ።
በተቃራኒው ሴት ልጅ ቤቷ ላይ መሆን እንዳለባትና የመሀይማን አይነት መገላለጥ እንዳትገላለጥ አዟል ። የመሀይማን አይነት መገላለጥ የሚለውን ከፊል የኢስላም ሊቃውንቶች ጎዳና ላይ ወጥቶ ከባዳ ወንዶች ጋር መደባለቅ ብለው ፈስረውታል ። ከእነዚህ ውስጥ ታላቁ ታቢዕይ ሙጃሂድ ይገኝበታል ።
ይህ ክልክል የሆነው መቀላቀል በተለያየ መንገድ ሊሆን ይችላል ። ከእነዚህ ውስጥ በተለያዩ አንድ ወንድና ሴት ተለይተው ሊገናኙ በሚችሉባቸው ግሩፖች ላይ መቀላቀል ይገኝበታል ። የዘመናችን ትላልቅ የሱና ዑለሞች ሴቶች ለብቻቸው ግሩፕ መክፈት እንዳለባቸውና ከወንድ ጋር እንዳይቀላቀሉ ይከለክላሉ ። ምናልባት ግዴታ መቀላቀል ካስፈለገ ሴት መሆኗ በማያስታውቅ ስም ትቀላቀል ሀሳብ ስትሰጥም በዛው መልኩ ይሁን ይላሉ ። ይህ ሁሉ የፊትና በሮችን ለመዝጋት ነው ። ምክንያቱም ኢስላም አንድን ነገር እርም ሲያደርግ ወደዛ የሚያዳርሱ መንገዶችንም እርም ያደርጋል ( ይዘጋል) ። ዝሙትን እርም ሲያደርግ ወደዛ የሚያደርሱ መንገዶችንም እርም አደረገ ።
ሴት ሸሪዓዊ እውቀት ካላት ለሴቶች ማስተማር ትችላለች ምናልባት ወንዶች ዘንድ የማይገኝ እውቀት ካላት ሸሪዓ ባስቀመጠው መስፈርት ወንዶችን ማስተማር ትችላለች ። ነገር ግን አሁን እያየነው ያለው አይነት ኡሙ እገሌ እያለች ግሩፕ ወይም ቻናል ከፍታ እየፃፈች ወንዶች በተለያየ ቻናልና ግሩፕ ሼር ማድረጋቸው ፊትናን ለማስፋፋት እንደመተባበር ይቆጠራልና ከዚህ ተግባር እህቶችም ወንድሞችም ሊቆጠቡ ይገባል ። እንዲህ አይነት አደባባይ መውጣት በፍፁም ከሰለፍይ እህት የሚጠበቅ አይደለም ። ምክንያቱም እሙ እገሌ ማን ነች ስሟ ማን ነው ስልኳን እንዴት ማግኘት እችላለሁ የሚሉ የፊትና በሮችን ይከፍታል ።
ፈተና ይርቁታል እንጂ አያቀርቡትም ስለዚህ እንዲህ አይነት ተግባር ውስጥ የገባችሁ እህቶችና ሼር የምታደርጉ ወንድሞች ከዚህ ተግባራችሁ ተቆጠቡ እላለሁ ።
ለስሜታችን የሚከብድ ሊሆን ስለሚችል ጉዳዩን ወደ ዑለሞች ማድረስና መጠየቅ ጥሩ ነው ።
አላህ ሐቅን አውቀው ከሚሰሩበትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ባሮቹ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka

hace 4 semanas, 1 día

ወሳኝ ሙሃዶራህ
ርዕስ :- በሙስሊሞች መካከል ያለውን ኺላፍ መደበቅ!

በሸይኻችን አቡዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ ሀፊዘኹምሏህ

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha

https://t.me/UstazAbuzarhassenAbutolha

hace 4 semanas, 1 día
***✅*** ሰለፍዮች በትግላችሁ ቀጥሉ

ሰለፍዮች በትግላችሁ ቀጥሉ

የአላህ መሺኣ ነውና የሐቅና ባጢል ግብግብ እስከ ቂያማ ይቀጥላል ። በዚህም እውነተኛች በጫፍ ላይ ካሉት ይለያሉ ። ነገሮች ሲመቻቹ ሁሉም አማኝ ነው ሁሉም ሱና ወዳጅ ነው ነገር ግን በፈተና ጊዜ ነው እንክርዳዱ ከፍሬው የሚለየው ። የተወሰኑ የአላህ ባሮች እሳት ውስጥ ገብቶ እንደ ወጣ ወርቅ የዲኑ ጌጥ ሲሆኑ አብዛኞች ጎርፍ ያመጣው አረፋ ሆነው ዳር ይቀራሉ ።
የአላህ መልእክተኛ ፈተናን አስመልክተው ሲናገሩ ከኋላ የሚመጣው የፊተኛውን ቀላል ያደርገዋል ብለውናል ። አሁን እያየን ያለነው ይሄው ነው ። ድሮ የኢኽዋን አንጃ በነ ሓሚድ ሙሳ አማካይነት ወደ ሀገራችን ሳይገባ በፊት ሁሉም ወደ ተውሒድና ሱና ሲጣራ ሱፍዮች ካጠቃላይ የተውሒድ ሰዎች ጋር ነበር ትግላቸው ።
የሱናው ወጣት በኢኽዋን አስተሳሰብ መጠለፍ ሲጀምር ሰለፍይና ኢኽዋንይ ተብሎ ተከፈለ ። ሰለፍዮች ከሱፍይና ኢኽዋን ጋር ትግል ጀመሩ ። ብዙም ሳይቆይ ኢኽዋኖች ከሱፍዮች ጋር ተደመሩ በጋራ ሰለፍያን ለመጣል መስራት ጀመሩ ። ሰለፍዮች በጋራ የተከፈተባቸውን ትግል ተቋቁመው ወጣቱን ለማዳን የሞት ሽረት ትግል አደረጉ ። ተሳክቶላቸው የጥምር ሀይሉን መቋቋም ቻሉ ።
በዚህ ሁኔታ እያሉ የአሕባሽ አስተሳሰብ መጥቶ መጅሊሱን ተቆጣጥሮ የአወሊያ ተማሪዮችን ሲያባርር ኢኽዋኖች አጋጣሚውን ተጠቅመው መድረኩን ይዘው ከጫፍ እስከ ጫፍ ፀረ አሕባሽ ንቅናቄ አካሄዱ ።
ከአሽባሽ ጋር የነበረው ፀብ የስልጣን እንጂ የዐቂዳ አልነበረም ። ለዚህ ማስረጃው ኢኽዋን ያደርገው በነበረው ሀገራዊ ሰልፍ መፈክሩ " አሽ ሻዕብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ " ( ህዝቡ መጅሊስን መጣል ይፈልጋል ) የሚል የነበረ መሆኑ ነው ። በዚህ ንቅናቄ ኢኽዋን ካገኘው ያልጠበቀው ትርፍ አብዛኛው ሱና ሲደግፍ የነበረው ወጣትና ባለሀብት ወደ ትግሉ መቀላቀሉና የሰለፍያን ዳዕዋ ሲመራ የነበረውን ናጂያን መኮነኑ ነበር ። ጊዜው አብዛኛዎች የናጂያ ዱዓቶች አገር ጥለው የተሰደዱበት ወቅት ነበርና ይህ ሁኔታ ዋና ዋና የናጂያ መሪዮች አቋማቸውን እነዲቀይሩ አደረጋቸው ።
የሰለፍያው ዳዕዋ በተለያዩ መሻኢኾችና ዱዓቶች አማካይነት ትግል እያደረገ የነበር ሲሆን በሚዲያው ላይ በነኢብሙነወርና ሳዳት አማካይነት ዳዕዋው መነቃቃት ጀመሮ ከፍተኛ ትግል ይደረግ ነበር ።
በዚህ ጊዜ ትግሉ በዋነኝነት ወደ ኢብኑ መስዑድ ከተዘዋወረው ናጂያ አመራሮች ጋር ነበር ። በዚህም የሰለፍያው ዳዕዋ ትግል ከኢኽዋኖችና ኢብኑ መስዑዶች ጋር ሆነ ። ትግሉ ቀጥሎ የሰለፍያው ዳዕዋ ወጣቱን መልሶ መቆጣጠርና ከተቃራኒዮቹ መዳፍ አብዛኛውን ማውጣት ቻለ ።
ይህ በንዲህ እያለ ስርአቱ ከኢሀዲግ ወደ ብልፅግና ሲሸጋገር የመደመር ስሌት አሕባሽን ፣ ሱፍይን ፣ ኢኽዋንና ወደ ነሲሓ የተዛወረው ኢብኑ መስዑድ ተቋም አመራሮች አንድ ሆነው ወደ መጅሊስ መጡ ። ይህን የድምር ውጤት ያዩት እነኢብኑ ሙነወር መደመሩ ነው የሚያዋጣው ብለው የጥምሩ የእንጀራ ልጆች ሆኑ ። ባለውለታ ለመሆንም ሰለፍዮችን ባለ በሌለ ሀይላቸው መዋጋት ጀመሩ ። እነ ኢብኑ ሙነወር በእስክሪብቶ የጥምሩ መጅሊስ አመራሮች በመሳሪያ አፈሙዝ የሰለፍያ ዳዕዋ መዋጋት ጀመሩ ።
የጥምሩ መጅሊስ አመራሮች ሰለፍዮችን ከዳዕዋው ሜዳ ለማስወጣት መስጂዶችን መረከብ የመጀመሪያው ተግባር አድርገው ያዙት ። ይህ አካሄድ የሰለፍዮችንም መስጂዶች ጭምር መረከብን ያካተተ ነው ። ለዚህ ደግሞ በሰለፍዮች መስጂዶች ላይ ሁከትና ረብሻ በመፍጠር ሰለፍዮች የፈጠሩት በማስመሰል ለጅምላ እስር መንገድ ይከፍታል ብለው ነው ። በአሁኑ ሰአት በስራ ላይ ያዋሉት በስልጤ ዞን ላይ ሲሆን እንደሞመከሪያ ነው እየሰሩት ያሉት ። ሰለፍዮች መርሳት የሌለባቸው ኢብኑ ሙነወር ላይደርሱላችሁ መስጂዳችሁን ያሰነጥቁዋችኋል ማለቱን ነው ። ይህ ማለት እስትራቴጂውን ያውቀው ነበርና ለመጅሊስ እጅ ስጡ ነበር መልእክቱ ።
ማስገንዘቢያ ለሰለፍዮች :–
ሰለፍዮች ይህን እስትራቴጂ ማስቆም የምትችሉት በዳዕዋ ላይ በመፅናት ነው ። የተዘጋጀላችሁን ወጥመድ ተጠንቀቁ በፍፁም ስሜታዊ እንዳትሆኑ ። ከመስጂድ ቢያስወጡዋችሁ ጊቢ ውስጥ ዳዕዋ አድርጉ, ልጆቻችሁን እቤትችሁ አስተምሩ, አንዱ ዳዒ ሲታሰር ሌላው ይቀጥል ፍፁም ዳዕዋ እንዳታቆሙ, እነርሱ ይሰሩ እናንተ ዳዕዋችሁን ቀጥሉ, ሀይለቃልም ከመጠቀም ተቆጠቡ አብዛኛው ማህበረሰብ እናንተ ዲን ለማጥፋት የመጣችሁ ተደርጎ ስለተሳለለት እዘኑለት ። ትግላችሁ አፈር የለበሰውን ሐቅ አፈሩን ጠርጋችሁ ለማሳየት መሆን አለበት ።
ከአላህ ጋር እውነተኛ ሁኑ አላህ እውነተኞች ይረዳልና አብሽሩ ። ፅናት የትግል ድልድይ ናት ። ትግሉን ለመሻገር ፅኑ ። ለዚህ በሶብር ፣ በኢኽላስና ዱዓእ ታገዙ ። የነብዩ ሱና መርከብ ነውና ከሱ እንዳትወርዱ በቢዳዓ ባሕር እንዳትሰጥሙ ተጠንቀቁ ። ሌላው በፍፁም ዳዕዋ ላናደርግ ብላችሁ እንዳትፈርሙ ያለ ፈቃድ ለሚሉዋችሁ የህገመንግስቱ ፈቃድ በቂያችን ነው በመጅሊስ ደብዳቤ ከተሻረና ዳዕዋ ማድረግ ወንጀል ከሆነ ቅጣቱን ለመቀበል ዝግጁ ነን በሉ ። በሱና መርከብ ላይ ለመሳፈር ቆራጥ መሆን ያስፈልጋል ቆራጥ ያልሆናችሁ አላህ ፊት እንዳታፍሩ ፀንታችሁ ታገሉ ።
አላህ ተውሒድና ሱናን የበላይ ለማድረግ ሰበብ ያድርገን ።

https://t.me/bahruteka

hace 1 mes
***👉*** ራቁት ሆኖ ከመዝፈን በአላህ ላይ …

👉 ራቁት ሆኖ ከመዝፈን በአላህ ላይ ማጋራት ይበልጣል !

ወንጀል በየትኛውም ሀገር በማንም ቢሰራ ወንጀል ነው ። የሆነ ሀገር ስለተሰራ ከወንጀልነት አያወጣውም ። ሪያድ ላይ በሆነ ፕሮግራም ላይ የነበረ አሳዛኝና አስቀያሜ ተግባር ሶሞኑን ሰዎች ሲያወሩ ሰምቼ ምንድነው ብዬ ለማየት ሞከርኩ ። ድርጊቱ በጣም ፀያፍና አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ነው ። የካዕባ ምስል ተሰርቷል ለብሰዋል ለማለት የማያስደፍር ዘፋኝ ሴቶች በምእራባዊያን አኳኋል ያብዳሉ ። የዚህ አይነቱ ተግባር ፍፁም ከኢስላም አስተምሮ የራቀ አስቀያሚ ተግባር ነው ። ይህን ክስተት በተለይ የግብፅና የፍልጢን አክቲቪስቶችና ጋዜጠኞች የሳውዲን መሪዮች ለማክፈርና ለመርገም ምቹ አጋጣሚ ሆኖላቸው አየሁ ።
በጣም የሚገርመው አንድ የእናቱን ፊት የተዋሰ የሚመስል የግብፅ ጋዜጠኛ ከሱረቱል ق የተወሰኑ አንቀፆችን ቀርቶ አላህ ፊት የቂያማ ቀን ስለመቆምና ስለሚኖረው ጭንቅ ከተናገረ በኋላ ለሳውዲ መሪዮች ጥያቄ ያቀርባል ። ሱብሓነላህ እንዴት የሚገርም ለዲን መቆርቆር ነው በጣም ደስ ይላል ። በዚህ መልኩ ወንጀልን መፀየፍና ማውገዝ ከኢስላም መርሆች ውስጥ ዋነኛው ነው ።
ነገር ግን እኔ ለእነዚህ አካላት ጥያቄ አለኝ እነዚህ ወንጀሎች ሳውዲ ውስጥ ሲሰሩ ነው በዚህ መልኩ የምትቆረቆሩትና የምታወግዙት ወይስ ሀገራችሁም ላይ ? ለመሆኑ ከአላህ ውጪ ላለ አካል ለአላህ እንጂ የማይገቡ የአምልኮ አይነቶችን መስጠት አሁን እያወገዛችሁት ካለው ወንጀል እንደሚበልጥ ታውቃላችሁን ? በግብፅ ምድር ላይ የአሕመደል በደዊ ቀብር ከ3 · 5 ሚሊየን ህዝብ በላይ ጠዋፋ ሲያደርግበት ፣ የቀብሩን አፈር በጥብጦ ሲጠጣ ፣ ከአላህ እንጂ የማይጠየቁ እንደ ከጭንቅ አውጡኝ ፣ አፍያ ስጡኝ ፣ ርዝቄን አስፉልኝ ፣ ዘር ስጡኝ ፣ እና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ለአሕመደል በደዊና ለዱሱቂ ፣ ለዘይነብና ለመሳሰሉ ሙታኖች ሲጠይቁ የት ነበራችሁ? የዚህ አይነቱ የቀብር አምልኮ መንግስታችሁ ባጀት መድቦ ሰራዊት አሰልፎ እንደባአል እንዲከበር ሲያደርግ ታወግዛላችሁ ? ወይስ ይህ በናንተ ሀገር ሲሰራ ወንጀል አይደለም ? ቤቱ በመስታወት የሆነ ሰው በሰው ቤት ላይ ድንጋይ አይወረውርምና ተረጋጉ እንላለን ።
ሳውዲ ላይ የሚሰራ የትኛውም ወንጀል ከወንጀልነት ሊወጣ አይችልም ። በወንጀልነቱ ይወገዛል ። ነገር ግን መሪዮችን ለማክፈር መንገድ አድርጎ መጠቀም የኸዋሪጆች አካሄድ ነውና ተጠንቀቁ ነው የሚባለው ። የሳውዲ መሪዮች ደማቸው አረንጓዴ ነው አይነኩም ለማለት አይደለም ። ከመሪዮች የሚሰራ ስህተት የሚታረምበት መንገድ መልእክተኛው ነግረውናል ። ሰለፎችም ተግብረው አሳይተውናል ። የመሪዮችን ስህተት በኹጥባ ፣ በሙሓደራ ፣ በጋዜጣ ፣ በመፅሄት ፣ በተለያዩ ሚዲያዎች ማሰራጨት የነብዩና የሶሓቦች መንገድ የሚከተሉ ሰዎች አካሄድ አይደለም ።
መጥፎን ነገር ስንለካ በሸሪዓ መለኪያ እንጂ በስሜታችን መሆን የለበትም ። የወንጀሎችን ክብደትና ቅለትም እንደዚሁ ይህን መሰረት አድርገን ነው ሁሉንም በልኩ ማውገዝ ያለብን ። ሳውዲ በሽርክ ጉዳይ አንገት እየቀላች ድግምተኞችንና መተተኞችን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣች ከተለያየ ሀገር መውሊድ ለማክበር የተሰበሰቡ ሱፍዮችን እየበተነችና አሰተባባዮችን በቁጥጥር ስር እያዋለች ማየት ያልቻሉት ወይም አይተው አላየንም የሚሉት በሀገራቸው ላይ ከሚሰራው አመፅና ወንጀል ሊወዳደር የማይችል ወንጀል ሳውዲ ላይ ሲሆን መሪዮች ለማክፈር መንገድ አድርጎ መጠቀም በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ።
መሪዮች ሲያጠፉ በግል ይመከራሉ ዱዓእ ይደረግላቸዋል ። እንጂ በአደባባይ ከበሮ አይደለቅም ። ምክንያቱም የዚህ አይነቱ ተቃውሞ መሪዮቹ አፀፌታውን እንወስዳለን ብለው የበለጠ ጥፋት ሊመጣ ስለሚችልና መሪና ተመሪ መካከል ያለው መተማመን ጠፍቶ ሀገር ስለሚበጠበጥ ነው ። ከላይ ለመግለፅ እንደሞከርኩት ወንጀል ማንም የትም ቢሰራው ወንጀል ነው ይጠላል ይወገዛል ። ነገር ግን የሚወገዝበት መንገድ ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ መሆን አለበት ነው ትልቁ ነጥብ ።
በአሁኑ ጊዜ ሰዎች የሆነ ሰው ነፍሰጡር ሴትን ገደለ ፣ እናቱን ተገናኘ ፣ ከእህቱ ወለደ ፣ አስገድዶ ደፈረ ፣ ህፃን አረደ ሲባል ቢሰሙ ይሰቀጥጣቸዋል ይዘገንናቸዋል በጣም ያወግዙታል እንደ ጭራቅ ያዩታል ። ይህ ባልከፋ ነበር ። ከባድ ወንጀል ስለሆነ ሊወገዝ ይገባልና ነገር ግን እገሌ የሚባል ሰው የቀብር አፈር በጥብጦ ጠጣ ፣ ቀብር ጋር ሄዶ ጫማውን አውልቆ ስልኩን ዘግቶ እያለቀሰ የሞተውን ሰው እርዱኝ ድረሱልኝ አለ ፣ ሌላኛው ለጂኒ አርዶ ደሙን ጠጣ ፣ ሌላኛው ልጅ ፍለጋ ጠንቋይ ቤት ሄደ ቢባሉ ምንም አይመስላቸውም ። ይህ ሊስተካከል ይገባል ሙስሊሞች በሽርክና በቀባባድ ወንጀሎች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲያውቁ ማስተማር ያስፈልጋል ።
አላህ በሱ ላይ ማጋራትን በፍፁም አልምርም ሲል ከሽርክ ውጪ ያሉ ወንጀሎችን ለሻው ሰው እንደሚምር ነግሮናል ። ሽርክ ስራን በሙሉ አበላሽቶ የዘላለማዊ ጀሀነም ባለቤት ሲያደርግ ከባባድ ወንጀሎች ግን አላህ ለሻው ሰው የሚምር ሲሆን ከቀጣውም በወንጀሉ ልክ ተቀጥቶ ከእሳት እንደሚወጣና የጀነት እንደሚሆን ኢስላም ያረጋግጣል ።
ታዲያ ግብፅ ውስጥ ያለው የቀብሮች አምልኮ ሳውዲ ውስጥ ከተሰራው የሴቶች ተራቁቶ መዝፈን ጋር ሲነፃፀር የሰማይና የምድር ያክል ልዩነት አለው ። ነገር ግን ሁሉም ወንጀሎች በመሆናቸው ይወገዛሉ ይሁን እንጂ አይገናኙም ።

https://t.me/bahruteka

hace 1 mes
[***1⃣******9⃣******6⃣***ኩን ሰለፊያ ዓላል ጀዳህ](https://t.me/Mehabetu_aselefyah/11802) [በሸይኽ ዓብዱልሓሚድ …

1⃣9⃣6⃣ኩን ሰለፊያ ዓላል ጀዳህ በሸይኽ ዓብዱልሓሚድ አል-ለተሚይ ሀፊዘሁ አሏህ
1⃣9⃣7⃣አል አጅዊበቱል ሙፊዳህ በሸይኽ ዓብዱልሓሚድ አል-ለተሚይ ሀፊዘሁ አሏህ
1⃣9⃣8⃣ሱለመል ዉሱል ኢላ ዒልሚል ኡሱልበሸይኽ ዓብዱልሓሚድ አል-ለተሚይ ሀፊዘሁ አሏህ
1⃣9⃣9⃣አል ዑቡዲያ ኪታብ በሸይኽ ዓብዱልሓሚድ አል-ለተሚይ ሀፊዘሁ አሏህ2⃣0⃣0⃣መንሃጅ ፊርቀቱል ናጂያህ በሸይኽ ዓብዱልሓሚድ አል-ለተሚይ ሀፊዘሁ አሏህ
2⃣0⃣1⃣ሻርሑ ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ ዑሠይሚን በሸይኽ ዓብዱልሓሚድ አል-ለተሚይ ሀፊዘሁ አሏህ
2⃣0⃣2⃣ሸርሁ ኡሱሉ ሰላሳ አል ኡሰይሚን
በታላቁ ዓሊም ሸይኽ አብዱልሓሚድ አል ለተሚይ ሀፊዘሁ አሏህ

2⃣0⃣3⃣አል ፊቅሁል ሙየሰር በታላቁ ዓሊም ሸይኽ አብዱልሓሚድ አል ለተሚይ ሀፊዘሁ አሏህ
2⃣0⃣4⃣የ "ጂናየቱ ተመዩዕ" (የመለዘብ ጥሰት በወንድም አቡ ዘከሪያ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ ሀፊዘሁ አሏህ
2⃣0⃣5⃣የአል_ሀቁል አውከድ ትንታኔና ማብራሪያበኡስታዝ አቡ ኡበይዳ አብራር አወል ሀፊዘሁ አሏህ
2⃣0⃣6⃣በይቁኒየህ በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

hace 1 mes
***♻️*** «وقد كان السلف يحبون من …

♻️ «وقد كان السلف يحبون من ينبههم على عيوبهم
ونحن الآن في الغالب أبغض الناس إلينا من يعرفنا عيوبنا !

ሰለፎች በስህተታቸው (በነውራቸው) ላይ የሚያነቃቸውን የሚነግራቸውን ሰው ይወዱ ነበር!!
- እኛ ግን አሁን ከሰዎች ሁሉ ጠላታችን ነውራችንን የሚያሳውቀን ሰው ነው!!

ምንጭ
📚( منهاج القاصدين (196

hace 1 mes
**የተጠናቀቀ ደርስ**

የተጠናቀቀ ደርስ

የመንዙመቱ'ል በይቁኒየህ ማብራሪያ
شرح منظومة البيقونية

🎙በሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)

የግጥሟ pdf ⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/7936

ከመግቢያ እስከ ክፍል 20 የመጨረሻ ክፍል

ሙሉ 👇👇የድምፅ ፋይል
መግቢያ ⤵️
https://t.me/DarASSunnah1444/8922
ክፍል 1
https://t.me/DarASSunnah1444/8923
ክፍል 2
https://t.me/DarASSunnah1444/8924
ክፍል 3
https://t.me/DarASSunnah1444/8925
ክፍል 4
https://t.me/DarASSunnah1444/8926
ክፍል 5
https://t.me/DarASSunnah1444/8927
ክፍል 6
https://t.me/DarASSunnah1444/8928
ክፍል 7
https://t.me/DarASSunnah1444/8929
ክፍል 8
https://t.me/DarASSunnah1444/8930
ክፍል 9
https://t.me/DarASSunnah1444/8931
ክፍል 10
https://t.me/DarASSunnah1444/8932
ክፍል 11
https://t.me/DarASSunnah1444/8933
ክፍል 12
https://t.me/DarASSunnah1444/8934
ክፍል 13
https://t.me/DarASSunnah1444/8935
ክፍል 14
https://t.me/DarASSunnah1444/8936
ክፍል 15
https://t.me/DarASSunnah1444/8937
ክፍል 16
https://t.me/DarASSunnah1444/8938
ክፍል 17
https://t.me/DarASSunnah1444/8939
ክፍል 18
https://t.me/DarASSunnah1444/8940
ክፍል 19
https://t.me/DarASSunnah1444/8941
ክፍል 20
https://t.me/DarASSunnah1444/8942

hace 1 mes
***🔹*** ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም

🔹  ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም

የፊታችን እሁድ ታሕሳስ 6/2017 በእነሞር ወረዳ ጉንችሬ ክ/ከተማ ጉንችሬ ማዞሪያ ዑመር መስጂድ ላይ ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኃል ።
    ተጋባዥ እንግዶች
1ኛ – ሸይኽ ዐ/ሐሚድ
2ኛ – ወንድማችሁ ባሕሩ ተካ
3ኛ – ኡስታዝ ሱደይስ

ፕሮግራሙ የሚጀመረው አላህ ካለ ጠዋት 2 : 30 ይሆናል ።

https://t.me/bahruteka

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago