እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo Media

Description
እሔ የቴሌግራም መንፈሳዊ ቻናላችን ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀይማኖታችን ምንማማርበት መንፈሳዊ መድረክ ነው። ለሌሎች ያጋሩ፣ አዳዲሶችም ተቀላቀሉ(join) አድርጉ።
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

3 Wochen, 2 Tage her
እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo …
3 Wochen, 2 Tage her
እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo …
3 Wochen, 2 Tage her
እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo …
1 Monat her
"በፊት ታጣቂዎች ፣ አሁን ደግሞ እራሱ …

"በፊት ታጣቂዎች ፣ አሁን ደግሞ እራሱ መንግሥት እየገደለን ነው!" ነዋሪዎች! #ከደራ_እስከ_ ሽርካ! #የማያባራው_የቁማር_ፖለቲካ_ሰለባዎች! #ልዩ_ዘገባ https://youtu.be/GvGeI1MX8rw?si=91cE80Fb5xnkr5ua

1 Monat her
የኤርትራ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ …

የኤርትራ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ብጹዕ አቡነ ባስልዮስ ቀዳማዊን ስድስተኛው የቤተክርስቲያኒቱ ቅዱስ ፓትርያሪክ አድርጎ መረጠ !!!

ብጹዕነታቸው የሰሜን ቀይ ባሕር አካባቢ ሐገረ ስብከት ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙ ነበሩ ::ሲመተ ፕትርክናቸው የአኃት አብያተክርስቲያናት ተወካዮችና የቤተክርስቲያኗ ሊቃውንት በተገኙበት በአስመራ ርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ጥር 18 / 2017 ዓ.ም የሚፈጸም ይሆናል::

1 Monat her

"ሁልጊዜ መሞገሥ የክርስቶስ መስቀልን ያስረሳል
ብዙ ጊዜ የተገኘ መሞገሥ ትምክህትን እንጂ ስጋትን አያሳይም።
እኛንም የገጠመን ይሄ ነው።
ተሞጋሽ ጳጳሳት፣ተሞጋሽ፣ሊቃውንት፣ተሞጋሽ ካህናት፣ተሞጋሽ ማኅበራት፣ተሞጋሽ ሰባክያን ...ስለሆነ ያሉን መወቀስን እና ተዋርዶ መሥራትን አንወዳትም።
ተሞጋሽ ሰው ስሜቱን እየተከተለ እንጂ ስሜቱን እየቀደመ በዓላማ መሄድ ይከብደዋል።
ባዶ ሙገሳ ብቻ በጎ እና ትሁት አገልጋይ መንፈስን ከሀገራችን ከደብራችን ያጠፋል።
በትሁት ልቡና በዓላማ ለሚያገለግል ሰውም ተሞጋሾች የፊት አጥሮች ወይም የኋላ ገመዶች ይሆኑበታል።
በዚህ ሁኔታ በወንጌል ስም የሚፈጸም ወንጀል፣በጽድቅ ስም የሚፈጸም ክፋት፣ በርህራሄ ስም የሚሠራ ጭካኔ፣...ቤተ ክርስቲያንን ምን ያህል እንደጎዳት ማወቅ አይከብድም።
ሙገሻና ምስጋና ተሸክሞ በትክክል መራመድ ለማይችል ሰው እርግማን ይሻለዋል።ወይም በዱላ መደብደብ ይሻለዋል።
በዚህ የሙገሳ መንገድ የዓውደ ምህረት ጩልሌዎች በሙገሳ ብዛት አንድ ቀን ምእመኑን ገነት የሚያስገቡት ይመስላሉ።
በዚህ ምክንያት ሕዝበ ክርስቲያኑም የመከራ አገልጋይ ሁኖ ሊኖር የተፈጠረ ይመስል በተሞጋሾች ህልውናው ተረሳ።
በሰላም ጊዜ ሀብቱን በመከራ ጊዜ ሕይወቱን እየሰጣ ያደለባቸው ተሞጋሾች ችግሩን ታገሠው፣ መከራውን አገልግለው አይነት ማታለያ ሰብከው ወደ ማያውቀው የሰቆቃ ኑሮ ይከቱታል።
ስለዚህ አቅዶ መሥራትን፣ቀድሞ መገኘትን፣የኑሮ ጨውነትን፣ነገን ማየትን..ምእመኑ ስለማይማር ድንቡልቡል ተከታይ ብቻ እየሆነላቸው መጣ።
ጎበዝ፦ተወቅሰው የማያውቁ ተሞጋሾች በበዙበት ቤት መኖር በጣም ያስፈራል።
ፌዝና ቧልታ፣መሞገሥ፣አቦ አቦ መባል..የአገልጋይነት ልቡና ጠላቶች ናቸውና።
ተሞጋሽ መሪዎች እንኳን በመንፈሳዊ በዓለማዊም እንኳን ሀገር አጥፊዎች ትውልድ ጨራሾች ነው የሚሆኑት።
እኛ ተዋርደን ከሙገሳው ወርደን አፈር ልሰን ሠርተን በኢትዮጵያ ያለች ቤተ ክርስቲያን ከመጥፋት ብትድን ጥሩ ነው።
ክርስቶስም ክብርን የገለጸልን ጨርቅ ለብሶ መስቀል ተሸክሞ ነው።
የክርስቶስ ወዶ ፈቅዶ መዋረዱ ግን ለምእመናን ክብር ነው።
እስቲ እንዋረድ እና ለምእመናን፣ለገዳማት፣ለጉባኤያት ህልውና እና ክብር የማሆን የተቆጠረ ዘመን ተሻጋሪ ተግባር እንሥራ።
"እንደ ግብዞች አትሁኑ ለሰው ይታዩ ዘንድ በምኩራብና በመንገድ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸው ውዳሴ ከንቱን ተቀብለዋል።"ማቴ.፮፥፭ እንዲል። እናት የነገ አባቶች ናችሁ ባዶ መክበስበስን እና መሞገሥን የገሀነም ያክል ተጸየፉት እኔን ጉድፍ እናንተ አሳዩኝ የእናንተንም እኔ ላሳይ አንድ ልብ ሁነን ትሁት አገልጋይነትን እንላበስ።".... ከሥልጠናው የተወሰደ..

መ/ር ገብረ መድኅን

1 Monat, 1 Woche her
***♦***"በእንጦጦዋ ኪዳነ ምህረት በእግሬ ቆሜ መራመድ …

"በእንጦጦዋ ኪዳነ ምህረት በእግሬ ቆሜ መራመድ ቻልኩኝ። ዶክተሮቹ 6 ወር እድሜ ብቻ እንዳለኝ ነገሩኝ ከዛ ሀገሬ ሄጄ ልሙት ብዬ መጣው ።"

"ከመጣሁ 6 ቀኔ ነው የእንጦጦዋን ኪዳነምሕረት ፀበል እየጠጣው ይህው አሁን በእግሬ ቆሜ ለመራመድ በቅቻለሁኝ። መጀመሪያ እንዲህ ጉልበት አልነበረኝም፤ አሁን ግን ተመልከት"

"አሜሪካን ሀገር ሁለት ጊዜ የመኪና አደጋ አጋጠመኝ፤ ስመረመር ዶክተሮች የጀርባ አጥንት ካንሰር ይዞሃል እሱም ወደ ጉበትህ ሄዷል እንዲሁም የጉበትም ካንሰር አለብህ አሉኝ። ብዙም እንደማልቆይ ነገሩኝ። እኔ ግን እግዚአብሔር ያሸንፋል አልኩ። እነሱም በጣም ገረማቸው"

አርቲስት አሳዬ ዘገየ ሰይፉ ሾዉ ላይ ቀርቦ ከተናገረው የተወሰደ።

1 Monat, 1 Woche her
ጳጳሳት ዛሬ ዝም ብለው ሚመለከቱት አክራሪ …

ጳጳሳት ዛሬ ዝም ብለው ሚመለከቱት አክራሪ ነገ ሲመጣ እነሱንም ከማረድ እንደማይመለስ አላወቁም ዛሬ ወንበራችን እና ደሞዛችን ካልተነካ ምን አገባን ያሉ ሁሉ ነገ ግን እነሱም አብረው ሳቱን እንደሚሞቁ አያውቁም

1 Monat, 1 Woche her
እምየ ተዋሕዶ ሚዲያ - Emye Tewahedo …
1 Monat, 1 Woche her

የሌሊት ወፍ

"የሌት ወፍ እንደ ዓይጥ ጥርስ አላት፤ እንደ ወፍም ከንፍ አላት፡፡ አንድ ጊዜ የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊቶች ተጣልተው አራት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፡፡

የሌት ወፍ ግን በዳር ሁና ትመለከትና የዱር አራዊቶች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ ትሔድና እኔ እኮቁጥሬ ወደናንተ ነው እዩት ጥርሴን! እዩት ጡቴን እስቲ ከሰማይ ወፎች እንደኔ ጥርስና ጡት ያለው ማነው ትላቸዋለች፡፡

ደግሞ የሰማይ ወፎች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ
ትሔድና እኔ እኮ ቁጥሬ ወደናንተ ነው! እዩት ክንፌን እስቲ ከዱር አራዊት ወገን እንደኔ በከንፍ እየበረረ በአየር ላይ የሚሔድ ማነው ትላቸዋለች፡፡

ወደ ጦርነቱ ግን ምንም ቢሆን አትገባም፡፡

ከጥቂት ቀን በኋላ ዕርቅ ተደረገና ጦርነቱ ቆመ፡፡ ስለዚሁም የሰማይ ወፎችና አራዊቶች ትልቅ በዓል አደረጉ፡፡

የሌት ወፍም ወደ ወፎች ድግስ ብትሔድ እኛ እንደ አውሬ ጥርስ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡ ወደ ዱር አራዊትም ብትሔድ እኛ እንደወፍ ክንፍ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡

ከዚህ በኋላ አፈረችና ወፎችም አራዊትም እንዳያይዋት ቀን ቀን እየተደበቀኝ እየዋለች፤ ማታ ማታ ምግብዋን ለመፈለግ ጀመረች። ቀን ወፎችም ቢያገኝዋት! አራዊትም ቢያገኝዋት አይተዋትም ይገድልዋታል እንጂ

የሌት ወፍ የተባለችውም ከዚያ ወዲህ ነው ይባላል፡፡" (ብላቴን ጌታ ኅሩይ)

አንዳንዶች እንዲህ ናቸው፤ያጠቃ ያሸነፈ ከመሰላቸው ጋር ቦርጫቸውን ያስተካክላሉ፤ላጠቃው መወድስ ለተጠቃው ተረት አያጡም። ጥርሳቸውንና ክንፋቸውን እያቀያየሩ እያሳዩ "እኔ ያንተ አሽከር ያንተ ቡችላ" ይላሉ።

እንደ ንሥርም እንደ አንበሳም ኮራ ብሎ መብረር ወይም መንጎማለል የሚቻለው ወይ ወፍነትን ወይ አውሬነትን መምረጥ ሲቻል ነው!

ጦርነትም ሆነ ጠብ በእርቅ አልያም በመሸናነፍ ይጠናቀቃል። ያኔ እንደ ሌት ወፍ ሌት መጓዝ ይመጣል።

ያድኅነነ እመዓቱ ይሰውረነ

መርጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago