ግዕዝ ሙላት / ግጥሞቹ/

Description
አነ ግጥም_
አነ ቃል _
አነ ግዕዝ _
አነ ጥበብ_
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

2 months, 2 weeks ago

ልትኖሪ ነው የመጣሽው
ልትከርሚ ነው ያፈቀርሽው

ኑራ ኑራ እስካኖራት
ስሟስ ማነው እስክጠራት

ነፃነት ናት የኔ ሀገር
ልብ አይገድም ላሳብ ደንበር

አግብቻት እንድኖር
ስመኝ ስመኝ በቀለበት
ሀገር ሚያክል ትክሻዋ
አጎበጣት እንደ እመት

ልጆች ሚያክል ስትወልድልኝ
የነፃነት ንፁህ ዘርን
ልብ መች እኩል ሊወድ
ባል እና ሀገርን

ስብከነከን በየጫካው
ሳስብ ደሞ በገጠሩ
ፋጨት ሁሉ ወፍ ሲጠራ
ቤቴ ሆነ ያንቺ ዱሩ

ፀጉርሽ እንኳ ጎፈሬ ነው
ጉንጉን እንኳ አትሰሪም
መስመር የለው የዱር ጫካ
ታይተሽ እንኳ አትጠሪም
ደሞም እኮ አታስፈሪም

የዱር ወይን በለስ ፍሬ
አጋም እሾህ ብታገቢም
አፍቃሪ እግር ቢወጋበት
ቢደማ እንኳ አያምም

እጠራጠራለሁ ያንቺን ደረት
እጠረጥራለሁ ያንቺን እሸት
አብረሽኝ እውነት ነሽ
ወይስ የቀን ውሸት

ፀጉር ሰሪዋ ሞታለች
ማነው ከቶ የሚሰራሽ
ጉንጉን ከራስሽ መንገድ ባገኝ
ገባኝ ኑሮ እንዳስፈራሽ

ቤታችን ላይ ካለው ማዶ
ይታየኛል ፊላ ዛፍ
አልጋ ሰርተን ደጅ እንተኛ
ጨረቃዋን ለማትረፍ
በዛው እንኳ ለማቀፍ

በዛው እንኳ እንዲሞቅሽ
እልም ካለ ቀዝቃዛ ሀገር
ስንት ሌት ደጅ አደርኩኝ
ለመሳም ያንቺን ከንፈር

አትገኝም እንደልብ
ቢራቢሮ መንገደኛ
በዛው ቀንቶሽ ከመጣሽስ
ባልሽ ነኝ ነይ እንተኛ

ደረትሽ ላይ እስኪ ስጭኝ
ሀገር ጠፋቶኝ ደክሜለሁ
ማረፊያ እንድትሆኝኝ
ወታደር ሴት አፍቅሬለሁ

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

"የአንዲት ወታደር ሴት መንገድ "

2 months, 2 weeks ago

ሀገር እና እምነት
እውነት እና ሀቅ
ባንድ ላይ ሲኖሩ ፣
ሞት እና ፍርስራሽ
በህዝብ አደሩ ፣

@geez_mulat

2 months, 3 weeks ago

'
'
ፋኖ ትለኛለች ቤቴን ከውስጥ ዘግታ
የድሮ ባሏ የኑሮ ኪሷ መሆኔን ረስታ

ፀጉሬ እንኳ ያደገው ፋኖ ሆኜ አደለም
ፀጉር ያለው ሁሉ
ልብ ካልመረረው ሞትን አልገደለም

በሩን ክፈችልኝ
ያነኛው ወንድሜ ከፍቶኝ ነው አረሳም፣
በሌት መምጣቴ
ጫካ ማደሬ ቤቴን አያስረሳም፣

ፊቴ ከሰል ሆኖ መለየት ቢያቅትሽ
ፀጉሬ ተጨንጨብርሮ አይኔን ቢጋርድሽ
ወደውስጥ ስገባ እኔ እንድታወቅሽ
ያኔ ታቅፊኛለሽ....
ቀዝቃዛው ግድግዳ አውርቶ ሲነግርሽ

@geez_mulat

5 months, 3 weeks ago

ባንድ ሀገር እየኖርን
ባንድ መንደር ሳለን ፣
ወዲያ ሲስቁ
ወዲህ እናለቅሳለን ፣

ባንድ ግቢ ሀገር
ባንድ አጥር እያለን፣
ወዲያ ድግስ ሲሆን
ተስካር እንውላለን ፣

ወዲህ ማዶ ሰባራ እንባ፣
ወዲያ ሰፈር ደስታ መባ፣
ዓለም ገፋን እንደ ዕንባ፣
ተንቀናል ተከፍተናል
እንዳብሽ አበባ ፣

ወዲያ ማዶ ሰባራ ሳቅ
ወዲህ ማዶ ሙሉ ማቅ

ንጉስ መላ ጠፍቶት
ኳስ ይጫወታል፣
ሞት ሬሳ ወገን
በስታዲየም ተኝቷል፣

ወዲህ ሲሆን፥የእግዜር ሰንበት
ሞት ይገኛል ባለንበት

ዜጎች ሁሉ ዝም አሉ
አለም ሁሉ ሸሼን፣
በውስጥ ተባይ አለ
ሁሉም አጠለሼን፣
ምንድነው ጥፋታችን
በሞትስ የታሼን

ባንድ ቤት እያለን
ማዘን ካሳቀቀን
እንግዲህ ዝም ነው
ጊዜ ያፈራርደን

@geez_mulat

ግዕዝ ሙላት

መታሰቢያነቱ

ለኢትዮጵያውያን

5 months, 3 weeks ago

አፍሽ ውሸት ሲሸት
ንግግርሽ መች ገባኝ
ጆሮሽ መጥፎ የቻይና ቃል
ምታደምጭው አይሰማኝ

ከንፈርሽ የድርቅ ምች
ተቀብቶም ሚያስደነግጥ
ሰው እኮ ሞኝ ነው
ላንቺ ፀጉር እንጨት ሲልጥ

ስኬት አለሽ እንደሚሉት
ሱፍ ለብሳ ምታገሳ
ከራባትሽ ከአባትሽ ሞት
ትታያለች ተከልሳ
እንዳንቺ ተልከስክሳ...

አይንሽ ጥቁር፥ ፀጉር የለው
ብሌን የለው፥ ነጭም የለው
ለተመልካች
አይቶ አይመርጥም
ግራ አጋቢ ሸንጋራ ነው፣

ዳሌሽ ወጥ ሲርገበገብ
ህፃን ነበርሽ ገና ገና፣
ለንቋጣ ነው ላጣጥ ግርፊያ
ውበትሽን ለሚያጠና፣

ባንባ ፍሬ እዬወደቀ
ምግብ ሆኖ ቡፌ ሲቀርብ
እንጨት ፈላጭ ይሳሳታል
ምግብሽን ቀምሶ ሲጠርብ

ሆኖም ሆኖም ይወዱሻል
ቆንጆ ወንዶች በየተራ
ጡትሽን ለመታሸት
ማሳጅ ነው ያንቺ ጣራ

ይወዱሻል እነ እግዜሩ
ይወዱሻል እነ አምላኩ
የፈጠረ ሲኮራብሽ
ያልፈጠሩሽ ተሳቀቁ

@geez_mulat
ግዕዝ ሙላት

6 months, 1 week ago

ተስፋችን ማሪያም ነሽ
መቀነትሽ የዕንባ ሙሾ ፣
ጣቶችሽ ሰላም ሰጭ
ዝምታሽ ጥኡም እርሾ ፣

ወይን ነሽ ስምሽ ውቡ
አይኖችሽ ያለም ምግብ ፣
ተልፈስፍሶ ለሚሞተው
መድኑ ነሽ ለግብግብ ፣

ቀሚስሽ የወርቅ ሀምሎ
ካባሽም ፀሀይ መውጫ፣
ሰፊ ነሽ ሰማይ ግዛት
ለአዳም ሀዘን መቀመጫ፣

ደመና ነሽ ለሚቃጠል
ስስ ሙቀት  ለበረደው ፣
ዝናብ ነሽ ለገበሬ
ጠባቂ ነሽ ለምኝታው

መስኮት ዘግቶ ሰዉ ተኛ
እመቤቴን ሳይለምንም ፣
መመስገን ማይጎልባት
ምታረግ ካለምንም ፣

እንቅልፍ ነሽ የእርግብ ላባ
ስስ ነሽ ሰላም ትራስ
የህፃን ልብ ንፁህ የዋህ
ብሩክ ነሽ የጌታ ራስ

ተስፋችን አንቺ ነሽ...
እመቤቴ እባክሽ
ሀገሬ እያት እባክሽ ፣
ጣልቃ ግቢ መላ በይን
ተስፋ አንጣ ልጆችሽ !
'
'

ግዕዝ ሙላት
@geez_mulat

8 months, 1 week ago

የቄስን እና የደራሲን
የሳቅ ትርጉም መለዬት ከባድ ነው ።

@ግዕዝ ሙላት

8 months, 1 week ago

ሰው ተደብቆ መጠጣት ስለሚፈልግ ነው።
የክለብ መብራቶች የሚጠፉት ።

@ግዕዝ ሙላት

8 months, 1 week ago

ጠላ ጠጅ ደብልቄ...
አረቄ ጨምሬ ፥ ብጠጣ አልሰክር
ነገር ነው ያሰከረኝ ፥ ውሎዬን ስጀምር
'
'
@ግዕዝ ሙላት

8 months, 1 week ago
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад