Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ISLAM IS UNIVERSITY

Description
⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇

T.me/Aisuu_bot
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

2 weeks, 1 day ago
«ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ …

«ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህ ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ፡፡ »
[አልበቀራህ 249 ]

አላህ እውነትን ተናገረ!

2 weeks, 2 days ago
**ፈጣሪን አግኝቼ የመጠየቅ ዕድል ቢኖረኝ**አልበርት አይንስታይን …

ፈጣሪን አግኝቼ የመጠየቅ ዕድል ቢኖረኝአልበርት አይንስታይን እንዲህ ይላል:: ፈጣሪን አግኝቼ ጥያቄ መጠየቅ ብችል  ዓለምን(Universe) ለምን እንደፈጠረ እጠይቀው ነበር፡፡ ዓለምን ለምን እንደፈጠረ ካወቅኩ በኋላ እኔ ለምን እንደተፈጠርኩ አውቅ ነበር ይላል፡፡

እስልምና ውስጥ ግን እርሱ ለጠየቃቸው  ጥያቄዎች መልስ አለ፡፡

ጥያቄ 1. የሰው ልጅ ለምን ተፈጠረ?
መልስ፡- وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
[ ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56 ]
ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡

ጥያቄ 2. ለምን ይህንን አለም ፈጠረ?
መልስ፡✔️ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ {الذاريات:56
✔️ هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الأَرْضِ جَمِيعاً  {البقرة:29
✔️ وَسَخَّرَ لَكُم مَّا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا مِّنْهُ  {الجاثية:13
✔️  الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الأَرْضَ فِرَاشاً وَالسَّمَاء بِنَاء وَأَنزَلَ مِنَ السَّمَاء مَاء فَأَخْرَجَ بِهِ مِنَ الثَّمَرَاتِ رِزْقاً لَّكُمْ  {البقرة:22
✔️ وَهُوَ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ النُّجُومَ لِتَهْتَدُواْ بِهَا  {الأنعام:97
"" በአጭሩ…አላህ(ሱ.ወ) በሰማይም በምድርም እንዲሁም በውስጡ ያሉ ነገሮች በሙሉ  መጠቀሚያ(መገልገያ) እንዲሆኑላችሁ ነው የፈጠርኳቸው ይለናል፡፡ ""

الحمد لله على نعمة الاسلام

✍️ዐምማር ዐሊ

2 months, 1 week ago

የረመዳን ተአምራት እና ዮሺኖሪ

በ አውሮፓያኑ አቆጣጣር 2016 የ አለማችንን ትልቁን ሽልማት Nobel Prize in Physiology or Medicine ሽልማት ያሸነፈው ፊዚዮሎጂስት Yoshinori Ohsumi ነው። ያሸነፈውም የ ሰውነትን controlled autophagy “የጽዳት ዘመቻ” ሳይንስ በድንቅ ምርምር ከደረሰበት በኋላ ነው። ታድያ ይህ ድንቅ ሰው የሰራው ስራ ስለ ረመዳን ጾም የተለየ ግንዛቤን የፈጠረ ነበር። እናብራራው...

የሰው ልጅ ለ 12 ሰአትና ከዚያም በላይ ብቻ ከጾመ "ኦቶፋጂ" (autophagy) በመባል የሚታወቀውን የሴል ሂደት ለመጀመር ያስችለዋል። ይህን ሂደት "የ ሰውነት የጽዳት ዘመቻ" በማለት ልንጠራው እንችላለን። እናም በዚህ የ "ኦቶፋጂ ጽዳት ዘመቻ በ ሰውነት በየቦታው የወዳደቀ ፕሮቲን (Damaged protein) የተበላሹ ሴሎችን ሳይቀር በሙሉ ጠራርጎ በማቃጠል ያስወግዳል።

በተፈጥሮ ያረጁ ሴሎች በ ህይወት እያሉ በምትካቸው ወጣት ሴል አይመረትም። ለምሳሌ ይህንን ሁኔታ በ መከላከያ ሴሎች (Immune system) አንጻር ብናይ የሰውነት ባረጁ ሴሎች መሞላት ተጸኖው ቀላል አይደለም። ሽማግሌ ፖሊስ ከሌባ እንደማያስጥለው ሁሉ ሽማግሌ የ መከላከያ ሴልም ከ በሽታ አያድንም። አንድ ሰው 12 ሰአት ጾም ሲጾም ሰውነት የ ምግብ ጉድለቱን ለመሙላት ሲል ሽማግሌ ሴሎችን ገድሎ ለምግብነት ይጠቀማቸዋል (ይበላቸዋል) (ሰው በተፈጥሮ የሚከሳው የራሱን አካል በልቶ ነው)። ሆኖም ስናፈጥር (ስንበላ) አዲስ ንቃት ያለው ወጣት ሴል እንዲፈጠር እድል ይሰጣል (immune cell recycling) ። በዚህም ሂደት ሁሉም ሴል ሲታደስ በዛውም የመከላከያ ሚኒስተር ታደሰ ማለት ነው። ያማለት የበሽታ መከላከል አቅም በ ጾም ምክኒያት ተሻሻለ ማለት ነው።

ይህ ሂደት ሴሎች የራሳቸውን ክፍሎች የሚያድሱበትና እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያደርግም የተፈጥሮ አሠራር ነው።ይህ ሂደት በተለይ ኒውሮዲጀነሬቲቭ ሁኔታዎችን ካንሰርን ጨምሮ ገዳይ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ስለሚችል ለሰው ልጅ እጅጉን አስፈላጊ ነው ።ይህም ሴሎችን ለመጠገንና ለማጽዳት የሚረዳ ከመሆኑም በላይ ለረጅም ዕድሜና እርጅናንም ለመከላከል ተጽእኖ አለው።
እጅግ የሚገርመው ሰውነት autophagyን ለመጀመር በትንሹ ለ12 ሰዓት እና በላይ ያህል ይፈልጋል። ከሃይማኖት ጾም አንጻር ስናየው ከእስልምና ጾም ጋር ብቻ ትይዩ ነው (ፊጥራ)።

ዛሬ ላይ ፈረንጆች እንደ ጤናማ ባህል promote እያደረጉት ነው።ዩሽነሪ በሽልማቱ ለጋዜጠኞች ስለ autophagy ሲያብራራ ጾሙ ለ4 ሳምንት ሲተገበር እጅግ የተዋጣለት ይሆናል።
እናም አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በጤና እንድንከርም በ ፊጥራ ይህንንም ሲስተም በዓመት አንድ ጊዜ ሰውነት ላይ ለአንድ ወር እንዲካሄድ የወሰነለት ሀቅ ይሆን እያልን ተገረምነ 😍😍😍 “ተባረከላሁ አህሰኑል ካሊቂን” አልን።

ፎቶው የ ፕሮፌሰር Yoshinori Ohsumi ነው።

2 months, 2 weeks ago

ፌሚኒስቶችን ጠይቃቸው ፦

«አይፎንን በአንድሮይድ የአጠቃቀም መመሪያ (Manual) ወይም አንድሮይድን በአይፎን (አይ ኦ ኤስ)  Manual መጠቀም እንችላለን? »

መልሳቸው አጭር ነው ፦ «አንችልም» ።

ሁለቱም የስልክ ምርቶች ለተመሳሳይ አላማ የተፈበረኩ መሆናቸውን ያምናሉ።ነገር ግን አፈጣጠራቸው የተለያየ የአጠቃቀም መመሪያ እንዲወጣላቸው አስገድዷል። ፌሚኒስቶች ይህን ሐቅ ለአላህ ሲሆን የማይቀበሉበት ምክንያት አይገባኝም።

አላህ ጀለ ጀላሉህ ወንድና ሴትን በተስተካከለ ቁመና ላይ ለአንድ አላማ ፈጥሯቸዋል። በአፈጣጠራቸውም ልክ መብትና ግዴታቸውን አለያይቶ ደንግጓል።

የአንዱን መብትና ግዴታ  ለሌላው መስጠት በደል ነው። ለተለያዩ አፈጣጠሮች ተመሳሳይ ማንዋል እንጠቀም ማለትም ነው። ሴት ልጅ ከወንድ እኩል ናት በሚለው መፈክራቸው መብቷን እንዳስከበሩላት ይሞግታሉ። ነገር ግን ከወንድ ልጅ እኩል ነች ሲሉ የወንድን ግዴታም እያሸከሟት መሆኑን መቀበል አይፈልጉም።

ለዚህም በሴት ላይ የሆነ በደል ሲከሰት «እንዴት ሴት ላይ ይህ ይፈፀማል?!» በማለት መልሰው ይጮሃሉ። ውስጣቸው በውጭ የሚያስተጋቡትን አቋም መልሶ ስለሚፃረረው ነው። እኩል ናቸው ብለው ካመኑ «እንዴት በሴት ላይ?» ብለው መጮህ አልነበረባቸውና! 

ፌሚኒዝም ሀሰትን እውነት በማስመሰል እልኸኝነት ላይ የተመሰረተ ቆሻሻ እምነት ነው። የሰው ልጅ ያመረተውን እቃ ካምራቹ በላይ ስሪቱን አናውቅም በማለት ማኑዋሉን አክብረው ይጠቀማሉ። በትንሹ በሳምሰንግ ኬብል አይፎንን ቻርጅ አያደርጉም፤ አይሞክሩትምም።ስለማይሆንም ስህተት ነው ብለው ያምናሉ።

የሰው ልጅን አስተካክሎ የፈጠረው አላህ ለፈጠራቸው ፆታዎች ያስቀመጣቸው መብትና ግዴታዎች ላይ ግን ጥያቄ ያነሳሉ፤ ይከራከራሉ!
ለመሆኑ አላህ ወይስ እናንተ ናችሁ አዋቂዎች?
አላህን ስለፈጠረው ነገር ልትከራከሩት ትፈልጋላችሁ? 

«እናንተ ታውቃላችሁን? ወይንስ አላህ?» በላቸው፡፡
(አልበቀራህ 140)

ነገሩ  ያለው ወዲህ ነው። እርሱም አላህ ወንድን ሲፈጥረው በጥንካሬ፣ በብርታትና ልፋትን በመቻል (በመቋቋም) ላይ እንዲሁም በማስተዳደር ሃላፊነት ሹመት ላይ ነው። ሴትን ደግሞ በልስላሴና በድካም ላይ ነው። ለዚህም አላህ ወንድን በሴት ላይ አብልጦታል። አላህ በተከበረ ቃሉ እንዳለው ፦

«ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፡፡ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡» (አን ኒሳእ 34)

የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፦

« አላህ ሆይ!  የሁለቱን ደካሞች ሐቅ ማጓደልን ወንጀል አድርጌያለሁ ፤ የቲምና ሴትን»
(ነሳኢይ)

ይህን የአላህ ህግ የጣሰ ፍልስፍናና አስተሳሰብ ሁሉ ውድቅና የጥመት አስተሳሰብ ነው። ፌሚኒዝምን ኢስላማዊ አድርገው በሚያቀርቡ ደናቁርቶች ልንሸወድ አይገባም ። አላህ ይምራን!

Ismaiil Nuru

2 months, 2 weeks ago
2 months, 3 weeks ago

የቀለበት አደራረግ

ሴት ልጅ የወርቅም ይሁን የብር ቀለበት በፈለገችው ጣት ላይ ማድረግ ትችላለች። ነገር ግን ቤት ውስጥም ይሁን ከቤት ውጪ ስትሆን ጌጧን ባዕድ/አጅነቢይ ወንድ እንዳያይ ጌጡን መሸፈን ግዴታ ይሆንባታል። ይህም የቁርኣን ህግና ትእዛዝ ነው።

ወንድ ልጅ ግን የወርቅ ቀለብት ማድረግ አይችልም። ከወርቅና ከብረት ውጪ ካሉ ነገሮች የተሰራ (የብርም ይሁን ሌላ) ቀለበት ሲያደርግ በመጨረሻው ትንሹ ወይም ከሱ ቀጥሎ ባለው ጣት እንጂ በመሃለኛው ረጅሙ ጣት፣ ከሱ ቀጥሎ ባለው ሌባ (አመልካች) ጣትና አውራ ጣት ላይ ለወንድ ልጅ ቀለበት ማድረግ አይቻልም።
በተለይ በመሃለኛው ረጅሙ ጣትና ቀጥሎ ባለው አመልካች ጣት ላይ ቀለበት ማድረግን ነቢዩ صلى الله عليه وسلم
በግልጽ ከልክለዋል።
ከመሆኑም ጋር ብዙ ወንዶች በነዚህ ጣቶች ቀለበት ሲያደርጉ ይታያል።
ዲናችንን እንወቅ! እውቀት ብርሃን ነው፤ አላዋቂነት ጨለማ ነው።

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

4 months, 1 week ago
ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ …

ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ ላይ ተቀምጦ የአሜሪካ ቴፕላይን ካምፓኒ ሃላፊን አስጠራ
"አንዲት የነዳጅ ጠብታ ወደ እስራኤል እንዳይላክ" ሲልም አዘዘ።

አሜሪካ ትዕዛዙን ጥሳ ለእስራኤል እርዳታ እንደላከች ሲሰማ ከአሜሪካ ጋር የነበረውን የነዳጅ ሽያጭ ውሉን አቋረጠ።
በሀገረ አሜሪካ ሰላማዊ ሰልፍ ነገሰ
ሰዎች በነዳጅ ማደያዎች ፊት ተሰልፈው
ነዳጅ እንጂ እስራኤልን አንፈልግም የሚለውን መፈክር አስተጋቡ።
በዚህ ጊዜ ንጉስ ፋይሰል ታዋቂ ንግግሩን አደረገ
"ነዳጅ ከቁድስ ክብር አይበልጥብንም። አያቶቻችን በተምርና በወተት ኖረዋል እኛም ወደዛው ህይወት እንመለሳለን"
አላህ ይዘንልህ

ዛሬስ አረቦች
ዛሬስ የአለም ሙስለሞች??
በቀን ይሄን ያህል ንፁሀን ሞቱ ቆጣሪ ሁነናል

4 months, 1 week ago
9 months, 3 weeks ago
ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጎልማሳ አባቱ …

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጎልማሳ አባቱ በህይወት እስካለ የሚወዳትን ሴት አግብቶ መኖር በነፍሱ ላይ እርም አደረገ። ለዘመናት ብቸኝነትን መርጦ አባቱን እየተንከባከበ ለመኖር በመወሰኑ የተደነቁ ምክንያቱን ማወቅ ፈለጉ። ለምን ሲሉም ጠየቁ።

"ለሊት ሲተኛ...." በማለት ንግግሩን እንደጀመረ ሳግ ተናነቀውና አለቀሰ "አባቴ ሲተኛ በጎኑ መገላበጥ አይችልም። ከቀኝ ወደ ግራ የማዟዙረው፣ ገላውን አጥቤ ምግብም የማበላው እኔ ነኝ። ሚስት አግብቼ እሷን አቅፌ ስተኛ ባባስ?! ነጥቶ ገርጥቶ፣ ከስቶ ኮስምኖ፣ ጀርባው በሀዘን ጎብጦ፣ ሸክም ጫንቃው ላይ ተደራርቦ ያሳደገኝን አባቴን በዚህ መልኩ ትቼ እንዴት ለአንድ ቀን ከርሱ ርቄ ማደር ይቻለኛል?!" አለ።

ሊላሂ ደሩክ

ይህ ደግሞ እስር ቤት ነው
ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚለውን መርህ ያልተቀበሉት ታላቁ ዓሊም የህየል ቡርሙኪ በዘመኑ መንግስት ተቀፍድደው ከነልጃቸው ዘብጥያ ወረዱ። አካላቸው የደከመ በመሆኑ ለሊት በቀዝቃዛ ውሀ ውዱዕ ማድረግ እየከበዳቸው ብርዱም ሰውነታቸውን ለህመም እያጋለጠ ጤና ራቃቸው። ይህን ያስተዋለው ልጅ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ በመጋባት ውስጥ ተውጦ እየዋለለ በድንገት አንድ መላን ዘየደ። አባት አይናቸው ተከድኖ ረፍት እስኪወስዱ ይጠብቅና ግርግዳውን ተደግፎ ውሀውን በማንቆርቆርያ ይዞ ሆዱ ላይ ይለጥፈዋል። ከሰውነቱ የሚመነጨው ሙቀት ውሀውን ያሞቅለት ዘንድ ለሊቱን ቆሞ ያነጋል። አባት ከዕንቅልፋቸው ሲነቁ
"አባቴ ሆይ በዚህ ውዱእ አርጉ" በማለት ማንቆርቆሪያውን ያቀብላቸዋል።

በመልካምነታቸው አትገረሙንምን?!!

Mahi Mahisho

9 months, 3 weeks ago
ኡጋንዳ ***🇺🇬***

ኡጋንዳ 🇺🇬

ተይዟል

ለፍቅረኛው ሲል እንደ ሴት

  • ጡት መያዣ አድርጎ
  • ሜካብ ተሰርቶ
  • ፁጉር ተሰርቶ

በፍቅረኛው ስም ፈተና ሲፈተን የነበረው ግለሰብ

ሙሳ ሴሞጎሮሬ ይባላል::
ኡጋንዳዊ ሲሆን በኡጋንዳ ሀገር የአንድ አውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ነው

ይህ ምስኪን የህግ ሰው ኢሬኔ ሙቶኒዪ የምትባል የሴት ፍቅረኛ አለችው:: ኢሬኔ በኡጋንዳ የህግ ጥናት ማእከል የህግ ተማሪ ስትሆን ሀምሌ 29 ላይ የማጠቃለያ ፈተና ነበረባት

መቼም የዚህ ጾታ መከራ አያልቅም አይደል?🤗😝

ሙሳ ሶሞጎሮሬ :-

  • ሹሩባ ተሰርቶ
  • ጡት መያዣ አድርጎ
  • ቀሚስ ለብሶ
  • ታኮ ጫማ አድርጎ እና ሜካፕ ተሰርቶ

እንደ ሴት ቂን ቂን እያለ ለሴት ፍቅረኛው ፈተና ሊፈተን ይገባል

በፈተናው መሀል ግን የሴት ፍቅረኛው ኢሬኔን ጠንቅቆ የሚያውቅ አንድ መምህር (በመልክ ይሁን በሽታ ያወቃት አልታወቀም እስካሁን😝)

ጥርጣሬውን ወደ ፍተሻ ሲቀይረው ወንድ ሆኖ ተገኝቷል

ወዲያው የኡጋንዳ ፖሊስም ሙሳን ከሴት ወደ ወንድ ቀይሮት በማጭበርበር እና
ፎርጂድ ሙከራ ከሶት ፍርድ ቤት ገትሮታል::

Via Zemelak Endrias

የዚስ ከፋ

😎😎
🌴🌴🌴

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 1 day ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago