ISLAM IS UNIVERSITY

Description
⭐️ሰው የሚገነዘብ አእምሮና የሚያፈቅር ልቦና ባለቤት ነው።እነዚህ ሁለቱ ካልተመጣጠኑ ስብእናው አደጋ ውስጥ ነው።የሚያገናዝበው አዕምሮው፣የሚያፈቅረው ልቡ፣የሚንቀሳቀሰው አካሉናወደ ሰማይ የሚወነጨፈው መንፈሱ በውህደት ካልተንቀሳቀሱ ሰውየው ላይ ችግር አለ ማለት ነው
📨የፍቅር እና የጥላቻ ስሜቱ፣የፍላጎት እናየፍርሃት መንፈሱ በአዕምሮ ብስለት ካልተገራ አስቸጋሪ ነው
አስተያየት👇

T.me/Aisuu_bot
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago

2 months ago

የረመዳን ተአምራት እና ዮሺኖሪ

በ አውሮፓያኑ አቆጣጣር 2016 የ አለማችንን ትልቁን ሽልማት Nobel Prize in Physiology or Medicine ሽልማት ያሸነፈው ፊዚዮሎጂስት Yoshinori Ohsumi ነው። ያሸነፈውም የ ሰውነትን controlled autophagy “የጽዳት ዘመቻ” ሳይንስ በድንቅ ምርምር ከደረሰበት በኋላ ነው። ታድያ ይህ ድንቅ ሰው የሰራው ስራ ስለ ረመዳን ጾም የተለየ ግንዛቤን የፈጠረ ነበር። እናብራራው...

የሰው ልጅ ለ 12 ሰአትና ከዚያም በላይ ብቻ ከጾመ "ኦቶፋጂ" (autophagy) በመባል የሚታወቀውን የሴል ሂደት ለመጀመር ያስችለዋል። ይህን ሂደት "የ ሰውነት የጽዳት ዘመቻ" በማለት ልንጠራው እንችላለን። እናም በዚህ የ "ኦቶፋጂ ጽዳት ዘመቻ በ ሰውነት በየቦታው የወዳደቀ ፕሮቲን (Damaged protein) የተበላሹ ሴሎችን ሳይቀር በሙሉ ጠራርጎ በማቃጠል ያስወግዳል።

በተፈጥሮ ያረጁ ሴሎች በ ህይወት እያሉ በምትካቸው ወጣት ሴል አይመረትም። ለምሳሌ ይህንን ሁኔታ በ መከላከያ ሴሎች (Immune system) አንጻር ብናይ የሰውነት ባረጁ ሴሎች መሞላት ተጸኖው ቀላል አይደለም። ሽማግሌ ፖሊስ ከሌባ እንደማያስጥለው ሁሉ ሽማግሌ የ መከላከያ ሴልም ከ በሽታ አያድንም። አንድ ሰው 12 ሰአት ጾም ሲጾም ሰውነት የ ምግብ ጉድለቱን ለመሙላት ሲል ሽማግሌ ሴሎችን ገድሎ ለምግብነት ይጠቀማቸዋል (ይበላቸዋል) (ሰው በተፈጥሮ የሚከሳው የራሱን አካል በልቶ ነው)። ሆኖም ስናፈጥር (ስንበላ) አዲስ ንቃት ያለው ወጣት ሴል እንዲፈጠር እድል ይሰጣል (immune cell recycling) ። በዚህም ሂደት ሁሉም ሴል ሲታደስ በዛውም የመከላከያ ሚኒስተር ታደሰ ማለት ነው። ያማለት የበሽታ መከላከል አቅም በ ጾም ምክኒያት ተሻሻለ ማለት ነው።

ይህ ሂደት ሴሎች የራሳቸውን ክፍሎች የሚያድሱበትና እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያደርግም የተፈጥሮ አሠራር ነው።ይህ ሂደት በተለይ ኒውሮዲጀነሬቲቭ ሁኔታዎችን ካንሰርን ጨምሮ ገዳይ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና ሊጫወት ስለሚችል ለሰው ልጅ እጅጉን አስፈላጊ ነው ።ይህም ሴሎችን ለመጠገንና ለማጽዳት የሚረዳ ከመሆኑም በላይ ለረጅም ዕድሜና እርጅናንም ለመከላከል ተጽእኖ አለው።
እጅግ የሚገርመው ሰውነት autophagyን ለመጀመር በትንሹ ለ12 ሰዓት እና በላይ ያህል ይፈልጋል። ከሃይማኖት ጾም አንጻር ስናየው ከእስልምና ጾም ጋር ብቻ ትይዩ ነው (ፊጥራ)።

ዛሬ ላይ ፈረንጆች እንደ ጤናማ ባህል promote እያደረጉት ነው።ዩሽነሪ በሽልማቱ ለጋዜጠኞች ስለ autophagy ሲያብራራ ጾሙ ለ4 ሳምንት ሲተገበር እጅግ የተዋጣለት ይሆናል።
እናም አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በጤና እንድንከርም በ ፊጥራ ይህንንም ሲስተም በዓመት አንድ ጊዜ ሰውነት ላይ ለአንድ ወር እንዲካሄድ የወሰነለት ሀቅ ይሆን እያልን ተገረምነ 😍😍😍 “ተባረከላሁ አህሰኑል ካሊቂን” አልን።

ፎቶው የ ፕሮፌሰር Yoshinori Ohsumi ነው።

2 months, 1 week ago

ፌሚኒስቶችን ጠይቃቸው ፦

«አይፎንን በአንድሮይድ የአጠቃቀም መመሪያ (Manual) ወይም አንድሮይድን በአይፎን (አይ ኦ ኤስ)  Manual መጠቀም እንችላለን? »

መልሳቸው አጭር ነው ፦ «አንችልም» ።

ሁለቱም የስልክ ምርቶች ለተመሳሳይ አላማ የተፈበረኩ መሆናቸውን ያምናሉ።ነገር ግን አፈጣጠራቸው የተለያየ የአጠቃቀም መመሪያ እንዲወጣላቸው አስገድዷል። ፌሚኒስቶች ይህን ሐቅ ለአላህ ሲሆን የማይቀበሉበት ምክንያት አይገባኝም።

አላህ ጀለ ጀላሉህ ወንድና ሴትን በተስተካከለ ቁመና ላይ ለአንድ አላማ ፈጥሯቸዋል። በአፈጣጠራቸውም ልክ መብትና ግዴታቸውን አለያይቶ ደንግጓል።

የአንዱን መብትና ግዴታ  ለሌላው መስጠት በደል ነው። ለተለያዩ አፈጣጠሮች ተመሳሳይ ማንዋል እንጠቀም ማለትም ነው። ሴት ልጅ ከወንድ እኩል ናት በሚለው መፈክራቸው መብቷን እንዳስከበሩላት ይሞግታሉ። ነገር ግን ከወንድ ልጅ እኩል ነች ሲሉ የወንድን ግዴታም እያሸከሟት መሆኑን መቀበል አይፈልጉም።

ለዚህም በሴት ላይ የሆነ በደል ሲከሰት «እንዴት ሴት ላይ ይህ ይፈፀማል?!» በማለት መልሰው ይጮሃሉ። ውስጣቸው በውጭ የሚያስተጋቡትን አቋም መልሶ ስለሚፃረረው ነው። እኩል ናቸው ብለው ካመኑ «እንዴት በሴት ላይ?» ብለው መጮህ አልነበረባቸውና! 

ፌሚኒዝም ሀሰትን እውነት በማስመሰል እልኸኝነት ላይ የተመሰረተ ቆሻሻ እምነት ነው። የሰው ልጅ ያመረተውን እቃ ካምራቹ በላይ ስሪቱን አናውቅም በማለት ማኑዋሉን አክብረው ይጠቀማሉ። በትንሹ በሳምሰንግ ኬብል አይፎንን ቻርጅ አያደርጉም፤ አይሞክሩትምም።ስለማይሆንም ስህተት ነው ብለው ያምናሉ።

የሰው ልጅን አስተካክሎ የፈጠረው አላህ ለፈጠራቸው ፆታዎች ያስቀመጣቸው መብትና ግዴታዎች ላይ ግን ጥያቄ ያነሳሉ፤ ይከራከራሉ!
ለመሆኑ አላህ ወይስ እናንተ ናችሁ አዋቂዎች?
አላህን ስለፈጠረው ነገር ልትከራከሩት ትፈልጋላችሁ? 

«እናንተ ታውቃላችሁን? ወይንስ አላህ?» በላቸው፡፡
(አልበቀራህ 140)

ነገሩ  ያለው ወዲህ ነው። እርሱም አላህ ወንድን ሲፈጥረው በጥንካሬ፣ በብርታትና ልፋትን በመቻል (በመቋቋም) ላይ እንዲሁም በማስተዳደር ሃላፊነት ሹመት ላይ ነው። ሴትን ደግሞ በልስላሴና በድካም ላይ ነው። ለዚህም አላህ ወንድን በሴት ላይ አብልጦታል። አላህ በተከበረ ቃሉ እንዳለው ፦

«ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፡፡ አላህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡» (አን ኒሳእ 34)

የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) እንዲህ ይላሉ፦

« አላህ ሆይ!  የሁለቱን ደካሞች ሐቅ ማጓደልን ወንጀል አድርጌያለሁ ፤ የቲምና ሴትን»
(ነሳኢይ)

ይህን የአላህ ህግ የጣሰ ፍልስፍናና አስተሳሰብ ሁሉ ውድቅና የጥመት አስተሳሰብ ነው። ፌሚኒዝምን ኢስላማዊ አድርገው በሚያቀርቡ ደናቁርቶች ልንሸወድ አይገባም ። አላህ ይምራን!

Ismaiil Nuru

2 months, 1 week ago
4 months ago
ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ …

ንጉስ ፈይሰል አሸዋ ላይ በተዘረጋው ምንጣፍ ላይ ተቀምጦ የአሜሪካ ቴፕላይን ካምፓኒ ሃላፊን አስጠራ
"አንዲት የነዳጅ ጠብታ ወደ እስራኤል እንዳይላክ" ሲልም አዘዘ።

አሜሪካ ትዕዛዙን ጥሳ ለእስራኤል እርዳታ እንደላከች ሲሰማ ከአሜሪካ ጋር የነበረውን የነዳጅ ሽያጭ ውሉን አቋረጠ።
በሀገረ አሜሪካ ሰላማዊ ሰልፍ ነገሰ
ሰዎች በነዳጅ ማደያዎች ፊት ተሰልፈው
ነዳጅ እንጂ እስራኤልን አንፈልግም የሚለውን መፈክር አስተጋቡ።
በዚህ ጊዜ ንጉስ ፋይሰል ታዋቂ ንግግሩን አደረገ
"ነዳጅ ከቁድስ ክብር አይበልጥብንም። አያቶቻችን በተምርና በወተት ኖረዋል እኛም ወደዛው ህይወት እንመለሳለን"
አላህ ይዘንልህ

ዛሬስ አረቦች
ዛሬስ የአለም ሙስለሞች??
በቀን ይሄን ያህል ንፁሀን ሞቱ ቆጣሪ ሁነናል

4 months ago
9 months, 1 week ago
ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጎልማሳ አባቱ …

ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጎልማሳ አባቱ በህይወት እስካለ የሚወዳትን ሴት አግብቶ መኖር በነፍሱ ላይ እርም አደረገ። ለዘመናት ብቸኝነትን መርጦ አባቱን እየተንከባከበ ለመኖር በመወሰኑ የተደነቁ ምክንያቱን ማወቅ ፈለጉ። ለምን ሲሉም ጠየቁ።

"ለሊት ሲተኛ...." በማለት ንግግሩን እንደጀመረ ሳግ ተናነቀውና አለቀሰ "አባቴ ሲተኛ በጎኑ መገላበጥ አይችልም። ከቀኝ ወደ ግራ የማዟዙረው፣ ገላውን አጥቤ ምግብም የማበላው እኔ ነኝ። ሚስት አግብቼ እሷን አቅፌ ስተኛ ባባስ?! ነጥቶ ገርጥቶ፣ ከስቶ ኮስምኖ፣ ጀርባው በሀዘን ጎብጦ፣ ሸክም ጫንቃው ላይ ተደራርቦ ያሳደገኝን አባቴን በዚህ መልኩ ትቼ እንዴት ለአንድ ቀን ከርሱ ርቄ ማደር ይቻለኛል?!" አለ።

ሊላሂ ደሩክ

ይህ ደግሞ እስር ቤት ነው
ቁርአን መኽሉቅ ነው የሚለውን መርህ ያልተቀበሉት ታላቁ ዓሊም የህየል ቡርሙኪ በዘመኑ መንግስት ተቀፍድደው ከነልጃቸው ዘብጥያ ወረዱ። አካላቸው የደከመ በመሆኑ ለሊት በቀዝቃዛ ውሀ ውዱዕ ማድረግ እየከበዳቸው ብርዱም ሰውነታቸውን ለህመም እያጋለጠ ጤና ራቃቸው። ይህን ያስተዋለው ልጅ ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ በመጋባት ውስጥ ተውጦ እየዋለለ በድንገት አንድ መላን ዘየደ። አባት አይናቸው ተከድኖ ረፍት እስኪወስዱ ይጠብቅና ግርግዳውን ተደግፎ ውሀውን በማንቆርቆርያ ይዞ ሆዱ ላይ ይለጥፈዋል። ከሰውነቱ የሚመነጨው ሙቀት ውሀውን ያሞቅለት ዘንድ ለሊቱን ቆሞ ያነጋል። አባት ከዕንቅልፋቸው ሲነቁ
"አባቴ ሆይ በዚህ ውዱእ አርጉ" በማለት ማንቆርቆሪያውን ያቀብላቸዋል።

በመልካምነታቸው አትገረሙንምን?!!

Mahi Mahisho

9 months, 1 week ago
ኡጋንዳ ***🇺🇬***

ኡጋንዳ 🇺🇬

ተይዟል

ለፍቅረኛው ሲል እንደ ሴት

  • ጡት መያዣ አድርጎ
  • ሜካብ ተሰርቶ
  • ፁጉር ተሰርቶ

በፍቅረኛው ስም ፈተና ሲፈተን የነበረው ግለሰብ

ሙሳ ሴሞጎሮሬ ይባላል::
ኡጋንዳዊ ሲሆን በኡጋንዳ ሀገር የአንድ አውራጃ ፍርድ ቤት ዳኛ ነው

ይህ ምስኪን የህግ ሰው ኢሬኔ ሙቶኒዪ የምትባል የሴት ፍቅረኛ አለችው:: ኢሬኔ በኡጋንዳ የህግ ጥናት ማእከል የህግ ተማሪ ስትሆን ሀምሌ 29 ላይ የማጠቃለያ ፈተና ነበረባት

መቼም የዚህ ጾታ መከራ አያልቅም አይደል?🤗😝

ሙሳ ሶሞጎሮሬ :-

  • ሹሩባ ተሰርቶ
  • ጡት መያዣ አድርጎ
  • ቀሚስ ለብሶ
  • ታኮ ጫማ አድርጎ እና ሜካፕ ተሰርቶ

እንደ ሴት ቂን ቂን እያለ ለሴት ፍቅረኛው ፈተና ሊፈተን ይገባል

በፈተናው መሀል ግን የሴት ፍቅረኛው ኢሬኔን ጠንቅቆ የሚያውቅ አንድ መምህር (በመልክ ይሁን በሽታ ያወቃት አልታወቀም እስካሁን😝)

ጥርጣሬውን ወደ ፍተሻ ሲቀይረው ወንድ ሆኖ ተገኝቷል

ወዲያው የኡጋንዳ ፖሊስም ሙሳን ከሴት ወደ ወንድ ቀይሮት በማጭበርበር እና
ፎርጂድ ሙከራ ከሶት ፍርድ ቤት ገትሮታል::

Via Zemelak Endrias

የዚስ ከፋ

😎😎
🌴🌴🌴

9 months, 2 weeks ago

......, #ፍቅር ...,
አሚር ሰይድ

🔰አንዲት እህቴ ፍቅር ይዞኛል ግን ፍቅር ምንድን ነዉ ብላ ጠይቃኝ የዛሬ 2አመት በፊት የመለስኩላት ነዉ እናንተ ስለፍቅር ምን ትላላችሁ⁉️
☞ፍቅር ህልም ነዉ ስትነሺ የማታገኚዉ
☞ፍቅር ንፋስ ነዉ ከየት በኩል እንደመጣ የማታየዉ
☞ፍቅር ዉሀ ነዉ ጨብጠሽ ይዘሽ የማታስቀምጪዉ
☞ፍቅር የእሳት እረመጥ ነዉ አንዴ የእሳት ረመጥ በእግርሽ ከረገጥሽዉ እግርሽ እንደመግል ሁኖ ያመረቅዛል በዛ እግርሽ መሬት መንካት አትችይም ሳታነክሽ ብዙ ወር ትቆያለሽ ከዛ በስንት ድካም ይሻልሻል
☞ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ በዉንም በህልምም አብሮ እሱ ጋር እየኖሩ አብረዉ ልጅ ሲወልዱ ተከባብረዉ ሲኖሩ የሚያሳይ የህይወት ስዕል ነዉ ...ስዕል ደግሞ እዉነት አይደለም ያዉ ስዕል ነዉ...,ፍቅር የማያገኙትን ሰዉ ልብሽ ላይ ስለሽ ያንን ስዕል እንዳይጠፋብኝ እያሉ የመጨነቅ የመጠበብ ኑሮ ነዉ..ስዕሉ እንዳይጠፋ የመታገል ህይወት ነዉ
☞ፍቅር ተራራ ነዉ ይላሉ ግን ፍቅር ተራራ አይደለም ሜዳ ነዉ ..ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ...ተራራ ስትወጪ ይደክምሻል ግን በግድም ቢሆን ወጥተሽ ትጨርሻለሽ ከተራራዉ ጫፍ ላይ ደርሻለሁ በስንት ድካም ብለሽ  ራስሽን ታደንቂያለሽ ደክመሽም ቢሆንከተራራዉ ጫፍ በመድረስሽ
...ፍቅር ግን የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ሂደሽ ሂደሽ አጨርሽዉም ጫፉ ላይ የማይደረስ ነዉ...ለምን ብትይ ተራራ ወጥተሽ ከጫፍ ትሆኛለሽ...የወጣሽዉን ተራራ ደግሞ መዉረድ አያቅትም ተራራ የሚከብደዉ መዉጣቱ ነዉና
ሜዳ ግን ብትሄጅ ብትሄጅ ብትሄጅ አያልቅም....ለምሳሌ ከደሴ አዲስ አበባ 401 km ነዉ ያንን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሽዋለሽ?በጭራሽ አጨርሺዉም ግን ጠንካራ ነኝ ብለሽ ካሰብሽ አያቶቻችን መኪና በሌለበት ዘመን ሂደዋል እኔም በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ከተሳካልሽ ☺️ አአ  ከሄድሽ😉 ከአአ አሶሳ ሱዳን ድንበር 660 km አለ እሱን በእግርሽ ሂደሽ ትጨርሺዋለሽ?በጭራሽ አሞክሪዉም ...አይታወቅም የሰዉ አቅሙ☺️ ጠንካራ ከሆንሽ ሄድሽ እንበል አሶሳ ደረሽ ምድር ታበቃለች?ምድር ተሂዶ አያልቅም ከሱዳን ጀምሮ ስንት ሀገር አለ...በእግርሽ በመኪና በአየር ሂደሽ የማጨርሺዉ....በእግርሽ ሱዳንን አልፈሽ ብትሄጅ ስትሄጅ ስትሄጅ ዉቅያኖስ ወይ ባህር ታገኛለሽ በእግርሽ ከሞከርሽ ሰምጠሽ ትቀሪያለሽ ...ወደ ጀመርሽበት አትመለሽ ሩቅ ነዉ ባለሽበት ቀባሪ ሳትገኝ ትሞቻለሽ ማለት ነዉ☺️ ፍቅርም ሂደዉ ሂደዉ የማይመለሱበት የቁም ሞት መሞቿ ህይወት ነዉ
ፍቅር ተራራ ሳይሆን ሂደሽ ሂደሽ የማጨርሺዉ የሜዳ ላይ ተራራ ነዉ ...
እናም ይሄን ረጅም መንገድ ሂደሽ የማጨርሽዉ አለም ...በእግሬ እሄዳለሁ ብለሽ ማሳመን ነዉ ፍቅርም እወጠዋለሁ ብለሽ ሂደሽ የማጨርሽዉን ጉዞ መጀመር ነዉ...ከጀመርሽም ይሄን የማይጨረስ አለም አንድ እርምጃ ሳትረመጅ ሀሳብሽ ተበታትኖ እግርሽ ተሳስሮ ሳትሄጅ ትመለሻለሽ ..,ፍቅር አሰቡበት ሳይደርሱ ወደ ፊት የሆዱ መስሎ በማያቁት መንገድ ወደ ሆላ መመለስ ነዉ.. ግን ወደ ሆላ መመለስሽ የሚገባሽ ቡሀላ ሳትሄጅ ከተመለሽ ቡሀላ ነዉ
☞ፍቅር ካልተሳካ ከህይወት ተስፋ መቁረጥ ነዉ ...ደግሞም ሴት ነሽ ይከብዳል ወንዱ ሌላ ሊኖረዉ ይችላልና ....እሱ ካልተረዳሽ ስቃይ ነዉ
☞ፍቅር ያለዉ አማረኛ ፊልም እና ዘፈን ላይ ነዉ...አማረኛ ፊልም ስናይ ዘፈን ስናዳምጥ ያንን ያየነዉ ያዳመጥነዉ ሙዚቃ ወደ ዉስጣችን ገብቶ ያንን ለማዋሀድ እኔስ የለኝም ወይ? ብለን በአየነዉ ፊልም ሙዚቃ ፍቅርን እየሳልን የምንረበሽበት የሙዚቃዉ የፊልሙ አይነት አፍቃሪ ሳናገኝበት የምንኖርበት የፊልምና የሙዚቃ ኑሮ ነዉ

☞ፍቅር ጥልቀት ያለዉ ክብ ዲንጋይ  ነዉ...ያንን ዲንጋይ ለማዉጣት ብቻሽን ብትቆፍሪም ሰዉ ቢረባረብ የማይወጣ ነዉ...ፍቅርም ጥልቀት ያለዉ ከልብ የማይወጣ ክብ ዲንጋይ ነዉ

☞እኔ የምልሽ ፍቅር ከሚይዝሽ ኮረንቲ ያዝ አርጎ ቢለቅሽ ይሻላል...ለምን ኮረንቲ አስደንግጦ ይተዉሻል ፍቅር ግን ያፈቀርሺዉ የኔ ይሆን በሚል እልክ ....እራስሽን በራስሽ አሳምነሽ የምትኖሪበት ህይወት ነዉ፡፡

☞ፍቅር ያፈቀሩትን ሰዉ የማያገኙበት ህይወት ነዉ...ትዋጀሻለሽ ግን አብሮ ለመሆን የምትሰቃይበት ኑሮ ነዉ.
  የማይረዳሽ ለትዳር የማይሆን ከሆነ የወደድሽዉ አደራ አደራ ፍቅርሽን አፍነሽ አላህ እንዲያነሳልሽ ዱአ አርጊ ካልሆነ እሱ በፍቅር ልብሽ ላይ ይጫወትብሻል ሀራም ያሰራሻል...የሴት ልጅ ፍቅር ከባድ ነዉ ፡እኔ ይሻላል የምለዉ ወንድ ቢያፈቅር ነዉ ወንድ ከወደደ ይታገሳል ተስፋ ቆርጦም ይነሳል...ሴትግን ብታፈቅር ትጎዳለች በተለይ
የማይረዳ ለትዳር የማይሆንሽ ከሆነ

ደግሞ ማወቅ ያለብሽ በፍቅር መለየት አለ ምክንያቱን ሳታቂ የኔ ነዉ ያልሽዉ ሊከዳሽ ይችላል.....ወይም በቤተሰብ ወይ በእትህት ወንድም ወይ በተሳሳተ መረጃ ልብ ላይ ያርፍና የሆነ ጊዜ ይቆረፍዳል የዛን ጊዜ ከወዳጅ ከምወጂዉ ትለያለሽ የዛን ጊዜ ማፍቀርሽን ትጠያለሽ ፍቅር ልብሽ ላይ ተቀምጦ ትሰቃያለሽ ከሰዉ በታች ልትሆኝ ትችያለሽ....ከሚወዱት መለየት ከባድ ነዉ እምባስ ይወጣል የልብ እምባ ግን እዛዉ አልቅሶ ይቀራል😔...የማይወጣ ነገር የቀረ ደግሞ ለዉስጥ በሽታ ነዉ መቼም ጤነኛ አትሆኝም....
አሏህ በተከበረ ቁርአኑ እንኳን ከወዳጅ መለያየት
ሀዘኑ በጣም ጥልቅ እንደሆነ ይናገራል
የአይን ብርሃን እስከማጣት

( وتَوَلَّىٰ عَنْهُمْ وَقَالَ يَٰٓأَسَفَىٰ عَلَىٰ يُوسُفَ وَٱبْيَضَّتْ عَيْنَاهُ مِنَ ٱلْحُزْنِ فَهُوَ كَظِيمٌۭ )
" ከእነሱም ዘወር አለና ኣ«በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!» አለ ፡፡ ዓይኖቹም ከሐዘን (ለቅሶ) የተነሳ ነጡ ፡፡ እርሱም በትካዜ የተሞላ ነው ፡፡"
_....የየሱፍ አባት ወደዉ አልቅሰዉ አይናቸዉን ያጡት ነብይን ነዉ..እኛ ግን አላህ ለፈጠረዉ ተራ ሰዉ አልቅሰን አይናችንን ታመን ልባችንን ማድማት የለብንም
ሆነም ቀረ...የሰዉ ልጅ ለራሱ ሳያቅ የራሴ ህይወት ሳይገባኝ  በሰዉ እፈርዳለሁ ...
በጥላቻ ድልድይ መረማመድ ቁልቁለት ነው።
ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነው።
ስለ በደል ማውራት ተራ ነው።
የተበዳይን እንባ ማበስ ከባድ ነዉ😔
መፍረድ ቀላል ነው።
ፍትሀዊ መሆን ምጥ ነው።
መለያየት ቀላል ነው። አንድ መሆን ፈተና ነው።
ትልልቅ ነገሮችን ማሰብ ቀላል ነው። ትንንሽ ነገሮችን ማድረግ ከባድ ነዉ።
በምኞት መኖር ቀላል ነው። እውነትን መቀበል መራር ነው።
ተስፋ ማድረግ ቀላል ነው። አማኝ መሆን ፅናት ነው።
ብቻ አሏህ ከሁላችንም ጋር ይሁን ከፍቅር የዉሸት ኑሮ ይሰዉረን

እናም እኔ የምለዉ ልብን አትዉደድ አይባልም ግን መጀመሪያ ለይል ተነስተሽ አልቅሰሽ ዱአ አርጊበት

ይቅርታ ግን እኔ ለፍቅር ጥሩ አመለካከት የለኝም😊 እኔ ለአንቺ የምረዳሽ ቢኖር ከፍቅር ተስፋ ማስቆሮጥ....የምወጂዉን እንደማታገቢ ተስፋ ማስቆረጥ ...ፍቅር በሌለበት አለም አፍቃሪ እንዳትሆኝ አእምሮሽን እንድትጠርጥሪ ማድረግ...የፍቅር ህይወትሽ እንዲጨልም ማረግ ብቻ ነዉ😂
ለፍቅር ጥሩ አመለካከት ያላቸዉ በፍቅር ያተረፉ ካሉ እነሱን ብትጠይቂ ጥሩ ነዉ ባይ ነኝ☺️
⚠️ Warning
ፍቅርን በተግባር ማረጋገጥ ዳገት ነዉ
መለያየየት ቀላል ነዉ አንድ መሆን ግን ፈተና ነዉ
ጨርሻለሁ ከአጠፋሁ አዉፍ በይ 😊
እርስዎ ስለፍቅር ምን ይላሉ
#ለአስተያየት👇
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot
T.me/Aisuu_bot T.me/Aisuu_bot

9 months, 2 weeks ago
ሀያሉ የጂንጊስ ኻን ጦር አለምን ሊቆጣጠር …

ሀያሉ የጂንጊስ ኻን ጦር አለምን ሊቆጣጠር ከምስራቅ የሞንጎሊያ ኦቶኬን ተራሮች ተነስቶ ወደ ምእራብ እየገሰገሰ ነው ። እናም በርካታ ከተሞችን ተቆጣጥሮ ከውቧ የኢማም አልቡኻሪ ከተማ ቡኻራ ደጅ ደርሷል ።

ጂንጊስ ኻን ከቡኻራ ከፍተኛ መከላከል እንደሚገጥመው ስለገመተ አንድ መላ ዘየደ - የከተማዋን ህ ለሁለት መክፈል ! ስለሆነም ለከተማዋ ህዝብ እንደዚህ የሚል ደብዳቤ ላከ " ከኛ ጋር የምትሰለፉ ከሆነ እናንተ ነፃ ናችሁ " የሚል ።

በዚህ ጊዜ የከተማዋ ህዝብ ለሁለት ተሰነጠቀ ግማሹ ከጂንጊስ ኻን ጎን እንሰለፍ ሲል ግማሹ እርሱን እንዋጋለን እንጅ አንሰለፍም አለ ። የጅንጊስ ኻን እቅድ የመጀመሪያ ግቡን መታ ።

በመቀጠል ጂንጊስ ከእርሱ ጎን እንሰለፋለን ላሉት ሌላ ደብዳቤ ላከ " ከእኛ ጋር ሆናችሁ እምቢ ያሉትን የምትዋጉ ከሆነ ከተማዋን ለናንተ አስረክባችሗለሁ " አላችሁ ። እነርሱም " ታድያ ምን ገዶን " በማለት የገዛ ወንድሞቻቼውን ተጋደሉና አሸነፏቸው ።
በዚህ ጊዜ ጅንጊስ ኻን ለጦሩ እነዚህን ከነርሱ ጋር የተሰለፉትን እንዲገድሉ አዘዘ ።
ለምን ? ተብሎ ሲጠየቅም " እነዚህ ህዝቦች ጥሩ ሆነው በነበሩ ለእኛ ለማያውቁን ህዝቦች ብለው የገዛ ወገኖቻቼውን ባልተጋደሉ ነበረ ስለዚህ ግደሏቸው " አለና አስጨፈጨፋቸው ። ቡኻራም በቀላሉ ካለብዙ መስዋዕትነት በእጁ ገባች ።

እዚህ ጋር ዋናው ትምህርት ምን መሰላችሁ ዛሬ አንዱን ከድቶ ካንተ ጋር የተሰለፈ ነገ አንተንም ይከዳሀል ! አንዴ የከዳ ሁሌም ይከዳልና !

እናም በህይወታችሁ ውስጥ የሆነን አካል ሲከዳን ያያችሁትን ሰው በፍፁም በጭራሽ እንዳታቀርቡት ለዚህ ለክ*ህደቱ ሚሊዮን ምክንያት ቢደረድር እንኳ !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

t.me/IslamisUniverstiy_public_group

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago