ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

Description
ኦርቶዶክሳዊ ጽሑፎች ይቀርቡበታል !
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago

2 months, 3 weeks ago
ታትሟል!

ታትሟል!

የመጀመሪያው ቅጽ ከድርሳን ፩-፳፬ የነበረ ሲኾን፥ ይህ አሁን የታተመው ኹለተኛው ቅጽ ደግሞ ከድርሳን ፳፭-፶ ያሉትን 26 ድርሳናት የያዘ ነው። ትጠቀሙበት ዘንድ እጋብዛችኋለሁ።

3 months, 4 weeks ago

🌻 ሌላ ዕድል 🌻

በሕይወት ዘመናችን ብዙ ዕድሎችን እንደምንፈልግ የታወቀ ነው፡፡ የሥራ ዕድል፣ የደመወዝ እድገት ዕድል፣ የትምህርት ዕድል፣ የዲቪ ዕድል፣ የኮንዶሚንየም ቤት ዕድል፣ የሎተሪ ዕድል፣ ብቻ እዚህ መዘርዘር የማንችላቸው በጣም ብዙ ዕድሎች እንዲገጥሙን እንመኛለን፡፡ ከመመኘትም አልፈን እነዚህን ለማግኘት ብለን ብዙ ጥረቶችን እናከናውናለን፡፡ እነዚህን ዳር ለማድረስ ብለን የሚበላ ብናጣ እንኳን ያገኘናትን ብቻ ተቃምሰን አያሌ ቀናትን እናሳልፋለን፡፡ በውኃ ጥም ጉሯሯችን እስኪደርቅ ድረስ እንታገሣለን፡፡ እንቅልፍ አጥተን እንታትራለን፡፡ አንዴ ወይም ኹለቴ ያመለጠንን ዕድል መልሰን ለማግኘት ስንል የሞት ሽረት ትግል እናደርጋለን፡፡

እንደዚህ መጣጣሩ፣ መፈለጉ፣ መጓጓቱ በራሱ ጤናማ ነው፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ ሲፈጠር የተሻለ ነገርን ለማግኘት የተፈጠረ ነው፡፡ ችግሩ “የተሻለ ነገር ምንድን ነው?” የሚለውን መለየቱ ላይ ነው፡፡ የተሻለ ነገር የተባለው ፈጣሪው ነው፡፡ ፈጣሪውን እንዲፈልግ፣ ፈጣሪውን እንዲያገኝ፣ ከፈጣሪው ጋር እንዲገናኝ ውስጡ የሚገፋፋው ኾኖ የተፈጠረ ነው፡፡ ክፍተቱ የሚመጣው ይህን በሌሎች ነገሮች ሊሞላው ስለሚሻና ዋናውን ግብ መርሳቱ ነው፡፡ ቀዳማዊ አዳም አምላክ ለመኾን መመኘቱ በራሱ ጤናማ ነበር፡፡ ችግሩ የጸጋ አምላክ ሳይኾን የባሕርይ አምላክ ለመኾን በምክረ ከይሲ መታለሉ ነው፡፡ ለመብላት መጓጓቱ በራሱ ጤናማ ነበር፡፡ ችግሩ ዕፀ ሕይወትን ጨምሮ ሌሎች ብዙ መብሎች እያሉለት የተከለከለውን መብላቱ ነው፡፡ ስለዚህ የሰው ልጅ የተሻለ ነገርን ፈልጎ መውደቁ በድንገት የመጣት እንግዳ ነገር ሳይኾን ራሱ የሰው ልጅ የተሻለ ነገርን የማግኘት ኃይል በውስጡ ስለ ነበረና ያንንም ለማግኘት ስለ ተፈጠረ ነው፡፡

አሁን ዓለማዊነት ከወሰደብን ኦርቶዶክሳዊ መነጽሮች አንዱ ይኼ ነው፡፡ የተሻለ መብል፣ የተሻለ መጠጥ፣ የተሻለ ቤት፣ በአጠቃላይ የተሻለ ሕይወት መኖር ሲባል ቅዱስ ሥጋው፣ ክቡር ደሙ፣ መንግሥተ ሰማያት፣ በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ጋር በተሻለ የቅድስና ሕይወት መኖር ሳይኾን ከላይ የገለጽናቸውን ቁሳዊ ነገሮች ብቻ ማግኘት እንደ ኾነ በቀጥታም በዘዴም ወስዶብናል፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ነጽሮታችንን በብልሐት ነጥቆ ከላይ በጠቀስናቸው ርእዮተ ዓለሞች ገዝቶናል፡፡ ቁስ አቅርቦ ዋናውንና መንፈሳዊውን ማንነታችን ጋርዶብናል፡፡

አንድ ሰው እስከ ማስተርስና እስከ ፒ.ኤች.ዲ. ድረስ እየተማረ መንፈሳዊ ትምህርትን ለመማር ግን “ጊዜ የለውም”፡፡ አንዳንዱ’ማ ጊዜ ብቻ ሳይኾን ጥንቱንም አሳቡ የለውም፡፡ ይህን ትምህርት ለመማር ብዙ ጊዜ፣ ብዙ ገንዘብ፣ ብዙ ጉልበት፣ ብዙ መሥዋዕት ይከፍላል፡፡ መማሩ በራሱ ምንም ክፋት ባይኖረውም ቅሉ የሚመራው የዓለማዊነት ነጽሮት ብቻ ከኾነ ግን ችግር ነው፡፡ ዓላማውን የሳተ ሕይወት ነው፡፡ ሕይወት አልባ “ሕይወት” ነው፡፡ ይህ ሰው ትምህርቱን ጨርሶ የተሻለ ደመወዝ ቢከፈለው፣ የተሻለ ድርጅት ቢመራ፣ የተሻለች መኪና ቢያሽከረክር ይህን እርሱ ስኬት ብሎ ቢያስበውም ቅሉ ከመንፈሳዊ ሕይወት የተራቆተ ጉዞ ከኾነ በኦርቶዶክሳዊ አተያይ ትርጉም አልባ ጉዞ ይባላል፡፡

ተመልከቱ! አሁን አዲስ ዓመት ደርሷል፡፡ የተሻለ ነገርን ለማግኘት ብለንም ልክ እንደከዚህ በፊቶቹ ዓመታት ብዙ ዕቅዶችን አቅደናል፡፡ ከላይ እንደ ተናገርነው ይህ በራሱ ጤናማ ነው፡፡ ነገር ግን ዓላማውን የሳተ ዕቅድ እንዳይኾን ማስተዋል ያስፈልገናል፡፡ የተወሰደብንን ኦርቶዶክሳዊ አተያይ መልሰን ገንዘብ ልናደርገው ይገባናል፡፡ አዲሱ ዓመት የተሰጠን ይህን እንድናከናውንበት ነውና፡፡

ወደዚህ ዓመት የተሸጋገርነው በራሳችን ብርታት አይደለም፡፡ የተሸጋገርነው “ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም” እንዲል ምግብ ስለ በላን፣ ወይም ንጹሕ ውኃ ስለ ጠጣን፣ ወይም ንጹሕ አየር ስለ ተነፈስን ብቻ አይደለም፡፡ የተሻገርነው ወደ ሌላ ዕድል ነው፡፡ የተሻገርነው ወደ ሌላ “እንደ ገና” ነው፡፡ የተሸጋገርነው የተሻለውን ነገር እንድናገኝ ነው፡፡ የተሸጋገርነው አምና ላይ እግዚአብሔር ወደ ንስሐ አባቶቻችን ሔዶ ምግባር ትሩፋት ባያገኝብን ጠባቂ መላእክቶቻችን “ተራድተን ሥራ እስክናሠራው ድረስ የዘንድሮውን ተወው፤ ምናልባት በሚመጣው ዓመት ሃይማኖት ቢይዝ ምግባር ቢሠራ” ብለው ማለደውልን ነው (ሉቃ.13፡8)፡፡ የተሸጋገርነው አምና ያልመጸወትነውን ዘንድሮ እንድንመጸውት፣ አምና የተጣላነውን ዘንድሮ እንድንታረቀው፣ አምና የተሻለ ሕይወት ነው ብለን የተጓዝነውን መንገድ አስተካክለን ወደ ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት እንድንመለስ፣ ዓለማዊ መነጽራችንን አውጥተን ኦርቶዶክሳዊ መነጽራችንን ገንዘብ እንድናደርግ ብሎም በዚህ የሕይወት መስመር እንድንጓዝ፣ የኦርቶዶክሳዊነት ጠባይ ያልኾነውን በዘርና በቋንቋ በወንዝም መቧደንን አሽቀንጥረን ጥለን ዘርና ቀለም የሌለበትን ሕይወት ገንዘብ እንድናደርግ ነው፡፡ የተሸጋገርነው ከትናንቱ ውድቀታችን እንድንነሣ ነው፡፡

ወንድሜ ሆይ! አምና ንስሐ ለመግባት ዐቅደህ “አልተሳካልህምን”? እኅቴ ሆይ! ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ለመቀበል አስበሽ አልቻልሽምን? በያዕቆብ መሰላል የሚመሰለውን ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት መጓዝ ጀምረህ/ሽ ወደ ኹለተኛው እርከን፣ ወደ ቀጣዩ ማዕርግ ለመውጣት አቅቶህ/ሽ ወድቀሃልን/ ወድቀሻልን? ወይስ እዛው ባለህበት ወደ ላይም ሳትወጣ ወደ ታችም ሳትወርድ (maintenance phase ላይ) ቆመሃልን? ሰውን የሚወድ እግዚአብሔር ሌላ ዕድል ሰጥቶሃል! መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ሌላ እንደ ገና አሰናድቶልሃልና ተስፋ አትቁረጥ! አንተ ብቻ ከምኞት ያለፈ ፈቃደኝነትን አሳይተህ በተግባር ጥቂት ጥረትን ጀምር እንጂ ስፍር ቊጥር የሌላቸው መላእክት አንተን ለመርዳት ከአጠገብህ ናቸው፡፡ እመብርሃን ከፊትህ ናት፡፡ ቅዱሳን ኹሉ በቃል ኪዳናቸው አንተን ለመርዳት የታመኑ ናቸው፡፡
“መልካም አዲስ ዓመት ይኹንልን” ብለን መልካም ምኞታችንን የምንለዋወጠው ይህን ሕይወት ገንዘብ ለማድረግ ነው፡፡

ይህን “ሌላ ዕድል” በአግባቡ እንድንጠቀምበት ከባሕርይ አባቱ ከአብ፣ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት፣ ኃይልና ክብር ገንዘቡ የኾነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን፤ አሜን!
(Re_posted)

4 months, 2 weeks ago

ሰላም ለእናንተ ይኹን!

ድጋሚ በቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ሥራ መጥቻለሁ።

ከዚህ በፊት የማቴዎስ ወንጌል ቅጽ አንድ ወጥቶ ብዙ ሰው ተጠቃሚ ኾኗል። አሁን ደግሞ ቅጽ ኹለቱ አልቆ ለኅትመት ዝግጁ ኾኗል።

ቅጽ አንድ ከድርሳን 1-24 ያጠቃለለ ሲኾን፥ ቅጽ ኹለት ደግሞ ከድርሳን 25-50 የያዘ ነው።

እግዚአብሔር ቢፈቅድ በአዲሱ ዓመት የኅትመት ብርሃን ያያል።

8 months ago

"ማንን ላግባ?" የሚለው የሥልጠና መጽሐፍ በውስጡ ምን ምን አካቷል?

መጽሐፉ በዋናነት ስድስት ክፍለ ጊዜዎችን የሚሸፍን ሲኾን፡-

#አንድ፡- በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መዳን ጉዞ ነው - እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚደረግ ጉዞ! ይህን ጉዞ ለመጓዝም እግዚአብሔር ለሰው እንደ ዓቅሙ የሚሰጠው የጉዞ መስመር (ጥሪ) አለው:: ለአንዳንዱ የድንግልናን ጸጋ ሲሰጠው ለሌላው የጋብቻን ጸጋ ይሰጠዋል፡፡ የኹለቱም ዓላማቸው መንግሥተ እግዚአብሔርን መውረስ - መዳን እንደ መኾኑ፥ ወጣቶች ጥሪያቸው የትኛው የጉዞ መስመር እንደ ኾነና ይህን እንዴት መለየት እንደሚችሉ በመጀመሪያው ክፍለ ጊዜ ይዳስሳል፡፡

#ኹለት፦ ትዳር በሃይማኖትም በማኅበረሰብም ዘንድ ቅቡል ስለ ኾነ፡ ሌሎች ሰዎች ሲያገቡ እነርሱ ካላገቡ የዕድለቢስነት ስሜት የሚፈጥርባቸው ሰዎች ቍጥራቸው ቀላል አይደለም፡፡ ክርስቲያኖች ማግባት ያለባቸው ግን ጋብቻ አንዱ የድኅነት መንገድ ስለ ኾነ ነው፡፡ በመኾኑም ወጣቶች ጥሪያቸው ማግባት ከኾነ ስለ ጋብቻ ምንነትና ዓላማ ሊኖሯቸው ስለሚገቡ መሠረታዊ ነጥቦችን በኹለተኛው ክፍለ ጊዜ ያስመለክታል፡፡

#ሦስት፦ ወጣቶች አሁን ስለ ትዳር ያላቸው ግንዛቤ በዋነኝነት የተማሩት ከወላጆቻቸው/ ከአሳዳጊዎቻቸው/ ከትምህርት ቤት/ ካነበቡት/ ከሰሙት ነው፡፡ ስለዚህም “የትዳር አጋር ይኾነኛል/ ትኾነኛለች" ብለው ለመምረጥ ከመነሣታቸው በፊት ራሳቸውን እንዲመለከቱ/ እንዲያውቁ፣ መለወጥ ያለባቸውን እንዲለውጡና ኦርቶዶክሳዊ የትዳር ጉዞን ለመጀመር በምን ረገድ መዘጋጀት እንዳለባቸው በሦስተኛው ክፍለ ጊዜ ይቃኛል፡፡

#አራት፦ ከውሳኔዎች ኹሉ እጅግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ውሳኔ ከሚያሻቸው ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው የትዳር አጋርን በመምረጥ ረገድ የሚደረግ ውሳኔ ነው:: መዳረሻቸውን መንግሥተ ሰማያት ወይም እሳተ ገሃነም የማድረግ ዓቅም ያለው ነውና። በመኾኑም ወጣቶች እንደሚገባ ራሳቸውን ከለወጡና እንደ ዓቅማቸው ብቁ አድርገው ካዘጋጁ በኋላ የወደፊት የትዳር አጋራቸውን እንዴት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚመርጡ፣ በተለይም እንደ ተባለው መዳረሻቸውን የሚወስነው ኋኝነታቸውን (their Compatibilities) እንዴት አድርገው ማየት እንዳለባቸው በአራተኛው ክፍለ ጊዜ ይዳስሳል፡፡

#አምስተኛ፡- ወጣቶች ውሳኔያቸው ትክክል ይኹን አይኹን ማወቅ የሚችሉበት ምትሐታዊ ቀመር የለም፡፡ ስለዚህም ከመወሰናቸው በፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው በአምስተኛው ክፍለ ጊዜ ያስቃኛል፡፡

#ስድስተኛው፡- በትዳር አጋር ምርጫ ብቻ ሳይኾን በኹሉም የሕይወት ዘርፍ እርግጠኛ እየኾንን እንወስናለን ማለት አስቸጋሪ ነው:: የሚቻለውን ያህል እግዚአብሔር በሰጠን አእምሮ ከእኛ የሚጠበቀውን ማድረግ ነው:: ከዚህ ውጪ ያለው እምነት ነው፡፡ በመኾኑም በስድስተኛው ክፍለ ጊዜ የወሰኑት ውሳኔ ትክክል መኾኑን እንዴት እንደሚያውቁና ወደ ቀጣዩ ደረጃ - ወደ ዕጮኝነት - እንዴት እንደሚያሳድጉት፣ ምናልባት ግንኙነታቸው ጤናማ ካልኾነ ደግሞ ሲያቋርጡት በምን ረገድ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አስዳስሶ ሥልጠናውን ያሳርጋል።

9 months ago

ጥንዶች አንዳቸው ለሌላኛቸው የሚያደርሱት ጸሎት

በቅዱሱ ሐዋርያህ [በተወዳጅ] ጳውሎስ በኩል አንዳችን የሌላኛችንን ሸክም እንሸከም ዘንድ ያስተማርከን እግዚእነ ወአምላክነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ቅዱስ የኾነውን ትእዛዝህን እፈጽም ዘንድ፥ እንደ ምሕረትህ የሚስቴን ሸክም በ[መንፈሳዊት] ፍቅር መሸከም ይቻለኝ ዘንድ ጸጋህን አትንሳኝ፤ ትሰጠኝ ዘንድ እማልድሃለሁ! ፍጹምና ሰላምን የሚያጎናጽፍ ፍቅርህን ወደ እኛ በመላክም፣ በአንድ ልብ በአንድ አሳብ በመጠበቅም፣ በአሚን እንድንጸና በማድረግም ትዳራችንን ባርክልን። አንተ በምትሰጠው ደስታ ደስ እንድትሰኝና በነገሮች ኹሉ አንተን ደስ ማሰኘት ይቻላት ዘንድ በሚስቴ (የክርስትና ስሟ ጥቀስ) ላይ ፍቅርህን አሳድርባት። ለዘለዓለም ቅዱስ የኾነውንና አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የተሰኘ [የሦስትነት] ስምህን በአንድነት ማክበር ማግነን ይቻለን ዘንድም ከጸብ ከክርክር ከፈተናም [ኹሉ] ጠብቀን፤ በሰላምና በአንድነት አጽናን፤ ዛሬም ዘወትርም እስከ ዘለዓለሙ ድረስ፥ አሜን!

© Orthodox Faith

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 6 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 month ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 weeks ago