Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ABX

Description
ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

5 days, 3 hours ago

ኢስላምን በመስበካቸው ብቻ ነቢዩን ሶ.ዐ.ወ. በመካ ቁረይሾች ዘንድ እንደትልቅ ወንጀለኛ ነበር የተቆጠሩት፡፡ ለዚህም የግድያ ቅጣት ሊፈጽሙባቸው ብለው አሳልፈው እንዲሠጧቸው በቤተዘመዶቻቸው በበኒ ሃሺም ላይ ማዕቀብ ተጣለ። እንዳትገዟቸው፣ እንዳትሸጡላቸው፣ እንዳታናግሯቸው፣ እንዳትቀርቧቸው ተባለ።

በኒ ሃሺም ከሰዎች ተገልለው በአንድ ዋሻ ዉስጥ እንዲቆዩ ተደረገ።
ነቢያዊው ቤተሰብ ከባድ መከራ ላይ ወደቁ። ታረዙ፣ ተቸገሩ፣ ከርሃብ የተነሳ ቆዳ፣ ቅጠል፣ ጨርቅ፣ እስከመብላት ደረሱ።

ከሰዎች መካከል የነርሱ መከራ የተሰማቸው ሰው ሰው የሚሸቱ ሰስብእናዎች ነበሩ ። እኛ እንበላለን እንጠጣለን እንለብሳለን በኒ ሃሺሞች በርሃብና እርዛት ያልቃሉ? አሉና የተጣለባቸው ማዕቀብ እንዲነሳ አነሳሱ። በዚህም በኒ ሃሺሞች ከ3 ዓመታት በኋላ ከከበባ ማዕቀብ ወጡ፡፡

ዛሬ የፍልስጤም ጋዛ ሕዝብ በሁሉም አቅጣጫ ተከቦ ቦንብ ይዘንብበታል። 8ኛ ወሩን በያዘው ጭፍጨፋ ከ35ሺ በላይ ወገን ሲያልቅ ከሰዉነት ተራ የወጡት የዐረብ መሪዎች ዛሬም ድረስ አልሞቃቸው አልበረዳቸው፡፡ በተቃዉሞ ትንፍሽ የሚል የለም። የሚሞግትላቸው አታገኝም።

ከዚያ ይልቅ በደምና ሃይማኖት የማይገናኟቸው ደቡብ አፍሪካውያን በፍርድ ቤት ቆመው ሲከሱላቸው፤ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መኖሪያቸዉን ጎዳና አድርገው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተው ሲጮኹላቸው ታያለህ። የሙስሊሙ ዓለም ዝም ጭጭ ያስደነግጣል። የመካ ቁረይሾችና የዛሬዎቹን ካፊሮች ያህል እዝነት ማጣታቸው ግራ ያጋባል፡፡ እኛ አቅም የለሾቹ መላ ጠፍቶናል፡፡ በሙስሊሞች የእልቂት የዕለት ዜና ደከመን፡፡ መተንፈስ አቃተን፡፡
ሰሞኑን በዋናነት የማደርገው ዱዓ ቢኖር
"አላህ ሆይ የዐረብ መንግሥታትን አጥፋቸው!" የሚል ነው፡፡
ያ አላህ አጥፋቸው!!።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

1 week, 1 day ago

በዚህ የኢንተርኔትና ሶሻል ሚዲያ ዘመን በሚገርም ፍጥነት ወደ ጃሂሊያው ዘመን እየተመለስን ነው። የሚያሳዝነው ደግሞ የመጨረሻው ነቢይ አልፈዋል። ካሁን በኋላ ነቢይ አይመጣም።
እናም ለራሳችሁ ሁኑ። ራሳችሁን ምከሩ። ከደጋግ የአላህ ባሮችና ዑለሞች ተጠጉ። የማይጠቅሟችሁን ግንኙነቶች በድፍረት በጥሱ። መጥፎ መድረኮችን ራቁ። ብቸኝነትን ምረጡ። ብዙ ወሬያችሁ ስለሰው ሳይሆን ስለራሣችሁ ይሁን።

መሳአል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

1 week, 1 day ago

እኛ ማለት ሞኞች ያልተጠቀሙብን ዉድ ዕድሎች ነን ብዬ ለመሰከስ አስብና መልሸ እተወዋለሁ።

መቸሰ በቅርብ መሞታችን ስለማይቀር ብንጠቃቀም ይሻላል ብዬ እኮ ነው።

እውነቴን ነው የምላችሁ ይህንን ቻናል ለሌሎችም ብትጠቁሙ መልካም ነው።

ባለፈው በቁምነገር አስተዋውቁ ስላችሁ ሳቃችሁ። ቆይ ይህችን ምልክት 😀 አጠፋትና በምን ጥርስ እንደምትስቁ አያለሁ ።

https://t.me/MuhammedSeidAbx

1 week, 4 days ago

"ምን አርጌው ነው ግን የቦለከኝ?" ብለህ አሁን ድረስ የምትብከነከንበት ሰው አጋጥሞህ ያውቃል ?
ካላጋጠመህ ወደፊት ያጋጥምሃል አብሽር ።

ያኔ ባጋጠመህ ጊዜ ደግሞ ብዙ አትገረም።

ሞኝ አትሁን፣ አትብሰልሰል፣ ብቻህንም አታውራ።
ቆይ እጠይቀዋለሁም አትበል።

ወዳጄ!
ሰው ከራሱ ጋር ተጣልቶ ምንም ሳታረገው ሰው ላይ በብሎኬት ማለቴ በብሎክ ብሶቱን የሚወጣበት ዘመን ላይ ደርሰናል ።

አትረበሽ፡፡
ዝምብለህ ኑር ያልኩህ እኔ ነኝ።

መሳአል ኸይር!

https://t.me/MuhammedSeidAbx

1 week, 4 days ago

ደስ የሚለው ነገር ...
ጠዋት ላይ የምትወጣው ፀሐይ ብቻ አይደለችም፡፡
ለመኖር ተስፋ እንዲኖረን የሚገፋፉ መልካም ሰዎች፣
ማማረር እንደማይገባንና በሕይወት ለመቆየት ብዙ ምክንያት እንዳለን የሚመመክሩ ደጋግ ባሮችም አብረዋት ይወጣሉ፡፡

አላህን የሚያስታውሱን ዉብ ፊቶችም ይወጣሉ፡፡

ነግቶ እስክናያቸው የምንጓጓላቸው፣ የምንወዳቸው፣ የምንናፍቃቸው ሰዎችም ይወጣሉ፡፡
አላህ ያቆይልን።

እናንተን በማየቴ ደስ ብሎኛል በሉ፡፡
ተደሰቱ!።
ሰዎችም ከአንደበታችሁ በሚወጣው ቃል ይደሠቱ፡፡

ሶባሐል ኸይር

https://t.me/MuhammedSeidAbx

1 week, 5 days ago

ስለራስህ ታሪክ አንተ የማታውቀዉን ሁሉ መልሰው ይነግሩሃል፡፡
አትከራከር፤ ዝምብለህ አዳምጣቸው ምን አደከመህ፡፡ የጉድ ዘመን፡፡

https://t.me/MuhammedSeidAbx

2 weeks, 4 days ago

አለመፈለግህን ከሚያመለክቱ መገለጫዎች መካከል ስልክ ሰትደዉል አለማንሳት አንዱ ነው፡፡ አንድ ሁለት ምክንያት ፈጥረው ለዚህ ነው ያላነሳሁት ብለው ዑዝር ካቀረቡ ለክፉዉም ለበጎዉም ትንሽ ጠብቅ፡፡ ከዚያ በላይ ከሆነ ግን ተሠልችተሃል ማለት ነዉና ነቃ በል፡፡

ደዉለህ በሌላ ሰው አስነስተው “የለም” ወይም ቻርጅ ላይ ነው ከተባልክማ ሞተሃል፡፡ ጅሎች ጊዜ ባለፈበት ሙድ እየቀጡህ ነዉና ክብርህን ጠብቅ መልሰህ አትደዉል፡፡

https://t.me/MuhammedSeidAbx

2 weeks, 4 days ago

በመጨረሻም ...
ያሸማቀቁንን፣ ያሳፈሩንን፣ ያዋረዱንን፣ የተዉንን፣ የተጠራጠሩንን፣ የሰደቡንን፣ የናቁንን ... ሁሉ የምናመሰግንበት ጊዜ ይመጣል ።

ምክንያቱም እነኚህ ሁሉ ቀና ለማለታችንና ለመጠንከራችን ምክንያት ሆነዋል።

ሶባሐል ኸይር ወዳጆች

https://t.me/MuhammedSeidAbx

2 weeks, 5 days ago

ለመናፈቅ ብለው የራቁንን ሁሉ ረስተናቸዋል።

እስቲ አንዳንዴ ጨከን በሉና እንደኔ ሁኑ።

አለሁ አልሐምዱ ሊላህ

https://t.me/MuhammedSeidAbx

3 weeks, 6 days ago

ሶባሐል ኸይር መጽሐፍ
የመገኛ አድራሻዎች

በዉጭ አገር

ደቡብ አፍሪካ

MAYFAIR JOHANNESBURG
ሱመያ ሱፐር ማርኬት
ከመንዲ ሬስቶራንት በግራ በኩል
ጀማል ዳውድ
NO- 0622117711

ሪያድ
0535109794

ጂዳ
0509230683
0592348102

ዱባይ
971565542936
971551482240

ኩዌት
+965 55949211

ባሕሬን
0097332002858

ኳታር
‎+97455799676‎

በመላው አውሮፓ
+31 6 26063873

https://t.me/MuhammedSeidAbx

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago