Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago
اللهم يسر أمورنا وفرج همومنا واستر عيوبنا وأصلح أحوالنا واغفر لنا ولوالدينا وتوفنا وأنت راض عنا يا أرحم الراحمين
ይህ ከላይ የምታዩት ጽሑፍ 98 መጨረሻ ጽሑፍ የጀመርኩ ሰሞን ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ የፃፍኩት ነው። 19 ዓመት ወደኋላ ። የልጅነት ስሜት። አልሐምዱ ሊላህ አሁንም እዚያው ነው። ጥንካሬው ባይኖርም ጉጉቱ አለ።
ወዳጆቼ በወጣትነታችሁ ዘመን ጠንክራችሁ ሥሩ። ሰው ከፍ እያለ ሲሄድ ይደክመዋል። ከኢማኑ ይንሸራተታል።
የወጣትነት ዘመን ሥራችሁ ይኸው እንደምታዩት ትዝታ ሆኖ ዋ ያ ዘመን ያስብላችኋል።
ሐምሌን ተስፋ አድርገህ ነበር፤
ነሐሴን ገና ከጅምሩ ተደነቃቀፍክ፤
መስከረም እንዳሰብከው አልሆነልህም፤
ጥቅምት ጭራሽ ሌላ ችግር ገጠመህ፤
ህዳር ፈተናህ በዛ፣
ታህሳስስ ምን ይዞ ይሆን??
ባይሆን አትማረር፣
አሁንም ተስፋህን ሰንቅ።
ወዳጄ
እየጣርክ እየለፋህ ባይሳካልህ አላህ ከወደደልህ ውጭ ምን ሌላ ነገር ታመጣለህ?
እውነቴን እኮ ነው የምልህ እስቲ ምን ታመጣለህ?
በሁሉም ሁኔታህ ውስጥ አልሐምዱ ሊላህ በል።
አልሐምዱ ሊላህን ሕይወትህ አድርግ፤
ይዘሃት ተኛ፣
ይዘሃት ተነስ።
ኢላሂ ሆይ በዲናችን አትፈትነን፤
ፈተናህም የቁጣና የጥላቻህ አይሁንብን።
አምላኬ ሆይ የማንችለውን አታሸክመን፣
በማንችለውም አትፈትነን።
ቲስበሑ
ሶባሐል ኸይር
አንድ ነገር ልንገራችሁ ።
አላህ ምስክሬ ነው።
ከአላህ ለምኜ ያጣሁት አንድም ነገር የለም።
ስለችሮታው ሁሉ ለምስጋና ቃላት አጣለሁ።
ወደ አላህ በምንመለስባቸው ጊዜያት ሁሉ ነፍሳችን ምልስ ትላለች።
ሰው ነንና
አንዳንዴ ይደክመናል፤ ሁሌም ኢስቲቃማ አይኖረንም እንንሸራተታለን። ሳይታሰብ እንወጣለን ።
የወጣን ቀን በዚያው ከመንገዱ ወጥተን አንቅር።
ስንሄድ አንዳችንን በዚያው አንሂድ። እየተመለስን እሺ።
ወደ አላህ
መሳአል ኸይር❤️
ሶባሐል ኸይር
ሓና እና ማና
.
አንድ ሰውዬ ሓና እና ማና የሚባሉ ሚስቶች ነበሩት አሉ ፡፡ ሓና ዕድሜዋ ሀያ ያልዘለለ ወጣት ነች፡፡ ማና ደግሞ ሃምሳ ያለፈች ፀጉሯን ሽበት የወረራት ባልቴት ናት፡፡ በየተራ ሁለቱ ቤት ያድራል፡፡
ሓና ዘንድ ሲሄድ ፂሙን ታይና የሸበተውን ነጫጩን እየመረጠች አንድ በአንድ ትነቅላለች፡፡ ‹ሆ ሽማግሌ አገባ ይሉኛል፤ አንተ እኮ ገና ወጣት ነህ፡፡› እያለች ፡፡
.
ማና ዘንድ ሲያድር ደግሞ ‹አንተ እኮ ትልቅ ሰው ነህ፡፡ ልጇን ነው ያገባችው ብለህ አታሰድበኝ፤ ጥቁር ፀጉር ምን ያደርግልሃል፤ ከእኔ ጋር የዕድሜ እኩያ መምሰል ይኖርብሃል › በማለት ጥቁር ጥቁሩን ፀጉር እየመረጠች ትነቅላለች፡፡
.
በዚሁ መሃል ፀጉሩ እየተነጨ ሳሳ፡፡ በረሃ ሆነ። ለመላጣነትም ቀረበ፡፡ ታዲያ አንድ ቀን በመስታወት ፀጉሩን ቢመለከት ደነገጠ፡፡ ሳስቶና አልቆ ተመለከተው፡፡ ከዚያም ራሱን በመያዝ ጮኸ
‹ ወይ ሐና ወይ ማና
በሁለታችሁ መካከል ዐይናችን እያየን አለቅና፡፡› አለ አሉ፡፡
.
እና ሁላችንም ወደራሣችን እየጎተትነው አደራ ይህን ዲን ሸጋ ፀጉሩን ነቃቅለን እንዳንጨርሰው ብዬ ነው..
(ተአንድ ኪታብ ነው ያገኘሁት)
አል-ሐሰን አል-በስሪ
“መተናነስ ማለት ከቤት ከወጣህበት ቅጽበት ጀምሮ አንድ ሙስሊም ባጋጠመህ ቁጥር እሱ ከኔ ይበልጣል ብለህ ማሰብህ ነው።” ይሉ ነበር።
ሰባሐል ኸይር!
.......የፈራ ማልዶ ይነሣል፡፡ እወድቃለሁ ብሎ የሠጋ በርትቶ ያጠናል። የድህነትን ክፋት የፈራ በርትቶ ይሠራል፡፡ በጊዜ ሂደትም ድህነትን ይገላገላል፡፡ እውቅናን ማግኘት ዓላማው የሆነ ሰው መግባት መውጣት፤ መቆም መነሣት ፤ በአደባባይ መታየት ከፊት ለፊት መገኘት ያዘወትራል፡፡ በዚህም ከጊዜያት በኋላ የሃሣቡን ያሣካል፤ የኒያውም ይሞላለታል፡፡ ለብር የቋመጠ ሰው በእንቅልፍ ልቡ ሲዞር ያድራል፤ በጧት ተነስቶ ይሮጣል፤ በቀን አብዝቶ ይደክማል፤ ምሽቱን ገፍቶ ይተኛል፤ ኋላም ሀብት ያገኛል፡፡ ለትዳር የተመኛትን ከእጁ ማስገባት የፈለገ ሰው መላዎችን ያውጠነጥናል፤ ዘዴዎችን ይቀይሣል፤ በዚህም በዚያም ይጥራል፤ ከብዙ ድካምና ልፋት በኋላም የሀሣቡን ያሣካል የምኞቱን ያገኛል፡፡ የሰው ልጆች እንዲህ ለዱኒያዊ ስኬቶች እንለፋለን፡፡ ለዓለማዊ እድገቶችም በብዙ መልኩ ስንጥር እንታያለን፡፡ የጥረትን ውጤት የድካምን ፍሬ እናውቃለንና ብዙ የምንደክምላቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለብር እንደክማለን፡፡ ለትምህርት እንደክማለን። ለእውቅና እንደክማለን፡፡ ለጥሩ ትዳር እንደክማለን፡፡ የምንደክምላቸው ነገሮች ብዙ ከመሆናቸው ጋር የዋጋውን ያህል ያልደከምንለት አገር ቢኖር ጀነት ነው፡፡ ጀነት ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች በላይ ሁሉ ውድ ሆኖ ሳለ ብዙም ግምት የሰጠነው አይመስልም፡፡ አብዛኞቻችን ተዘናግተናል፡፡ ኑሮአችንም የደመነፍስ ሆኗል.......
ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ ሣለን በዚህች ዓለም ላይ የተሠጠን እድሜ አልቆ ቆይታችንም አብቅቶ ያ ስሙ እንኳ እንዲነሳ የማንፈልገው ሞት ድንገት 'መጣሁ' ቢለን ያኔ ምን ሊውጠን መሸሻችን ወዴት ነው… መጠጊያችንስ ከየት ይሆን? ሰማይ እንደሆነ ሩቅ ነው፡፡ መሰላል ተይዞ አይወጣ፡፡ መሬት እንደሆነች ክብ ናት ብንዞርም አንለያት፡፡ ወይ ወደ እናት ማህፀን አይመለሱ ነገር። 'አፈር በሆንኩ' ም አይጠቅም፡፡
ስለሆነም አሁኑኑ በአጭሩ እንታጠቅ፡፡ ለአኼራችን በወጉ እንሰንቅ፡፡
ብንኮራ መሬት ላንሰምጥ የተራራን ያህል ላንረዝም ምነው መንጠባረር መወጠሩ… ሞት ላይቀር ነገር ምን ቢኖሩ!!
-----
'ልብ ላላሉ ልቦች' ከሚለው የMuhammad Seid Abx መፅሃፍ የተወሰደ
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago