Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

ትዳር የአማኞች ምሽግ

Description
ትዳር የአማኞች ምሽግ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 weeks ago

1 month, 3 weeks ago

ረመዳን 7
Suretu An-Anfal
ቃሪእ:- አቡ በክር አሽ-ሻጢሪይ
القارئ= ابو بكر الشاطري

https://t.me/SileTidarEnmekaker

1 month, 3 weeks ago
1 month, 3 weeks ago

"ፍቅር ማለት በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ቦታ መውሰድ አይደለም......ፍቅር ማለት ማንም ሊወስደው የማይችለውን ቦታ መፍጠር ነው"።

3 months, 3 weeks ago

❍   ሴት ከቤት ስትወጣ አካሏን
       መሸፈን ግዴታ ነው፡፡ የልብሱ
       አይነት እንዲህ መሆን አለበት፡፡ 
❒ ❝ገላዋን ሁሉ የሚሸፍን❞
❒  ❝በራሷ ውበት ያልሆነ❞
❒ ❝የማያጠብቅ ሰፊ❞
❒ ❝ሽቶ ያልተቀባ❞
❒ ❝የካፊረ ሴቶች ልብስ የማይመስል❞
❒  ❝የወንድ ልብስ የማይመስል❞
❒  ❝ልዩ የማያደረግ የሚሉት ናቸው፡፡❞
ይቺን ኢስላም ያዘዛትን የምትተገብር እንቁ ሴት ጃሂሉም አሊሙም ለትዳር ይመኛታል አየሽ እህቴ
መሰተር ለትዳር አያግድም

3 months, 3 weeks ago
3 months, 3 weeks ago

ሙሽራው አዲስቱን ሚስት ይዞ ጫጉላ ክፍል ገባ። ፊቷ ላይ የሸፈነችውን መቅረምያ ከፈት ሲያደርገው ፈፅሞ ያልጠበቃት ጥቁር ሴት ሁና ተመለከታት።

ተበሳጭቶ ትቷት ተኛ። ብስጭቱ ለቀናት ኩርፍያን ወልዶ ለተከታታይ ቀናት ብቻውን አደረ። ሙሽሪት በጥቁረቷ መ'ጠላቷን በተገነዘበች ግዜ፦‹‹ማሊክ! ምናልባት መልካም ነገር ከመጥፎ ስር ተሸሽጎ ይሆናል›› ብላ በቅኔ ወደ አልጋ ጠራችው። ያችን ሌት አብረው አደሩ።

ግና ጥቁረቷ ምቾት የነሳው ባል ዳግም ወደ ኩርፍያው ገባ። በዚህኛው ዙር ግን ኩርፍያው 20 አመታትን የፈጀ ነበር።

ባል ከእንዲት ቀን የጫጉላ አዳር በኋላ ከተማይቱን ትቶ ጠፋ። ከ20 አመታት ቆይታ በኋላ ባል ወደ ከተማይቱ ዳግም ተመለሰ። መዲና ሲገባ ወደ ቀዬው ከመሄዱ በፊት መስጅድ ለሰላት ገባ፤ ከመስጅዱ ውስጥ ሰዎች አንድን ሰው ከበውት በተመስጦ እና በፅሞና ሲያዳምጡት ተመልክቶ ጠጋ ብሎ ተቀመጠ።

ንግግሩ ማራኪ ነው፣ አገላለፁ እፁብ ነው፦‹‹ይሁ ምጡቅ ማን ይሁን?››  ብሎ ሀገሬውን ጠየቀ።
‹‹አባቱ ማሊክ ይባላል። ይህ ልጅ ሳይወለድ በፊት የዛሬ 20 አመት ነበር ከዚህ ከተማ የጠፋው›› ብለው የገዛ ታሪኩን ባዳ አድርገው አወጉት።

ግራ መጋባት ወረረው፣ የጥፋተኝነት ስሜት አሳፈረው። ወደ ልጁ ተጠግቶም፦‹‹እቤታችሁ ውሰደኝ›› ብሎ ተማፀነ።
ልጅም እንግዳውን ይዞ ወደ ቤቱ አመራ። ግና እንግዳው ደጅ ላይ ቁሞ፦‹‹ምናልባት መልካም ነገር ከመጥፎ ስር ተሸሽጎ ይሆናል ብለህ ለእናትህ ንገርልኝ›› ብሎ ላከው።

ልጅም ገብቶ መልዕክቱን አደረሰ። እናት በትዝታ ወደ ኋላ 20 አመታትን አወሳች፤ ቂም ስሜቷን ውጣ፦‹‹ልጄ ውጣ አባትህን ተቀብለህ አስገባው፤ ለ20 አመታት በመጥፋቱም ፈፅሞ እንዳትወቅሰው›› ብላ ትዳሯ ላይ ዳግም ህይወት ዘራች።

ይህች ጥቁር እናት ለበርካታ ዘመናት ትውልዶች የሚሸጋገር የሀዲስ ጥርቅሞችን የሰነደ ልጅም በመልካም አስተዳደግ አሳድጋ ለኡመቱ አበረከተች።

3 months, 4 weeks ago

ዘዋጅ ጋብቻ ማለት ጥሩ የሆነ መከናነቢያና መደበቂያ ነው
ላጤ ሚስት የሌለውና ያገባ በፍጹም አንድ አይደሉም ሊሆኑም አይችሉም

ትዳር የአንቢያዎች መንገድ ነው
~ ያገባ ሰው የነብያቶችን ፈለግ ተከትሏል ማለት ነው
~ እራሱንም ከሀራም እየጠበቀ ነው ማለት ነው
~ የኢማኑን ግማሽ ክፍል ሙሉእ አድርጓል ማለት ነው
~ ለሚስቱ በሚያደርገው እያንዳንዱ ነገር ከአላህ ሱበሀነሁ ወተአላ አጅር እያገኘ ነው ማለት ነው .....ይህ ብቻ አይደለም በትዳር።
ውስጥ ተዘርዝረው የማያልቁ በርካታ ጥቅሞች አሉ ታድያ ላጤና ባለትዳር ልዩነት የላቸውምን ? ወላሂ ብዙ ለውጥ አላቸው ታድያ ለምን አታገባም ወንድሜ ???
ለምን አታገቢም እህቴ ??
ለሁላችሁም ላላገባችሁ እህትና ወንድሞቸ አላህ ሷሊህ የትዳር አጋር ይወፍቃችሁ

3 months, 4 weeks ago

እውነተኛ ፍቅር

➲እውነተኛ ፍቅር ከልብ የመነጨ
ትዳር ተፈላልጎ በክብር ከታጨ!

➲ከሚሁኑት ጋር ከተገጣጠመ
ሲያምኑት ለማይከዳ በቃሉ ለቆመ
ፍቅር ይጨምራል ደጋግሞ እየጣመ!

➲በግልፅነት መንገድ እውነትን አውርቶ
ስህተት እንኳን ቢኖር በይቅርታ ትቶ!

➲ስህተትን ተረድቶ አጠፋሁኝ ብሎ
ለጠብ ሳይቸኩሉ ነገርን አቅልሎ!

➲በክብር ከያዙት እውነተኛ ፍቅር
አብሮ ዘላቂ ነው ተጀምሮም አይቀር!

➲እውነተኛ ፍቅር አክባሪውን ያውቃል
እስከእድሜ ፍፃሜ በክብር ይዘልቃል ማንነውየማልኮ አይጠፍም

3 months, 4 weeks ago

ሼይኽ አልባኒ ረሂመሁሏህ እንዲህ አሉ፦ በእውነቱ ከሆነ በዚህ ዘመን ሁለት ሚስት ማግባት በጣም ይከብዳል፡ በዚ ጊዜ ከአንድ በላይ ማግባትን (መደራረብን) አልመክርም።

4 months, 1 week ago

ኒካሕ ባሰርን በስንተኛው ቀን እጮኛዬ ሊዘይረን መጣ፣
ገና ቁጭ ብለን ወግ ከመያዛችን እናቴ መጥታ ፊት ለፊታችን ጭማቂ እና ፒዛ ነገር አስቀመጠች፣

መቼ እንደሠራችው እያሰላሰልኩ፣ ፍጥነቷንም እያደነቅኩ ነበር፣
መብላት ጀመርን፤
ባሌ ቆረሰና ወሰደ፣ …
አሁንም መልሶም አነሳ፡፡
“ፒዛው ተመቸህ መሠለኝ።” አልኩት
“ማሻአላህ ይጣፍጣል!።” አለኝ።

“ እኔ ነኝ የሠራሁት፣ ሙያችን ይህን ይመስላል፡፡” አልኩት ዐይን ዐይኑን እያየሁ፣ የወደፊቱን ቤታችንን እየናፈቅኩ፡፡

ፈገግ አለ …
“ኦ ጎበዝ ነሽ፣ ባለሙያ ሚስት ሊኖረኝ ነው።” እያለ ማዳነቅ ጀመረ፡፡

ከቆይታ በኋላ ሸኘሁትና ተመልሼ ወደ እናቴ ሮጥኩኝ፤
“ ዛሬ የሠራሽው ፒዛ ልዩ ነበር!” አልኳት ደስ እያለኝ፡፡
“ኦ እጮኛሽ ያመጣው እኮ ነው!” አለችኝ

ዉይ እናቴ! አንች ደግሞ አንዳንዴ እኮ አቤት ችኮላሽ …

ሊበላ ...
አታዋርደን ክክክክክክ ፈገግ በሉ ያጀመአ
https://t.me/SileTidarEnmekaker

Telegram

ትዳር የአማኞች ምሽግ

ትዳር የአማኞች ምሽግ

ኒካሕ ባሰርን በስንተኛው ቀን እጮኛዬ ሊዘይረን መጣ፣
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 weeks ago