Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago
?ልብ በይ‼️
??
ንብን የምታገኙዋት አበባዎች አከባቢ ነው ከዛም ስለምትቀስም ማርንም ለማነብ አስፈላጊዋ ስለሆነ መገኛዋ እንዲህ አይነቱ ስፍራ ነው። ታዲያ ግን ንብን ሽንት ወይም መፀዳጃ ቤት ድንገት ብታገኙዋት ምን ትላላችሁ⁉️
በቅርብ ጊዜ ንብ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ሆና #እዛ መጥፎ ጠረን ባለበት ስፍራ ስትበር አየሁ ? "አይይ... ድንገት ይሆናል" ብዬ ችላ ብዬ አለፍኩ ነገር ግን በንጋታው ቀጥሎ ባሉትም ቀናት በዛው ቦታ ተመለከትኩና ገረመኝ "ንብ አይደለች እዚህ ምን ትሰራለች!" ብዬ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ? በጊዜ በሂደት ግን ጌታ አንድ ነገር አስተማረኝ ?
1⃣ ለካ የውድነታችሁ ብሎም ጠቃሚ የመሆናችሁ ምስጥር ካልገባችሁ መገኛችሁ ምናምንቴው አልያም ብልጭልጩ የአለም ስፍራ ነው። ውድነታችሁን ደብቆ ጊዜና ጉልበታችሁን ይበዘብዛል? በጊዜ "እዚህ ምን እሰራለው!" ብላችሁ ካልነቃችሁ መጨሻችሁ አያምርም ልክ እንደ ንቧ ጥቅም ይዛችሁ ግን ስትባክኑ ትኖራላችሁ
2⃣ ንብ ውሎዋ ከንብ ጋር ነው‼️ የዝንቦች ሰፈር መዋል ጀመረች ማለት ከባድ አደጋ ላይ ነት ማለት ነው። ⚠️ንቁ ውሎዋችሁን አስተካክሉ፣ የት ነኝ በሉ አንድም ያለማፍራታችሁ ምክንያት ይህ ነውና‼️
"ውድነታችሁን ያቀለለባችሁ ስፍራችሁ!!"
✒️ ከደካማው ቦና ?
ለአስተያየት ? @onlyforjesus1 / 0942305601
Share? @lebamsetoch
?አስተዋይ አድማጭ ሁኚ‼️
??
እነዚህ ሁለት(2) ነገሮች በቅርቡ ገቡኝ
1⃣ ለሰው ጆሮ መስጠት ትኩረት ጊዜም መስጠት እንደሆነና ለዛ ሰው ትልቅ ቦታ እንዳለው የኔ ማዳመጥ ለካስ ለዛ ሰው አንድም እረፍቱ እንደሆነ?
2⃣ እኔ ይቺ ነች ብዬ ቀለል አድርጌ የምሰማትና ለመመለስ የምፈጥንበት ነገር ለካስ ለዛ ሰው ቀላል አይደለም ሕይወቱ ነው? ጥያቄው በኔ አእምሮ ያነሰ ቢመስልም ለዛ ሰው ግን አይደለም ስለዚህ በጥሞና አዳምጬ ማውራት እንዳለብኝ ተረዳው የቱንም ያክል ያ ሰው በጥያቄ ተሞልቶ በየቀኑ ቢጠይቅ አትሰልቹት ጆሮ ስጡት እረፍቱ ትሆኑታላቹና?
ታዲያ ይህ ማለት አስፈላጊ ላልሆነ ጥቅም ለሌለው ለሚረብሻቹ ይልቁኑስ ከሕይወት መስመር ለሚያስወጣችሁ ለዛ ጆሮ ስጡ ማለት አይደለም❌ ስለምታውቁት መሸሽ ካለባችሁ ነገር ሽሹ?♂➡️
አድምጭ ሁኚ?፣ ለሰው ጊዜ ይኑርሽ፣ ከራስሽ ሰው ይብለጥብሽ አድማጭ ሴት ማለት ዝላ ብላ ሰምታ የምታልፍ ሳትሆን ለተነሳው ላዳመጠችው ለዛ ነገር ከራሷ ስሜት አልፋ እውነተኛ ሕይወትንም የሚያቀና መፍትሄ አስተውላ የምትናገር ጥበበኛ ሴት ናት?♀
አስተውይ ⚠️ መራቅ በግልፅ ከሚታይ አላስፈላጊ ንግግር ብቻ ሳይሆን ጠቃሚነት ያለው ይዘት ኖሮት በሳቅና ጨዋታ ከሕይወት መስመር ሊያስወጣሽ ካለውም ጭምር እንጂ‼️
✒️ ደካማው ቦና ?
ለአስተያየት ? @onlyforjesus1 / 0942305601
share ? @lebamsetoch
?ያልተኖረ......አለሽ‼️
??
በትላንት መጥፎ ትዝታ ስር ሆነው ዛሬያቸውን መኖር የከበዳቸው ነገያቸውም ላይ ተስፋ የቆረጡ ጥቂቶች አይደሉም? ከትላንት የተነሳ መኖር መጥላት፣ ራስን በኩነኔ ውስጥ ማቆየት፣ ችላ ባይነት ለነገ የማሰብ መንቀሳቀስ ሞራል ማጣት ላይስተካከል እንደተበላሸ እያሰቡ በቁጭት ውስጥ ራስን መሰወር የተለመደ ነው?
ልብ በሉ የመኖር ትርጉምን ለማግኘት "በነገ ልብን መጣል ተስፋ ማድረግም መልካም ነው!" ከትላንት ይልቅ ነገን ማሰብ ለቁስላችሁ ፈውስን ያመጣል። አንቺ ሴት ?
ገና ያልተኖረ ነገ አለሽ ያልተነካ?♀ ይልቅስ ትላንትን ልትበቀይ ምቹና ሰፊ ጊዜ አለሽ። እንዳበቃላት ሴት የምን ተስፋ መቁረጥ ራስንም በኃዘንና በኩነኔ መደበቅ ነው? ነገሽ እኮ የአንቺ ነው ማንም አልቀማሽም የምን ለቅሶ ማብዛት ነው ታዲያ ቀና በያ ቀና ለማለት ብዙ ምክንያት አለሽ "ከትላንትሽ ይልቅ ነገሽ ትልቅ ነውና!!"
ከትላንትሽ ተማሪ እንጂ አታግዝፊው "ነገን አተልቂ" ሁሌም የተሻለ ነገ አለና? እንኳን አንቺዋ ሰው በጌታ መልክና ምሳሌ የተፈጠርሽዋ ቀርቶ ዛፍ እንኳ ቢቆረጥ ሊያቆጠቁጥ ሊያበቅል ተስፋ የለውምን ስለዚህ ቀና በይ "ያልተኖረ ነገ አለሽና‼️"
⚠️" ካስተዋሉ ለመኖር ከትላንት የነገ ምክንያት ይበልጣል!!" ?
✒️ ከደካማው ቦና ?
ለአስተያየት? @onlyforjesus1 / 0942305601
share? @lebamsetoch
⚠️ ይነበብ??
ቲሸርት ስለብስ ምናልባት የፊቱን ወደኋላ ደግሞ የኋላውን ወደፊት አዙሬ ቢሆን "ውይ ይህ ልብስ አይሆነኝም በቃ አልያም አይጠቅምም" ብዬ በፍፁም አልቀደውም ደግሞም አልጥለውም ይልቅስ የሚስተካከል ነውና ተረጋግቼ እንደገና አዙሬ ለብሰዋለው ይስተካከላልና አልጥለውም
አላውቅም ምን እንደሆነ ደጋግሞ ሕይወታችሁ ላይ እየመጣ ያሰለቻችሁ ነገር!?♂ አላውቅም "የኔ ነገር አይስተካከልም ብላችሁ ተስፋ እየቆረጣችሁበትና ደግሞም የቆረጣችሁበትን!" ነገር ምን እንደሆነ። ነገር ግን በርግጠኝነት አውቃለው?
⚠️" ያበቃለት ሕይወት እንደሌላችሁ!"
ላይስተካከል ተበላሽቶብኛል የምትሉበት ያ ጉዳይ ምንድን ነው⁉️ የእውነት ሁሉን ላይችል ከእግዚአብሔር በላይ ትልቅ አለን❕
አበቃልኝ ወድቄያለው አልነሳም ያላቹበት ነገር ምንድን ነው⁉️ የእውነት የወደቀ አይነሳም የሳተስ አይመለስምን❕
በራሳችሁ ተስፋ ያስቆረጣችሁ ምንድን ነው⁉️ የእውነት በሰው ተስፋ የማይቆርጥ ሩህሩህ ጌታ እንዳለ አታውቁምን❕
ከእናንተ የሚጠበቀው አንድ ነገር ብቻ " መረባችሁን በጌታ ላይ መጣል" ግድ የለም እህቴ የተበላሸ ነገ የለሽም በራስሽም ተስፋ አትቁረጪ ላይስተካል የተበላሸ አንዳች የለምና❌
⚠️" ያልተኖረ ነገ አለሽ!"?
✒️ ከደካማው ቦና ?
ለአስተያየት @Onlyforjesus1 / 0942305601
Share @lebamsetoch
አንድ ሰው ለሁለት ሴቶች ጠቀም ያለ ገንዘብ ሰጣቸውና "ላተረፈ" መልካም ነገር ተዘጋጅቶለታል ይላቸዋል ሁለቱም ይስማሙና ድርሻቸውን ይዘው ወደቤታቸው ይሄዳሉ።
አንዷ የተቀበለችውን ገንዘብ ምን ላድርግበት ብላ ስታስብ ትቆይና "እንዴ እስከ መቼ በባለቤቴ ራስነት የበላይነት ተመርቼ እቆያለው ራሴን ለውጥና እኔው እመራለው እቆጣጠራለው ያለውን ነገር" ትልና በገንዘቡ ሁሉን አድርጋ ሃብታም ሆና የበላይነት በሚሰማው ስሜት ተገዝታ ባሏን ወደታች እየተመለከተች ራስ በመሆን በመሻት ተይዛ እንዲህ ነው እንጂ ማትረፍ እያለች መልካሙን ሽልማት ለመቀበል ተዘጋጀች?
ሁለተኛዋ ደግሞ "ገንዘቡን ለምን ባለቤቴ ዘንድ አልወስደውምና አናወራበትም ራስ ነው" ትልና እንዳሰበችውም ወስዳ ፊቱ ቁጭ ታደርግና መመካከር ትጀምራለች የሚያስፈልጉትን ነገሮች ቦታ ቦታ አስይዘውም ይነሳሉ ራስነቱን አምነ ስለተቀበለች እርሱ እንዲያስተዳድር እንዲመራ ፈቅደችለች በምላሹ እሱም በመውደዱን በብዙ ገለፀላት አሳያትም ከቤቱ ያለፈ ህልሟን እንድትፈፅምበት ብርታት ሆናት። ሁለተኛይቷ ሴት ይህን አድርጋ መልካሙን ሽልማት ለመቀበል ተዘጋጀች?♀
ታዲያ ጊዜው ደረሰና ሰጪው ምላሹን ሊቀበል ደግሞም ሊያመሰግን መጣ ሁለቱም ትርፌ ነው ያሉትን አሳዩ እርሱም "ለሁለተኛይቱ ከሁሉ የሚበልጠውን አድርገሻል በሁሉ ዘንድ የምትመሰገኚው አንቺ ነሽ ትርፍ ማለት የተፈጠሩበትን አላማ ፈፅሞ ከማለፍ ባለፈ የአምላክን ቃል ተግባራዊ ማድረግ ራስ አድርገች በመቀበልሽ ያስደስተሽው ፈጣሪን ነው" ይላትና ሁሉም ሰው የሚያየውን ውድ የሆነ የወርቅ አክሊል ያደርግላታል?
አንቺ እህት በወንድ አልያም በባል የቤት ራስነት ደስ ይበልሽ አምነሽውም ተቀበይ በረከትሽ ምስጋናሽ ያለው በዛ ውስጥ ነው። አሁን ላይ የዘመናዊነት መልክ ለብሶ እንደመጣውና የብዙዎችን ሴቶች ልብ እንዳሸፈተው እኩልነት ነው እንደፈለኩ መሆን ከሚባል ነገር ራቂ በጌታ ዘንድ የእኩልነት ጥያቄ የለም ነገር ግን ድርሻ አለሽ በታማኝነት ከአንቺ የሚጠበቀውን መልካሙን መፅሃፍ ቅዱስ የሚልሽን ፈፅሚ አደራ‼️
"የሚገባትን ሽልማት ስጧት ፤ ስራዋም በአደባባዩ ያመስግናት" ምሳ 31,31
✒️ ከደካማው ቦና ?
ለአስተያየት? @onlyforjesus1 / 0942305601
Share? @lebamsetoch
?ልብ በይ??
?አስተዋይ ሴት ሁኚ "ስለ ነገ ምን አገባኝ!?♀" እያሉ በደንታ ቢስነት ራሳቸውን ጥለው በጭፍን ከሚራመዱቱ መኃላ ቆመሽ አትገኚ! ማስተዋል ስለነገም ማሳብ ህይወት ነውና‼️
? ገላሽ ሰውነትሽ ውድ ነው ውድ ተብለው ሚዛን ከተመዘነላቸው ወርቅ አልማዝ እንቁ የላቀ፤ እንኳን ለሽያጭ ለድርድርም ሊቀርብ የማይገባ ታዲያ ራስሽን ጠብቂ ሰውነትሽን ደብቂ ሸፍኝም ሰውነትሽን ለእግዚያብሄር ክብር አውይ‼️
? መድከም፣ መዛል መውደቅ ሞት አይደለም የተሻለ ነገ አለ ተስፋ አትቁረጪ ተስፋ በአንቺ ሁሌም የማይቆርጥ ጌታ አለና‼️
? ጓደኛ ምረጪ "ክፉ ባለንጀራ መልካም ፀባይሽን ከማበላሸት ያለፈ ከህይወት ነውና የሚያጎድልሽ" ዙሪያሽ የከበቡትን ሰዎች በንቃትና በጥበብ ተመልከቺ መልካም የመሰለው ምክራቸው ከወደ ገደሉ ነውና ምሪቱ‼️
? ታላላቆችን አክበሪ ለታናናሾችሽም ታዘዢ ቦታ ስጪ ነገ ላይ ሃያል ሴት ትሆኛለሽና‼️
? ለምትሰሚውና ለምታይው ነገር ተጠንቀቂ⚠️ ጆሮሽን ለማን እንደሰጠሽ እውቂ! የምትሰሚውና የምታይው ወይ ሊያጠፋሽ አልያም ሕይወት ሊሆንሽ ነውና‼️
⚠️ "ከክፉ ሽሺ ፅድቅን ተከተይ ጌታን ደስ የሚያሰኘውን አድርጊ በምድር ላይ በምክንያት የፈጠረሽ እግዜር ደስ ይሰኝብሻልና‼️"
ከደካማው ቦና ?
ለአስተያየት? @onlyforjesus1 / 0942305601
Share? @lebamsetoch
?አንቺ ሴት??
ይህን የመሰለ ውበትና ቁመና ይዘሽ የምን መፍዘዝ ቀልጠፍ ማለት ነው እንጂ አማራጭ እንደሆነ በዝቷል ብለውሽ ይሆን?⁉️
ጊዜሽን እድሜሽን ተጠቀሚ እንጂ ስንቱ መሰለሽ በዚህ መንገድ ሄጆ ሃብትን ያገኘ ብለው ገላሽን ስለመሸጥ አውግተውሽ ይሆን?⁉️
ከህልምሽ ለመድረስ ከፈለገግሽ ይህ ነው መንገዱ ብለው እያባበሉ ከአለም ሊቃላቅሉ አቻኮሉሽ?⁉️
አንቺ ሴት ልብ በይ ይህንንም እወቂ የምትኖሪው ለራስሽ አይደለም የራስሽም አይደለሽም የራሱ ያልሆነ ደግሞ ለራሱ ለፈቃዱ አይኖርም!! ዛሬ አቃለው ምንም ያውሩሽ አቋምሽና ውሳኔሽ እንዳይለወጥ❌ ምናልባት ዛሬ በማጣት ውስጥ ብትሆኚ እንኳ ፅኚ ለፈጠር እግዚያብሄር መኖርሽ በቅድስና መመላለስሽ ከክፉው በመሸሽሽ አሸናፊ ነሽ ስኬት ማለት ያ ነውና?
?መልካም የመሰለው ምክራቸው ገዳይ ነውና ከክፉ ጓደኛ ሽሺ‼️
?ፈሪሃ እግዜር ከሌለባቸው ለአንቺም አይሆኑምና ራቂ ቆሎ አምልጪ!!
?ውበትሽና ጊዜሽን ለጌታ አውይው ክስረትን በህይወትሽ ዘመን አታይምና‼️
?አንቺ ሴት እምቢ ማለትሽ መፍዘዝን የሚገልፅ አይደለም ንቁ መሆንሽን እንጂ ህይወትሽን ከማትረፍ ባላይ በዚህ መጨረሻው ዘመን ምንም የለም "በገገማነትሽ" ቀጥይ ነገሽ መልካም ነውና‼️
?ነገሽን አልተባለሸም ዛሬ አይሆንም ያልሽው ነገ በአደባባይ ያከብርሻል፤ እናንተ ግን በክፉ ጓደኛና ጊዜዬ ሄደብኝ ብላችሁ በዚህ ክፉ መንገድ የምትጓዙ ቀኑ ሳይመሽ ተመለሱ ለእናንተም ቢሆን የተባለሸ ነገ የላችሁም ግን ወስኑ‼️
ከደካማው ቦና ?
ለአስተያየት? @onlyforjesus1 / 0942305601
Share? @lebamsetoch
⚠️መልስ በተነሳው ጥያቄ ላይ??
መሰረት ጥለን ብንጀምር ምን ይመስላችኋል መሰረታችንም " ለእግዚአብሔር የሆነ ለአንቺም ይሆናል‼️"
አንቺን ለመውደዱ ማረጋገጫሽ ይህ ነው ብዬ አምናለው "እግዚያብሄርን መፍራቱ!" ልብ በይ የእርሱ አንቺን መውደድ የሚለካው ለእግዚአብሔር ባለው ልብ ነው!! ለእግዚያብሔር ያልሆነ በፍፁም ለአንቺ አይሆንም❌
ለአንቺ ያለውን እንክብካቤ ከሌላው ጋር ማስተያየት ማነፃፀር ውስጥ ከገባሽ ልክ አይደለሽም እንክብካቤ መውደድን አስቀድመሽ በራስሽ ልትረጂ ልታውቂ ይገባል ያኔ ያወቅሽ ለት ለመኖር አይከብድሽም እንኳን ለአንቺ ለሌላው ትተርፊያለሽ
ከትዳር በፊት መሳሳም፣ አብሮ መተኛት፣ አላስፈላጊ የአካል ንኪኪ የእንክብካቤና የመውደድ አካል ሳይሆን ለጥፋት መንደርደሪያ ለውድቀትም መንገድ መነሻ ነው የሆነው አካል ነው!! ለአንቺ ማሰቡን ማረጋገጫ ስለ ነገሽ ማሰብ ነው የነገ ሰው መሆኑ የነገ ሰው ደግሞ አስተዋይ ነው ህይወትን ያያልና?
አንቺን ለመውደዱ ለማወቅ "ለእግዚአብሔር ባለው ልብ መዝኚው!" ፈራለው ማለቱ ብቻ ሳይሆን እየኖረ የሚያሳይሽ መሆንን ተመልከቺ ከሁሉ አስቀድመሽ ግን "ራስሽ ላይ ስራ ስለ እንክብካቤና መውደድ ግንዛሬ ይኑርሽ ሁለት አይነት መውደድና እንክብካቤ አለና የላይኛውን መርጠር በውስጥ ካሳደርሽ እድለኛ ሴት ነሽ ህይወትን መርጠሻልና የተበላ ነገር አይኖርሽም‼️"
ከደካማው ቦና ?
ለአስተያየት? @onlyforjesus1 / 0942305601
Share? @lebamsetoch
1.ፍቅረኛሽ አንቺን መውደዱንና ማፍቀሩን ከሚያሳይበት መንገድ ዋናው ላንቺ ያለው አመለካከት እና ዋጋሽን ዝቅ አርጎ አለማየቱ ነው ያከብርሻል ጊዜውን ትኩረቱን ከዚያም ሲያልፍ ራሱን እንኳን አሳልፎ ይሰጥሻል ሚደብቅሽ ምንም ነገር አይኖርም በዚ ማወቅ ትችያለሽ
2.ለዚ ጥያቄ ዋናው መልስ እነዚህ ከላይ ጥያቄው ላይ ያሉት ሃሳቦች የፍቅር መለኪያ ሊሆኑ አይችሉም B/C አንድ ወንድ ጊዜያዊ ስሜቱን ለማርካት ሲል ፈፅሞ ከማያውቃት ሴት ጋር እንኳን ገንዘብ ከፍሎ ይትኛል ይሳሳማል...... ያ ማለት እቺን ሴት ይወዳታል ማለት ነው??አይደለም ይልቅስ ለጊዜያዊ ደስታው ብሎ እንጂ ስለዚህ ይሄ የፍቅር ልኩም ትርጉሙም መሆን አይችልም ማለት ነው::
በእርግጥ የእውነት የሚወድሽ ወንድ ከራሱ ስሜት እና ጊዜያዊ ደስታው ያንቺን ማንነት እና ስብዕና ያከብራል ስለሚወድሽም በትግስት እስከ ጋብቻ ቀናችሁ ድረስ ራሱን በመግዛት እና በቅድስና ይጠብቅሻል ::
መሳሳም መነካካት አብሮ መተኛት የፍቅር መለኪያ አይደሉም::?
3.እንደሚወድሽ ማረጋገጫው የጀመራችሁት ፍቅር ግቡ/መጨረሻው ትዳር እንደሆነ የሚያስብ እና ይሄም ፍቅር ግቡ ጋር እንዲደርስ ዋጋ የሚከፍል ሰው ከሆነ
ከእርሱ ጋር ያለሽን የፍቅር ግንኙነት የሚያከብር
አንቺንና በዙሪያሽ ያሉትን ሰዎች የሚያከብር
ትኩረቱን እና ጊዜውን የሚሰጥሽ
በተጋጫቹ ጊዜ ሁሉ መለያየትን አማራጩ የማያደርግ ነገሮችን ለማስተካከል ዋጋ የሚከፍል ከሆነ ይወድሻል::
ብፁዓን✍️
1ኛ እጮኛዬ እንደሚወደኝ በምን አውቃለው??
➡️ለጌታ ነገር እና መልካም ሴት እንድሆን በበጎ መልኩ ካበረታኝ
➡️በጌታ ቃል ካነፀኝ
➡️አላስፈላጊና ጌታን ማያከብር ስፍራ ካላቆመኝ
➡️እግዚአብሔርን እና ቤተሰብን ከወደደ እና ካከበረ
➡️ስለ ወደፊት ቤቱ ሲያወራ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማስቀደም/በፀሎት አብዝቶ ሚቃትት እና ሚፀልይ ከሆነ
➡️ስለ ትዳር Biblical የሆነ ግንዛቤ ካለው for sure ይወደኛል
2ኛ የተጠቀሱት እንክብካቤ መሳይ ነገሮች ግን "ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው" እንደሚባለው አይነት ነው። አንድም እንደሚወደኝ ምረዳው ከነዚህ physical ንክኪዎች ነፃ ሲሆን ነው ምክንያቱም ለገላዬም ለጌታ ቃልም ክብር ስላለው ነው።
ተሊሌ
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago