Red-8

Description
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 7 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 months ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 week, 1 day ago
***🌍*** = ***🎶***

🌍 = 🎶

1 week, 6 days ago
ባለቅኔ ነበርኩ

ባለቅኔ ነበርኩ
ባለኝ ሰዓት ቅኔ
ያ...ኔ!

ቅኔ ይሏት እርግብ
አፍኜ ስመግብ
ስታዜም ስሰማት
መዝሙሯን ስቀማት
ቀምቼ ሳፏጨው
የሷን እየቀዳሁ፡ አድማስ ላይ ስረጨው፤
የሰማ ታማሚ፡ መስሎት የፈለቀኝ
ወደኔ እየመጣ፡ ፈውስ ሲጠይቀኝ፤
እሷ የምትለውን፡ ስሰማ ሳቀብል
ከሷ የሚፈሰውን፡ ስቀዳ ሳፀብል
የዳነው መስካሪ፡ ታምሬን ሲነዛ
ደጄን የሚናፍቅ፡ አማኝ እየበዛ
ለፀጋ ለስሜ፡ ሲመታለት ድቤ
በድንገት አምልጣኝ፡ በረረች እርግቤ።

ሄደች ከነድምጿ፡ በስም አስቀርታኝ
ሄደች ከነፈውሷ፡ ከገድሌ ጋር ትታኝ
የምበትንላት፡ ጥሬ ቀርቶኝ ከጄ
ቢረክስም በዜማ የፀደቀው ደጄ
በፈውስ ናፋቂ፡ ሰርክ ይጨናነቃል
ምስኪን! ኪን እርግቤ
እንኳንስ መሄዷን ፡መኖሯን ማን ያውቃል?

ብቻዬን አዘልኩት፡ አግኝቶ ማጣቱን
ጸጋው የተቀማ ፡ስም ሆኖ መቅረቱን
ማቃቴን አፍኜ፡ ብቻዬን ታመምኩት
በነበር ስወደስ ፡መቻልን ቃተትኩት፥

ግን አልሆነልኝም
አልጮህ ድምፅ የለኝም
ያድናቂዬ ድቤ፡ ዜማው ይበልጠኛል
አልጠፋ እንደርግቤ ማን ክንፍ ይሰጠኛል?
ታዲያ ከዚህ ስቃይ፡ ማን ያስመልጠኛል?

እውነት!

ባለቅኔ ነበርኩ፡ ያ...ኔ!
ቅኔ ይሏት እርግብ፡ እያለች ከጎኔ
ዜማዋ ሲያደምቀኝ ትንፋሿ ሲሞቀኝ
አርፎ እንደማጣጣም፡ እየቀዳሁ ስቀኝ
ያየ ሲያጨበጭብ፡ የሰማ ሲያደንቀኝ
ስጨምቃት ተጨንቃ የምታስጨንቀኝ
አንድ እርግብ ነበረች፤
አሁን ግን የለችም!
ለጠየቀኝ ሁሉ ፡እሺ ስል በርራለች።

ልክ እንደዛ ተረት፡ የልጅ መጫወቻ

ባለቅኔ ነበርኩ፡ አሁን ግን ፍራቻ
ሁሉን ነገር ላጣው፡ የቀረኝ ስም ብቻ።

Red-8

2 weeks, 3 days ago
ወንድም Gebrela Shewakena «ረስቶለታል!» የሚለው ግጥሜ …

ወንድም Gebrela Shewakena «ረስቶለታል!» የሚለው ግጥሜ ላይ የሲኒማ ነፍስ ዘርቶ አስደነቀኝ!
ሲኒማቶግራፊውንና ዳይሬክቲንጉን «Gebrela G Films»
ትወናውን Geza Geza Z Dbremrte
ዝማሬውን @ምንተስኖት ፈቀደ
ንባቡን እኔ ተወጥተነዋል።

እኔ እንደወደድኩት... እናንተም አይታችሁ ውደዱ...
የሰራውን ልጃችንንም አበረታቱ....
ሊንክ

https://youtu.be/TxjrBUjF-0A?si=l5R1Yij0lDPtBl0I

1 month ago
ለምን ይመስለናል

ለምን ይመስለናል
የሚሆነው ሁሉ የነበር የነበር ?
ይኖራቸው ይሆን
የሚመጣው እና ያሳለፍነው ድንበር ?
እየኖርን ያለነው
አዲስ የመሰለ ቀን እየቆጠርን
ስለረሳን ይሆን
ካሳለፍነው ጋራ እንደተቃጠርን?

እየኖርን ያለነው እንዳልነበረ ሰው
የሚመጣው መጥቶ እስክናስታውሰው
አይተን እስኪገባን ያላወቅነው ነገ
ባለፍንበት ትናንት የተደነገገ
ካከረምነው ጠላ፡ ከድፍድፍ ያደገ
ቅራሪ መሆኑን ገና ያልተቀዳ
ደርሶን ፉት ብለን እስከምንረዳ
ይሆን ወይ በተስፋ
ቀኑን የምንገፋ?

ይሆን ወይ በተስፋ ባዶ ጣሳ ታቅፈን
እሞላለሁ ብሎ ደጁ ያሰለፈን
የጊዜ አሳላፊው ሰክረን እንዳለፈን
ረስተነው እንጂ የምንጠብቀው
ተኑሮ ይሆናል ገና ያልታወቀው።

1 month ago

ዓመት በዓላት ወደልጅነታችን መልሰው የሚያስገቡ መስኮቶቻችን ናቸው።

በተለይ በተለይ ገና...

የክፍል የገና በዓል ዝግጅታችን፥ ቀኑ እስኪደርስ ጉጉታችን፡ የክፍል ክፍል ፉክክራችን፡ የዴስክ ላይ ፅድ እና ሪባኖቻችን፥ የገና መዋጯችን፥ ዛፋችን፥ የምንጠራቸው አስተማሪዎቻችን፡ ምንሰራው ድራማ፡ የብላክቦርድ የቾክ ዲዛይንና "ሜሪ ክሪስማስ"ፅሁፋችን፡ የገና መዝሙራችን፥ ድፎ ዳቦ፥ ለስላሳ... ከዛ ወደቤት ተመልሰን የምናከብረው በዓል ትዝታው...

እንኳን አደረሰን

1 month ago
Red-8
3 months ago

"ጨው ሆኖ መቅረት"
የግጥም ቪዲዮ ተከታተሉ...

https://vm.tiktok.com/ZMh4qj1AX/

3 months, 1 week ago
3 months, 2 weeks ago
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 7 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 months ago

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 1 month, 2 weeks ago