A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 2 months, 1 week ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 3 weeks, 5 days ago
አዳራችሁ በአማንና በኢማን የተሞላ ይሁን፣ የነገ ሰው ይበለን።
ፊልም ውሸት እንደሆነ እያወቀ የሚያለቅስ ቁርዓን እውነት መሆኑን እያወቀ የሚያፌዝና ለህጉ የማይገዛ ትውልድ ታሪክ አይሰራም::
@Furqan_Oficial
➞የቀኑ ➌ቱ ሐዲሶች‼️
1) #ከደጃል ፈተና ለመጠበቅ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿مَن حَفِظَ عَشْرَ آياتٍ مِن أوَّلِ سُورَةِ الكَهْفِ عُصِمَ مِنَ الدَّجّالِ.﴾
“ከምዕራፍ አልካህፍ የመጀመሪያ አስር አንቀፆችን በጭንቅላቱ የሸመደደ ከደጃል ፈተና ይጠበቃል።” 📚** ሙስሊም ዘግበውታል: 809
2) #ሲገናኙ መጨባበጥ!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿ما من مُسلمَينِ يلتقيانِ فيتصافحانِ إلا غُفر لهما قبل أن يفترِقا﴾
“ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው አይጨባበጡም
ከመለያየታቸው በፊት ወንጀላቸው የተማረላቸው ቢሆን እንጂ።” 📚 ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 525**
3)አቡ ሁረይራ እንዲህ አሉ:-
«አንዴ ነብዪ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሆነን ሰው በሆዱ በኩል ተደብቶ ተኝቶ አዩትና እንዲህ አሉት:- ይይች አተኛኘት አላህ የማይወዳት የአተኛኘት አይነት ነች አሉት»።
ምንጭ:-📒*📙*📕 ሶሒሁ ቲርሚዚ (2768)**https://t.me/Furqan_Oficial
*⭐️ሱረት ዩሱፍ*
☄️"አህሰነል ቀሰስ"ብሎ አላህ ተባረከ ወተዓላ ገልጿታል።
?በቁርዐን ውስጥ ብቸኛዋ ታሪኩን ጀምሮ የሚጨርስ ሱራ ነው።
✍️ሙሉውን ስለ ነብዩላህ ዩሱፍ አለይሂ ሰላም ታሪክ ነው የምትተርክልን።
⭐አተራረኩ አጂብ በሚያሰኝ ውብ በሆነ መልኩ አላህ ተባረከ ወተዓላ ተርኮልናል።
ታድያ ይህችን ሱራ ተደቡር ልናደርግ ወደድን!
?በተደቡር ፅሁፉ አጂብ በሚያሰኝ አገላለፁ የምናውቀው ወንድማችን #khrebin ሱረት ዩሱፍን ሊያስቃኘን ወዷል።
?የት ነው ምናገኘው ካላቹ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ላይ join በሉ
“በወርቅ እና በብር መጠጫ አትጠጡ። በትሪዎቿም አትመገቡ። እርሷ ዱንያ ላይ (በቀጣዩ ዓለም) ለእነርሱ (ለካህዲያን) ናት ለእኛ ደግሞ በአኼራ (በቀጣዩ አለም) ነው።”
ረሱል [ ﷺ ] እንዲህ ብለዋል፦
? ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 5426
በመስጠት ውስጥ ካለው በበለጠ እርካታ....ሌሎችን በማስደሰት ውስጥ ካለው በበለጠ ደስታ የትም የለም ። እኔነት ጠባብ መንገድ ነው ... ድብርት ...ወናነት እና ትርጉም የሌለው ህይወት ከዚህ ጠባብ መንገድ የተገኙ መጥፎ መሳፈሪያዎች ናቸው ። እመኑኝ የሌሎችን ቁስል በማከም ውስጥ፤ የሌሎችን ሸክም በማቅለል ውስጥ ..ሌሎችን በመርዳት ውስጥ የመኖር ጣዕም አለ ። ለሌሎች ፍቅር በመስጠት ውስጥ ተስፋ አለ ...ለሌሎች በመኖር ውስጥ መኖር አለ !
ተውሂድ ማለት ምን ማለት ነው ¿
?ስለ ዒዳ ቲኒሽ ነገር...... ¡¡
?ዒዳ ማለት አንዲት የተፈታች ወይም ባሏ የሞተባት ሴት ሌላ ሰው ማግባት የምትከለከልበት የጊዜ ገደብ ሲሆን በቁርኣንም፣ በሐዲሥም፣ በኢጅማዕም የፀና ሐቅ ነው።
የወር አበባ የምታይ ሴት የዒዳዋ ዘመን ሶስት የወር አበባ ጊዜ ነው። ከነጭራሹ ግንኙነት ያልተፈፀመበት ኒካሕ ከሆነ ግን ዒዳ መቁጠር አይጠበቅባትም። መመለስም ከፈለገ ሙሉ ለሙሉ አዲስ ኒካሕ ነው የሚጠበቅበት።
ነፍሰ ጡር ሴት ዒዳዋ የሚጠናቀቀው ስትወልድ እንደሆነ ቁርኣን ውስጥ ሰፍሯል። [አጦ፞ላቅ: 4]
ቢያስወርዳትስ? ያስወረዳት ፅንሱ 4 ወር ከሞላው በኋላ ከሆነ ዒዳው በዚያው ይጠናቀቃል። ያስወረዳት ፅንሱ ቅርፅ ማውጣት ከጀመረበት ጊዜ በኋላ ከሆነም ዒዳው በዚያው ያልቃል።
ባሏ የሞተባት ሴት ዒዳዋ 4 ወር ከ10 ቀን ነው። የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል:–
እነዚያም ከናንተ ውስጥ የሚሞቱና ሚስቶችን የሚተዉ (ሚስቶቻቸው) በነፍሶቻቸው አራት ወሮች ከዐስር (ቀናት ከጋብቻ) ይታገሱ፡፡ [አልበቀራህ: 234]
ሚስቱን ለአንዴ ወይም ለሁለተኛ ጊዜ ፈቶ ዒዳ እየቆጠረች ባለችበት ሁኔታ እሱ ቢሞት ዒዳዋን ከሞተበት ጊዜ ጀምራ እንደገና ትቆጥራለች። ንብረት ካለውም ትወርሳለች።
ፍቺው መመለስ የማይቻልበት የመጨረሻ ፍች ከሆነ ዒዳዋን ሳታጠናቅቅ ቢሞትም የጀመረችውን ብቻ ነው መጨረስ የሚጠበቅባት።
በአንድ ወይም በሁለተኛ ፍች የተነሳ ዒዳ የምትቆጥር ሴት ዒዳዋ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከቤቷ መውጣት የለባትም። ግልፅ ብልግና ካልታየ በስተቀር ከቤት ማስወጣትም አይፈቀድም። [አጦ፞ላቅ: 1]
በዚህ ሁኔታ ላይ መመለስ የሚቻልበት ፍች ላይ ያለች ሴት ለባሏ ፊቷን መግለጥ፣ መዋዋብ፣ ከሱ ጋር ማውራት፣ ተገልሎ መቀመጥ ትችላለች። ግንኙነት የሚፈፀመው ግን ከመለሰ በኋላ ወይም በመመለስ ኒያ ሲሆን ነው።
በአንድ ወይም በሁለተኛ ፍች የተነሳ ዒዳ የምትቆጥር ሴት ዒዳዋ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከልብስም ከጉርስም ለሚስቱ እንደሚያደርገው ሊያሟላ ይገባዋል። ዒዳዋ እስካልተጠናቀቀ ድረስ በቀላሉ መመለስ ይችላል። ዒዳዋ ከተጠናቀቀ በኋላ መመለስ ቢፈልግ ግን አዲስ ኒካሕ ነው መስፈርቱን አሟልቶ የሚያስረው።
ለሶስተኛ ጊዜ ከፈታ ግን ከዚህ በኋላ መመለስ የሚችለው በትክክለኛ ኒካሕ ሌላ ሰው አግብታ ከተፈታች ብቻ ነው። ለቀድሞ ባሏ ሐላል ለማድረግ ታስቦ የሚፈፀም ጊዜያዊ ጋብቻ እጅጉን የተወገዘ ነው። አዋቂው አላ፞ህ ነው።
[ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 18/2012]
®IbnuMunewor
النفس المطمئنة(የረጋች ነፍስ)
ያላችሁ ልክ
አላህ የኛንም ነፍስ እንዲህ ከተባሉት ነፍሶች አንዱ ያርግልን!!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿صلاةُ الرجلِ تطوُّعًا حيثُ لا يراهُ الناسُ تَعدِلُ صلاتَهُ على أعينِ الناسِ خمسًا وعشرينَ.﴾
“ሰውዬው ሰዎች ሳያዩት የሚሰግደው ትርፍ (የሱና ሰላት) ሰዎች አይተውት ከሚሰግደው ሰላት በሃያ አምስት ደረጃ ትስተካከላለች (ብልጫ አለው)።”
? ሶሂህ አልጃሚ: 3821
A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 2 months, 1 week ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 3 weeks, 5 days ago