?©« ዲነል ኢስላም»

Description
??አል ተውሒዱል ኑር ?

?አጫጭርና ✔
አስተማሪ ?
ፁሑፎችን
?የሚተላልፍበት
ቻይናል
ነው ።✔
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

3 года, 1 месяц назад

ይህ የአብዱረሂም አህመድ መልእክት ነው :: ፌስቡክ ለ 3 ቀናት ያህል ምንም አይነት ፖስት ማድረግ እንደማልችል በመግለፅ አግዶኛል :: የቴሌግራም ቻናሌን ጆይን በማድረግ በሱ እንገናኝ :: ፌስቡክ ላይ ያላችሁ ይህን መልእክቴን ኮፒ ፔስት በማድረግ ሰዎችን ወደ ቴሌግራም ጋብዙልኝ ሊንኩን በመጫን ጆይን ያድርጉ https://t.me/abdure99

3 года, 2 месяца назад
3 года, 2 месяца назад

ቃላት የማይገልፀው ደግነት ...!

አሚናት ሰዒድ መንታ ልጆች ነፍሰ ጡር ሁና በመውለጃዋ መቃረቢያ በጦርነቱ ምክኒያት ከጊራና ወደ ደሴ ተፈናቀለች :: በዚህ ከባድ ጊዜ አውላላ ሜዳ ላይ ወደቀች :: ነገር ግን ደግ የሆኑ እናት አገኘች ::
እትዬ እናኑ ተፈራ ከአሚናት ጋር ትውውቅም ሆነ ዝምድና የላቸውም::የነፍሰ ጡራ መንከራተት አሳዘናቸው:: እናም ሆስፒታል ሂዳ በኦፕሬሽን እንድትወልድ አደረጉ:: ከዚያም አልፈው ገንፎውንም ሙቁንም ይዘው ተመላልሰው ተንከባከቡ:: ከዚያም ከሆስፒታል አውጥተው ቤታቸው መንታ ልጆቿን እንዲሁም ሌሎች ሰተፈናቃዮችንም ጨምረው እየተንከባከቡ ነው ::

እናኑ ተፈራ አቅም ባይኖራቸውም ደግነታቸው እናትነታቸው በደካማ ኑሯቸው ላይ የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ነው:: ሚዲያ ላይ የቀረቡት ስለደግነታቸው ሊናገሩ ሳይሆን እኔ የምችለውን እያደረኩ ነው የምትችሉትን አግዟት ባታግዟትም የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ ለማለት ነው :: እትዬ እናኑ ተፈራ
በዚሁ ሁሉ መከራ መካከል እምነት ያልገደበው ንፁህ ሰብአዊነት እና ደግነት ዛሬ በህዝባችን መካከል መኖሩ ተስፋችንን ያለመልማል ::

አሚናት ሰዒድን ማገዝ የምትፈልጉ በውስጥ ፃፉልኝ የሚያገናኛችሁን ሰው አመቻቻለሁ:: ሌሎችም የባሰባቸው አሉ::

የሃሩን ሚዲያ ባልደረቦች ከእትዬ እናኑ ጋር እና ከመንታ ልጆቿ ጋር ያደረጉትን ቆይታ እነሆ ሊንኩን ከፍታችሁ ተከታተሉ https://youtu.be/7wMLRDP6lKU

(አብዱረሂም አህመድ)

YouTube

አስገራሚ ታሪክ መንታ የወለደችው ተፈናቃይ እና ያስጠጓት ደግ ሴት በደሴ ||ሃሩን ሚዲያ ልዩ ዝግጅት

3 года, 3 месяца назад
በአማርኛ ተፅፎ ወደ ዐረብኛ የተተረጎመ የመጀመሪያው …

በአማርኛ ተፅፎ ወደ ዐረብኛ የተተረጎመ የመጀመሪያው ኢስላማዊ የታሪክ መፅሃፍ።

«ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከ615-1700 የጭቆናና የትግል ታሪክ» የተሰኘውና የዛሬ አስር ዓመት ለሕትመት የበቃው የኡስታዝ አህመዲን ጀበል የታሪክ መጽሐፍ ወሂብ አብዱልዋሲ እና ሙክታር ከዋጃ በተሰኙ ግለሰቦች አማካኝነት ከአማርኛ ወደ አረብኛ ተተርጉሞ ለዐረብኛ አንባቢያን በኳታር ሀገር ዶሃ ለህትመት በቅቷል።

መጽሐፉ ለጊዜው በኳታር ሀገር በሚገኘው በግዙፉ «ጀሪር የመጽሐፍት መደብር» ሦስቱ ቅርንጫፎች ዉስጥ በመሸጥ ላይ ይገኛል።

3 года, 4 месяца назад

መረጃውን ካደመጡ በኋላ ለሌሎችም በዋትስአፕ፣በቴሌግራም ማስተላለፉን አይርሱ

3 года, 4 месяца назад
3 года, 4 месяца назад

?? السلام عليكم ورحمة الله وبركاته?

???? صلاة.العيد.????
السؤال??
ما هي صفة صلاة العيد ؟
? الجواب
صفة صلاة العيد أن يحضر الإمام ويؤم الناس بركعتين قال عمر رضي الله عنه :
صلاة الفطر ركعتان وصلاة الأضحى ركعتان
يُكبر في الأولى تكبيرة الإحرام ، ثم يُكبر بعدها ست تكبيرات
أو سبع تكبيرات
لحديث عائشة رضي الله عنها :
" التكبير في الفطر والأضحى الأولى سبع تكبيرات وفي الثانية خمس تكبيرات سوى تكبيرتي الركوع
" رواه أبو داود ( 639 ) .
??ثم يقرأ الفاتحة ،
ويقرأ سورة " ق " في الركعة الأولى ، وفي الركعة الثانية يقوم مُكبراً
فإذا انتهى من القيام
يُكبر خمس تكبيرات ،
ويقرأ سورة الفاتحة ،
ثم سورة
" اقتربت الساعة وانشق القمر "
فهاتان السورتان كان النبي صلى الله عليه وسلم يقرأ بهما في العيدين ،
??وإن شاء قرأ في الأولى بسبح
وفي الثانية بـ
" هل أتاك حديث الغاشية "
فقد ورد أنه صلى الله عليه وسلم كان يقرأ في العيد بسبح اسم ربك الأعلى والغاشية .
وينبغي للإمام إحياء السنة بقراءة هذه السور حتى يعرفها المسلمون ولا يستنكروها إذا وقعت .
وبعد الصلاة يخطب الإمام في الناس .
الإسلام سؤال وجواب
?https://t.me/AltwhiduNur

Telegram

👉©« ዲነል ኢስላም»

***📚******👉***አል ተውሒዱል ኑር ***🌷*** ***🌷***አጫጭርና ***✔*** አስተማሪ ***🌷*** ፁሑፎችን ***🌷***የሚተላልፍበት ቻይናል ነው ።***✔***

***?******?*** السلام عليكم ورحمة الله وبركاته***?***
3 года, 5 месяцев назад

የመዳም ሳአዳ መልዕክት

https://youtu.be/zhnthMFWpkk

YouTube

ማሥተካከል ያለብኝኝ አሳዉቁኝ

3 года, 5 месяцев назад

ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ የአሳይታውን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ቃል ገቡ

T.me/ahmedin99

በአፋር ክልል በአሳይታ ከተማ በሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ አማካኝነት ለአፋር ህዝብ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ታላቁን የሱልጣን አሊ ሚራህ ኢስላማዊ ማዕከል እና ሌሎች የልማት ስራዎች አስገንብቶ ለማስረከብ ወደ ስራ ተገብቶ የነበረ ቢሆንም እውቁ የሃገራችን ባለሃብት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ብዙ ገንዘባቸውን ውጪ ካደረጉ ቡኃላ በፖለቲካ አሻጥር ምክንያት በክልሉ እያካሄዱ ከነበሩት በርካታ የልማት ስራዎች ተገፍተው እንዲወጡ በማድረግ እና የዚህን ፕሮጀክት ፋይናንስ ማድረግ እንዲያቆሙ በመግፋት ግንባታው እና የልማት ስራዎች እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል::

ሼይኽ መሐመድ በክልሉ በርካታ ኢንቨስትመንት እና የልማት ስራዎች በመስራት ህዝባቸውን እና መላው ሃገራቸውን ለመጥቀም ብዙ ቢንቀሳቀሱም በቀድሞ ስርኣት ከክልሉ ከሁሉም የልማት እንቅስቃሴያቸው ሙሉ ለሙሉ ተገፍተው እንዲወጡ ተደርገዋል::

ለሁለት አስርት አመታት ግንባታው የቆመው እና እሳቸው ያስጀመሩት ይህ ታላቅ ፕሮጀክት ዳግም ተጠናቆ ህዝቡን እና ሃገርን እንዲጠቅም ለማስቻል እንቅስቃሴ ሲደረግ የቆየ ሲሆን ከቀናት በፊትም ተቋሙ በሚገኝበት አሳይታ ከተማ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል እርሱን ጨምሮ የተለያዩ ታላላቅ ኡለሞች፣ዱዓቶች እና የክልል መጅሊስ አመራሮች የተካፈሉበት ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሂዷል::

በዚህ ፕሮግራም ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አወል አርባ ፕሮጀክቱን ላስጀመሩት እና ከክልሉ በግፍ ተገፍተው እንዲወጡ ለተደረጉት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ በይፋ ወደ ክልሉ ተመልሰው ለህዝባቸው ማድረግ የሚፈልጉትን የልማት ስራዎች ሁሉ ይሰሩ ዘንድ ሁኔታዎችን በሙሉ እንደሚያስተካክሉ ቃል በመግባት ጥሪ አድርገውላቸዋል::

ይህን ለአፋር ህዝብ እና ለሃገር የሚጠቅም ግዙፍ ተቋም የተፈጠሩ ችግሮችን በማስተካከል ዳግም ግንባታው ይጠናቀቅ ዘንድ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ የቀረበላቸው ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ምንም እንኳን ከበርካታ የልማት ስራዎቻቸው በግፍ ተገፍተው እንዲወጡ ቢደረጉም ለህዝባቸው እና ለሃገራቸው ካላቸው ፍቅር እና መልካም እሳቤ የተነሳ የቀረበላቸው ጥሪ በመቀበል ፕሮጀክቱን ሙሉ ለሙሉ ለማጠናቀቅ ቃል መግባታቸውን በተወካያቸው አማካኝነት አሳውቀውኛል:: አልሐምዱሊሏህ

እኚህ ታላቅ ሃገር ወዳድ ባለሃብት ሃገራቸውም እና ህዝባቸውን ለመጥቀም ለልማት ሥራዎች ብዙ ገንዘባቸውን አፍስሰው በግፍ ተገፍተው እንዲወጡ ቢደረጉም ከህዝባቸው እና ሃገራቸው የሚበልጥባቸው ምንም እንደሌለ በማስመስከር ይህን ታላቅ ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ ቃል በመግባታቸው በራሴ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ

የህዝቡን ጥሪ ለሳቸው በማድረስ እና ሁኔታዎች እንዲመቻቹ በማድረግ ትልቁን ሚና ለተጫወተው ለሳቸው ተወካይ ወንድም ጀማል አህመድም ምስጋናዬ የላቀ ነው:: ወንድም ጀማል ሃገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችንም ሆነ ሌሎች ኸይር ስራዎችን እሳቸው እንዲሳተፉበት በማድረግም ሆነ በግሉም በርካታ የኸይር ስራዎችን በመስራት ለማህበረሰቡም ለሃገርም ትልቅ አስተዋፅኦ እና ድጋፍ እያበረከተ ያለ ሃገር ወዳድ ወንድማችን ነው::

ሼይኽ መሐመድ አል አሙዲ ወደሚወዱት ሃገራቸው አላህ በሰላም እንዲመልሳቸው፣ መልካም ስራቸውን ሁሉ አላህ እንዲቀበላቸው፣ ለሃገራቸው እና ለህዝባቸውም ብዙ ማድረግ የሚፈልጉትን መልካም ስራ ሁሉ ለመስራት ይችሉ ዘንድ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ይወፍቃቸው ዘንድ ዱዓዬ ነው::

በተጨማሪም ይህ እንዲሳካ ላገዘን እና በርካታ የኸይር ስራዎች ላይ እየተሳተፈ ለሚገኘው የሳቸው ተወካይ ለሆነው ወንድም ጀማል አህመድም አላህ መልካም ስራውን ይቀበለው!

©ኡስታዝ አቡበክር አህመድ

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago