Abu hatim /ابو حاتم

Description
ይህ የተለያዩ የዲን ትምህርቶች፣ ዳዐዋዎች እንዲሁም አስተማሪ ኢስላማዊ ፅሑፎች የሚተላለፉበት ቻናል ነው። ይከታተሉ!
በተቻለኝ አቅም ማበጀትን እንጂ አልሻም!
ለሀሳብ መስጫ @Abu_hatim7
Advertising
We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 6 days, 10 hours ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት ??
@mujaabot

For Advertisement??
@atcads

Last updated 2 months, 2 weeks ago

NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ

ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 1 month, 4 weeks ago

1 month, 2 weeks ago
በግንኙነት ዓለም ውስጥ ብዙ አይነት ሰዎች …

በግንኙነት ዓለም ውስጥ ብዙ አይነት ሰዎች ያጋጥሙሃል ።አንዳንዱ ልክ እንደ ፌክ ሽቶ ነው ለግዜው ማዕዛው ቢማርክህም ዘውታሪ አይደለምና ወዲያው ሽታው ብን ብሎ ይጠፋል - የማይዘልቁ ግንኙነቶች በዚህ ይመሰላሉ ። እንደ በሽታ የሆነ ግንኙነትም አለ ከዛ ሰው መለየትህ Reliefን የሚሰጥህ ፣  ሌላኛው ደግሞ በትውልድ ሀገር  ይመሰላል ስትለያቸው ባይተዋርነት እንዲሰማህ ሁላ የሚያደርግ። ከዚህም የባሰ አለ እንደ ሩህና ጀሰድ አይነት ሆኖ እነሱን መነጠል እንደ ሞት የሆነ አይነት ወዳጅነት። ብቻ ሁሉንም ግንኙነቶች ጊዜና መከራ ይገልጣቸዋል።

@Abuhatim7

1 month, 2 weeks ago

?المنتقى من فتاوى الأئمة الأعلام

@Abuhatim7

1 month, 3 weeks ago

*?በጫማ መስገድና ተያያዥ ነጥቦች*
~
[ሀ] በጫማ መስገድ ይቻላልን?

አንዳንድ ሰዎች በጫማ መስገድ የማይፈቀድ ወይም ጋጠወጥነት የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው። እንዲህም እንዲያስቡ ያደረጋቸው ጉዳዩ በዑለሞች ሲፈፀም ወይም ሲነገር ስላላጋጠማቸው ይሆናል። ነገር ግን በጫማ ከመስገድ የሚከለክል አንድም ማስረጃ የለም። ይልቁንም በተቃራኒው በጫማ መስገድ የማያሻማ ሸሪዐዊ መሰረት ያለው ሱና ነው። ይህንን  ከሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ውስጥ ከፊሉን ለመጥቀስ ያህል፦

  1. አቡ መስለማ ሰዒድ ብኑ የዚድ አልአዝዲ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
    سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ: أَكَانَ النَّبِيُّ ﷺ يُصَلِّي فِي نَعْلَيْهِ؟ قَالَ: «نَعَمْ»
    “አነስ ኢብኑ ማሊክን ‘ነብዩ ﷺ በጫማዎቻቸው ይሰግዱ ነበርን?’ ብዬ ጠየቅኩት። እሱም ‘አዎ’ አለኝ።” [ቡኻሪና ሙስሊም

  2. ዐምር ብኑ ሹዐይብ ከአባታቸውና፣ ከአያታቸው ተይዞ እንዲህ ብለዋል፡-

رأيت رسول الله ﷺ يصلي حافيا ومنتعلا.
“የአላህ መልእክተኛን ﷺ በባዶ እግራቸውም ተጫምተውም ሲሰግዱ አይቻቸዋለሁ።” [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 660]

  1. አቡ ሰዒድ አልኹድሪ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
    “አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ﷺ አሰገዱን። በከፊል ሶላታቸው ላይ ሳሉ ጫማዎቻቸውን አወለቁና በግራቸው በኩል አስቀመጧቸው። ሰዎች ይህንን ሲያዩ ጫማዎቻቸውን አወለቁ። ሶላታቸውን ሲያጠናቅቁ ‘ምን ሆናችሁ ነው ጫማዎቻችሁን ያወለቃችሁት?’ አሉ። እነሱም ‘ጫማዎችህን ስታወልቅ ስናይ ጫማዎቻችንን አወለቅን’ አሉ። በዚህን ጊዜ እሳቸው ﷺ እንዲህ አሉ፡-
    "إن جبريل أتاني، فأخبرني أن فيها قذراً؛ فألقيتهما، فإذا جاء أحدكم إلى المسجد؛ فلينظر في نعليه: فإن رأى فيهما قذراً؛ فليمسحهما، ولْيصلِّ فيهما"
    ‘ጂብሪል ከኔ ዘንድ መጥቶ በነሱ (በጫማዎቼ) ላይ ቆሻሻ እንዳለባቸው ሲነገረኝ አወለቅኳቸው። አንዳችሁ መስጂድ ሲመጣ ጫማዎቹን ይመልከት። ቆሻሻ ካየባቸው ይጥረጋቸውና ይስገድባቸው።’” [ሲፈቱ ሶላት፡ 80]

  2. ከሸዳድ ብኑ አውስ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
    «خالفوا اليهود فإنهم لا يصلون في نعالهم ولا خفافهم»
    “አይሁዶችን ተፃረሩ። እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3210]

?ማሳሰቢያ

ከላይ በተመለከትናቸው ከፊል ሀዲሶች እንዲሁም ሌሎች ያልጠቀስናቸው ግን በጫማ መስገድን የሚጠቁሙ ሀዲሶች በዙ ከመሆናቸው ጋር አንድ ሰው በጫማው መስገድ የፈለገ ጊዜ ጫማው ላይ ነጃሳ ካለ በአፈር አሸት አሸት አድርጎ በማፅዳት መብቃቃት ይችላል ምክኒያቱም በሐዲስ የመጣው በመሬት ማሸት ስለሆነ ማጠብ አይጠበቅበትም።

ሌላኛው በጫማው መስገድ ይችላል ሲባል በተፀዱና ንፅህናቸው በተጠበቁ የመስጂድ ምንጣፎች ላይ ከነጫማው መጥቶ መስገዱ አግባብ እንዳልሆነና የተከለከለም እንደሚሆን ኡለሞች ይናገራሉ። እንዲሁም ሜዳ ላይ በሚሰግድ ግዜ ይህንን የተረሳ ሱና ህያው ለማድረግ ከመነየት ጋር ምናልባት እውቀት የሌላቸው ሰዎች ተግባሬን ካዩ ይደናገራሉ ብሎ ከፈራ ከመተግበሩ በፊት መጀመሪያ ለሰዎች ማስተማሩ ተገቢና በላጭ ይሆናል።

@Abuhatim7

1 month, 3 weeks ago

?بتر الكلام عن السياق ليس منهاج علميا"
?الشيخ عبد الله العنقري

https://t.me/Abuhatim7

1 month, 3 weeks ago

በምታደርገው እና ማድረግ በሚገባህ መካከል ሰፊ ልዪነት አለ።

@Abuhatim7

1 month, 4 weeks ago

?كتاب  أحاديث إصلاح القلوب

https://t.me/Abuhatim7

4 months, 2 weeks ago
ሸይኽ መሐመድ አማን አልጃሚ ረሂመሁሏህ እንዲህ …

ሸይኽ መሐመድ አማን አልጃሚ ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

"ዑለማዎች እንዳሉት ከከራማዎች ሁሉ ያማረ ከራማ ማለት አላህ ለባሪያው ኢስቲቃማ
(በዲን ላይ መፅናትን) ሲረዝቀው ነው ። በኢስቲቃማ ላይ ሆኖ እሱን እስኪገናኝ ድረስ"

? ሸርህ ቁረቱል ዑዩኑል ሙወሂዲን

https://t.me/Abuhatim7

4 months, 2 weeks ago

*አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት!*

አላህ ለባሮቹ ወደ እርሱ የሚያቃርቡ ልዩ የመልካም ስራ እድሎችን ፈጥሯል!
ከእነዚህም እድሎች ውስጥ አንዱ አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው።

በእነዚህም ቀናት ውስጥ በመጠነኛ ጥረት ብዙ ምንዳን የሚያስገኙ ኸይር ስራዎች/ዒባዳዎች አሉ!

እነሱ ዒባዳዎች እነማን ናቸው? የሚለውን በአላህ ፍቃድ ከዚህ በታች ባያያዝኩላችሁ PDF ላይ ለማንበብ በሚመች መልኩ ሰብሰብ አድርጌ አቅርቤዋለሁ። እየገባችሁ ማንበብ ትችላችሁ! ተጠቀሙበት ሌሎችም እንዲጠቀሙበትና የአጅሩም ተካፋይ እንድትሆኑ ሼር አድርጉት። ባረከላሁ ፊኩም

✍? ዓማር ዐብድልወሃብ (አቡሃቲም)
ዙልቃዒዳህ/29/1445 አ.ሂ

?https://t.me/Abuhatim7

4 months, 2 weeks ago

الجمع بين الزوجين صعب جدا شيخ الباني

https://t.me/Abuhatim7

We recommend to visit

A place to learn English easily.

Owner - @Samson_G

Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian

Last updated 6 days, 10 hours ago

#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት ??
@mujaabot

For Advertisement??
@atcads

Last updated 2 months, 2 weeks ago

NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ

ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12

Last updated 1 month, 4 weeks ago