- القناة الرسمية على التيليجرام استمتعو بالمشاهده ? ♥️ .
•┊اقتباسات ? •
•┊رمزيات ?
•┊فيديوهات ?
- @xxzbot // ? بوت تنزيل ستوريات انستا -
- @zzxzz // ? لـ التمويل -
Last updated 1 year, 8 months ago
- القناة الرسمية على التيليجرام استمتعو بالمشاهده ? ♥️ .
•┊فيديوهات ? •
•┊رمزيات ?
•┊اختصارات ?
- @zezbot // ?بوت زخرفه -
- @zzxzz // ? لـ التمويل -
Last updated 1 year, 8 months ago
- بوت تحميل من الأنستا ومن جميع مواقع التواصل الإجتماعي: ✅ .
- بوت التحميل من التيك توك: @EEEBOT
- بوت التحميل من الأنستا: @xxzbot
- بوت التحميل من اليوتيوب: @EMEBOT
- ? ? .
- للتمويل: @NNEEN
Last updated 1 year, 7 months ago
የኢርሻድ ኪታብ ( ክፍል 7) ወይም
👆 ከዚኛው ደርስ በፊት የተቀራው ቅጂ ያለው ካለ በዚህ bot ☞ @Alijema_bot ላኩልን
የነ "ሙፍቲ" እስልምና ይሄ ነው!
~
ከመጅሊስ ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ ስለ ገንዘብ ምዝበራ ሲወራ እናያለን። እውነት ይሁን አይሁን አላውቅም። እውነት ቢሆን እንኳ ዐቂዳውን በቅጡ ለሚለይ ሰው እነ "ሙፍቲ" ዑመርን የሚያስናፍቅ ምንም አይነት ምክንያት የለም። እንዲያውም ለኔ የዚህ መጅሊስ ትልቁ ችግር በአሕባሽ ላይ መሬት የረገጠ ጠንካራ ስራ አለመስራቱ ነው። አማና ጋር በተያያዘ ከአሉባልታ ባለፈ ችግሩን በተጨባጭ የሚያውቅ ሰው አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ አለበት። ይሁን እንጂ ሁሌም ቢሆን ቀዳሚው መለኪያ ዐቂዳ ነው መሆን ያለበት። ከዚያ እንደተዋረዱ ሌሎች ርእሶች ይከተላሉ።
ለማንኛውም የነ "ሙፍቲ" ቡድን ማለት፦
እስኪ ይህንን ጥቅምት 30/2012 በሸገር ሬዲዮ ከቀረበው የ "ሙፍቲ" ዑመር ቃለ ምልልስ የተወሰደ ንግግሩን አስተውሉ!
"ለባለስልጣኖቹም፣ ለእነ አባይ ፀሃዬ – የዚያን ግዜ የደህንነት ኃላፊ ነበሩ –
‘ተው እባካችሁ! ይኼ ችግር (#ሰለፍያን ማለቱ ነው) መንግስት ላይ ይወጣል። እኛ ላይ ብቻ ሳይሆን እናንተም ላይ ይደርሳል’ እላቸው ነበር።
በኋላ እንግዲህ በእነመለስ ግዜ እነርሱ ላይ ሲደርስ መጥፋት አለበት ብሎ ያ ሁሉ ችግር ተፈጠረ። መጀመሪያውኑ ከውጥኑ ማጥፋት ይቻል ነበር።"
•
ተመልከቱ! መንግስት ሳያስብ በፊት አሕባሽ ያልሆኑ ሙስሊሞችን እንዲያጠፋላቸው ሲወተውቱ ነበር ማለት ነው። እነዚህ አቅሙ ቢኖራቸው እንደነ ዮሐንስ አጋድመው ያርዱ ነበር።
ቀጠለ:—
"መንግስት የዚያን ግዜ በጎናችን አልቆመም። መፈለግ አይፈልገውም። ሙስሊሙ ላይ ብቻ ይቀር መስሎታል እንጂ ወደ መንግስት ያልፋል አልመሰለውም። አሁን ሀገሩ በሙሉ ተዳርሷል። ለማጥፋት አልተቻለም። ወደአንድነት መጥተን ሰላም ቢሆን ይሻላል ሀገሩ ብለን ነው። ወደን አይደለም በአንድነት የምንታየው። ማጥፋት ካልተቻለ አብሮ በሚሆንበት ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል በሚል ነው።"
•
ምንኛ ልብ የሚያደማ ንግግር ነው?! ይሄ እንግዲህ የተሰማው ነው። በርግጠኝነት የተዳፈነው ከዚህ የከፋ ነው። በነዚህ ሰዎች የተሸወዳችሁ አሁንም አልረፈደም። ንቁ! ከነሱ ጋር መጨማለቃችሁን ትታችሁ በጊዜ ተመለሱ።
(یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ لَا تَتَّخِذُوا۟ بِطَانَةࣰ مِّن دُونِكُمۡ لَا یَأۡلُونَكُمۡ خَبَالࣰا وَدُّوا۟ مَا عَنِتُّمۡ قَدۡ بَدَتِ ٱلۡبَغۡضَاۤءُ مِنۡ أَفۡوَ ٰهِهِمۡ وَمَا تُخۡفِی صُدُورُهُمۡ أَكۡبَرُۚ قَدۡ بَیَّنَّا لَكُمُ ٱلۡـَٔایَـٰتِۖ إِن كُنتُمۡ تَعۡقِلُونَ)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከእናንተ ሌላ ምስጢረኛን አትያዙ፡፡ ማበላሸትን አይገቱላችሁም፡፡ ጉዳታችሁን ይወዳሉ፡፡ ጥላቻይቱ ከአፎቻቸው በእርግጥ ተገለጸች፡፡ ልቦቻቸውም የሚደብቁት ይበልጥ ትልቅ ነው፡፡ ልብ የምታደርጉ እንደሆናችሁ ለእናንተ ማብራሪያዎችን በእርግጥ ገለጽን፡፡" [ኣሊ ዒምራን: 118]
IbnuMunewor
فهواها مرضها ،، وشفاؤها مخالفتها ،،
فياربـي،،
ኡስታዝ አብድረዛቅ ሙሰማ(ሀፊዘሁላህ)
እውነተኛ የረሱል(ሰ·ዐ·ወ) ውዴታ ከሰሀቦች
✍ በሶሪያው ድል ደስታችንን ስንገልፅ «መድኸሊዮች (ሰለፊዮች) ትግሉን የኢኽዋን ነው ብላችሁ ስትተቹ እንዳልነበር አሁን ድል ሲገኝ የድል አጥቢ ጀግና ሆናችሁ ደስታችሁን እየገለፃችሁ ነው!» ብለው የሚተቹ አንዳንድ ነፍስ ያላወቁ ልጆችን ተመልክቼ ስለ ዲንም ሆነ ፖለቲካ ምንም ስለማያውቁ ትንሽ ልጠቁማቸው ወደድኩ።
በመጀመሪያ ደረጃ «ኢኽዋን» ለዲን የሚታገል ሳይሆን እንደየአስፈላጊነቱ በዲን ሽፋን የሚንቀሳቀስ ለፖለቲካ የተፈጠረ ፖለቲካዊ ቡድን ነው። ከተመሰረተበት ጀምሮ እስካሁን ባለው ታሪኩ ከጥፋት ውጭ አንድም ሃገር ላይ በርሱ የተመራ ትግል ከውድመት ውጭ ውጤት አምጥቶ አያውቅም። ከግብፅ ጀምሮ ሁሉም የተሳተፈባቸው ሃገራት ሕያው ምስክር ናቸው።
የሶሪያን ጉዳይ በተመለከተ ሲጀመር ኢኽዋን እዛ አካባቢ ላይ በግልፅ ከሚንቀሳቀሱት ተዋጊዎች ውስጥ የለበትም። ይልቁንም የተለያዬ ስያሜ የተሰጣቸው ራሳቸውን "ሰለፊይ ነን" የሚሉ ቡድኖች ናቸው ከአል-አሰድና ሺዓዎች ጋር ያኔ ጀምሮ የገጠሙት።
አሁን ይህቺን ካርድ የመዘዛችሁት «የአል-አሰድ መንግስት የተገረሰሰው በአመፅ ስለሆነ እንዲህ አይነት አመፅንና ሰላማዊ ሰልፍን የምትቃወሙ አልነበራችሁም ወይ? እንደት ነው በዚህ መልኩ የመጣን ድል የምትደግፉት?» ለማለት ነው። (መች ጠፋኝ ሃሳባችሁ¡)
ለዛ'ኮ ነው ነገሮችን በጥልቀት የማታዩ፣ ጫፉን ይዛችሁ ብቻ የምትሮጡ የዲንም፣ የፖለቲካም ጥልቅ ግንዛቤ የሌላችሁ ግልቦች፣ በየአገኛችሁበት አጋጣሚ ሁሉ ራቁታችሁን ያስቀራችሁን ሰለፊያ (መድኸሊይ) የምትሉትን ቡድን ለመተቸትና ጥላሸት ለመቀባት የምትጋጋጡ የምላችሁ!
ለማንኛውም ኑ ተረጋጉና አዳምጡ። ለወደፊቱም ይጠቅማችኋል።
አዎ! በሙስሊም መሪ ላይ አምፆ መውጣት አይቻልም። ሰማችሁኝ? ልድገመው! በሙስሊም መሪ ላይ አምፆ መውጣት አይቻልም‼
ይህ እኛ የፈበረክነው አዲስ ፈሊጥ ሳይሆን ከቀደምት አበው ትውልዶች ጀምሮ አኢማዎች የተስማሙበት አቋም ነው። ሐዲሥም አለ። መሪ ይመከራል፣ ከመጥፎ ይከለከላል፣ በመልካም ይታዘዛል፣ ዱዓእ ይደረግለታል እንጂ ሙስሊም ከሆነ በአመፅ አይገረሰስም። እስከ መቼ? ግልፅ የሆነ ክህደት እስካልታየበት ድረስ!
ይህ ነቢያዊ አስተምህሮ ነው። ታላቁ ሶሐባ ዑባደት ኢብኑ ሷሚት ባስተላለፈው ሐዲሥ ላይ አል-ቡኻሪይና ሙስሊም የዘገቡት መልዕክት መጥቷል።
ጁናደህ ኢብኑ አቢ ኡመይያህ አስ'ሰዱሲይ እንደተናገረው
(دَخَلْنا علَى عُبادَةَ بنِ الصَّامِتِ وهو مَرِيضٌ، قُلْنا: أصْلَحَكَ اللَّهُ، حَدِّثْ بحَدِيثٍ يَنْفَعُكَ اللَّهُ به، سَمِعْتَهُ مِنَ النَّبيِّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ،…
«ዑባደት ኢብኑ ሷሚት ታሞ ሳለ (ልንጠይቀው) ገባንና «አላህ ነገርህን ያሳምርልህና በርሱ ከአላህ አጅር የምታገኝበትን (የምትጠቀምበትን) ከነቢዩ ﷺ ከሰማኸው ሐዲሥ መካከል ንገረን?» አልነው።
ዑባዳህም ይህን ሐዲሥ ነገራቸው፦
قالَ: دَعانا النَّبيُّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ فَبايَعْناهُ، فقالَ فِيما أخَذَ عَلَيْنا: أنْ بايَعَنا علَى السَّمْعِ والطَّاعَةِ، في مَنْشَطِنا ومَكْرَهِنا، وعُسْرِنا ويُسْرِنا، وأَثَرَةً عَلَيْنا، وأَنْ لا نُنازِعَ الأمْرَ أهْلَهُ، إلَّا أنْ تَرَوْا كُفْرًا بَواحًا، عِنْدَكُمْ مِنَ اللَّهِ فيه بُرْهانٌ!)
«ነቢዩ ﷺ ጠሩንና ቃል ኪዳን ተጋባናቸው። ቃል ኪዳን በተጋባን ጊዜ ይህን አሉን፦ (መሪን) እንድንሰማና እንድንታዘዝ ቃል ኪዳን ተጋባን፤ በደስታም ሆነ በጠላን ጊዜ፣ በምቾት ጊዜም ሆነ በችግር ጊዜ፣ በኛ ላይ ባስበለጠ ጊዜ (ራሱን ወይም ሌሎች የማይገባቸውን በከፊል ዱንያዊ ጉዳዮች ለኛ ከሚገባን በተቃራኒ በበደል ሲያስበልጥ)፣ ጉዳይን (ስልጣንን) ከባለቤቱ እንዳንነጥቅ፣ ለናንተ አላህ ዘንድ የማያሻማ ማስረጃ ያለው ግልፅ የሆነ ክህደትን እስካላያችሁ ድረስ (መሪን እንድንሰማና እንድንታዘዝ ቃል ተጋብተናል)።»
[አ-ን'ነሳኢይ: 4151፥ 4162፣ አል-ቡኻሪይ: 7055፥ 7199፥ 7200፣ ሙስሊም: 1709፣]
√ ያየነው ነገር ኩፍር መሆን አለበት። የፊስቅ ወንጀል ቢሆን አንወጣም። ለምሳሌ፦ ሲሰርቅ፣ ዝሙት ሲፈፅም፣ ኸምር ሲጠጣ ብናይ አመፅ አንወጣም። ስለዚህ የፈፀመው ነገር ኩፍር ነው ፊስቅ የሚለውን ለማወቅ ትክክለኛ ሸሪዓዊ ዕውቀት ያስፈልጋል (كفرًا)፣
√ ኩፍርነቱ ደግሞ ግልፅ የወጣ መሆን አለበት። የሚያጠራጥር መሆን የለበትም። ለምሳሌ፦ መድረክ ላይ ወጥቶ መስረቅ፣ ዝሙት… የተፈቀደ ነው ቢል ግልፅ ነው። (بواحًا)
√ ለዚህም ደካማ ማስረጃ ሳይሆን ቁርጥ ያለ ማስረጃ ከሸሪዓህ ሊኖረን ይገባል። ( عندكم فيه من الله برهان )
በዚህ መልኩ ኢብኑ ዑሠይሚን አብራርተውታል።
ይህ መስፈርት ሳይሟላ የተደረጉ አመፆች በርካታ ንፁሐንን ፈጅተው፣ ንብረት ወውደም ተከስቶ፣ በርካታ ደም ፈሷል፣ ሃገር ወድሟል፣ በሚሊዮን ዜጎች ተሰድተዋል። ንግስናን ያለ አግባብ በዚህ ደረጃ ባልሆኑ ነገሮች ተነሳስቶ ከባለቤቱ ለመንጠቅ መሞከር ከያኔ የዑሥማን ዘመነ ኸሊፋ ጀምሮ እስካሁን ጎድቶናል።
ለዚህም ሲባል ያኔ ከ13 አመት በፊት በዓረብ ጸዴይ አብዮት ጊዜ የሶሪያው ጦርነት ሲቀሰቀስ፤ እናንተ ከምትወቅሷቸው መሻይኾች መካከል አንዱ የሆኑት የሳዑዲው ታላቅ ዓሊምና የለጂን'ነቲ-ድ'ዳኢማህ አባል ሸይኽ ሷሊሕ አ-ል'ሉሐይዳን (አላህ ይዘንላቸውና) ስለ ሶሪያው መሪና በርሱ ላይ አምፆ ስለ መውጣት ፈታዋ ተጠይቀው በርሱ ላይ አምፆ መውጣት እንደሚቻል፣ የኩፍር አገዛዝ እንደሆነ፣ ባይሆን የርሱ ስልጣን አስወጋጆች አላማቸው የአላህን ቃል ከፍ ማድረግ እንዲሆንና ኩፍርን መገርሰስ እንዲሆን፣ እርሱ ለማስወገድ አቅሙ ያላቸው እንደሆኑ ማሰብ እንዳለባቸው መክረዋል።
ስለዚህ እኛ ሰለፊዮች በነቢያችን ﷺ መመሪያ መሠረት አንድ መሪ ግልፅ የሆነ ኩፍር ከታየበትና ጥቅምና ጉዳቱ ተመዛዝኖ ያንን ለማስወገድ አቅም ካለ በመሪ ላይ ማመፅን እንደግፋለን፤ አድርገነዋልም፣ ድል አድርገናልም። ያለ መረጃና ማስረጃ በስሜትና በደስ አለኝ ሁሉንም በደፈናው አልደገፍንም፣ አልነቀፍንም፣ ወደፊትም እንደዚህ አናደርግም። በየሞቀበት ድግስ እናንተ ናችሁ ድንኳን ሰባሪና የድል አጥቢያ ጀግኖች፣ ሁሌም ከአሸነፈው ጎን ያለ አግባብ አጨብጫቢዎች! ወይ ዕውቀት የለ፣ ወይ ብልጠት!
✍Murad tadesse
💫💫💫
Ali medresa 📚 إقرأ:
ኢርሻድ 06
Ali medresa 📚 إقرأ:
አዋጅ 📣 አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋሉ
ታስታውሱ ከሆነ መጀመሪያ ላይ አርተጀንቲና በሳዑዲ አራሱ ተሸንፋ ነበር መጨረሻ ላይ ግን ዋንጫውን ማንበላው ………አርጀንቲና 💪😅🙈😅
- القناة الرسمية على التيليجرام استمتعو بالمشاهده ? ♥️ .
•┊اقتباسات ? •
•┊رمزيات ?
•┊فيديوهات ?
- @xxzbot // ? بوت تنزيل ستوريات انستا -
- @zzxzz // ? لـ التمويل -
Last updated 1 year, 8 months ago
- القناة الرسمية على التيليجرام استمتعو بالمشاهده ? ♥️ .
•┊فيديوهات ? •
•┊رمزيات ?
•┊اختصارات ?
- @zezbot // ?بوت زخرفه -
- @zzxzz // ? لـ التمويل -
Last updated 1 year, 8 months ago
- بوت تحميل من الأنستا ومن جميع مواقع التواصل الإجتماعي: ✅ .
- بوت التحميل من التيك توك: @EEEBOT
- بوت التحميل من الأنستا: @xxzbot
- بوت التحميل من اليوتيوب: @EMEBOT
- ? ? .
- للتمويل: @NNEEN
Last updated 1 year, 7 months ago