MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™

Description
አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@mikreaimro
ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
?Welcome to your Home! ?
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

2 months, 1 week ago

*⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ*

?አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
?እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ?

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ

የቻናሉ Link??**
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA

2 months, 1 week ago

እርሱ ያያል!
፨፨//////፨፨
ከፍፁም ቅድስናው የተነሳ፤ ከጠቢብነቱ የተነሳ፣ ከሙሉ ልዕልናው፣ ከሃያልነቱና ከከፍታው የተነሳ በእርግጥም እግዚአብሔር በሁሉም አለና ሁሉን ያያል፤ በእርግጥም አምላክ ምሉዕ በኩሉ ነውና የተሸሸገ እራሱ አይደበቅበትም፤ አይሰወርበትም። እርሱ ሁሉን የሚያይ፣ ሁሉን የሚሰማ፣ ሁሉን የሚያውቅ፣ ምድርን በመዳፉ የያዘ የአማልክት አምላክ፣ የጌቶች ጌታ፣ የነገስታት ንጉስ ህያው አምላክ ቅዱስ ጌታ ነው። ስንቶች እንሆን ከእርሱ ጋር ድብብቆሽ ውስጥ የገባን? ስንቶች እንሆን ዝምታውን የአላዋቂነቱ መገለጫ አድርገን በጥፋታችን የገፋን? ስንቶች እንሆን የፍርዱን መዘግነት ያለመፍረዱ ልክ አድርገን እንዳሻን የምናጠፋ? እንደፈለግን የምንጠፋ? ስንቶች እንሆን አያይም ብለን በጨለማ ውስጥ እራሳችንን የምናስኮንን? በደልን የምንሰራ? ጥፋትን የምንደጋግም ስንቶች እንሆን?

አዎ! ጀግናዬ..! እርሱ ያያል! እግዚአብሔር ሁሉን በሚገባ ይመለከታል፤ አምላክ እያንዳንዱን ያደምጣል። የፈጣሪን አይን ጨለማ አይጋርደውም፤ የእግዚአብሔርን ጆሮ ጩሀት አይሸፍነውም፤ ማስተዋሉን ተንኮል አይገድበውም። ጥበቡ ከጥበብ ሁሉ ትልቃለች፤ እውቀቱ የእውቀት ሁሉ ቁንጮ ናት፤ አምላክነቱ የባህሪ ነው፤ ጌትነቱ ፍፁም ቅዱስ ነው። ለሁሉ መልስ መስጠት የሚችል አምላክ፣ የሚሰጠውን ሊያጣ አይችልም፤ ሁሉን የፈጠረ ጌታ አጥፊውን ማጥፋት፣ ክፉው ላይ መክፋት፣ ለተበደለው መፍረድ፣ ለተጎጂውም መበቀል አይሳነውም። ሁሉን የሚያይ አምላክ የልጆቹን ጩሀት ይሰማል፤ በደላቸውን ያደምጣል፤ ስቃያቸውን ይመለከታል። ልጆቹ እርስ በእርስ ሲገፋፉ ያያል፤ በጎራ ሲቦዳደኑ፣ ሲጨካከኑና ሲጎዳዱ በሚገባ ይመለከታል። የምንሰራውን ስራ ሳይሆን የምናስበው፣ በውስጣችን የሚመላለሰው ክፉም ሆነ ደግ ሃሳብ ከእርሱ የተሰወረ አይደለም።

አዎ! ዘወትር የሚያየን አምላክም ዝምታው እስከ መጨረሻ አይደለም። በብዙ መንገድ ሊያስተምረን መምጣቱ አይቀርም። ስራው በየቀኑ አዲስ ነው፤ እራሱ እግዚአብሔር አዲስ ነው፤ ስም አጠራሩ፣ ዙፋኑ፣ ልዕልናው ዘወትር አዲስና ረቂቅ ነው። ተሸሽገን አናመልጠውም፤ ተደብቀን አንሰወርበትም። በሚያየን ርቀት ውስጣችንንም ጭምር ይመለከታልና ዛሬ ማለዳ ብዙ ነገር ይቀየራል፤ በዚሁ ንጋት የተስፋ ብረሃን በጉልህ ይፈነጥቃል፤ ምድር ትፈካለች፤ ጨለማዋን ትገፋለች፤ ወደ ሰማይ አባቷ ታንጋጥጣለች፤ ምርጫውን ትጠብቃለች፤ በረከቱን በስስት ትጠባበቃለች። አምላክ አዲስ ነው፤ እግዚአብሔር አዲስ ነው፤ ቃሉ የዘወትር ምግብ ነው፤ ስጦታው በየጊዜው ሙሉ ነው። አንዳንች ያጎደለብን፣ አንዳችም የሚያመልጠው የለም። ህይወታችን በሙሉ ከአይኖቹ በታች፣ ከጆሮው አጠገብ ነውና ስናስብ እናስታውሰው፤ ስናደርግም እይታው ውስጥ መሆናችንን እንገንዘብ።
ግሩም ምሽት ይሁንልን! ???
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! ?

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
?? SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro ??

2 months, 1 week ago

ሴትን አክብር!
፨፨፨////፨፨፨
ስለ ወንድነት ብዙ የሚባሉ ነገሮች ይኖሩ ይሆናል። አንደኛውና ዋንኛው ግን ሴትን ማክበር መቻል ነው። የምርጫ ጉዳይ ሰይሆን የተፈጥሮ ጉዳይ ነው። ወንድ ሆኖ ሴትን የሚንቅ፣ ወንድ ሆኖ በሴት ላይ የሚጨክን፣ ወንድ ሆኖ ሴትን ለማጥቃት የሚንደረደር ወንድ ወንድነቱ አጠራጣሪ ነው። ማንም ሰው እናቱን ወይም የእናቱን አምሳያ ሊንቅና ሊያንቋሽሽ አይችልም። ሁላችንም ኬት እንደመጣን፣ እንዴት እዚህ እንደደረስን፣ ቤተሰቦቻችን ምንያህል ዋጋ እንደከፈሉልን እናውቃለን። ትናንቱን የረሳ ሰው ምንም አይነት ወደፊት ሊኖረው አይችልም። በምድር ላይ የህይወት ዘመን ደጋፊህ ትሆን ዘንድ የተሰጠችህ ስጦታ ሴት ልጅ ነች። ሴትን የመውደድና የማክበር ጌታ አለብህ። አስተምህሮው ግልፅ ነው። የምትወዳትና የምታከብራት ባደረገችልህ ነገር ወይም በምትሰጥህ ፍቅር ልክ ሳይሆን በሴትነቷ ብቻ ነው። ሴት የምትልህን መስማትና ለእርሷም ሀሳብና አስተያየት ቦታ መስጠት ጂልነት ሳይሆን ብልህነት ነው። አብራህ ያለችን ሴት ብትሰማ ብታተርፍ እንጂ አትጎዳም። ካመንክበት ትቀበላለህ ካላሳመነህ ትተወዋለህ። እንዲሁ ሴት ነች ብለህ ሀሳቧን አትናቅ፣ ፍላጎቷንም አትግፋ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሴትን አክብር፣ ጆሮ ስጣት፣ ጊዜ ስጣት። የወንድነት ሀላፊነት ብዙ ነው። ወንድ ስትሆን ቤተሰብ የሚመሰረተው ባንተ ላይ ነው፣ በከባባድ ችግሮች ውስጥ የምታልፈው አንተ ነህ፣ ውስጥህ የታመቀውን ህመም ለማውጣት የምትቸገረው አንተ ነህ፣ አብዛኛው የህይወትህ ክፍል በውጣውረድ የተሞላ፣ በፈተናም የታጠረ ነው። ካለብህ የአሁንም ሆነ የወደፊት ሃላፊነት አንፃር ያለህ አማራጭ ጥንካሬ ብቻ ነው። ጠንካራ ወንድ የእናቱ ኩራት ነው፣ ጠንካራ ወንድ የአባቱ ደጀን ነው፣ ጠንካራ ወንድ የእህቱ ጠባቂ ነው። ግፋ ሲልም ሃላፊነቱ ከቤተሰብ ከፍ ሲል ጠንካራ ወንድ የፍቅረኛው ወይም የባለቤቱ አይን ማረፊያ ነው፣ የህይወቷ ማዕከል ነው፣ ለሴት ልጅ በሙሉም ተከላካይ ነው። የትኛዋም ሴት ልትጎዳህ ትችላለች፣ በምንም አይነት መንገድ ልትከዳ ትችላለህ፣ ምንም ሊደርስብህ ይችላል በስተመጨረሻ ግን ወንድ መሆንህን እንዳትረሳ። ወንድ ልጅ ቆፍጣና ነው፣ ወንድ ልጅ ቆዳው ጠንካራ ነው፣ ወንድ ልጅ ወድቆ መቅረት እጣፋንታው አይደለም፣ ወንድ ልጅ መገፋትና መከዳት ብርቁ አይደለም። የበደልህ ምንጭ ሴቶች በሙሉ እንደሆኑ አታስብ። ያንተ ያይደለችው ብታቆስልህ ያንተዋ በሚገባ እንደምታክምህ እወቅ።

አዎ! እያደር እድሜህ ሲጨምር፣ ሃላፊነት ሲሰማህ፣ እውቀትና ነገሮችን የመረዳት አቅምህ እየጨመረ ሲመጣ ብዙ ነገር ይገባሃል። እያንዳንዱ ያለአግባብ ሲባክን የነበረው ጊዜህ የሚያሳዝንህ ወቅት ይመጣል። አውደልዳይ ወንድ መጨረሻው የት እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነው። ዛሬ ራስህን ሰብሰብ የማታደርግና ጡዘትህን የማትገታ ከሆነ አወዳደቅህ እጅጉን የከፋ ይሆናል። ኩሩ ወንድ ሁን፣ ህይወትን እንደ እቃቃ ጫወታ አትኑራት፣ ከዚችም ከዛችም አትለጠፍ። የምትሆንህ አንድ ሴት ላይ ብቻ አተኩር። አተራማሽ መሆን የወንድነት መለኪያም አኩሪ ተግባርም አይደለም። ቅጣትህ እጅግ የከፋ ነውና ደጋግመህ አትሳት፣ የማይገባህ ውጥንቅጥ ውስጥ አትግባ። ለየትኛውም ሴት ህይወት መበላሸት ተጠያቂ ከመሆን ራስህን ጠብቅ። በብዙ መንገድ እየተፈተነ ያለውን ወንድነት ለማቆየት የምትችለውን ሁሉ አድርግ። የማይመጥንህ የወረድ ወሬ ውስጥ አትግባ፣ ራስህን አክብር ራስህን አስከብር። ጥንቅቅ ያለ ኩሩ ወንድ ሆነህ ተገኝ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! ???
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! ?

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
?? SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro ??

2 months, 2 weeks ago

በሚያድንህ ታመም!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
እለት እለት በስራህ ላይ በሰዓቱ የመትገኘው በወሩ መጨረሻ የሚከፈልህን ደሞዝ ታሳቢ አድርገህ ነው። ለአመታት ሳታቋርጥ ጠንክረህ ትምህርትህን የምትከታተለው ህይወትህን በፈለከው መንገድ እንደሚመራልህ ታሳቢ በማደረግ ነው። ህልሜ ለምትለው ነገር ወዳጆችህን የምትለው፣ ገንዘብህን ወጪ የምታደርገው፣ ጊዜህን የምትሰዋው፣ የምትገፋው፣ የምትሰቃየውና የምትታመመው አንድም ለውጣዊ እርካታህ ሁለትም እግዚአብሔር በፈቀደው መንገድ ወገኖችህን ለማገልገል ነው። ነገር ግን በዚህ ሁሉ ጉዞህ ውስጥ ምንም ነገር በነፃ የምታደርገው ነገር የለም፤ ምንም ነገር በቀላሉ የሚያልፍ ነገር የለም፤ ምንም ነገር ዋጋ ሳትከፍልበት አይመጣም። እያዳንዱ ትልቅ ግኝት የእራሱ ውድ ክፍያ አለው፤ የትኛውም የተሻለ ውጤት አደጋ (Risk) አለው። ማግኘት ከፈለክ የማጣትንም ሪስክ መውሰድ ይኖርብሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! በሚያድንህ ታመም! ሔዶ ሔዶ ዋጋህን በሚመልሰው፣ ጥረትህን በሚያስተካክለው፣ የህይወት ደረጃህን በሚጨምረው ታመም። ደስታ ያለው ህመም ምን አይነት ነው? በእርግጥም ስሙ ብቻ ህመም የሆነ ነገር ግን ህመም የሌለው፣ በተቃራኒው እረፍታና ሰላምን የሚያድለው ህመም ምንድነው? ጂም ስትገባ ህመም እንዳለው፣ ስቃይ እንዳለው፣ ፈታኝ እንደሆነ፣ ላብህን እንደሚያንጠፈጥፈው ታውቀዋለህ ነገር ግን ስቃዩንም ጭምር ከልብህ ወደሀዋል፤ ከማንነትህ ጋር እንዲዋሃድ አድርገሀዋል፤ በሂደትም ለውጡን በሰውነትህ ላይ መመልከት ጀምረሃል። ቁጭ ብሎ፣ ጊዜ ወስዶ፣ እራስን ገዝቶ፣ ከሌሎች ማራኪና አጓጉዊ ነገሮች ተቆጥቦ አንድን መፅሐፍ አንብቦ መጨረስ ትግል አለው፤ ህመም ይኖረዋል፤ ዋጋም ያስከፍላል፤ ነገር ግን ከፈተናውና ከህመሙ በላይ የሚሰጥህ የተለየ ስሜት፣ የሚጨምርልህ እውቀትና እሴት ከልብህ እንድትወደውና እንድትዋሃደው አድርጎሃል።

አዎ! ሂደቱን እስከ ጥግ መውደድህ ህመሙን ያስረሳሃል፤ ሃላፊነትን መውሰድህ ውጤቱን ያማረ ያደርገዋል፤ ዋጋ ባለው ነገር መልፋትህ በእርግጥም ህመምህን ያቀለዋል። በምትወደው አለምና በማትወደው አለም ውስጥ ያለሀው አንተ እንድ አይነት ልትሆኑ አትችሉም። ህይወትህን ስትወዳት ምርጫዎችህን ታከብራለህ፤ በድግግሞሽህ ታድጋለህ፤ በተግባሮችህ ደስ ትሰኛለህ፤ እራስህ ላይ እሴትን ትጨምራለህ፤ ለምስጋና የፈጠንክ፣ ሌሎችንም ለማገዝ የተዘጋጀህ ትሆናለህ። ከወትሮው የተለዩት ውሳኔዎችህ ያስፈራሉ፤ ያስጨንቃሉ፤ ህመም ይኖራቸዋል። ነገር ግን መወሰናቸው የግድ ነው፤ መደረጋቸው፣ ወደ ምድር መውረዳቸው የግድ ነው። ህመም በተባለው እልህ አስጨራሽ ጉዞ መደሰት ስትጀምር በህመምህ መፈወስ ትጀምራለህ፤ በስቃይህ እየዳንክ፣ ህይወትህን እያሻሻልክና እያደክ ትመጣለህ። በሚያድንህ ታመም፤ በእርሱም ነፃ ውጣ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! ???
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! ?

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
?? SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro ? ?

2 months, 2 weeks ago

ለውጥን አትፈልጉት!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
ለውጥን አትፈልጉት ይልቅ ለውጥን ምረጡ። ስለምን ለመለወጥ ብላችሁ ረጅም ርቀት ትጓዛላችሁ? ስለምን ለውጣችሁን ከማይፈልጉ ሰዎች ጋር ትሆናላችሁ? ስለምን መለወጥ ስለምትፈልጉት ነገር አብዝታችሁ ትጨነቃላችሁ? ለውጥን ፈልጋችሁ ወይም ያለልክ አስባችሁ አታገኙትም፣ ምክንያቱም አጠገባችሁ ነውና፣ ምክንያቱም በየቀኑ እያለፋችሁበትና እየኖራችሁት ነውና። ብዙ ሰዎች ለመለወጥ ብዙ ሲያወጡ ብዙ ሲያወርዱ ይስተዋላል ነገር ግን ከማውጣትና ከማውረድ በላይ እራሳቸው የት እንዳሉና ምን እያደረጉ እንዳሉ መገንዘብ ይኖርበታል። ለውጥ ተራራ ላይ የተቀመጠ ወይም ከርሰምድር ውስጥ የተቀበር ማዕድን ወይም እንቁ አይደለም። ለውጥ ግልፅ ነው። ትናንት ነበረ፣ ዛሬም አለ እንዲሁ ነገም ይኖራል። እርሱን ለማምጣት ከመታገል በላይ ራስን ማየትና የግልን የህይወት አቅጣጫ መረዳት እጅጉን ወሳኝ ነው። እናንተ የምትሰሩትን ስራ ከልብ ከሰራችሁ፣ ሁሌም ትኩረታችሁ ራችሁ ከሆነ፣ ከጊዜ ጊዜ ከቀን ወደ ቀን ከመሻሻል ወደ ለውጥ ከለውጥም ወደ እድገት የማትገቡበት ምንም ምክንያት አይኖርም።

አዎ! ለውጥን አትፈልጉት፣ እርሱን ለማግኘት ብዙ አትልፉ፣ በስሜታችሁ እንዲጫወት፣ ከሰዎች ጋርም እንዲያነካካችሁ አትፍቀዱ። ለውጥ በየቀኑ በሁላችንም ህይወት ውስጥ ሊከሰት የሚችል ነገር ነው። የእኛ ድርሻ የለውጡን አይነት መምረጥ ነው። በሚያሳድጋችሁ ወይም በሚጥላችሁ የለውጥ መንገድ የመጓዝ መብቱ አላችሁ፣ በአዎንታዊው ወይም በአሉታዊው አቅጣጫ የመሔድ ምርጫ አላችሁ። ማንም ሰው እንደ አቅሙ የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ጠንቅቆ ያውቃል። "ውሃ ውሃ ነው ያሰምጥሃል፣ እሳትም እሳት ነው ያቃጥልሃል" መባል ያለበት ሰው የለም። ማንም ሰው የራሱ የእውቀትና የመረዳት ደረጃ አለው። ህይወት በብዙ አቅጣጫ ትሰራናለች፣ ህይወት በብዙ ዘርፍ ታንፀናለች። አንዴ በደስታ አንዴ በሃዘን፣ አንዴ በፍቅር አንዴ በጥላቻ፣ አንዴ በማቅረብ አንዴ በማራቅ ትገለፅልናለች። ለምን ብላችሁ መድከም እንዳለባችሁ አስቀድማችሁ እወቁ፤ መውጣት መውረዳችሁ፣ መሰደብ መተቸታችሁ፣ መገፋት መጠላታችሁ ለምን እንደሆነ አስቀድማችሁ ተረዱት። ይሔ የምትከፍሉት ዋጋ በእርግጥም ለሚመጣው ውጤት የሚገባው ነው? ጥያቄውን በጥንቃቄ መልሱ።

አዎ! ጀግናዬ..! በየቀኑ ህይወትህ እየተቀየረ ነው። ነገር ግን ወዴት እየተቀየረ እንደሆነ መረዳቱ ከሌለህ እየጠፋህ እንዳሆነ አስተውል። አንድ ቀን ስትነቃ አስበህ እንኳን የማታውቀው የማትፈልገው ቦታ ራስህን እንዳታገኘው ዛሬውኑ እያንዳንዱን እርምጃህን በጥልቀት መርምር። ማንንም ለመግዛት ከማኮብኮብህ በፊት ስለራስህ መነሻና መዳረሻ እውቀቱ ይኑርህ። ህይወትህን በምታሻሽልበት በእያንዳንዱ ቅፅበት የምታስተውለውን ነገር አስቀድመህ የምታጣጥመው አንተ ነህ። በሰዎች ላይ የምትመለከተውን ለውጥ መመኘት አቁም፣ በምትኩ ባንተ ህይወት እየተከናወነ ስላለው ለውጥ ግንዛቤው ይኑርህ። አንተ በንቃት የምትረዳውም የማትረዳውም ብዙ ነገር በህይወትህ ውስጥ እየተከናወነ ነው። አይንህን ክፈት፤ አሁን በዋናነት በህይወትህ ውስጥ እየተከናወነ ያለውን ክስተት ትወደዋለህ? ትፈልገዋለህ? ያንን የምትመኘውን ለውጥ ለማምጣት የሚጠቅምህ ይመስልሃል? ጊዜ አታጥፋ፣ የምትፈልገውን ለውጥ አሁኑ ምረጥ፣ በእርሱ ላይም ለመስራት በልበሙሉነት ተነስ።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! ???
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! ?

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
?? SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro ? ?

2 months, 3 weeks ago

ከብዛት ጥራት!
፨፨፨//////፨፨፨
ከብዛት ጥራት አጭርና ግልፅ መርህ። በዙሪያችሁ መቶ ሰዎች አያስፈልጓችሁም፤ በአንዴ ብዙ ስራ መስራት አይጠበቅባችሁም፤ ሁሉም ቦታ ለመገኘት መሯሯጥ አይኖርባችሁም፤ የምታውቁትን ሰው ሁሉ ለማስደሰት መጨነቅ አይኖርባችሁም። ቀላሉን መርህ አስታውሱ፦ "ከብዛት ጥራት" አለቀ። ኮተት አታብዙ፣ ህይወታችሁን ጥራት ባላቸው ሰዎች፣ ተግባሮችና ውጤቶች ሙሉ። ጥራት ያለው፣ ትርጉም የሚሰጥ፣ የተገደበና የተመጠነ ስራን ስሩ። አስር ቦታ ተበጣጥሳችሁ ከአስሩ አንዱንም ሳታገኙ እንዳትቀሩ ተጠንቀቁ። በሁሉ አማረሽ እሳቤ ሁሉን አጥታችሁ እንዳትቀሩ። ተሰብሰቡ፣ ጥቂቱን ወሳኝ ነገር ምረጡ፣ ዙሪያችሁን በተወሰነ ጠቃሚ ነገር ሙሉት። አስከዛሬ የተማራችሁትን ወይም የምታውቁትን ሁሉ በአንዴ ለማድረግ ብትሞክሩ ምንያህል ጭንቀት ውስጥ ትገቡ ነበር? ለአስሩም ጓደኞቻችሁ ጥሩ ለመሆን ስትሞክሩ ለራሳችሁ ምንአይነት ሰው ትሆኑ ነበር? እዚም እዛም፣ የሚመጥናችሁም የማይመጥናችሁም ቦታ እየተገኛችሁ ቢሆን የጊዜ አጠቃቀማችሁ ብሎም የህይወት ጥራታችሁ ምን ይመስል ነበር?

አዎ! ከብዛት ጥራት! ከምርጥም እጅግ በጣም ምርጥ፣ ከጥሩ እጅግ በጣም ጥሩ። በአማካኝ ነገሮች መከበብ አቁሙ፤ ዞሮ ዞሮ እዛው ከሆነ አካሔድ ውስጥ ውጡ። የትኛውም የሰው ልጅ ሊከተለው ከሚገባው የህይወት መርህ ውስጥ አንዱ  "ከብዛት ጥራት" የሚለው መርህ ነው። አቅሙ አለኝ ወይም ጊዜ አለኝ ተብሎ ሁሉም ነገር አይነካካም፣ ሁሉም ነገር አይሞከርም። የያዙትን አንድ ነገር አድምቶ መስራት፣ የፈለጉትን አንድ ነገር እስከመጨረሻው መከተል፣ ለሚያውቋቸው ጥቂት ሰዎች ህይወት ቀያሪ ተግባርን መፈፀም። አዋቂ የሚባሉ ሰዎች ምናልባትም ብዙ ነገር ያውቁ ይሆናል የሚኖሩት ግን የመረጡትንና በህይወታቸው ለውጥ እንደሚያመጣ የሚያምኑትን የተወሰነ እውቀት ነው። ከሚታወቀው ጥቂቱ እንኳን ፍሬ ያፈራ ዘንድ ተመረጦ ሊከወን ይገባዋል። ልኬት የህይወት ጠዓም መሰረት ነው። እዚም እዛም ማለት አቁማችሁ የያዛችሁት ላይ ብቻ አተኩሩ።

አዎ! ጀግናዬ..! ራስህን ቆጥብ። ችሎታው አለኝ ብለህ ያገኘሀው ዛፍ ላይ አትንጠልጠል፣ ያየሀውን ነገር ሁሉ አትሞክር። ሁሉንም ነገር ለማየት በጣርክ ቁጥር የምርም ያንተ የሆነውንና ላንተ ህይወት የሚመጥነውን ነገር ታጣዋለህ። ጓደኞችህን መጥን፣ ስራህን መጥን፣ ውሎህን መጥን። ሰብሰብ በል፣ ጥራት ያለው ህይወት ለመኖር አማራጮችህን ገድባቸው። ከመደበኛው ትንሽ ከፍ ያለ ህይወት ከተለመደው የተለየና ጠለቅ ያለ እውቀትና ተግባርን ይፈልጋል። ከባዱ ነገር ብዙ ነገር መሞከር ሳይሆን አንድ የያዙትን ነገር እስከመጨረሻው ታግሎ ማሸነፍ መቻል ነው፤ የእውነትም ትልቅ ጥረትን የሚፈልገው ነገር ከብዙ ሰዎች ጋር ከአንገት በላይ መተዋወቅ ሳይሆን ከጥቂቶች ጋር ልብለልብ መተዋወቅ ብሎም መግባባት ነው። ህይወትህን በፈተና የተሞላች አታድርጋት። መርሁን ተግብረው። ብዙ ከማሳደድ ጥቂቱን ጥራት ያለውንና የሚጠቅምህን ነገር ብቻ በመያዝ አሳድግው።
ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን! ???
(Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! ?

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
?? SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro ? ?

2 months, 3 weeks ago
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™
2 months, 3 weeks ago

*? *መታደስ ትችላለህ! *?***
እንደ አዲስ፣ ቀድሞ እንዳልነበረ፣ ሆነህ እንደማታውቀው፣ በማንም እንደማትታወቀው እንደሌላ ሰው በሌላ ማንነት፣ በሌላ አመለካከት፣ በሌላ አስተሳሰብ እንደገና መታደስና መሰራት ትችላለህ። ያለፈው ታሪክህን እንደ አዲስ መፃፍ፣ የተበላሸው ስብዕናህን ዳግም መገንባት፣ ያጠፋሀውን ጥፋት ማረምና ማስተካከል ትችላለህ። ያለፈው ማንነትህ የአሁን መገለጫህ አይደለም፤ የቀድሞው መታወቂያህ አንተን አይደለም። በልብህ የያዝከው፣ በውጥህ የሚመላለሰው የጥፋተኝነት ስሜት የሚከስምና ሊጠፋ የሚችል ነው። እንደነበር ሊቀጥል የሚችለው የተኛውም ነገር ሲፈቀድለትና ሲፈቀድለት ብቻ ነው። ህይወት አንድ ነችና ውድ ነች፤ መተኪያ የላትም። በዚህ ህይወትም እራስህን በጥፋተኝነት ስሜት እየወቀስክ የምታጠፋው ጊዜ ሊያሳስብህ ይገባል። የተበላሸው ቢበላሽ ስለሚስተካከለውና መታረም ስለሚችለው ነገር ማሰብ ይኖርብሃል።

አዎ! ጀግናዬ..! መታደስ ትችላለህ! ከቀድሞ ታሪክህ ምን አተረፍክ? ከነበርክበት የፍቅር ህይወት ምን አገኘህ? ከከበቡህ ሰዎች ምን ተሰጠህ? ከጓደኞችህ ምን ተማርክ? ትናንት ከባድ ችግር ውስጥ ነበርክ፤ ትናንት የሚያልፍ ያልመሰለህ አጣብቂኝ ውስጥ ነበርክ።  ነገር ግን የማያልፉት የለምና ያ ሁሉ ከባድ የህመም ጊዜ፣ የስቃይ ጊዜ፣ የመከዳት ጊዜ፣ ፊት የመነሳት፣ የመገፋት፣ የመጠላት ጊዜ ሁሉ አብቅቷል። ነገሮች ሁሉ አብቅተው አዲስ ሰው ለመሆን በቅተሃል። የየለት እድሳትህ አዲስ ማንነትን ከተለየ ስብዕና ጋር ያድልሃል። ለመታመምህ ምክንያት የሆነን ሰው የመተው አቅም እንዳለህ አስታውስ። መቼም ዋጋ እንዳለህ እንዳትረሳ፤ መቼም ብትወድቅ ዳግም መነሳት እንደምትችል እንዳትረሳ፤ መቼም ከቁስና ከገንዘብ የላቀ ማንነት እንዳለህ እንዳትረሳ፤ ትላንትህ ዛሬህን እንደማይወስን እወቅ፤ ዛሬህ ነገህን እንደማይለካ ተረዳ።

አዎ! ምቾት ያለው እድሳት የለም፤ አልጋ በአልጋ የሆነ ለውጥ አይኖርም። ለእራስህ እንደምታዝን እያሰብክ የሚመችህን ብቻ እየመረጥክ ልታደርግ ሰትችላለህ፣ ነገር ግን የትናት ታሪክህን ከመድገም ሌላ ነገር አትሰራም። እራስህን ለማድስ፣ በአዲስ ማንነት ለመመለስ፣ የተለየውን አንተ ለመፍጠር የሆነብህን፣ የደረሰብህን ነገር በሙሉ መናገርና ማስረዳት አይጠበቅብህም። የሆድህን በሆድህ ይዘህ፣ ህመመህን እንደ ሃይል ተጠቅመህ፣ ስቃይህን እንደተለየ ወኔ ወስደሀው አዲሱን አንተ መፍጠር ትችላለህ። ገና ያልተፃፈባቸው ባዶ ገፆች ከፊትህ ይጠብቁሃል። በማትወደው ማንነት አዲስ ታሪክ መፃፍ አትችልምና የምትችለውን እድሳት በቻልከው ፍጥነት ከውነው። የማያኮራህን ትናንት እርሳው፤ አዲስ ታሪካዊና አኩሪ ዛሬን ወደመፍጠር ተሸጋገር።

2?17
? የስኬትና የደስታ አመት ይሁንሎ! ?
?ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! ?****

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
?? SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @MentalCounsel ? ?

2 months, 3 weeks ago
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago