Eliyah Mahmoud

Description
Advertising
We recommend to visit

Books only!

This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !

Join and share @Books_worldd

አስተያየት @BooksWorlddd_bot !

@books_worlddd መወያያ ግሩፕ

#share

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Last updated 5 months, 4 weeks ago

?"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው።
?በደረጃ የሚለቀቁ
1:-ነህው
2:-ሶርፍ
3:-ተጅዊድ
4:-ተፍሲር
5:-ፍቅህ
6:-አቂዳ
7:-መንሀጅ
8:-ሀዲስ
9:-ሲራ
10:-ሙስጦለህ
11:-ቀዋኢደል ፍቅህ
12:-ኡስሉል ፊቅ
13:-አህላቅ ወል አዳብ
14፡-ስለሴቶቻችን
15:-ንፅፅር

Last updated 2 months, 3 weeks ago

3 days, 18 hours ago

أقول وقد ناحت بقربي حمامة
أيا جارتا لو تشعرين بحالي
معاذ الهوى ما ذقت طارقة النوى
ولا خطرت منك الهموم ببال
أيا جارتا ما أنصف الدهر بيننا
تعالي أقاسمك الهموم تعالي

ይህንን ግጥም አቡ ፊራስ አልሐምዳኒ የተባለ ፈረሰኛ ጀግና በጠላቱ እጅ ምርኮኛ ኾኖ ከወደቀ በኋላ እንደተናገረው ይነገራል።

ግለሰቡ ከታሰረበት ቦታ ከፍ ብሎ ልብን በሚሰብር ድምጽ አንዲት እርግብ ስታንጎራጉር ይሰማታል።

የርሱን ድንገት ከቤቱ ወጥቶ ምርኮኛ መኾንና ምናልባትም በዛ ሊቀር መኾኑን አስቦ፣ይሕች ወፍ በሐገሯ ሰማይ ስር ኾና በዚህ ልክ በሐዘን ስትዘምር ሲያይ፣ ከራሱ ኹኔታ ጋር እያወዳደረ፦

"ከጎኔ ኾና ስታንጎራጉር ወፊቷ ድንገት
ጎረቤቴ ሆይ ቢሰማሽማ ኹኔታዬ ያለኹበት
ትዕቢትን ጣል አርገሽ ብለሽ ድብቅ ስትር
በቅጽበት መለያየትንም ባልቀመስሽ ነበር
ሐዘንም ባልነካሽ ባላልሽ ክስት ምርር
ጎረቤቴ ሆይ ጊዜ ሲፈርድ እኮ ይደንቃል!
ነይማ ጠጋ በይ ጭንቀቴን ለአንቺ ላካፍል "

በማለት ያለበትን ጭንቀት ነገራት ይባላል።

ይሕ ክስተት በሐበሽኛ "እናቱ የሞተችበትም እናቱ ገበያ የኼደችበት ሕጻን እኩል ያለቅሳሉ" እንደ ማለት ነው።

اللهم لا سهل إلا ما جعلته سهلا وأنت تجعل الحزن إذا شئت سهلا
https://t.me/E_M_ahmoud

6 days, 5 hours ago

راقـ ـصات حول مجسم الكعبة وشيخ سعودي يبكي على انتهاك حرمات الله في موسم ... https://youtube.com/watch?v=YjA1kGMy1V8&feature=shared

1 week, 2 days ago

አወወ ይህንን ቻናል እናስተዋውቅልኽ ያላችኹኝ ሰዎች በመጀመሪያ አላህ ምንዳችኹን ይክፈል እላለሁ።

ቀጥዬ ቻናሉ ለዛ በቂ ነው ካላችኹ አስተዋውቁት ግን የኔ ግፊት አይኹን።

የተከታዬ ቁጥር ጨመረም ቀነሰም ማለት የፈለግኹትን የምልበት ቤቴ ስለኾነ ከመጻፍ አልቦዝንም።

ላለፉት ስምንት ዓመታት የዚህ ቤት እድርተኛ ከአንድ ሺህ ከምናምን ዘሎ አያውቅም።

ግን ማስታወቂያም ኾነ እዚህ እናድርሰው የሚል ቻሌንጅ ከትቤ አላውቅም። አለከትብምም።

የሻ ሰው ሐሳቤ ተስማማውም አልተስማማውም አብሮኝ ይዝለቅ። የኮሰኮሰው ደግሞ ሊሰናበተኝ መብቱ ነው።

ለማንኛውም ወዳጄ የማስተዋወቅና የማዳረሱን ምርጫ ለእርሶ ትቻለኹ።

🙏አመሰግናለሁ 🙏

https://t.me/E_M_ahmoud

1 week, 5 days ago

ሶስት ነገራትህን ሸሸግ አድርግ
....

ኢብኑል ጀውዚ ስስት ነጋራትኽን ሸሸግ አድርግ ይላል።

፩ኛ) ንብረትኽን

ይህን ያህል ገንዘብ አለኝ፤ይህን ያህል እነገሌ ዘንድ ደግሞ በብድር የተወሰደ አለኝ ወዘተ...ማለት ታይታን ወይም ምቀኝነት ስለሚያስከትል የንብረትኽን መጠን አታውራ ይላል።

፪ኛ) ዕቅድኽን

ዕቅድ በሰውዬውና በአላህ መካከል መሸሸግ ያለበት ነገር ነው።

ምናልባት እዚህ ጋር የጋራ ዕቅድ፣ ወይም የመስራ-ቤት ራዕይ እንዳልኾነ ይሰመርበት።

ኢብኑል ጀውዚ ሊነግረን የፈለገው ኹሉም መድረስ የሚፈልግበት የሕይወት ግብና መዳረሻ ነጥብ አለው፤ ያንን ነጥብ ለራሱና ለአላህ ይተወው የሚል ነው።

አንድ ሰው የሕይወት ግቦቹን የባቄላ ወፍጮ አድርጎ በየደረሰበት መበተኑ በአላፊ አግዳሚው አፍ እንዲገባ ከማድረግ በዘለለ የሚያተርፈው ሒስድን ወይም ተጠግቼ ልብላ የሚሉ ስግብግብ አፎችን ብቻ ነው።

፫ኛ) የሕይወት መርሆዎችኽን
....

ከኢስላማዊ ርዕዮት በዘለለ አንድ ሰው ከራሱ ተሞክሮ የሚከተላቸው የሕይወት ፍልስፍናዎች / አካሄዶች ሊኖሩት ይችላል።

ፍልስፍናው ለራሱ ሰርቶለት ለሌላው ግን ላይሰራ ስለሚችል ርዕዮቱን ቢደብቅ ይሻላል።

ማንም ሰው በግል ሕይወቱ ምከረኝ ካላለኽ በስተቀር ልምከረው ብለኽ አትጣደፍ።

ስለ ራስኽም ቢኾን ብዙ ከማውራት ተቆጠብ።

አንዳንዶች ሰዎች ስለነርሱ መስማት እጅጉን የሚጓጉ፣ ከልብ የሚያስደስታቸው የልጅነታቸው የእናታቸው የእሹሩሩ እንጉርጉሮ ይመስላቸዋል?

ወዳጄ ጉዳዩ ወዲህ ነው! ስለ አንተ ኹሉንም ነገር መስማት የምትወደው ብቸኛዋ ሰው እናትኽ ብቻ ናት።

ትላንት ከነምናምናችን ስማ ያጎረሰችንና ጀርባዋን እንዳይኾን ያደረግናት በሕይወት እስካለች ድረስ ስለ እኛ ምኑንም ሳትጠየፍ ኹሉንም ማወቅና መስማት ትወዳለች።

ከእናትህ ውጪ ያለ የትኛውም ሰው ራሱን የሚያዳምጥበት እንኳ በቂ ጊዜ ሳይኖረው ያንተን የጨረባ "ዘፈን" ሰለምን እንዲያዳምጥ ትፈርድበታለኽ?!

ወዳጄ ተቸገርኽ ከኾነ መቸገርኽ ለራስኽ ነው ! የኾነ ነገር መስራት ፈለግኽ እንደኾነ ለራስኽ ነው! ...በጥቅሉ አፍህን ከፍተኽ ላውራኽ የምትለው ኹሉ የኋላ ኋላ ቢታዘብኽ እንጂ ዘንጋዳ ዘግኖ አይሰጥኽም። ለአንተ ከሚሰጥኽ ይልቅ ቢበትነው እጅግ ይወዳል።

ወዳጄ ይህችን "ኹሉም ለራሱ ነው!!" የምትለውን የዱንያም የአኺራም መርሆን ልብ ይበሉ።

ዱንያ ላይ ኹሉም ለራሱ ብቻ ነው!!!! አኺራ ላይም ኹሉም ስለ ነፍሱ ብቻ ተሟጋች ነው።

لكل امرئ منهم يومئذ شأن يغنيه

ኢብኑል ጀውዚን (ዐለይሂ ረሕመቱላህ) ይህችን ውድ ነገር ስለነገረን አመሰገንን፦

اكتم عن الناس ذهبك وذهابك ومذهبك
....
ማብራሪያዎቹ የግሌ ናቸው
https://t.me/E_M_ahmoud

2 weeks ago

ኺንፊሻር
....

በዐረቦች ተረተ አንድ ኹሉን ዓዋቂ መሐል ጠሊቅ ነኝ የሚል ሰው ነበር አሉ።

ይህ ሰው ስለተጠየቀው ነገር ኹሉ ዐውቃለኹ እያለ ከጥንት ስነ-ግጥምም ከስነ-ቃልም ጭምር ምሳሌ እያደረገ ይመልስ ነበር።

አንድ ቀን የአካባቢው ሰዎች እርስ በርስ " ይህ ሰው እንዴት ይህንን ኹሉ ነገር ሊያውቅ ቻለ? ትላንት ከኛ ዘንድ ሲመላለስ የነበረና በዕድሜም ታናሻችን የኾነ የምናውቀው አይደለምን?" ተባባሉ።

ቀጠሉናም " ዕውነተኛ መኾኑን ለማወቅ አንድ የኾነ ቃል እንፍጠርና ይህ ምንድን ነው ብለን እንጠይቀው፤ ዐውቃለኹ ብሎ ከመለሰ ውሸታም መኾኑን እናውቃለን። እናጋልጠዋለንም።" ተባባሉ። ተስማሙም።

ከዚያም ሰውየው የሚያስተምርበት ቀን ላይ ሄደው ከፊቱ ተኮለኮሉ። ለጥቀውም "ኺንፊሻር" ምንድነው ብለው አዲስ የፈጠሩትን ቃል ጠየቁት።

ሰውየው አሰብ አደረገና " ኺንፊሻር ማለት የእጽዋት ዓይነት ነው። ቅጠሉ የዚህ ዓይነት ነው። ግንዱ ደግሞ ...ወዘተ" እያለ አናቶሚውን ዘረዘረው።

አስከተለናም ከጃሂሊያ ግጥሞች ማሰረጃ ለማድረግ የራሱን ስንኝ ፈጠረ፦

لقد عَقَدَت محبتُكم فؤادي

كما عقد الحليبَ الخنفشار

"ኺንፊሻር ወተትን እንደሚያረጋ
የናንተም ፍቅር ልቤን አረጋጋ"

ካለ በኋላ ከሐዲስም ጭምር ማስረጃ ለማምጣት ሲያኮበኩብ " በሌላው ላይ የዋሸኸው ይበቃል፤ በመልክተኛው ላይ ስትዋሽ መስማት አንፈልግም" ብለው ጮኸው ተነሱ። ሰውየውም ውሸታም መኾኑ ታወቀ።

ከዚያ ቅጽበት በኋላ ሰውዬው ከልቡ ውሸታም እንደኾነና በዙሪያውም ያሉ ከዕውቀት የተጣሉ የሰሙትን በጥሬው አምነው የሚቀበሉ መኾናቸው ይፋ ኾነ።

ወዳጄ ይህንን ምሳሌ ከዛሬዎቹ ኹሉን እናውቃለኖች ጋር አገናኙት።

ለኛ ትምህርት ይኾነን ዘንድ ደግሞ፦

"وَلا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَـٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْؤُولًا"

https://t.me/E_M_ahmoud

2 weeks, 1 day ago

መልካም ጥርጣሬ
.....

ልጅቷ በኹለት እጆቿ ቱፋሕ ይዛለች። እናት ከኹለቱ ቱፋሖች አንዱን ትሰጣት ዘንድ ጠየቀቻት።

ልጅቱም አሰብ አድርጋ በቀኝ እጇ የያዘችውን ቱፋሕ ግምጥ አድርጋ ማለመጥ ጀመረች።

እናት በግራ እጇ የያዘችውን ትሰጠኛለች ብላ ስትጠብቅ፣ልጂቱ ቀጥላ በግራ እጇ የያዘችውን ደግሞ ገምጣ ማላመጥ ጀመረች።

ይህን ያየች እናት በልጇ ተግባር ተናዳ፣ "ለእኔ ለእናትሽ አንዱን መስጠት እንዴት ከበደሽ? አንቺ ከመች ጀምሮ ነው በዚህ ልክ ስስታም የኾንሽው?..." ብላ ኃይለ- ቃል ጨማምራላት እየተመናጨቀች ጥላት ከክፍሉ ወጣች።

ብዙም ሳይቆይ ልጅቱ " እናቴ ይህንን እንኪ" እያለች ከኋላ ትከተላት ጀመር።

እናቲቱ የበለጠ ንድድ ብላ "የበላሽለትን ነው እንዴ የምትሰጭኝ? ትንሽ አይከብድሽም?..." ብላ አጉረጠረጠችባት።

ልጂቱም " የትኛው እንደሚጣፍጥ ስላላወቅኹ ነው እንደጠየቅሽኝ ልሰጥሽ ያልፈለኩት፤ ይኽኛው የበለጠ ስለሚጣፍጥ ይህንን ውሰጂ" ስትላት፣ እናት በራሷ እፍር ብላ በልጇ አስተሳሰብ ተደንቃ ተቀበለቻት።

እናም ወዳጄ አንድ ሰው በተመኩሮውም ኾነ በዕውቀቱ የትም ይድረስ በመልካም ጥርጣሬ ካላጌጠ ሲከፍቱት ተልባ መኾኑ አይቀርምና ይታሰብበት።

ፈረንጆቹ "Don't judge a book by its cover _ የመጽሐፉን ሽፋን ዓይተህ ስለመጻፉ አትፍረድ" ይላሉ።

መረሳት የሌለበት አላህ በቃሉ እጅግ በጣም ተጠንቀቁ ያለን ክፉ ጥርጣሬን ነው፦

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اجْتَنِبُوا كَثِيرًا مِنَ الظَّنِّ إِنَّ بَعْضَ الظَّنِّ إِثْمٌ وَلَا تَجَسَّسُوا وَلَا يَغْتَبْ بَعْضُكُمْ بَعْضًا...

https://t.me/boost/E_M_ahmoud

3 months, 1 week ago

ኢራንና የበቀል እርምጃዎች
....

ዛሬ በወጣው መረጃ መሠረት ኢራን የበቀል እርምጃዎችን ላለመውሰድ የጽዮናዊው መንግሥት የተኩስ ማቆም አድርጎ ከጘዛ ለቆ መውጣት አለበት የሚል መስፈርት አስቀምጣለች።

መጨረሻው ምን እንደሚኾን ባናውቅም ኢራን ከነዳጅ ሽያጩ አኳያ ከአሜሪካ የሚጣልባትን ማዕቀብ ከልቧ የፈራች ይመስላል።

ሒዝቡላህ የሀኒዬ ደም እጃችን ላይ አለ፤በቀሉን አንረሳም እያለ ነው።

ፉከራው እንዳለ ኾኖ ሒዝቡላህ በኢራን የሚዘወር ማሽን ስለኾነ ኢራን ወደምትመራው መዘንበሉ አይቀሬ ነው።

ግራም ነፈሰ ቀኝ የፍልስጤም ምድር ሰላም እንዲኾን መከፈል ያለበት መስዋዕትነት መከፈሉ የተሻለ ይመስለኛል።

በኢራን የ"በቀል" ዱላ ተጨማሪ ሙስሊም ከሚሞት የተኩስ አቁም ድርድሩ ሲሻልም ይበልጣል።

https://t.me/E_M_ahmoud

3 months, 2 weeks ago

ጉድ ተሰምቶ መስከረም ጠብቶ...
.....

ሚዲያው ላይ ከተቃራኒ ጾታ ጋር የወደቁ የክርስቲያን ዐቃቤያንን ስታይ ኢስላም ዝሙትን እንዳትቀርቡ ብሎ ከመንደርደሪያው ጀምሮ የዘጋው በር ምንኛ ሰላማዊ እንደኾነ ትረዳለኽ።

በኢየሱስ ስም ወንድምና እህት ነን ያሉ ስጋ አሸናፊ መኾኑን ዘንግተው እንዳልኾነ ዕሙን ነው። ግን ደግሞ አጋጣሚዎችን ለፍቃደ- ስጋና ለጉልሙትና መጠቀሙ የተሻለና ወረቃማ ዕድልም ስለኾነላቸው ነው።

ለዛ ሰፈር ዐቃቤያን "በኢየሱስ ደም" ኹሉም ዕዳ ከተከፈለ፣ደጋግሞ ዝሙት -ወ-ምርዐት( ምርዐት= የድብቅ ድሪያና ንክኪ) ውስጥ መገኘት በ"ንስሐ" የሚሰረይ ከንቱ ነገር ነው።

ከካቶሊክ እስከ ጴንጤ እስከ አስጠማቂ የነፍስ አባት ኦርቶዎች በስጋው ረክሶ ተቋሙን ያላሰደበ አንድስ እንኳ የለም።

ዛሬ ላይ ደግሞ ሚዲያ ላይ የምናውቃቸው ትናንሽ አጋንንቶች በፍትወተ ስጋ -ወ-ነፍስ ጎጆአቸው ሲፈርስ አጓጉል የደመቁ ስሞቻቸው እንዳልኾነ ሲደበዝዙና ሲጠፉ እየታዘብን ነው።

ከሰሞኑን አንድ የዛ ሰፈር ኮርማ በየሜዳው ከሚያጅቡት አለሌዎች ጋር መውደቅ ማብዛቱና ከዚያም አልፎ አንዳንዶች "ቅዱስ" ዘር እንደተሸከሙለትም ያስረገጠ ወሬ ተሰምቷል።

ይህ ያልተኮላሸ ኮርማ የመሰሎቹን ኅልቆ-መሳፍርት ኮርማዎች ፈለግ ኅያው አደረገ እንጂ አዲስ ነገር እንዳላደረገ ይሰመርበት።

የዚህ የጉልምትና ትምህርት ክፍል ምስለኔዎችና ሊቃውንት ከኮሮዶቻቸው አልጋ ስር ተደበቁ እንጂ ገና ብዙ ናቸው። እያደር ከነረከሰ ገላቸው አደባባይ ይሰጣሉ።

"አንድ አንበሳ ገድሎ ይፎክራል ሐገር
መንጋውን ቢያሳዩት ለቅሶ ይቀመጥ ነበር"

ወዳጄ ልብ ይበሉ! በኢስላም ላይ ጦሩን የሰበቀ ኹሉ ይዘገያል እንጂ በገዛ ጦሩ መወጋቱ አይቀርም።

እኛ ባልጠበቅነው መንገድ ኢስላምን ለምን ያሉ ኹሉ መጨረሻቸዉ መቀመቅ ነው።

إنا لننصر رسلنا والذين آمنوا في الحيات الدنيا ويوم يقوم الآشهاد

አላህ እርዳታውን እንዴትና በነማን በኩል እንደሚያደርገው አናቅም። ከኾነ በኋላ ግን እናየዋለን እንዳስሰዋለን።

وما يعلم جنود ربك إلا هو

https://t.me/E_M_ahmoud

3 months, 2 weeks ago

ከአላህ ተስፋ የሚቆርጥ ጠማማ ብቻ ነው
......

ያለንበት ኹኔታ ምንም ደስ ባይልም፣ኑሮ ከጣራነት ወደ ጣርነት ቢለወጥም፣ነገ በትክክል ከነ ሙሉ ብርሃኗ ትነጋለች።

ወዳጄ ይህችን ዱዓ ደጋግመው ይበሉት ኢንሻአላህ ካላሰቡበት ስፍራ ሲሳዩ ይከፈታል።
اللهم إني أسألك من فضلك ورحمتك فإنه لا يملكها إلا أنت
አላህ ሆይ ከአንተ ውጭ ማንም ከየሌለው ከችሮታኽና ከእዝነትኽ እለምንኻለው

ዱዓውን መልክተኛው (ሰለሊሁ ዓለይሂ ወሰለም ) ያደረጉት እንደነበር ሰሒሕ ሐዲስ አለ።

https://t.me/E_M_ahmoud

3 months, 2 weeks ago

ትንሽም ብትኾን ካለኽ ላይ መስጠትን ካለመድኽ በባሕር አሸዋ ልክ ሐብት ቢኖርኽ እጅህን መዘርጋት በፍጹም አትችልም፡፡ ምክንያቱም ወዳጄ ነፍስ ያስለመድካትን ከመከተል በዘለል ኾነኽ ያላደከውን ከመቅጽበት አድርጋኽ ልትፈጥርኽ አትችልም፡፡

ዛሬ ላይ ካላቸው ሐብት አኳያ እጅግ ንፉግ ኾነው የምታያቸው ግለሰቦች እድገታቸውም እንዲኹ እንደኾነ ልብ በል፡፡ ይህ አበክሮ ንዋይን መውደድና የምጽዋት ድህነት በኹሉም የሕይወት ደራጃ ያሉ ኣካላት ላይ አለ፡፡ኢስላማዊ ትምህርት መማር የሚፈልጉ ግን ደግሞ ትንሽ ለትምህርቱ ማድረግ ሲጠበቅባቸው ወገቤን የሚሉ ኅልቆ-መሳፍርት የሚዲያ ሰዎች አሉ፡፡

የሚሰጠው ስልጠና በነጻ የኾነ ጊዜ እጅግ ት/ት ፈላጊ ኾነው የምታያቸው ለኢንተርኔት ከምታወጣው ላይ ለዳዕዋው ትንሽም ቢኾን መጽውትና ተማር.፤ለአንት በአንድ ድንጋይ ኹለት ወፍ መምታት ይኾናል፤ትማራለኽ ዳዕዋውንም ታግዛለኽ ስትለው ከደሙ ላይ አንጥፍጥፎ እንደሚሰጥ ኹሉ ነፍሱ ልትወጣ የምትደርስ የሚዲያ ስብስብ እንደምን ብሎ ነው ከኢስላም አኳያ ከፍ ላለ ነገር ዝግጁ የሚኾነው?

ይህ ነገር ኹሉ ካንገት በላይ የኾነበት የእብለት ክምችት ዩትዩብ ላይ የሚለቀቁ ቪዲዮዎችን በማየት ብቻ በብዙ ዳዕዋውን መደገፍ በቻለ ነበር፡፡ ግን የእነ እንቶኔን የቀልድና የጋብቻ መሰናዶ ማን ይይ?! የነ አያ እግሌን የዩትዩብ መሰናዶ ከነጭፈራቸውና ብልግናቸው ማን ይይ?

ቲክታክ ላይ በዳዕዋው እየታገሉ ያሉ ወጣቶቻችን ከፍ ባለ የትምሕርት ዝግጅት ውስጥ እንዲያልፉ ቢደረግ ምን ያሕል አኹን ካለው ከፍ ያለ ስራ ይሰሩልን ይኾን?! ብለን ኣዕላፍ ጊዜ ብንናገር ቲክቶክ ለመዝናናት የሚገባው ባለ ሐብት ጆሮ ሊሰጠን አልቻለም፡፡

እነዚህ ወጣቶች ከናለባቸው ችግር ብዙን ነገር ተሸክመው እንዳሉ እየታወቀ፣ እነሱን በምን እናግዝ ያለ ደፋር እስከ አኹንም ብዙ አላየንም፡፡

እመነኝ ወዳጄ ከፈለክ ትንቢተ-ዘሼኽ ጅብሪል በለው ወይም ኖስትራዳማስ (ኹለቱም ውሸት እንደኾኑ ይሰመርብት) ብቻ የኑሮው ኹኔታ በዚህ ልክ ፍሬን ከለቀቀ በኑሮ የተቀነበበው ዳዒ ኹሉ አንድ ከአንድ እንደ ጉም እየበነነ መጥፋቱ ቅርብ ነው፡፡ ያኔ ለምን ብለኽ የጠየቅኽ እንደኾነ የበለጠ ኃጢኣትኽ እንዳይከብድ ፍራ!!! አራት ነጥብ፡፡
https://t.me/E_M_ahmoud

We recommend to visit

Books only!

This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !

Join and share @Books_worldd

አስተያየት @BooksWorlddd_bot !

@books_worlddd መወያያ ግሩፕ

#share

➡️ በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች
➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

Last updated 5 months, 4 weeks ago

?"እውቀት የነብያት ውርስ ነው። ኡለሞች ደግሞ የነብያት ወራሾች ናቸው። እውቀትን እና የእውቀትን ባለቤቶች መውደድ የነብያትን ውርስ እና ወራሾችን መውደድ ነው።
?በደረጃ የሚለቀቁ
1:-ነህው
2:-ሶርፍ
3:-ተጅዊድ
4:-ተፍሲር
5:-ፍቅህ
6:-አቂዳ
7:-መንሀጅ
8:-ሀዲስ
9:-ሲራ
10:-ሙስጦለህ
11:-ቀዋኢደል ፍቅህ
12:-ኡስሉል ፊቅ
13:-አህላቅ ወል አዳብ
14፡-ስለሴቶቻችን
15:-ንፅፅር

Last updated 2 months, 3 weeks ago