የተዘጋ ልብ 🫀🖤

Description
የተነገረኝ ሰአት ቀጥታ ቤት እሄዳለው. እናቴ ስር ቁጭ ብዬ…ስለልጅነቷ እየነገረችኝ …ሞቴን እጠብቀዋለው

Cross @Asherhabeshaw
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

10 months, 2 weeks ago

ጥልቅ በሆነ ባህር ውስጥ አንድ የእንባ
ዘለላ ጠብ አደርጋለው ያንን የእንባ ዘለላ
ባገኘሽ ቅፅበት አንቺን ማፍቀሬን አቆማለው ባመንኩሽ ልክ ጎድተሽኛል
ግን ለምን ??

1 year, 4 months ago

የደበራት ትመስላለች…በቃ የህይወት መንገድ የጠፋባትና ሁሉም ነገር ያስጠላት…በእርግጥ እኔ ስለሷ ብዙ ነገር አላውቅም…ይመስለኛል ግን አንዳንዴ ስንሰጥ…ለእኛም አስቀርተን መሆን አለበት…ምክንያቱም በቃ ያለንን ሁሉ ከሰጠን… እኛም እናጣለን…ካጣን ደግሞ ብዙ ነገር ጥሩ አይሆንም…………………

ከጎኔ ቁጭ ብላ…በግራ እጇ የያዘችውን ስልክ በእርጋታ እያሽከረከረችው…ትዚ ይልህ ከሆነ …የሆነ ቀን ሁላችንም የምንኖረው የተፃፈልንን ነው ብለከኝ ነበር…እንዴ አዎና አልኳት ገርማኝ እያየዋት…ታዲያ ፈጣሪ ግን ምን አድርጌው ነው …ይሄን ለኔ የፃፈልኝ…እያማረርኩ ደሞ እንዳይመስልህ…ለበጎ ነውም ብለህ እንዳታፅናናኝ…አሁን ላይ የምሬን ነው የምልህ የእውነት ነው የደከመኝ…ማረፍ እፈልጋለው……

ማረፍ ሁለት ነው ትርጉሙ…አለ አይደል እረጅም እረፍት…በቃ እፎይ ማለት ናፍቆኛል…ባይገርምን ግን እብዱ እንዳንተ ብሆን እላለው…ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ብዬ ባስብና ነገን ብናፍቅ ምኞቴ ነበር…ብቻ የልቧን መሻት ፈጣሪ ይሙላላት…የኔ ተራ የቃላት ድርደራ ከገባችበት ድብርት እንደማያወጣት አውቃለው❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?

1 year, 5 months ago

አንዳንዴ ብዙ ነገሮችን አስባለው…መቀየር የማልችላቸውና ላስባቸው ማልፈልጋቸውን ብዙ ነገሮች…አለ አይደል ያው በህይወት መንገድ ላይ …ብዙ አዲስ ነገሮች ቢኖሩም አዲስ የማይሆኑም ብዙ ነገሮች አሉ …ሁሌም እንደ ነበሩ የሚቀጥሉና የማያስታውቁ ……

ግን ደግሞ በቃ እኔም የራሴን ህይወት መኖር አለብኝ …ለፍታ ያሳደገቺኝን እናቴን አለሁልሽ ልላት ይገባል…ለካስ በፊት አንቺን እያልኩኝ ብዙ ነገሮችን አጥቻለው…ራሴንና የብዙ ሰዎችን ደስታ ሸፍኛለው…በእርግጥ ጥፋቱ የኔ ነው …የኔ ብቻ…ያው እኔም ደደብ አይደለው ካለፈ በኋላ ነው የገባኝ…………

ግን አደራ እኔ የለውምና የሚወድሽ ሰው የለም ማለት አይደለም…ሁላችንም ብዙም ባይሆን የሚወደን ሰው አለን…አንቺን ደግሞ የሚወድሽ አይጠፋም ፈልጊ❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️

1 year, 5 months ago

በመንገዴ ብዙ ጥሩ ሰዎች አጋጥመውኝ ያውቃሉ… ሰላሜና ደስታዬ የሚያሳስባቸው …ጎንበስ ስል ቀና የሚያደርጉኝ ብዙ ሰዎችን አውቃለው …ግን በቃ የጥሩነትን ጥግ ያሳየቺኝ ያቺ እብድ ጓደኛዬ ናት …እሷ እያጠፋው ልክ ነህ…ሌሎችን እየጎዳሁና እምነት እያጎደልኩኝ ያራቀቺኝ እብድ ሴት …………

በእርግጥ እሷ ከቃላት በላይ ናት…እውነት ነው የሰው ልጅ ያጠፋል ማድረግ የሌለበትን ያደርጋል
ያመነውን ይከዳል ያቀፈውን ይገፈትራል ግን ደግሞ በቃ ሰውም ይለወጣል የሚገባውን ያውቃል ያበላሸውንም ያስተካክላል …ብላ ጥፋቶቼ ከባድ እንዳልሆኑ የምታሳምነኝ እብድ ጓደኛዬ…

ሁሉም ልብ ይለያያል ይሄ እውነት ነው ግን ሁሉም ባይኖር…ጨለማውም ባይነጋ ዝናቡም ባያባራ…ሰላሜም ቢርቅ …የዛኔም ከጎኔ የኔ ውድ ጓደኛ አንቺን አላጣሽም❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️

1 year, 6 months ago

የሚነጋ በማይመስል ጨለማ ውስጥ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ባለበት ሰአት …አብዛኞቻችን አልተኛንም ነበር…ስለ ራሳችንና የእኛ ስለሆኑ ሰዎች ተጨንቀን…ዝም ብለን በጨለማው ተጋርደን ብዙ ነገር እያሰብን ነበር …

በእርግጥ ለአብዛኞቻችን ያሰብነው አልተሳካም…የመጣነው መንገድ ያሳዝናል …አለ ቴዲ እውነቱን ነው…የምር የመጣንበት መንገድ በጣም ያሳዝናል…ለመኖር ብለን ያልኖርንባቸው ቀናቶች ብዙ ናቸው…

ግን እመኑኝ የመጣንበት መንገድ ቢያሳዝንም …የምንሄድበት ግን መልካም ይሆናል የምር እንዳትረሱት የሆነ ቀን ትልቁ ጨለማ …በትንሿ ሻማ የሚበራበት ቀን ይመጣል…

ታያለቹ በመጨረሻም ሁሉም ነገር መልካም ይሆንና …ደስተኞች እንሆናለን …እስከዛ እስካለን አለን…ከሌለንስ ግን…???❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?

1 year, 6 months ago

ይገርመኛል አይነሱም የተባሉት ተነሱ…ተነስተው ቆሙ…አበቃላቸው የተባሉት እንደገና ጀመሩ …አይሳካላቸውም የተባሉት ተሳካላቸው …ክብር ለፈጣሪ ይሁንና ተሸናፊዎችም አሸነፉ…አየሽ እብዷ እማይመጡ የሚመስሉ ነገሮች ይመጣሉ

የኔ እብድ ገብቶሻላ …አንዳንዴ ሙሴን ሆነን ሌሎችን እናሻግራለን…ነገር ግን አሻግረን እኛ አንሄድም ያሻገርናቸው እንጂ…ቢሆንም ግን በቃ እነሱም ሌሎችን አሻግረው ይቀራሉ…ቀርተው ይመለሳሉ…………………

አየሽ እብዷ ህይወት እንደዚህ ናት…እረጅም መንገድ አብሮኝ ይሄዳል ያልሽው ሰው ሸኝቶሽ ብቻ ይመለሳል…ለወር ቢቆይ ነው ብለሽ ያልሽው ሰው ደግሞ…እስከ መጨረሻው አብሮሽ ይሆናል…ብዬሽ የለ በቃ ህይወት እንደዚ ናት…ሁላችንም ከፍም…ዝቅም እያልን ነው ምንኖረው ❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?

1 year, 7 months ago

እኔ ደና ነኝ መሰለኝ…እዚህ እኛ ጋር መታመም የለም…ዝንብሎ መኖር ብቻ ነው…እናንተስ ጋር ምን አዲስ ነገር አለ…ወፎች ውሃ ውስጥ መኖርን ለመዱ…አሳዎችስ ከውሃ ወጡ ወይስ እዛው ናቸው…ሴጣንስ ግን ማሳሳቱን ተወ …ወይስ አሁንም እንደ ደረቀ ነው…ሰካራም ጓደኞቼስ እንዴት ናቹ…ስካሩን ተዋቹት

እሺ ታዲያ ምን አዲስ ነገር አለ…ወይስ ማብራት የለም ውሃ ጠፍቷል…አየር ሞቷል እያላቹ እያማረራቹ ነው…በነገራችን ላይ እዚህ እኛጋ ወንጀለኛ ስለሌለ …እስር ቤት ሚባል ነገር የለም …እናንተጋስ አሁንም ተሯሩጠው መጥተው እያሰሯቹ ነው?…ፊታቹ ላይ ያስታውቃል …ግን ምን ሆናቹ ነው እስካሁን ምን አዲስ ነገር አለ ስል ፀጥ ያላቹኝ?…………

ወይስ አዲስ ነገር ስለሌለ ነው …የምር እዚህ ሰማይ ቤት እኮ ብዙ ነገር ደስ ይላል…ምድር ላይ የኖሩት ሰዎች እንዳለ አሉ…ነገር ግን በቃ እናንተ እንደምታውቋቸው እንደ ድሮው አይደሉም … ማይክል ጃክሰን እንኳን እዚህ አይዘፍንም…ዞሮበት ቁጭ ብሏል…ደጉ አባታችን አብርሃምም ቢሆን እዚህ አይሰጥም …ለራሱም ተቀብሎ ነው ሚኖረው…ብቻ life ከሙታኖች ጋር ማራኪ ነው ስትመጡ ታዩታላቹ❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?❤️?

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад