የሱና ኡስታዞች ትምህርት ብቻ የምላክበት

Description
فاعلم أن العبادة لا تسمى عبادة إلا مع التوحيد، كما أن الصلاة لا تسمى صلاة إلا مع الطهارة. فإذا دخل الشرك في العبادة فسدت، كالحدث إذا دخل في الطهارة. ( القواعد الأربع: ٧)


40 ምንጭ (Arba Minch)

✍️ ابو رسلان حسين بن محمد
Advertising
We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 13 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 5 days, 2 hours ago

BoA Social media links
https://www.facebook.com/BoAeth
https://www.instagram.com/abyssinia_bank
https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 days, 6 hours ago

1 день назад

الأصول الثلاثة
                والقواعد الأربع
  ሶስቱ መሰረቶች እና አራቱ መርሆዎች                                                    ገፅ 24-28
                        للشيخ
    محمد بن عبدالوهاب التميمي          (ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ) ترجمة
محمد أحمد منور ( حفظه الله  تعالى)

✍️ #written_by_አቡረስላን (ابو رسلان)

•• ኢንሻአላህ ይቀጥላል ••

👉 @Twehid12

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

1 день назад

#ክፍል_7

الأصول الثلاثة 

ሶስቱ መሰረቶች

ودليل الخوف: قوله تعالى: {فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ}
(ال عمران:١٧٥)

ودليل الرجاء: قوله تعالى: {فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا} (الكهف: ١١٠)

ودليل التوكل: قوله تعالى:- {وَعَلَى ٱللَّهِ فَتَوَكَّلُوٓا۟ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ} (المائدة: ٢٣). وقوله:- {وَمَن يَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ فَهُوَ حَسْبُهُۥٓ ۚ } (الطلاق: ٣)

የመፍራት ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {አትፍሯቸውም፡፡ ይልቁንም አማኞች ከሆናችሁ እኔን ፍሩኝ፡፡} (ኣሊ ዒምራን፡ 175)

ተስፋ የማድረግ ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {የጌታውንም መገናኘት ተስፋ የሚያደርግ ሰው መልካምን ስራ ይስራ፡፡ በጌታውም አምልኮት አንድንም አያገራ፡፡} (አልከህፍ፡ 110)

የመመካት ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {አማኞችም ከሆናችሁ በአላህ ላይ ተመኩ፡፡} (አልማኢዳህ፡ 23) እንዲህም ብሏል፦ {በአላህ ላይ የሚመካ እሱ በቂው ነው፡፡} (አጥጦላቅ፡ 3)

ودليل الرغبة، والرهبة، والخشوع: قوله تعالى:- {إِنَّهُمْ كَانُوا۟ يُسَٰرِعُونَ فِى ٱلْخَيْرَٰتِ وَيَدْعُونَنَا رَغَبًۭا وَرَهَبًۭا ۖ وَكَانُوا۟ لَنَا خَٰشِعِينَ} (الأنبياء: ٩٠) ودليل الخشية: قوله تعالى:- {فَلَا تَخْشَوْهُمْ وَٱخْشَوْنِى} (البقرة: ١٥٠) ودليل الإنابة: قوله تعالى:- {وَأَنِيبُوٓا۟ إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا۟ لَهُۥَ} (الزمر: ٥٤)

የመከጀል፣ የመፍራት እና የመተናነስ ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦
{እነርሱ (ነብያቱ) በመልካም ስራዎች ላይ የሚቻኮሉ፣ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለኛ ተናናሾችም ነበሩ፡፡} (አልአንቢያእ፡ 90)

የመፍራት ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {አትፍሯቸውም፡፡ ይልቁንም ፍሩኝ፡፡} (አልበቀራህ፡ 150)

የመመለስም ➊➍ ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {ወደ ጌታችሁ (በመፀፀት) ተመለሱ፡፡ ለእርሱም እጅ ስጡ፡፡} (አዝዙመር፡ 54)

ودليل الاستعانة: قوله تعالى:- {إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ} (الفاتحة: ٥) وفي الحديث:- [وإذا استعنت فاستعن بالله]. ودليل الاستعاذة: قوله تعالى:- {قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلْفَلَقِ} (الفلق: ١). و {قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلنَّاسِ} (الناس: ١). ودليل الاسغاثة: قوله تعالى:- {إِذْ تَسْتَغِيثُونَ رَبَّكُمْ فَاسْتَجَابَ لَكُمْ} (الأنفال: ٩)

እገዛን የመሻት ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦
{አንተን ብቻ ነው የምናመልከው፡፡ ባንተ ብቻም ነው የምንታገዘው፡፡} ➊➎ (አልፋቲሐህ፡ 5) በሐዲሥም [መታገዝን በሻህ ጊዜ በአላህ ታገዝ] የሚል ይገኛል፡፡ ➊➏ ጥበቃን የመሻት ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ" በል፡፡} (አልፈለቅ፡ 1) {በሰዎች ፈጣሪ እጠበቃለሁ} በል፡፡ (አንናስ፡ 1) እርዳታን የመሻት ማስረጃው ደግሞ የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {ከጌታችሁ እርዳታን በጠየቃችሁ ጊዜ ለናንተ (ልመናችሁን) የተቀበላችሁን (አስታውሱ)፡፡} (አልአንፋል፡ 9)

ودليل الذبح: قوله تعالى: {قُلْ إِنَّ صَلَاتِى وَنُسُكِى وَمَحْيَاىَ وَمَمَاتِى لِلَّهِ رَبِّ ٱلْعَٰلَمِين
لَا شَرِيكَ لَهُۥ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُسْلِمِينَ َ} (الأنعام: ١٦٢-١٦٣). ومن السنة: [لعن الله من ذبح لغير الله]. ودليل النذر قوله تعالى: {يُوفُونَ بِٱلنَّذْرِ وَيَخَافُونَ يَوْمًۭا كَانَ شَرُّهُۥ مُسْتَطِيرًۭا} (الإنسان: ٧)

የእርድ ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦
{"ስግደቴ፣ የሐጅ ተግባራቴ (እርዴ)፣ መኖሬም መሞቴም ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ነው" በል፡፡ "ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ" (በል)፡፡} (አልአንዓም፡ 162-163) ከሱንናም ➊➐ [ከአላህ ሌላ ያረደን አላህ ረግሞታል] የሚል አለ፡፡ (ሙስሊም፡ 1978) ➊➑

የስለት ማስረጃው የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦
{(ደጋጎች) በስለታቸው ይሞላሉ (ይፈፅማሉ)፡፡ መከራው የሚሰራጭ የሆነን ቀንም ይፈራሉ፡፡} (አልኢንሳን፡ 7) ➊*➒
__

➊➍
       "ኢናባህ" ማ*ለት በሁሉም ነገር ወደ አላህ መመለስ፣ በአምልኮት ትኩረትን ወደሱ ማድረግ፣ ትእዛዙን መፈፀም እና ክልከላዎቹን መራቅ ማለት ነው፡፡

➊➎
         በጣም የሚደንቀው ዘወትር በሶላታቸው ውስጥ {አንተን ብቻ ነው የምናመልከው፡፡ ባንተ ብቻም ነው የምንታገዘው} እያሉ ዱዓእ እያደረጉ ነገር ግን ከሙታን፣ ከጂን፣ ... እርዳታ የሚጠይቁ ሰዎች ሁኔታ ነው፡፡ አላህ ከሺርክ ይጠብቀን፡፡

➊➏
       ሸይኹል አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና "ሶሒሕ" ነው በማለት ለመረጃ ብቁ የሆነ ጠንካራ ሐዲሥ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ (ሚሽካቱል መሷቢሕ፡ 5302)

➊➐
        "ሱንናህ" ማለት ሶስት ነገሮችን የሚያካትት ነው፡፡ እነሱም የነብዩ ሙሐመድ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተግባራቸው፣ ንግግራቸው እና አይተው ወይም ሰምተው ያለ ተቃውሞ ማፅደቃቸው ነው፡፡

➊➑
       በሃገራችን ከጂን፣ ከዛር፣ ... ለመጠበቅ እያሉ የተለያዩ መልክ ያላቸው ዶሮዎችን፣ ፍየሎችን፣ ወይፈኖችን "ሙወከል"፣ "ራሄሎ" ወዘተ እያሉ የሚያርዱ ሰዎች አሉ፡፡ ከላይ ከሰፈሩት ማስረጃዎች በግልፅ እንደምንረዳው ይህን የሚያደርግ ሰው ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቁን ሺርክ የፈፀመ ሲሆን በሐዲሥ እንደተገለፀውም የተረገመ ነው፡፡

➊➒
       ልጅ ወይም ሲሳይ ለማግኘት፣ ከህመም ለመዳን፣ የጠፋ እንስሳት እንዲገኝላቸው ለጂን ወይም ለሙታን የሚሳሉ ሰዎች ድርጊታቸው ትልቁ ሺርክ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ስኬትን ለመጎናፀፍ፣ ከህመም ለመትረፍ፣ የትምህርት ፈተና ለማለፍ ወዘተ በማለም ለፍጡር መሳል የተወገዘ ምግባር ነው፡፡

2 дня назад

#ክፍል_6

الأصول الثلاثة 

ሶስቱ መሰረቶች

وأنواع العبادة التي أمر الله بها مثل: الإسلام، والإيمان، والإحسان، ومنه: الدعاء، والخوف، والرجاء، والتوكل، والرغبة، والرهبة، والخشوع، والخشية، والإنابة، والاستعانة، والاستعاذة، والاستغاثة، والذبح، والنذر، وغير ذلك من أنواع العبادة التي أمر الله بها كلها لله تعالى. والدليل: قوله تعالى: {وَأَنَّ ٱلْمَسَٰجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا۟ مَعَ ٱللَّهِ أَحَدًۭا} (الجن: ١٨)

እነዚያ አላህ በነሱ ያዘዘባቸው የሆኑት የአምልኮት አይነቶች ለምሳሌ ኢስላም፣ ኢማን እና ኢሕሳን ናቸው፡፡ ከዚሁ (ከአምልኮት ምሳሌው) የሚጠቀሱት ፀሎት (ዱዓእ)፣ መፍራት፣ ተስፋ ማድረግ፣ መመካት፣ መከጀል፣ መፍራት፣ መተናነስ፣ መፍራት፣ መመለስ፣ እገዛን መሻት፣ ጥበቃን መሻት፣ እርዳታን መሻት፣ እርድ፣ ስለት፣ ... ከዚህም ሌላ ያሉ እነዚያ አላህ ያዘዘባቸው የአምልኮት አይነቶች ሁላቸውም የላቀው አላህ (ሐቅ) ናቸው፡፡ ➊➊ ማስረጃውም የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {እነሆ መስጂዶችም የአላህ ብቻ ናቸው፡፡ ስለሆነም ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ፡፡} (አልጂንን፡ 18)

فمن صرف منها شيء لغير الله؛ فهو مشرك كافر؛ والدليل قوله تعالى:- {وَمَن يَدْعُ مَعَ ٱللَّهِ إِلَٰهًا ءَاخَرَ لَا بُرْهَٰنَ لَهُۥ بِهِۦ فَإِنَّمَا حِسَابُهُۥ عِندَ رَبِّهِۦٓ ۚ إِنَّهُۥ لَا يُفْلِحُ ٱلْكَٰفِرُونَ}  (المؤمنون: ١١٧) وفي الحديث: [الدعاء مخ العبادة]. والدليل: قوله تعالى: {وَقَالَ رَبُّكُمُ ٱدْعُونِىٓ أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ ٱلَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِى سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ}   (غافر:٦٠)

ከነዚህ ውስጥ ምንም ቢሆን ከአላህ ሌላ ላለ የሰጠ እሱ አጋሪ ነው፣ ከሃዲ!! ማስረጃውም የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦
{#ከአላህም_ጋር በእርሱ ላይ ማስረጃ የሌለው ሲሆን ሌላን አምላክ የሚጣራ ሰው ምርመራው ከጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሃዲዎች አይድኑም፡፡} ➊➋ (አልሙእሚኑን፡ 117)

በሐዲሥም ውስጥ [ዱዓእ የአምልኮት መቅኒው ነው] የሚል አለ፡፡ ➊➌ ማስረጃውም የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦

{ጌታችሁም እንዲህ አለ፡ ለምኑኝ፡፡ እቀበላችኋለሁ፡፡ እነዚያ እኔን ከማምለክ የሚኩራሩት ተዋራጆች ሆነው ጀሀነምን ይገባሉ፡፡} (ጋፊር፡ 60*)
__

➊➊
      "ኸውፍ"፣ "ረ*ህባህ" እና "ኸሽያህ" የሚሉት ዐረብኛ ቃላት ተቀራራቢ ትርጉም ነው ያላቸው፡፡ ስለሆነም ሁሉንም "መፍራት" በሚል ቃል ተክቻቸዋለሁ፡፡ እዚህ ላይ የተፈለገው ታዲያ አምልኮታዊ የሆነው ፍራቻ ነው፡፡ ስለሆነም ሙታንን ወይም ጣኦታትን "የመጥቀምና የመጉዳት ሃይል አላቸው፣ ድብቅ ሚስጥራትን ያውቃሉ" ብሎ መፍራት ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቅ ሺርክ ነው፡፡ ነገር ግን አውሬን፣ ጠላትን እና መሰል አደጋ ያላቸውን ነገሮች መፍራት ይሄ ተፈጥሯዊ ፍራቻ ነው፡፡ የተጋነነ ደረጃ ከደረሰ ግን የተወገዘ ባህሪ ነው፡፡

➊➋
       ይስተዋል! በዚህች አንቀፅ ውስጥ አላህን ይዞ ከዚያም ፍጡርን ጨምሮ መጣራት ሺርክ (ማጋራት) እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ይሄ ብዙ ሰዎች የሚዘነጉት ነገር ነው፡፡ ስለዚህ ከአላህ ጋር ነብይም ይሁን ወልይም፣ ጂንም ይሁን መላእክት ከተጠራ አደገኛው የሺርክ (የማጋራት) ወንጀል ተፈፅሟል፡፡ አጋሪ ደግሞ በአንቀጿ ውስጥ እንደተገለፀው ከሃዲ ነው፡፡

➊➌
       ታላቁ የሐዲሥ ሊቅ ሸይኹል አልባኒ አላህ ይዘንላቸውና ይሄ ሐዲሥ በዚህ ቃል ዶዒፍ ማለትም ደካማ እንደሆነ ብይን ሰጥተዋል፡፡ (ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3003) ይሁን እንጂ ይህንን ሐዲሥ የሚተካ [ዱዓእ እራሱ ዒባዳህ ነው] የሚል ሶሒሕ ሐዲሥ አለ፡፡ (ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3407)

ሐዲሥ ሶስት ደረጃዎች አሉት፡፡ እነሱም በቅደም-ተከተል፦ "ሶሒሕ" (ትክክለኛ)፣ ሐሰን (መልካም) እና "ዶዒፍ" (ደካማ) ናቸው፡፡ "ሶሒሕ" እና "ሐሰን" የሆኑ ሐዲሦች ለመረጃነት ብቁ ሲሆኑ "ዶዒፍ" የሆነው ግን መረጃ ሆኖ የመቅረብ አቅም የለው፡፡

الأصول الثلاثة
                والقواعد الأربع
  ሶስቱ መሰረቶች እና አራቱ መርሆዎች                                                    ገፅ 21-23
                        للشيخ
    محمد بن عبدالوهاب التميمي          (ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻌﺎﻟﻰ)     
                      ترجمة
محمد أحمد منور ( حفظه الله  تعالى)
✍️#written_by_አቡ_ረስላን  (ابو رسلان)

•• ኢንሻአላህ ይቀጥላል ••

👉 @Twehid12

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

1 неделя назад

#ክፍል_2

                   الأصول الثلاثة

ሶስቱ መሰረቶች

قال الشافعي رحمه الله تعالى: "لو ما أنزل الله حجة على خلقه إلا هذه اسورة لكفتهم". وقال البخاري__ رحمه الله تعالي:- "باب: اعلم قبل القول والعمل؛ والدليل قوله تعالى: {فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ} (محمد:١٩)، فبدأ بالعلم"، قبل القول والعمل.

(ኢማሙ) ሻፊዒይ ➌ የላቀው አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፦ "አላህ በፍጡሩ ላይ ከዚች ምእራፍ ውጭ ሌላ ባያወርድ ኖሮ በርግጥም ትበቃቸው ነበር፡፡" (አልኢስቲቃማህ፡ 482) ➍ (ኢማሙ) አልቡኻሪ ➎ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፦ "ርእስ፡ እውቀት ከንግግርም ከተግባርም ይቀድማል፡፡ ማስረጃውም የላቀው (ጌታ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ {እነሆ ከአላህም በስተቀር እውነተኛ አምላክ እንደሌለ  እወቅ፡፡ ለወንጀልህም ምህረትን ጠይቅ፡፡} (ሙሐመድ፡ 19) (አስቀድሞ) በእውቀት ጀመረ፡፡" (ሶሒሑል ቡኻሪ፡ 1/24-25) ከንግግርም ከተግባርም በፊት (ማለት ነው)፡፡
__

    ኢማሙ አሽሻፊዒይ ስማቸው ሙ
ሐመድ ኢብኑ ኢድሪስ ይባላል፡፡ በ 150 ዓመተ ሂጅራ ዛሬ የፍልስጤም ግዛት በሆነችው ጋዛ ውስጥ የተወለዱ ሲሆን የሞቱት ደግሞ በ 204 ዓመተ ሂጅራ ግብፅ ውስጥ ነው፡፡ አሽሻፊዒይ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘር ሲሆኑ የሁለተኛው የሂጅሪያ ክፍለ ዘመን የተሀድሶ አራማጅ ናቸው፡፡ ከአራቱ የፊቅህ መዝሀቦች ውስጥ አንዱ የሆነው የሻፊዒያ መዝሀብ ወደሳቸው የሚጠጋ ነው፡፡ የኢማሙ ማሊክ ኢብኑ አነስ ተማሪ ሲሆኑ የኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ደግሞ ሸይኽ ናቸው፡፡


    ስለዚህ ሰዎች ባጠቃላይ አትራፊና ከሳሪ ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ ማለት ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ተገልጿል፡፡ ለተገለፁት አራት ነገሮች በሚኖራቸው አያያዝ ሰዎች የሚኖራቸው ትርፍና ኪሳራ ይለያያል ማለት ነው፡፡ የዚህችን አጭር ግና ታላቅ ምዕራፍ የላቀ ዋጋ ለመረዳት ይህን የሸይኹል አልባኒ ድንቅ ምክር እንመልከት፦

#ጠያቂ፦ አንድን ሰው ለአላህ ብሎ የወደደ ሰው "ለአላህ ብየ እወድሃለሁ" ብሎ ማሳወቅ አለበትን?

#ሸይኹል_አልባኒ፦ አዎ፡፡ ግን ለአላህ ብሎ መውደድ ዋጋው ከባድ በመሆኑ የሚከፍለው ጥቂት ነው፡፡ ለአላህ ብሎ የመውደድ ዋጋ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? እስኪ ማነው የሚያውቅ መልሱን የሚሰጠን?

#አንዱ_አድማጭ፦ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ [ሰባት አይነት ሰዎች አላህ ከሱ ጥላ ውጪ ጥላ በሌለበት (በቂያማ) ቀን ከጥላው ስር ያስጠልላቸዋል፡፡] ከነዚህም ውስጥ [ለአላህ ብለው ተዋደው በዚያም ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ ናቸው፡፡]

#ሸይኹል_አልባኒ፦ እሱ በራሱ ትክክለኛ ንግግር ነው፡፡ ግን የጥያቄው መልስ አይደለም፡፡ አንተ የጠቀስከው ነገር ሙሉ ለሙሉ ሳይሆን ቀረብ ባለ መልኩ ለአላህ ብሎ መውደድ ምን እንደሆነ የሚገልፅ ነው፡፡ የኔ ጥያቄ ግን "ሁለት ለአላህ ብለው የተዋደዱ ሰዎች አንዱ ለሌላው ሊከፍለው የሚገባው ዋጋ ምንድን ነው?" የሚል ነው፡፡ እንጂ የአኺራ ሽልማቱን (አጅሩን) ማለቴ አይደለም፡፡ ስለዚህ ማለት የፈለግኩት ሁለት ሰዎች እውነት መዋደዳቸው ለአላህ እንደሆነ በተግባር የሚያመላክተው ምንድን ነው የሚል ነው፡፡ ሁለት ሰዎች ሊዋደዱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ውዴታቸው እውነተኛ ያልሆነ እንዲሁ ቅርፃዊ ሊሆን ይችላል፡፡ እውነተኛ እንደሆነ የሚያመላክተው ምንድነው?

#አንዱ_አድማጭ፦ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ መውደዱ፡፡

#ሸይኹል_አልባኒ፦ ይሄ የመውደድ ነፀብራቅ ነው ወይም ከመውደድ ነፀብራቆች አንዱ ነው፡፡

#አንዱ_አድማጭ፦ የላቀው ጌታችን እንዲህ ብሏል፡ {"አላህን የምትወዱ ከሆናችሁ መልእክተኛውን ተከተሉ፡፡ አላህ ይወዳችኋልና" በላቸው፡፡}

#ሸይኹል_አልባኒ፦ ይሄ ትክክለኛ መልስ ነው- ግን ለዚህ ሳይሆን ለሌላ ጥያቄ!

#አንዱ_አድማጭ፦ ምናልባት መልሱ በዚህ ሶሒሕ ሐዲስ ውስጥ ሊሆን ይችላል፡ [ሶስት ነገሮች በውስጡ ያሉበት የኢማን ጥፍጥና አግኝቷል...] ከነዚህ ውስጥ [ለአላህ ብለው የተዋደዱ ናቸው፡፡]

#ሸይኹል_አልባኒ፦ ይሄ ለአላህ ብሎ መውደድ የሚያስከትለው ውጤት ነው- በልቡ የሚያገኘው ጥፍጥና!

#አንዱ_አድማጭ፦ የላቀው ጌታችን እንዲህ ብሏል፡ {በዘመን እምላለሁ! በእርግጥ ሰው ሁሉ በክስረት ውስጥ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት፤ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡}

#ሸይኹል_አልባኒ፦ በጣም ጥሩ ብለሃል! ይህ ነው ትክክለኛው መልስ!! ይህም ሲብራራ እኔ አንተን እውነት ለአላህ ብየ የምወድህ ከሆነ በምክር ልከተልህ ይገባል፡፡ አንተም እንደዚያው፡፡ ለዚህም ነው "ለአላህ ብለን እንዋደዳለን" በሚሉ ሰዎች ዘንድ ይሄ አንዱ ሌላውን በምክር መከተል በጣም ውስን የሆነው፡፡ ምናልባት መዋደዳቸው ከፊል እውነት ሊኖረው ይችላል፡፡ ግን ሙሉእ አይደለም፡፡ ለምን ቢባል አንዳቸው የሌላውን ስሜት ይጠብቃልና፡፡ "እውነቱን ስነግረው ቢቆጣስ፣ ቢሸሽስ፣... ወዘተ" እያለ ሐቅን ሳያስተላልፍ ይቀራል፡፡ ስለዚህ ለአላህ ብሎ መውደድ ዋጋው አንዳችን ለሌላው በምክር ኢኽላስ ሊኖረው ነው- እውነተኛ መካሪ ሊሆን፡፡ ሁሌም በመልካም ሊያዘው ከመጥፎም ሊከለክለው ይገባል፡፡ ወዳጅ ለሚወደው ከጥላው የበለጠ በምክር የሚከተለው ሊሆን ይገባል ማለት ነው፡፡ ሶሐቦች ተገናኝተው ሲለያዩ አንዱ ለሌላው ይችን ምእራፍ ይቀሩ እንደነበር የሚያመላክተው ሶሒሕ ማስረጃ ለዚህ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡ (አልሓዊ ሚን ፈተወል አልባኒ፡ 165-166)


    አልኢማም አልቡኻሪ ስማቸው ሙሐመድ ኢብኑ ኢስማዒል ነው፡፡ የተወለዱት በ194 ዓመተ ሂጅራ ቡኻራ ውስጥ ነው፡፡ ቡኻራ የዛሬዋ ኡዝቤኪስታን ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡ የቲም ሆነው ከእናታቸው ጋር ነው ያደጉት፡፡ የሞቱት ደግሞ በ 256 ዓመተ-ሂጅራ ሰመርቀንድ አካባቢ ነው፡፡ ሰመርቀንድም ኡዝቤኪስታን ውስጥ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ በኢማም አልቡኻሪ የተሰበሰበው ሶሒሕ አልቡኻሪ በትክክለኛነቱ ከቁርኣንና ከሐዲስ በመቀጠል ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዝ ድንቅ ጥንቅር ነው፡፡

الأصول الثلاثة
                والقواعد الأربع
  ሶስቱ መሰረቶች እና አራቱ መርሆዎች                                                    ገፅ 9-11
                        للشيخ
    محمد بن عبدالوهاب التميمي          (رحمه الله)     
                      ترجمة
محمد أحمد منور ( حفظه الله  تعالى)
✍️#written_by_አቡ_ረስላን (ابو رسلان)

•• ኢንሻአላህ ይቀጥላል ••

👉 @Twehid12

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

1 неделя, 1 день назад

#ክፍል_1
                   الأصول الثلاثة

ሶስቱ መሰረቶች

                     ሸይኽ
   ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲልወህሃብ
                ረሒመሁላህ
          (1115-1206 ዓ.ሂ.)

            بسم الله الرحمن الرحيم

እጅግ በጣም ርህሩህና አዛኝ በሆነው አላህ ስም
*______

اعلم رحمك الله أنه يجب علينا تعلم أربع مسائل.
المسألة الأولى: العلم: وهو معرفة الله، ومعرفة نبيه
صلى الله عليه وسلم*، ومعرفة دين الإسلام بلأدلة.
المسألة الثانية: اعمل به.
المسألة الثالثة: الدعوة إليه.
المسألة الرابعة: الصبر على الأذى فيه.

[#አራት_አንኳር_ነጥቦችን_ማወቅ]

እወቅ! አላህ ይዘንልህና፡፡ አራት አንኳር ነጥቦችን ማወቅ በኛ ላይ ግዴታ ነው፡፡
(እነሱም)፦
#የመጀመሪያው_አንኳር_ነጥብ፦ እውቀት ነው፡፡ እሱም አላህን ማወቅ፣ ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ማወቅ እና የኢስላም ሃይማኖትን በማስረጃዎቹ ማወቅ ነው፡፡ ➊

#ሁለተኛው_አንኳር_ነጥብ፦ በሱ (ባወቁት)  መስራት ነው፡፡

#ሶስተኛው_አንኳር_ነጥብ፦ ወደ እሱ መጣራት ነው፡፡

#አራተኛው_አንኳር_ነጥብ፦ በሱ (በደዕዋ) ሳቢያ በሚያጋጥሙ አስቸጋሪ ነገሮች ላይ መታገስ ነው፡፡

والدليل قوله تعالى: بسم الله الرحمن الرحيم { وَٱلْعَصْر ۞ِ
إِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ لَفِى خُسْر ۞ۖ
إِلَّا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّٰلِحَٰتِ وَتَوَاصَوْا۟ بِٱلْحَقِّ وَتَوَاصَوْا۟ بِٱلصَّبْر}ِ
ٍ
(ለነዚህ አራት ነጥቦች) ማስረጃው የላቀው (አላህ) እንዲህ ማለቱ ነው፦ እጅግ በጣም ርህሩህና አዛኝ በሆነው አላህ ስም፡፡ {በዘመን እምላለሁ! በእርግጥ ሰው ሁሉ በክስረት ውስጥ ነው፡፡ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት፤ በእውነትም አደራ የተባባሉት፣ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ፡፡} (አልዐስር፡ 1-3) ➋
______

    እነዚህ ሶስት ጉዳዮ
ች እያንዳንዱ ሰው ሲሞት በቀብር ውስጥ የሚጠየቃቸው ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ፈተናውን ለማለፍ ከቃል ማነብነብ ባለፈ እምነትን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ጥቅል በሆነ መልኩ ነው የቀረቡት፡፡ ወደፊት ዘርዘር ባለ መልኩ ይመጣሉ፡፡


    በዚች ምዕራፍ ውስጥ አራቱም ነጥቦች ተወስተዋል፡፡
1. {እነዚያ ያመኑት ሲቀሩ} በሚለው ውስጥ እውቀት አለ፡፡ ማመን ማወቅን ይጠይቃልና፡፡
2. {መልካሞችን የሰሩት ሲቀሩ} በሚለው ውስጥ ባወቁት መስራት አለ፡፡
3. {በእውነትም አደራ የተባባሉት ሲቀሩ} በሚለው ውስጥ ወዳወቁት መጣራት አለ፡፡
4. {በመታገስም አደራ የተባባሉት ሲቀሩ} በሚለው ውስጥ በደዕዋ ሂደት ላይ በሚያጋጥሙ ፈተናዎች ላይ መታገስ አለ፡፡

በደዕዋ ላይ የሚሰማራ ሰው እነዚህን አራት ነጥቦች በውል ሊረዳና በተግባር ሊያስገኝ ይገባዋል፡፡

الأصول الثلاثة
                والقواعد الأربع
  ሶስቱ መሰረቶች እና አራቱ መርሆዎች                                                    ገፅ 6-9
                        للشيخ
    محمد بن عبدالوهاب التميمي          (رحمه الله)     
                      ترجمة
محمد أحمد منور ( حفظه الله  تعالى)
✍️ #written_by_አቡ_ረስላን (ابو رسلان)
      •• ኢንሻአላህ ይቀጥላል ••

👉 @Twehid12

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

1 неделя, 1 день назад

ችላ ካልናቸው ርእሶች ውስጥ
~
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"የሲራ ኪታቦችን ማንበብ ልብ ላይ አስደማሚ ተፅእኖ አለው። ምክንያቱም ሰው ይገሰፅባቸዋልና። ልክ ከሶሓቦች ጋር እንዳለ ይሰማዋል። ይህም ልቡን ያለሰልስለታል።"
[ኑሩን ዐለ ደርብ፡ 12/19]
.
ዛሬ ላይ ታሪክን ማስተማር የሌሎች ቡድኖች መታወቂያ አድርገው የሚያስቡ አንዳንድ ሰዎች አሉ። መሰረታዊ ትምህርቶችን መግፋት ወይም ሳያጣሩ አሰስ ገሰሱን ሁሉ መጓፈፍ እንጂ የሚነቀፈው የነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፣ የቀደምት ነቢያት፣ የሶሐቦች እና የሌሎችም ደጋጎችን ታሪክ መማርና ማንበብ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ ከጠቀሱትም ያለፉ ብዙ ፋይዳዎች አሉት። ቁርኣን ውስጥኮ እጅግ ብዙ አይነት ታሪኮች ይገኛሉ። ነብዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ብዙ የቀደምት ህዝቦችን ታሪክ አውስተዋል። ከጥንት እስከ ዛሬ በርካታ ታላላቆች ለቁጥር የሚያታክቱ የታሪክ ድርሳናትን የፃፉት ያለ ምክንያት አይደለም።
ደግሞም ታሪክ ውስጥ ዘርፈ ብዙ የእውቀት አይነቶች አሉኮ። የተውሒድ፣ የፊቅህ፣ የሱሉክ፣ የአስተዳደር፣ ወዘተ.። በዚያ ላይ ሰዎች በአብዛኛው ለታሪክ ጉጉትና ተዘንባይነት አላቸው። በዚህ የተነሳ በሲራ እየተዋዛ የሚሰጥ ትምህርት ከሌላው በተለየ ሰዎችን የመያዝ አቅም አለው። ስለሆነም ለሲራ ትምህርት ትኩረት ልንሰጥ ይገባል ለማለት ነው።

©IbnuMunewor

👉 @Twehid12

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

1 неделя, 5 дней назад

እምቢ በይ እታለም!
(ከካፊር ጋር ትዳር ለሚያስቡ እህቶች)
ለአላፊ ደስታ ስትይ ………. ለምትከስመው ጠውልጋ
ትዳር ከምትመሰርቺ ………. ኢስቲንጃ ከሌለው ጋ
ለዚች ጤዛ ዱንያ ብለሽ ………. ብልጭ ብላ ለምትጠፋ
ከለጋሱ ጌታ ዘንዳ ………. ከትንኝ ክንፍ ለማትሰፋ
እያለቀስን መጥተን ሳለ ………. እያለቀስን ለምንለቃት
አኺራችንን አስበን ………. ምናለ ብንንቃት?!!
እቱ ከጌታችን ጋራ ………. ነገ ከባድ ሂሳብ አለ
አስፈሪ ጭንቅ የሚያይበት ………. መናጢ ሁሉ ያልታደለ
ዛሬን ከመስመር ለቆ ………. ወደ ጥፋት ያጋደለ
ከእርኩሳን ጋር ተጣምሮ ………. በክህደት ላይ የዋለለ
ነገን በዛሬ የሸመተ ………. የዋህ እራሱን ያታለለ
“ያ ለይተኒ” የሚልበት ………. ነገ የቁጭት ቀን አለ፡፡
ይልቅ ስሚኝ እህት አለም፡
ትዳር የጌታ ሲሳይ ነው ………. ከባለ ዐርሹ የሚወሰን
ስለቋመጥን ሳይሆን ………. ፈቃዱ ሲኖር የሚደርሰን
“ይታደሉታል እንጂ ………. አይታገሉትም” ነው ነገሩ
ውሳኔው ከላይ እስከሚወርድ ………. ከዱዓህ ጋር ይሶብሩ፡፡
እንጂ ከእንጨት አምላኪ ጋ
እንጂ “አንድም ሶስትም” ከሚል ዜጋ
በስሜት ናላው ዞሮ ………. ሊያጠምድሽ መረብ ቢዘረጋ
ማር በሚተፋ ምላሱ ………. በስልት ወዳንቺ ቢጠጋ
ምናባዊ ሐሴት አይተሽ ………. ጉም ለመጨበጥ መንጠራራት
ለተስፋ ዳቦ እየቋመጥሽ ………. አትሁኚ የ’ሳት እራት፡፡
በምታይው ብልጭልጭ ………. እራስሽን አትደልይ
ባለ ገዳይ መርዙ እባብም ………. ለስላሳ ነው አስተውይ፡፡
ይልቁንም ረጋ ብለሽ ………. ከአፅናፍ ማዶ ተመልከቺ
ጤፍ በሚቆላ ምላሱ ………. ለተኩላ አትረቺ
ለዚች አጭር ህይወት ስትይ ………. በራስሽ ላይ አትሸፍቺ፡፡
ለዚህ ብላሽ ፈራሽ ገላ
ለዚህ ከንቱ ገልቱ አተላ
ዛሬ እጅሺን አትዘርጊ
ነገ እንዳትጠወልጊ፡፡
ሶላት ቁርኣኑ ተትቶ
ሒጃብ አደቡ ተዘንግቶ
በላኢላሀ ኢለላህ ቦታ ………. “አንድም ሶስትም” ተተክቶ
ግንባር ለመስቀል ሲዋረድ ………. የሐያሉ ሱጁድ ቀርቶ
ከቤትሽ ግድግዳ ላይ ………. የፈረንጅ ስእል ተለጥፎ
ሐያእ ግብረ-ገብነትሽ ………. ከላይሽ ላይ ተገፎ
ከግንባርሽ ላይ ነጥፎ ………. ከልብሽ ላይ ተንጠፍጥፎ
መስጂድ የለመዱ እግሮችሽ ………. ወደ ከኒሳ ሲያመሩ
ጠላ ኮረፌ እየጠመቅሽ ………. ሰካራሞች ሲያጓሩ
ይሄ እውን የሆነ እለት
ያኔ ሆነሻል የቁም ሙት!!
.
.
.
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 21/2008)

👉 @Twehid12

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

1 неделя, 5 дней назад

💵 ነጋዴው ሆይ ጠንቀቅ በል!💵

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

“ነጋዴዎች አመፀኞች ናቸው
ሶሐቦች፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ “አላህ ንግድን ፈቅዶ የለ እንዴ?" ሲሉ ጠየቁ።

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ መለሱ፡-
“እንዴታ! ግን እነሱ
👉 ያወራሉ፡፡ ሲያወሩ ይዋሻሉ
👉 ይምላሉ፡፡ ሲምሉ ይወነጅላሉ"

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
ሸይኹል አልባኒ “ሶሒሕ” ብለውታል፡፡ (አስሶሒሓህ፡ 1/366)

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

👉 @Twehid12

1 неделя, 6 дней назад

🍀የምሽት ስንቅ🍀

📖 ከፊል አካልን ፀሀይ ላይ ከፊሉን ደግሞ ጥላ ላይ ማድረግ ክልክል ነው!!

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡ አንድ ሰው በፀሀይ ብርሃንና በጥላ ላይ መቀመጥን ከልክለዋል፡፡ “የሸይጧን አቀማመጥ ነው!” ሲሉም ገልፀውታል፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 3081]
ታላቁ ዓሊም አሽሸይኽ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ይላሉ፡-
“ይህም ማለት አንድ ሰው እንዲህ አይነቱን አቀማመጥ ከጅምሩም ይሁን አጋጥሞት ሊቀመጥ አይገባም፣ አይበጅምም፡፡ ከጅምሩም ስንል ሆን ብሎ በፀሀይና ጥላ ላይ መቀመጡን ለማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሊሆን የሚገባው ወይ ሙሉ ለሙሉ ፀሀይ ላይ ወይም ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ጥላ ላይ መሆን ነው፡፡ ምክንያቱም ሰውነት በአንድ ሁኔታ ላይ ማለትም ወይ ሙቀት ላይ ወይ ደግሞ ቅዝቃዜ ላይ ሲሆን ሚዛኑን የጠበቀ ይሆናል፡፡ ከፊሉ ጥላ ላይ ከፊሉ ፀሐይ ላይ ሲሆን ግን ከፊሉ ተፅእኖ ያርፍበትና ብርድ ያገኘዋል፡፡ ከፊሉ ደግሞ ሙቀት ያገኘዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ጎጂ ነው፡፡ …” [ሸርሑ ሱነን አቢ ዳውድ፡ 27/478]

👉 @IbnTaymiyyahrahimahullah

👉 @Twehid12

4 недели назад

?የንጋት ቅምሻ?

? ዑመሩል ፋሩቅ ሸይጧን የሚሸሸው ሶሐብይ!

ሶሐባው ሰዕድ ኢብን አቢል ወቃስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡፡በአንድ ወቅት ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ከነቢዩ (ዐለይሂሰላም) ቤት ሊገባ ፍቃድ ጠየቀ፡፡ ከነቢዩ
(ዐለይሂሰላም) ዘንድ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚያወሩ ሴቶች ነበሩ፡፡ የዑመርን ድምፅ ሲሰሙ ሒጃባቸውን አስተካክለው ሊለብሱ ተሯሯጡ፡፡ ረሱል (ዐለይሂሰላም) እየሳቁ ለዑመር እንዲገባ ፈቀዱለት፡፡ ዑመርም “አላህ ጥርስህን ያስቀው የአላህ መልእክተኛ ሆይ!” አላቸው፡፡
ነብዩም (ዐለይሂሰላም) “እነዚህ እኔ ጋር የነበሩ ሴቶች ገረሙኝ፡፡ ድምፅህን ሲሰሙኮ ወደ ሒጃባቸው ተሯሯጡ” አሉት፡፡ ዑመርም “አንተ ነህ ልትከበርና ልትፈራ የሚገባህ ያረሱለላህ” ካለ በኋላ “እናንተ የነፍሶቻችሁ ጠላቶች እኔን ትፈራላችሁ የአላህ መልእክተኛን አትፈሩምና?!” ሲላቸው “አዎ ከረሱል (ዐለይሂሰላም) ይልቅ አንተ ደረቅና አስፈሪ ነህ” አሉት፡፡ ከዚያም ረሱል (ዐለይሂሰላም) እንዲህ አሉ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ ይሁንብኝ ሸይጧን በአንድ መንገድ ላይ በጭራሽ አያገኝህም መንገድ ቀይሮ በሌላ መንገድ ቢሄድ
እንጂ” ቆይማ እዚች ጋ አንድ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ ሺዐዎች የዑመር ስም
ሲነሳ በጥላቻ እብደታቸው እንደሚነሳ ይታወቃል፡፡ ዛሬ ድረስ
ይሄ ነገር በግልፅ የሚታይ ነው፡፡ እ.ኢ.አ በ2005 ኢራቅ ውስጥ 15 ሰዎች ስማቸው ዑመር ስለሆነ ብቻ በሺዐዎች ተገድለዋል፡፡ በቅርቡም ኢራን ውስጥ በርካታ ዑመሮች በሌላ ሳይሆን በስማቸው ብቻ ከስራ ተባረዋል፡፡ ዑመርን ምን ያህል ቢጠሉት ነው በስም ብቻ እንዲህ የሚደረገው?
ሌላ ነገር፡፡ መዲና ውስጥ የሚገኘው የነብዩ (ዐለይሂሰላም)
መስጂድ ካሉት በሮች ውስጥ አንዱ “የዑመር በር” ነው፡፡ ታዲያ ሺዐዎች ምን አሉ “ለዑመር ካለን ጥላቻ የተነሳ ወደ መስጂዱ ስንገባ በዑመር በር በኩል አንገባም” አሉ፡፡ አንዱ ዐሊም ምን አላቸው “ረዲየላሁ ዐንከ ያ ዑመር! ሸይጧን በህይወትህ ሳለህ ብቻ አይለም ሞተህም ይሸሸሃል!!!”

አላሁአክበር!!!

©Ibnu Munewor

? @Twehid12

? @IbnTaymiyyahrahimahullah

We recommend to visit

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 13 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 5 days, 2 hours ago

BoA Social media links
https://www.facebook.com/BoAeth
https://www.instagram.com/abyssinia_bank
https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 2 days, 6 hours ago