A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 2 months, 2 weeks ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 1 month ago
"#የተቀመጠው_ስታንዳርድ_አሁን_ያሉብንን_የጥራት_ችግሮች_ይፈታል_ብለን_እናምናለን"
ዶ/ር ዱንካና ኑጉሳ -የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር
ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በሀገር ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ #ETV
SHEGER FM 102.1 RADIO
ጥር 18፣2017
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጡት ትምህርት ጥራት የሚፈተሽበት፤ ‘’የጥራት ኦዲት መመሪያ’’ እየተዘጋጀ ነው ተባለ።
በኢትዮጵያ እስከ ዛሬ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የትምህርት ጥራትን የሚፈትሽበት የኦዲት ስርዓትና መመሪያ አስገዳጅ ባለመሆኑ፤ የትኛው የትምህርት ተቋም፣ የትምህርት ጥራቱ ምን መሳይ ነው የሚለው ለማወቅ አስቸጋሪ ሆኖ መቆየቱ ተነግሯል።
ይህንን ችግር ያቃልላል፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት አሰጣጥ ጥራትን ለመፈተሽም ይረዳል የተባለ መመሪያ ሊወጣ መሆኑ ሰምተናል።
መመሪያው የመንግስትን ጨምሮ ሁሉም የግል ከፍተኛ የትምህርት እና የቴክኒክና ሞያ ተቋማትን ይመለከታል ተብሏል።
የትምህርት ተቋማቱ በየ 5 ዓመቱ ጥራት ላይ ኦዲት እንዲደረጉ በመመሪያው ሰፍሯል።
አንድ የትምህር ተቋም ጥራቱ ኦዲት ከተደረገ በኋላ ከአንድ እስከ ሶስት ባለት ደረጃዎች በአንዱ ይመደባል ተብሏል።
ይህ የተባለው ዛሬ የከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሞያ ስልጠና የጥራት ኦዲት መመሪያ እና ደረጃዎች ላይ በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ነው።
የትምህርት ተቋማት ጥራትን በተመለከተ ''ግለ ግምገማ'' ሊያከናውኑ ይገባል የተባለ ሲሆን እየተዘጋጀ ባለው መመሪያ መሰረት ግን ጥራታቸው የሚፈተሸው በትምህርትና ስልጠና በሚመደብ የጥራት ኦዲተሮች ነው ተብሏል።
በሀገሪቱ የትምህርት ዘርፍ የተለያዩ ለውጦች እየተደረጉ መሆኑ አንስተው ይህም የጥራት ኦዲት ልኬትም ከሚደረጉ ሪፎርሞች መካከል አንዱ ነው ሲሉ የነገሩን፤ በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሽኔ ናቸው።
አሁን ባለው አሰራር የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ጥራት በተመለከተ የሚያስገድድ መመሪያ ባለመኖሩ በተገቢው እንደማይፈተሹ ተነስቷል።
ይህ ''የጥራት ኦዲት መመሪያ'' ወጥቶ ተግባራዊ ሲሆን ግን የተቋማቱን የትምህርት ጥራት ተፈትሾ ደረጃ ለመስጠት እንደሚያግዝ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የቴክኒክና ሞያ ጥራት ዴስክ ሀላፊ ጎበዜ ይመር ተናግረዋል።
ዛሬ ይመለከታቸዋል ከተባሉት ጋር በተደረገ ውይይት ይህ የጥራት ኦዲት መመሪያ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር እንደሚላክ የሰማን ሲሆን ከመቼ ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል የሚለው ግን በግልፅ አልተቀመጠም።
ማንያዘዋል ጌታሁን
#ማስታወቂያ
#ለሁሉምየግልከፍተኛትምህርትተቋማት
#ባሉበት
ጉዳዩ፡- የዳግም ምዝገባ ዝግጅት ይመለከታል
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት እና ስልጠና ባለስልጣን የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያግዙ የተለያዩ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴዎችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያና ማሻሻያ ዘዴዎች መካከል አንዱ የፈቃድ አሰጣጥ ነው፡፡ ይህንን የትምህርት ጥራት ማስጠበቂያ ዘዴ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ መመሪያ እና ስታንዳርድ ጸድቆ ስራ ላይ ውሏል።
በመሆኑም መመሪያና ስታንዳርድ ተግባራዊ ለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ፈቃድ እና ፈቃድ እድሳት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 988/2016 አንቀጽ 4(26) መሠረት ሁሉንም በስራ ላይ ያሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በፌደራል ደረጃ ፈቃድ የተሰጣቸው ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለዳግም ምዝገባ መዘጋጀታችንን ሀምሌ 22/2016 ዓ.ም ባደረግነው ስብሰባ መግለጻችን ይታወሳል።
በዚህ መሠረት ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዳግም ምዝገባ መምሪያ መሰረት እስከ ነሃሴ 30/2016 ዓ.ም በተቋም፣ በካምፓስ እና በፕሮግራም ደረጃ በሀርድ ኮፒ እና ሶፍት ኮፒ የተደራጁትን መረጃዎች በአካል በመቅረብ እንዲሁም በየጊዜው በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት መረጃዎችን እንድታደራጁ እና በቂ ዝግጅት በማድረግ እንድታመለክቱ አጥብቀን እናሳስባለን።
በፊስቡክ -https://www.facebook.com/FDRE.ETA
በትዊተር- https://twitter.com/FDRE_ETA
በቴሌግራም -https://t.me/FDRE_ETA
በዌብሳይት Www. neta.gov.et ይከታተሉ
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
A place to learn English easily.
Owner - @Samson_G
Buy ads: https://telega.io/c/English_Ethiopian
Last updated 2 months, 2 weeks ago
NGO, የመንግስት እና የግል ድርጅቶች የስራ ማስታወቂያ እና ነፃ የትምህርት እድሎችን ያገኛሉ ቤተሰበ ይሁኑ ሌሎችንም ይጋብዙ
ለማስታወቂያ @Human133 ላይ አናግሩን
We need promoters
Website: www.abayjobs.com
Facebook: https://www.facebook.com/abayjobs12
Last updated 1 month ago