Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

Description
አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና"
اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا
አላህዬ 🙏 ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 month, 3 weeks ago

ቤትም እንስገድ! (ድጌ የተለጠፈ)

በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ

የመስጂድና መስጂድ የመስገድ ትሩፋቶች እንደተጠበቁ ሆነው ፤ ቤት በመስገድ ፣ በመቅራትና በሌሎችም ዒባዳዎች ፤ ቤታችንን የአምልኮ ስፍራ ማድረግ መዘንጋት የሌለብን ወሳኝ ነገር ነው ።

በተለይ ለሴት…

በአላህና በመጨረሻው ቀን አምና መልእክተኛዋን ለምትከተል ሙስሊም ሴት … በጥቅሉ የተሻለው መስገጃ ፤ ቤትዋ, ለዛውም ክፍሏ ነው ።

عَنْ عَمَّتِهِ أُمِّ حُمَيْدٍ - امْرَأَةِ أَبِي حُمَيْدٍ السَّاعِدِيِّ - أَنَّهَا جَاءَتِ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَتْ : يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنِّي أُحِبُّ الصَّلَاةَ مَعَكَ. قَالَ : " قَدْ عَلِمْتُ أَنَّكِ تُحِبِّينَ الصَّلَاةَ مَعِي، وَصَلَاتُكِ فِي بَيْتِكِ خَيْرٌ لَكِ مِنْ صَلَاتِكِ فِي حُجْرَتِكِ، وَصَلَاتُكِ فِي حُجْرَتِكِ خَيْرٌ مِنْ صَلَاتِكِ فِي دَارِكِ، وَصَلَاتُكِ فِي دَارِكِ خَيْرٌ لَكِ مِنْ صَلَاتِكِ فِي مَسْجِدِ قَوْمِكِ، وَصَلَاتُكِ فِي مَسْجِدِ قَوْمِكِ خَيْرٌ لَكِ مِنْ صَلَاتِكِ فِي مَسْجِدِي ". قَالَ : فَأَمَرَتْ، فَبُنِيَ لَهَا مَسْجِدٌ فِي أَقْصَى شَيْءٍ مِنْ بَيْتِهَا وَأَظْلَمِهِ، فَكَانَتْ تُصَلِّي فِيهِ، حَتَّى لَقِيَتِ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ.

ኢማም አሕመድ በሙስነዳቸው በዘገቡት ሐዲስ ላይ ኡሙ ሑመይድ የተባለች ሰሐቢያህ (ረዲየሏሁዐንሀ) ወደ ረሱል (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጥታ "አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ ከእርሶ ጋር (መስጂድ መጥቼ) መስገድ እወዳለሁ ።" አለቻቸው ። ረሱላችንም (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሲመልሱላት "በእርግጥ ከእኔ ጋር መስገድ እንደምትወጂ አውቃለሁ ። (ነገር ግን) በክልልሽ (የግል ክፍል ውስጥ ደበቅ ያለ ቦታ) የምትሰግጂው ሰላት ፤ በክፍልሽ ከምትሰግጂው የተሻለ ነው ፣ በክፍልሽ የምትሰግጂው ሰላት ፤ በቤትሽ ከምትሰግጂው የተሻለ ነው ፣ በቤትሽ የምትሰግጂው ደግሞ በሰፈርሽ መስጂድ ከምትሰግጂ ይሻልልሻል ፣ በሰፈርሽ መስጂድ የምትሰግጂው ደግሞ በእኔ መስጂድ ከምትሰግጂው ይበልጥልሻል ።" አሏት ። እርሷም… ከቤቷ ጥግ ፣ ድብቅና ጨለም ያለ ቦታ ላይ መስገጃ አሰርታ ፤ እስከለተሞትዋ ድረስ እዚያው ነበር የምትሰግደው ። (ረዲየሏሁ ዐንሀ)

ለወንድሳ? …

ወንድ ደግሞ ግዴታ ከሆኑና ከኢማም ጋር ከሚሰግዳቸው ሰላቶች ውጪ ያለውን ተጨማሪ ሱና ሰላቶች ፤ ቤቱ ቢሰግድ የተሻለ ነው ።

عَنْ زَيْدِ بْنِ ثَابِتٍ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ اتَّخَذَ حُجْرَةً ، قَالَ : حَسِبْتُ أَنَّهُ قَالَ : مِنْ حَصِيرٍ فِي رَمَضَانَ فَصَلَّى فِيهَا لَيَالِيَ، فَصَلَّى بِصَلَاتِهِ نَاسٌ مِنْ أَصْحَابِهِ، فَلَمَّا عَلِمَ بِهِمْ جَعَلَ يَقْعُدُ، فَخَرَجَ إِلَيْهِمْ فَقَالَ : " قَدْ عَرَفْتُ الَّذِي رَأَيْتُ مِنْ صَنِيعِكُمْ، فَصَلُّوا أَيُّهَا النَّاسُ فِي بُيُوتِكُمْ ؛ فَإِنَّ أَفْضَلَ الصَّلَاةِ صَلَاةُ الْمَرْءِ فِي بَيْتِهِ إِلَّا الْمَكْتُوبَةَ

"የወንድ ልጅኮ በላጩ ሰላት ፤ እቤቱ የሚሰግደው ሰላት ነው ።" ቡኻሪ ዘግበውታል

እናም… ግዴታችንን መስጂድ ከሰገድን በኋላ ወደ ቤታችን የምንመለስ ከሆነ ፤ አዝካርና ዱዐ መስጂድ ጨርሰን ሱናዎቹን ቤት ብንሰግዳቸው የበለጠ ነው ። ነገር ግን ቤት መስገድ የማይቻልበትና ለኹሹዕ ምናምን የምንቸገርበት ሁኔታ ሲኖር ፤ መስጂድ መጨረሱ የተሻለ ነው ።

والله أعلم

ለማንኛውም ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

**ቤትም እንስገድ**! (ድጌ የተለጠፈ)
1 month, 4 weeks ago

ክፍት የስራ ማስታወቂያ (ድጌ የተለጠፈ)

ከታች በሚዘረዘሩ 6 የስራ መደቦች ላይ ፤ ሁሉንም ወይም የተወሰነውን መስራት የምትችሉና መስፈርቱን የምታሟሉ ሰዎችን ሁሉ አሳትፈን የትልቅ ትርፍ ባለድርሻ እንድትሆኑ ስንጋብዝ በታላቅ ደስታ ነው ።

ፆታ ፡· ወንድ ወይም ሴት
እድሜ ፡· ለአካለ መጠን የደረሰ ሁሉ

የስራ አይነቶችና ደሞዞቻቸው

1, በቀን ከ24 ሰአታት ውስጥ 5✘10 (50) ደቂቃ ብቻ ወስዶ 5 ወቅት ሰላትን ጠብቆ መስገድ
ደሞዝ ፡· "በመካከላቸው ያሉትን (ትናንሽ) ወንጀሎች ይማርለታል ።" (ሀዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል)

2, ከሰላት በኋላ የሚባለውን አዝጋር አዘውትሮ ማለት ።
ደሞዝ ፡· "አንድ ሙስሊም ባርያ አያዘወትራቸውም ፤ ጀነት ቢገባ እንጂ" (አቡዳውድ ዘግበውታል)

3, "ረዋቲብ" የሚባሉ ሱና ሰላቶችን መስገድ ። እነርሱም ፡· ከሱብሒ (ግዴታ ሰላት) በፊት 2 ረከዐ + ከዝሁር በፊት 4 (2,2) ረከዐ + ከዝሁር በኋላ 2 ረከዐ + ከመግሪብ በኋላ 2 ረከዐ + ከዒሻ በኋላ 2
ደሞዙ ፡· "በእነርሱ (ሰበብ) ጀነት ውስጥ ቤት ይገነባለታል ።" (ሙስሊም ዘግበውታል)

ዘ ገራሚያን… ሐዲሱን ያስተላለፈቺው ኡሙ ሐቢባህ (ረዲየሏሁዐንሀ) "ከረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከሰማሁኝ ጊዜ ጀምሮ ትቼያቸው አላውቅም ።" ትላለች ። ከርሷ የሚያስተላልፈውም ዐንበሰህ "ከኡሙ ሐቢባ ከሰማሁኝ ጊዜ ጀምሮ ትቼያቸው አላውቅም ።" ይላል ። ከእርሱ የሚያስተላልፈው ዐምር ቢን ዐውስም "ከ ዐንበሳህ ከሰማሁ ጊዜ አንስቶ ትቼያቸው አላውቅም ።" ይላል ። ከእርሱ የሚያስተላልፈው ኑዕማን ቢን ሳሊምም "ከ ዐምር ቢን ዐውስ ከሰማሁኝ ጊዜ ጀምሮ ትቼያቸው አላውቅም ።" ይላል ።
… እኛስ? ስንቴ ሰምተን አልሰማንም?!

4, የምናውቀውንም ሆነ የማናውቀውን ሙስሊም ስናገኝ "አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ" በማለት ሙሉ ሰላምታን ማቅረብ ።
ደሞዝ ፡· በ1 ሙሉ ሰላምታ 30 ሐሰናት (አቡዳውድና ሌሎችም ዘግበውታል)
(አንድ ሐሰና ዱንያና ዱንያ ከያዘችው ይበልጣል)

5, ቢያንስ በቀን 5 ገፅ የጌታችንን ቃል ቁርኣን መቅራት ። (ከእያንዳንዱ ሰላት በኋላ 1 ገፅ ብንቀራ)
ደሞዝ ፡· አንድ ፊደል ለቀራንበት አስር አጅር ይከፈለናል ። (አንዱ ገፅ ከ1,000 በላይ ፊደል አለው ✘ 5 = 5,000 ✘ 10 = + 50,000 አጅር)
(ቲርሚዚይ ዘግበውታል)

6, ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ
ደሞዝ ፡· እኛ ሼር በማድረጋችን አንብቦ የሰራበትን ሰው አጅር ሁሉ እናገኛለን ። ሐቢባችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳሉት "ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰራው ሰውዬ ምንዳ አለው ።" (ሙስሊም ዘግበውታል)

አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ዐላ ሐቢቢና ሙሐመድ

(በዚህ ወርሀ ረመዳን ደግሞ የመልካም ስራዎች ምንዳ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይነባበራልና…)

ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

ክፍት የስራ ማስታወቂያ (ድጌ የተለጠፈ)
2 months ago

ቁርኣን መቅራት ለምትችሉ … (ድጌ የተለጠፈ)

(ሙስሊም ሆናችሁ ቁርኣን መቅራት የማትችሉ ግን ፤ ቲንሽ እንኳ አይሸምማቹም?)

በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ

ድምፅን ከፍ አድርጎ ማስረቅረቅ ደስ ይላል ። የመቅራት ነሻጣችንንም ይጨምራል ። እንዲሁም ከንፈራችንን ሳናንቀሳቅስ የምንቀራው ቁርኣንና የምንዘክረው ዚክር አጅር እንደሌለው ዑለማዎች ይናገራሉ ።

ነገር ግን … በአቅራቢያችን የሚሰግድ ፣ የሚዘክርና ፣ ዱዐ የሚያደርግና የተኛ ሰው ካለ ፤ ለርሱ በማይሰማውና በማይወሰውሰው ያህል ድምፃችንን መቀነስና በአፍ እንቅስቃሴ ብቻ መቅራት ይኖርብናል ።

عَنِ الْبَيَاضِيِّ ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ خَرَجَ عَلَى النَّاسِ وَهُمْ يُصَلُّونَ، وَقَدْ عَلَتْ أَصْوَاتُهُمْ بِالْقِرَاءَةِ، فَقَالَ : " إِنَّ الْمُصَلِّيَ يُنَاجِي رَبَّهُ، فَلْيَنْظُرْ بِمَا يُنَاجِيهِ بِهِ، وَلَا يَجْهَرْ بَعْضُكُمْ عَلَى بَعْضٍ بِالْقُرْآنِ ".

ኢማማ ማሊክ በ"ሙወጠዐ" እና ኢማም ማሊክ በ ሙስነዳቸው እንደዘገቡት "የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ድምፃቸውን በቁርኣን ከፍ አድርገው (በየግላቸው) በሚሰግዱ ሰዎችን አጠገብ ሲያልፉ እንዲህ አሉ ፡· አንድ ሰጋጅ ጌታውን ነው የሚመሰጥረውና ማንን እንደሚያናግር ያስተውል (በኹሹዕ ይስገድ) ። እናም አንዳቹ ሌላቹ ላይ ድምፁን በቁርኣን ከፍ አያድርግበት ። "

በተለይ …ፆመኛ በሆንን ወቅት የ "ኢነርጂ" እጥረት ስለሚኖር ፣ ድምፃችንን ከፍ ለማድረግ የምናወጣው ብክነት ከተጨመረ ፤ አቅም ያሳጣናልና ዝግ ባለ ድምፅ መቅራቱ የተሻለ ነው ።

በተያያዘ… የሚሰግድ ሰው እንዳይወሰወስ "ድምፅ ከፍ አያድርግበት" የተባለውኮ በቁርኣን ነው ። ከቁርኣን ውጪ ባሉ ድምፅና ጫጫታዎች የምንረብሸውስ ምን እንባል?!

ለማንኛውም ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

ቁርኣን መቅራት ለምትችሉ … (ድጌ የተለጠፈ)
2 months, 3 weeks ago

"ምራቻን ጨ’መራቸው"

በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ

እውቀት ወሳኝነቱ ለስራ መዳረሻነቱ እንደሆነ ከተረዳን ወዲያ ፡ "።ብዙ ጊዜ በምናውቀው (አንዳንድ) ነገሮች የማንሰራው ለምንድነው?" የሚለውን መመለስ አለብን ። በተለይ አምላካዊ መመሪያ የሆኑትን ቁርአንና ሐዲስ ፡ ትእዛዝና ክልከላዎቻቸውን ከተረዳን ኋላ ችላ የምንልባቸው ብዙ የተገለፁና የተደበቁ ሰበቦች አሉ ።

(1) ያወቅነውን ነገር በዝርዝር ተጨባጭ አምነን መቀበል የምንችልበት መረዳት ላይ ስላልደረስንና በተወሰነ መልኩ ትክክለኛነቱን ስለምንጠራጠር ።

(2) አሁን ካለንበት ጊዜ ፣ ቦታና ሁኔታ አንፃር ያንን ማድረግ ወይም መተው እንደማንችል ራሳችንን ስላሳመንን ።

ሌሌች ሰበቦች ቢኖሩም ለጊዜው ከላይ የጠቀስናቸውን ሁለት ምክንያቶች ጠቅልለን እናስቀምጠው ።

አንድ መደረግ አለበት ተብሎ የታዘዘን ነገር ለመስራትም ሆነ መተው አለበት ተብሎ የተከለከለን ነገር ለመተው ፡ ሁሉ ነገር በሳይንስና በልምድ ተረጋግጦ እስኪመጣልን እንጠብቃለን ። የዚያን ያህል ያሳመነን ነገርን ደግሞ አንድ ቀን በሚገርመው ተለውጠን ሁሉን የማድረግና የመተው አቅም እስክናገኝ ድረስ እናቆየዋለን ።

ልክ አይደለም ። ልክ የሚሆነው ባወቅነውና በቻልነው ልክ ስንታዘዝና ስንሰራ ነው ። "አጠቃላዩ ያልተገኘ ፡ ከነው አይተውም" በሚለው መርሆ መሰረት… በገባንና በምንችለው ልክ ስንኖር ያልገባንን ወደመረዳትና ያልቻልነው ወደመቻል በየጊዜው እናድጋለን

وَالَّذِينَ اهْتَدَوْا زَادَهُمْ هُدًى وَآتَاهُمْ تَقْوَاهُمْ

{እነዚያም የተመሩት (አላህ) መመራትን ጨመረላቸው ፡፡ (ከእሳት) መጥጠበቂያቸውንም ሰጣቸው ።} ሙሐመድ 17

የአንቀፁ ጉልህ መልእክት … "ጨመረላቸው" ቢሆንም አገላለፁ ግን "ጨመራቸው" የሚለውን ነው የሚያሲዘን ። ዛደ ፡ ጨመረ ፣ ሁም ፡ እነርሱ = ዛደሁም ፡ ጨመራቸው

= ምራቻ ፡ እኛ ባለንበት ሆነን የሚጨምር ነገር ሳይሆን ፡ እኛ ወደ ምራቻው ጎዳና ከፍ ብለን የምንጨመር መሆኑን ያስረዳናል ።

… ነገር ግን በገባውና በአቅሙ ልክ ፡ የአላህና የመልእክተኛውን ሀሳብና እውቀት ከራሱና ከሌሎችም ፍጡሮች ሀሳብና እውቀት አስቀድሞ ታዛዥ ያልሆነና…

وَمَن يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَىٰ وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّىٰ وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ ۖ وَسَاءَتْ مَصِيرًا

{ቅኑም መንገድ ለእርሱ ከተገለጸ በኋላ መልክተኛውን የሚጨቃጨቅና ከምእምኖቹ መንገድ ሌላ የኾነን የሚከተል ሰው (በዚህ ዓለም) በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ገሀነምንም እናገባዋለን፡፡ መመለሻይቱም ከፋች! ።} ኒሳእ 114

ገብቶት የነበረውን እውቀትና ይችልበት የነበረውንም አቅም እያጣ የተወዘጋገበ ኑሮ እንዲኖር ይደረጋል ። ና…

እንወቅ ፣ በገባንና በምንችለው ልክ ታዘን እንስራ ፡ ምራቻን እንጨመር … ሰሊምቱም!

ለማንኛውም ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

**"ምራቻን ጨ’መራቸው"**
3 months, 1 week ago

ጠቃሚ ንዴት

በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ

ንዴት ሁሉ ጎጂ አይደለም ። ንዴት ፡ አንድን መስተካከል ያለበትን ችግር ለመለወጥ እንድንነሳሳ የሚያደርገን ግፊት ነው ። ይህ አይነቱ (መጠነኛ) ንዴት ፡ ችግሮቻችንን እንድንፈታ በተፈጥሮ የተቸረን መልካም ስሜት ነው ።

ንዴት ጎጂ የሚሆነው ፡· (1) አያያዙን ካልቻልንበትና (2) ማስተካከል በማንችለው ነገር ከሆነ ነው ።

አቢ ሁረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንህ) ባስተላለፉትና ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ ላይ እንደተወሳው ፤ አንድ ሰው ወደ ረሱል (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጥቶ "ምከሩኝ" ባላቸው ጊዜ ፡ ደጋግመው "አትቆጣ ፣ አትቆጣ ፣ አትቆጣ " ብለውታል ።

ይህንንም ሐዲስ ያብራሩ ዑለማዎች ፡ "አትቆጣ!" ማለት (1) ለቁጣ የሚዳርጉህን (የተለመዱ) ነገሮችን ራቅ ። (2) ቁጣህ ገንፍሎ ወጥቶ አጓጉል ነገር እንዳታደርግ ተቆጣጠረው ። … ማለት ነው ፤ ብለዋል ።

እንዲሁም በሌላ አቢ ሁረይራህ (ረዲየሏሁ ዐንህ) ባስተላለፉትና ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ ላይ እንዲህ ብለውናል ፡· "ጠንካራነት ፡ ታግሎ በጣለ አይደለም ። ይልቁንም ጠንካራው ማለትማ ያ በንዴት ጊዜ ራሱን የሚቆጣጠር ነው ።"

ስለ አያያዙ የምናነሳው በመነሻው ጥሩ የነበረው ስሜት ወደ ጭፍንነት ስለሚከተን ነው ። አንዳንድ ችግሮች ደግሞ ካለንበት ሁኔታ አንፃር የመለወጡ እድል አናሳ ይሆናሉ ። እንደዚህ አይነት ችግሮች በተፈጠሩ ቁጥር ፡ እራሳችንን ለንዴት አሳልፎ መስጠት አለ ጥቅም መጎዳት ነው ።

አንቆጣ (አለ ጥቅም) … ወሰላም!

ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

**ጠቃሚ ንዴት**
3 months, 3 weeks ago

ዛሬ ማታ … ኢንሻአላህ

4 months, 3 weeks ago

የ ሌባም ሌባ

በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ

ሊተካ የሚችልን ተራ ንብረትና ገንዘብን የሚሰርቁ ሰዎችን ፤ ሌባ ብለን እናቃልላቸዋለን እንቀጣቸዋለን ፣… ። እኛም እነዚህን ንብረትና ገንዘቦች ስላልሰረቅን ጥሩዎች እንደሆንን እናስባለን ።

ነገር ግን የሌባም ሌባ በሆንን እኛና ሌሎችም ፤ ጊዜ ሲሰረቅ ያን ያህል አያንገበግበንም ። ሰዎችም ጊዜያችንን ሲሰርቁን የምንበግነው በወቅቱ ያሳጡንን የተወሰነ ጥቅም አስበን ነው ። እንጂ ለጊዜ ምን ገዶን!

ካሰብነውኮ… ማንኛውም ጥቅም ያለ ጊዜ ያገኘነውና የምናገኘው የለም ። እናም ጊዜዎች ወደዚያ ግኡዝ ጥቅም ተቀይረው እንደሆነ ካልገባን ነው ከጊዜያችን በላይ ለንብረትና ገንዘባችን መጥፋት የምንቆጨው ።

እና ማለት ነው… የተለያዩ የግልም ሆነ የህብረት ቀጠሮዎችን መፍታት ጊዜን መስረቅ ነውና (የሌባም) ሌብነታችን ይግባን ። የሰዎች ውድ ሀብት የሆነውን ጊዜ ከመስረቅ እንቆጠብ ።

ለማንኛውም ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

**የ ሌባም ሌባ**
5 months ago

የበላይ ልብ

በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ

الْيَدُ الْعُلْيَا خَيْرٌ مِنَ الْيَدِ السُّفْلَى

ሐኪም ቢን ሒዛም እንዳስተላለፉትና ቡኻሪ እንደዘገቡት ረሱሉላህ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይሉናል ፡· "የበላይ (ሰጪ) እጅ ፣ ከበታች (ተቀባይ) እጅ ይበልጣል ።"

ሁሌም ማንኛውንም መልካም ነገር ሰጪ ሰው ከተቀባይ ይበልጣል ። በመጥፎው ደግሞ ተቀባዩ ነው ከሰጪው የሚበልጠው ።

መልካምነት ይበልጥ የሚመዘነው መልካም ለሚያደርጉልን ሰዎች ውለታ በመመለስ አይደለም ። ያልነኩትንም አለመንካት ፣ ያልጎዱትን አለመጉዳት የመልካምነት መነሻ እንጂ ልኩ አይደለም ።

ከዚህ ከፍ ስንል በብዙ ወደተወደሰው ይቅር ባይነት እናድጋለን ። ከዚህ በደንብ ከፍ ብለን በነፃነት ስንበር ደግሞ የበላይ ልብ ላይ እንደርሳለን ። …አላህ ይወፍቀንና!

መልካምን ለማይሰጡንና ጭራሽ ለበደሉንም ሰዎች ሁሉ እንሰጣለን ፤ የበላይ ሰጪ ልብ ስላለን ።
ክፉን ላለመስጠት ከመጠንቀቅ ባለፈ ሌሎች ተሳስተውም ሆነ ሆን ብለው የሚሰጡንን ክፋት በጥሩ አያያዝ እንቀበላለን ።

መጥፎን በመጥፎ እኩኩል አድርጎ መመለስ በሸሪዐ ያልተከለከለ ነው ። ከዚህ ከፍ ብለው ይቅር የሚሉ ሰዎች የመልካምነትን አንድ ደረጃ ወጥተዋል ። ከዚህም ከፍ ብለው የተበላሸ ግንኙነትን ለማስተካከል መልካምን የሚሰጡና ፣ ክፋትን ችለው የሚቀበሉ ከፍተኛው ደረጃ ላይ ይሰቀላሉ ። ያላቸውንም ምንዳ ከሰጪው አላህ በቀር ማንም አያውቀውም ፤ እንዴሌሎች መልካም ስራዎች ተቆጥሮ አልተነገረምና ።

وَجَزَاءُ سَيِّئَةٍ سَيِّئَةٌ مِّثْلُهَا ۖ فَمَنْ عَفَا وَأَصْلَحَ فَأَجْرُهُ عَلَى اللَّهِ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الظَّالِمِينَ
{የመጥፎም ነገረ ዋጋ ብጤዋ መጥፎ ናት፡፡ ይቅርም ያለና ያሳመረ ሰው ምንዳው በአላህ ላይ ነው፡፡ እርሱ በደለኞችን አይወድም ።} ሹራ 40

ከፍተኛውን መልካምነትን ይብራብን ብለን ፣ ዝቅተኛው ዐውፍታ እንኳ ከብዳን መጥፎን በመጥፎ ለመለስ ስንሞክር ፤ ከተሰራብን ጨምረን በደል ውስጥ እንገባለን ። ከበላይ ልብ ተቃራኒ ክፋትን ሰጪ እንሆናል ።

ግና

ከመበደል መ’በደል ይሻላል ብለን ክፋትን ሰጪ ሳይሆን ተቀባይ ብንሆንና ዐውፍ ከማለት ከፍ ብለን መልካምን ብቻ የሚሰጡ የባለ ውድ ልቦች ባለቤት ብንሆን ፤ አቤት ሰላማችን ፣ አቤት ደስታችን… ፊ ዱንያ ወኡኽራ!

በሚለው ፡· እዝነትን ፣ ደስታን ፣ ተስፋን ፣ ይቅርታን እንስጥ… ከፍ ያለ የበላይ ልብ ይኑረን… ወሰላም!

ለማንኛውም ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

**የበላይ ልብ** …
5 months, 1 week ago

"እኛኮ ብናነብ… "

በሑሴን ኢብኑ ኡሚህ

ስለ መፅሐፍ ንባብ ብዙ ሰምተናል ፣ (በሚፖሰቱት) አንብበናልም ። የሆኑ ጊዜዎች ደግሞ አሉ ስለ ማንበብ በቁም ነገር ያሰብንባቸው ። አንባቢ ብንሆን ህይወታችን ላይ የሚመጣው የሆነ ለውጥ ፤ ከእኛም አልፎ ሌሎችን እንደሚያጠቃቅም ።

እናም የሆነ ጊዜ አንብበን ፣ አነብንበን ያገኘናትንና የተቋረጠች ጥቅም እያስታወስን "እኔኮ ባነም… " እንላለን ፤

ቆ’ራጭ ብንሆን ግን ከዚያን ወዲያ እንኳ እስከ አሁን ስንት አንብበን ፣ ስንት አውቀን ፣ ስንት ገብቶን ፣ ስንት ተለውጠን ነበር ። እኛኮ (በቆ’ራጭነት) ብናነብኮ …

አረ እናንብብ!

ለማንኛውም ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

Telegram

የሑሴን ሙንጭርጭሪቶች ✍📲👌👍

አላማችን (እኔና የቻናሎቼ ባለቤት) አንባቢ የሆኑ አሳቢዎችን ማብዛትና ነቄ ትውልድ ማፍራት ነው ። … በ "ኢዝኒረቢና" اللهم مكنا في الأرض وءاتنا من كل شيء سببا አላህዬ ***🙏*** ቻናሌን ለሙስሊም ወጣቶች የአይን ማረፊያ አድርግልኝ!

**"እኛኮ ብናነብ… "**
6 months, 2 weeks ago

ከቃል በላይ

እንግዲህ በፅሁፍ "እናድርግ" "አናድርግ" ከሚሉ መልእክቶች ባሻገር ተግባራዊ ት/ቶችም እንደሚያስፈልጉን መፃፍ አይጠበቅብኝም ። ያ ማለት "ለመተቸት አንቸኩል!" ብዬ በባዶ መሞነጫጨር እችል እንደነበር ጥርጣሬ አይገባችሁም ። ነገር ግን ከዛ ይልቅ (ራሴን "?" ውስጥ ከትቼም ቢሆን) ለመተቸት የሚያስቸኩለንን ሁኔታ ፈጥሮ ግምገማ ማድረግ እርማቱን የጠነከረ ያደርገዋል ።

ከዚህ በፊት በፖሰትኳዠቸው አንዳንድ ፅሁፎች ስር በሚፃፉ ኮሜንቶች ውስጥ አንዳንድ የተሳሳቱ አረዳዶችንና ለመተቸት መቸኮልን አይቼባቸዋለሁ ። በተለይ አርፍደው ቻናሉን የተቀላቀሉ ወንድምና እህቶች "እድሉ" እንዳያመልጣቸው በሚመስል ያህል ነው ለመቃወም የሚቸኩሉት ።

ስህተትን መቃወም ለሐቅ ያለንን መቆርቆር ስለሚጠቁም ደግ ነው ። በመጠኑም ቢሆን ሳናስብበት ለመቃመው መቸኮል ግን አይደግ ነው ። ለእያንዳንዱ ስህተት ፤ መልስ (ረድ) መስጠት በነፍስ ወከፍ ግድ እንደሚለን የምናስብ ጥቂቶች አይደለንም ። ይህ ልማዳችን ደግሞ ስህተትን ለማረም ከምናስበው በተቃራኒ ሊያባብስና ወደ አላስፈላጊ ስሜቶች ውስጥ ሊከት ይችላል ። ይባስ ብሎ የምናርምበት መንገድ ጤነኛ ካልሆነ ችግሩን ልናጦዘው እንችላለን ።

በተለይ … መልካምን በማሰራጨትና ክፋትን በመቃወም የምናውቅላቸው ሰዎች ዘንድ በሆነ አጋጣሚ "እንዴት?" በሚያስብል መልኩ የምናገኘውን ስህተት ለማረምና ሰውዬውን ለማማረር መቸኮል የለብንም ። ትንሽም ቢሆን "እንዲህ ለማለት ፣ ለማድረግ ፈልጎ ይሆን? " ብለን ማሰብ ይጠበቅብናል ። ቸኩሎ ከመቃወሙ ይልቅ የሚከብደው እርሱ ነውና ።

ወደ አነጋጋሪ ፖስታችን ስመለስ … ከእለታት በአንዱ ፤ ዑመር (ረዲየላሁዐንህ) ሑዘይፋ ኢብኑልየማንን (ረዲየላሁዐንህ) ያገኙዋቸውና "እንዴት አነጋህ?" ብለው ይጠይቋቸዋል ። ታድያ ሑዘይፋ ትንሽ ወጣ ያለ መልስ እንዲህ በማለት አስከተሉ ፡· "ፊትናን ወድጄ ፣ ሐቅን ጠልቼ ፣ ያለ ኡዱ ሰላት አድርጌ ፣ አላህ በሰማይ የሌለው በምድር ኖሮኝ ፤ አነጋሁኝ ።" … ኢሄኔ ዑመር ተናደውም ግራ ተጋብተውም ዝም አሉ ።

በዚህ ሁኔታ ላይ ባሉበት ወቅት ድንገት ዐሊይ (ረዲየላሁዐንህ) ይገቡና በዑመር ፊት ላይ ያዩትን ለየት ያለ ገፅታ ሰበብ ይጠይቃሉ ፤ ዑመርን ። ዑመርም ሑዘይፋን "እንዴት አነጋህ?" ብለው ሲጠይቁት የመለሰላቸውን መልስ ቃል በቃል ነገሯቸው ። ታድያ ይሄኔ ዐልይ ምንም ግራ ሳይጋቡ "እና ልክ ነውኮ… " አሉ ። "ልክኮ ነው… ፈተና ይወዳል! ያ ማለት ሀብትና ልጆች ይወዳል ማለት ነው ። …
إِنَّمَا أَمْوَالُكُمْ وَأَوْلَادُكُمْ فِتْنَةٌ ۚ وَاللَّهُ عِندَهُ أَجْرٌ عَظِيمٌ
{ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ ለናንተ ፈተና ብቻ ናቸው፤ አላህም እርሱ ዘንድ ታላቅ ምንዳ አልለ፡፡} ተጋቡን 15

"ሐቅን የሚጠላው ደግሞ ‘ሞት’ን ማለቱ ነው ።" (ሞት ጥርጥር ከሌለባቸው ሐቆች መካከል አንዱ ስለሆነ ነው በ "ሐቅ" የተሰየመው ።)

"ያለ ኡዱ ‘ሰላት’ አደርጋለሁ ያለው ደግሞ (ዐለነቢይ) በረሱል ላይ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነው ።" (‘ሰላት’ የ ‘ሰለዋት’ ነጠላ አይደል?!)

"አላህ በሰማይ የሌለውና ሁዘይፋ ያለው ደግሞ ሚስትና ልጅ ነው ።" ብለው አረጋጉአቸው ይባላል ። (ረዲየሏሁ ዐንሁም አጅመዒን)
… … …

ደግሞ በዚህ ፅሁፍ ኮሜንት ስር …

إِنَّ الَّذِينَ فَتَنُوا الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ثُمَّ لَمْ يَتُوبُوا فَلَهُمْ عَذَابُ جَهَنَّمَ وَلَهُمْ عَذَابُ الْحَرِيقِ
{እነዚያ ምእምንንና ምእምናትን የፈተኑ ፣ ከዚያም ያልተጸጸቱ ለእነርሱ የገሀነም ቅጣት አልላቸው፡፡ ለእነርሱም የመቃጠሉ ስቃይ አልላቸው ።} የሚለውን አንቀፅ ከነማብራሪያቹ አስቀምጡብኝ አልዋቹ ።

በተረፈ ስለ አራቱም ተከታታይ ፖስት ይኖረናል። … ኢንሻአላህ!

ለማንኛውም ተቃረቡ ↴
https://t.me/yehussenmun

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago