ህይወትን በግጥም 📜

Description
☺☺እዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ አስደሳች ህይወትን እና ስሜትን የሚገልጹ ግጥሞች ፣ወጎች ፣ታሪኮች፣ልብወለድ እንዲሁም የተለያዩ ጠቃሚና አስተማሪ ሀሳቦችን በፁሑፍ፣በምስል እና ትረካ ያገኛሉ

😍☺☺😍 ቻናላችንን ምርጫቹ ስላደረጋቹ እናመሰግናለን 🙏

😶😶😶ሁሉም ሰው ከልቡ ያለቀሰበት የሳቀበት በውስጡ ከትቦ ያኖረው የራሱ ታሪክ አለው
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

3 months, 1 week ago

"ሁሌ ባገኝህ አይሰለቸኝም" አለችው

"እውነትሽ ነው"

"አዎ ገና መተዋወቃችን ቢሆንም ደጋግሜ ላገኝህ እፈልጋለሁ"

ዝም ተባባሉ ረጅም ሰዓት።

"እኔ ምልህ ህይወት ላንተ ምንድነው አለችው?"

"ቀይሮ መድገም ነው" አላት

"ማለት"

"አሁን የሆነች ተራ ካፌ ቡና ትጠጪያለሽ ሲኖርሽ ሸራተን ነው ራሱን ቡና

አሁን አንድ ክፍል ቤትሽ ውሰጥ ትተኛለሽ
ሲኖርሽ አስር ክፍል ያለው ግን አንዱ ክፍል ብቻ ራሱን እንቅልፍ ትተኛለሽ

ደሀ ሆነሽ አረቄ ነው
ሀብታም ስትሆኚ ውስኪ ነው ቀይሮ መድገም

ሰው ለምን ይመስለሻል አንድ ደብር ደጋግሞ ከመሳለም ደብር የሚቀያይረው ቦታ ቀይሮ ጸሎት ለመድገም ነው።

በፊት የሆነ ልጅ ትወጃለሽ ስትለያይ
ልጅ የሆነ ትወጃለሽ
ያንኑ መውደድ ቀይሮ ነው መድገም ነው

የሆነ ዘፈን በሌላ ዘፈን ዘፋኝ ቀይሮ መድገም

የምታውቂውን ስብከት በሌላ ሰባኪ ወይም ቄስ ቀይሮ መድገም

በኢኮኖሚ ክላስ መሄድ ዝነኛ ስትሆኚ እዛው ፕሌን ውስጥ ቢዝነስ ክላስ ሆኖ ወንበር ቀይሮ በረራ መድገም

ሰው ሁሉ ገንዘብ የሚፈልገው የነበረውን ነገር ቀይሮ ለመድገም ነው።"

የሆነ ነገሯ ተዛባባት።

"በቃ የዘመኑን ከቨር ሙዚቃ ታውቂያለሽ?"

"አዎ" አለችው

"የኛ ሰው ህይወት እንደዛ ነው
የህይወት ከቨር በይው።
የሆነ የሆነ ነገር ቀንጭጮቦ መምጣት ቀጣጥሎ ማዜም
ቀያይሮ መድገም..."

"የሚቀጥለው አመት እደውልልሀለሁ" አለችው

(ኤልያስ ሽታሁን)

3 months, 2 weeks ago

የቱ ጋር መሰለህ…
(ሚካኤል አ)

መባቻ ጅምርህ
የነፍስህ ድባቴ
ውድቀት እንግልትህ
ያኔ …
ባሽትሪ መያዣ ፣ በሲጋራ ብናኝ
በርጋፊ ቅጠል ፣ ድባቧ የሚቃኝ
በዛች ጠባብ ክፍል
ምጥን መሰብሰቢያ
ዙሪያህን ሰው ሞልቶህ
ቀንህን ማጣፊያ
ለአፕላይ ግብዣ የተዘረጋች ጣት
በሚግተለተል ጢስ ፣ ሰንቃልህ እሳት
እሷን ለመቀበል ስትፈግግ ባ’ክብሮት
የሰበብ አስባብ ጢስ
ቀረ ቤትህን ወርሶት።
የቱ ጋር መሰለህ?
በቀይ መብራት ፍካት
በቅልቅል ሽቶ አዲስ አይነት ክርፋት
በጭላጭ ብርጭቆ ተላኮበት ድራፍት
ከስፒከር ማህፀን ሙዚቃ ተለቆ
ጭፈራ እና ዳንሱ አንድ ላይ ተዛንቆ
የቀይ ሴት ታፋ ዓይንህ በስስ ሰርቆ
በምራቅህ ድርቀት ጉሮሮህ ተጨንቆ
ጠቅሰህ ስትጠራት
ያቺን የሞት ብልቃጥ
ከባቷ ፈልቅቀህ ዕፅዋን ስትቀምሳት
በገላህ ፍሰሀ መቅደስህን ናድካት ።
የቱ ጋር መሰለህ?
የልጅነት ልምድህ
ከሰንበት ቤት ገዳም
ምልልስ ብርታትህ
በሀይኪንግ ሲቀየር
የያሬዱ ወረብ
በእስክስታ ሲዛወር
ሳትቆም ለፀሎት
ሳይንስ ከእምነት ልቆት
ኒቼ ቦታ ሲወርስ የየኔታን መንበር
የነፍስህ ቁዘማ መንደርደሪያ ነበር።
ትዝ አለህ?
ዘር መራጭ ስትሆን
የደም ሴል መንጣሪ
ጆሮህ ዳባ ሲለብስ
ለፍጥረት እንግልት
ለህፃናት ጥሪ…
መንገድህ ሲሳለጥ
በ V 8 መኪና
ዝርግ አስፓልት ሲመስልህ
ጉርብጥብጥ ጎዳና ፤
ስቆልኛል ስትል ጥርሱን የነከሰ
እንባው አንሸራሽሮህ ጌታ ዘንድ ደረሰ።
ምላሹስ የከፋው መቼ ላይ ሆነና?
ጥሬ እየቆረጥክ ሆድህ ሲመረመር
እስቲም ሳውና ገብተህ ፊትህ ሲጭበረበር
በድሎትህ መኃል
ገላን የሚያኮስስ የእሾህ ስንጥር ነበር።
ትዝ አለህ?
መኝታህ በምቾት ተሞልቶ በአጀብ
እንቅልፍህ ሲናጠብ?
ትዝ አለህ?
በውድ ቀለም ቤቶች ልጆችህ ሲማሩ
ከግብረገብ ታዛ ተናንሰው ሲቀሩ?
ትዝ አለህ?
የጉያህ መልካም ሴት
የአጥንትህ ፍላጭ
አሁን ከምን ጊዜው
ሆነችብኝ ምላጭ?
ብለህ ስትቆዝም …
እንዲያ ነው አይዋ
ግፍ ፅዋው ሲሞላ
በትሩን አይመርጥም።
ትዝ አለህ?
ታወሰህ?
የቱ ጋር መሰለህ?
የተፈታው ውሉ
የጎደልክ ከሙሉ
ኧረ ስከን ሲሉ
ከዕድሜ የተማሩ
የጋሽ ውቤን ምክር
የእመት ጉሌን ዝክር
ረግጠህ ስትበር…
ስትሻገር ፣ ስጥስ
የምስኪናን ድንበር
የዛሬ ውድቀትህ ፣ በግጥም ሊነገር
ክንፍህ የተመታው ይሄን ጊዜ ነበር።
ትዝ አለህ?

አዎን እሱ ጋር ነው!

@getem
@getem
@getem

4 months ago

አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?

አሁንም ግፍ አይበቃሽም
ዘንድሮም ለምለም ትያለሽ
ካቀፍሽው ቅጠል ባለፈ
የለመለመ ምን አለሽ?

ካቻምናም አምናም መተሻል
አቅፈንሽ አጥነን ደግሰን
አመትሽ ውበቱ ላይቆይ
እያደር ሊያተራምሰን

አንቺ ?
አንቺ እንቁጣጣሽ
ምናባሽ ልትሰሪ መጣሽ?

አምና ተስፋ አስደረግሺኝ
ደክሜ ቤቴን ሰራሁኝ
አልቅሼ ልገባበት ስል
ይፈርሳል ሁሉ ሰማሁኝ
አሁንም ተስፋ አልቆረጥኩም
ቃልሽን ስመላልሰው
አመትህ ተባርኳል ብለሽ
የላክሺኝ እንደ ሞኝ ሰው
ስታገል ከማይሽር ህይወት
መቀመቅ ነፍሴን ሲውጣት
ወደፊት ፈቀቅ እያልኩኝ
ሞት ልቤን እንዳይለውጣት

"አበባ አየሆሽ" አትበዪኝ
አበባ አልቸገረኝም
ዘፈንሽ አንገሽግሾኛል
ጨዋታሽ አይሰማኝም
በያመት ደምቀሽ ስትመጪ
ህፃን ልጅ ለምትመስዪው
ግጥሙን በምነግርሽ ቃል
ስትዘፍኚ አስተካክዪው

"የሀገሬ ልጆች ውጡ በተራ
ቅስም ሰብሬ  ሰው እስክሰራ
እንኳን ሰውና  የለኝም እድል
ሁሌ መጣለው አመት ላጎድል
አመት አጉድዬ ስገባ ቤቴ
ደስታ ይሰማታል የእንጀራ እናቴ"
አደዪ
የሞት ጉዳዪ
"ኡኡ" በዪ

እንደዚህ ብለሽ ዝፈኚ
ግጥሙን አስተካክለሽው
በቃ አንቺም እንዳገሬ ሰው
ጊዜን ነው የተማመንሽው?

"ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ
ሆ ብለሽ መጣሽ
ሆ ብለሽ"

ሆሆሆሆ!

አታፍሪም ደግሞ
ልክ እንደ ንፁህ እንዳልበደለ
ተስፋሽ ምስኪኑን እየገደለ
ከዘመን ዘመን ማትለወጪ
ጉድ ያዘለ አመት አቅፈሽ ምትሰጪ
ሆ ብለሽ መጣሽ?
ሆ ብለሽ ውጪ!

ለተድላ ሳይሆን
ለሞት ዋዜማ ፡ እያስጨፈርሺኝ
በመጣሽ ቁጥር
ሆ የምልልሽ ፡ ሞኝ አደረግሺኝ?

አሁን ንገሪኝ
ስለ አመትሽ
ይብስብኛል ወይስ ድናለው?
ዘፈኑን ተዪ ፡ ያንቺን ስሞታ ለምጄዋለው

ባለእንጀሮችሽ በተራ ገቡ
አዝማች አባትሽ ሌላ አገቡ
እንጨቱን ሰብረሽ ቤት እስክትሰሪ
ለእንጀራ እናትሽ ሳትናገሪ
እድጅ አድረሻል ኮከብ ስትቆጥሪ

እኔ ምስኪኑ

ምን ያገባኛል ስላንቺ ኮከብ
ምን ያገባኛል የእንቅልፍሽ ማጠር
የኔ ችግር ነው ወሰን የሌለው
የኔ ስቃይ ነው  የማይቆጠር

እህት አበባ  ፡ እህት አበባ
እህት አበባ  ስትልሽ ከርማ፤
ጥላሽ ብትሄድም በሀምሌ ጭለማ
እኔ ላይ "አዬዬ".. አትበዪብኝ፡
ለኔ አመቱ ነው  የጨለመብኝ።

ተይ ባለጊዜ..
ተይ እንቁጣጣሽ..
ሀገር ጉድ አቅፈሽ ፥
ሁሌ እየመጣሽ፦

እንኩ አትበዪን፡

ሀዘን ቁስላችን ፡ ድኖ ሳይገግም፤
ካምናው የሚብስ
ሌላ አዲስ አመት ..አንፈልግም!

by @mikiyas_feyisa
@getem
@getem
@paappii

6 months ago

ጥቁር ነጭ ግራጫ
(ነብይ መኮንን)

...ሰው እያለ አጠገባችን
ቅንነቱን ማየት ሲያመን
ከኛ አብሮ በሕይወት ቆሞ ፤ መልካሙን ስምን
መጥራት ሲያንቀን
"ሰው ካልሞተ ወይ ካልሄደ አይነሳም" እንላለን
እንዲህ እያልን፤
ስንቱን ጠቢብ እየሸኘን፤
አበባውን ቀጥፈን ጥለን፤ አበባ (እ)ናስቀምጣለን።

7 months, 1 week ago

ሁለት በይ

ስንቱን ጣለ ወገብ ዳሌ
:
ወንድ ይቀልጣል እንዳሞሌ።

በቃኝ አይሉት ደስታ ባለም
ስሜት አውሬ ጠገብኩ የለም።

ያጠምደዋል ስሜት መረብ
ለመለያየት ነው ያንዳዱ አቀራረብ።

ኤልያስ ሽታኹን

7 months, 1 week ago

አንድ በይ

አልቸኩልም ገላ አውቃለሁ
:
አልስምሽም ከንፈር ያው ነው::

ደክሜያለሁ በብዙ ሴት
ግና የለም አዲስ ሀሴት።

ኤልያስ ሽታኹን

8 months ago

ክልክል ነው!

(በዕውቀቱ ስዩም)

ማጨስ ክልክል ነው!
ማፏጨት ክልክል ነው!
መሽናት ክልክል ነው!
ግድግዳው በሙሉ ተሰርቶ በክልክል
የቱ ነው ትክክል ?
ትንሽ ግድግዳና ተንሽ ሃይል ባደለኝ
"መከልከል ክልክል ነው !" የሚል ትትእዛዝ አለኝ።

@astawesegnregasa
@astawesegnregasa

8 months ago

​​የውበት ጀርባው

(በእውቀቱ ስዩም)

ላንተ የሚታይህ፤ የሚያምር ፈገግታ ያበባ ጉትቻ
ላንተ እሚታይህ ውብ ገፅታ ብቻ
ጥርሷን ጉራማይሌ፤ የተነቀሰች ቀን
ያየቺው መከራ፤ ያየቺው ሰቀቀን
የጆሮዋን ጫፉን ፤ በሾህ ስትበሳ
የበላችው ፍዳ ፤ ያየቺው አበሳ
የዋጠችው ህመም፤ ከሬት የመረረ
የቀመሰው ማነው፤ከሷ በስተቀረ?
ከያንዳንዱ ታላቅ ፤ ውበት በስተጀርባ
ሲንዠቀዠቅ ኑሯል ፤ ብዙ ደምና እንባ
ይሄም ታላቅ ዜማ
ይሄም ታላቅ ስእል
ይሄም ታላቅ ተረት
ይሄም ታላቅ ድርሰት
ከፊትህ አልቆመም፤ እንደመና ወርዶ
ስቃይ ያቃልላል፤ ከስቃይ ተወልዶ።

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад