Poetry Madness

Description
"Poetry is not an opinion expressed. It
is a song that rises from a bleeding
wound or a smiling mouth."
Kahlil Gibran
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 4 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 11 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 day, 10 hours ago

2 months ago

`፨
ስንት ኪሎ ነው በሚሉት ሰፈር ከጓደኛዬ ጋር እየሄድን ሳለን ነው ፊትለፊታችን አንድስ የሚያህል ቻፓ ያላት ሴት ካንዲት ህፃን ጋር እጅለጅ ተያይዛ ውኒጥ ውኒጥ ትላለች...

_ አየኸው ይህን ውኒጥ ውኒጥ... አልኩት

_ በደምብ! ደስ የሚል መመላቀጥ በናትህ... አለኝና የታቸኛውን ከንፈሩን በምላሱ አረጠበ። ቀጥሎ..

_ ከፍቅረኛዬ ጋር የተለያየን ስለሌላት ነበር። መጀመሪያ ላይ እንዴት ታውሬ እንደነበር አላውቅም

_ ምንድን ነው የሌላት ?

_ ቂጥ

_ እና አንተ ለቂጥ ብለህ ትጣላለህ እንዴ? ምን አይነት ፋራነት ነው የያዘህ ጀለስ ?

_ ተዉ ባክህ የኔ ቂጥ ይበልጠዋል። 4 ኪሎ የማይሞላ ቂጥ ይዛ ሴት ነኝ ትላለች እንዴ? እኔ ኮ ተጨነኩ bro... ከወንድ ጋር የመጋደም ያህል ገላዋ ገላዬን ሲኒካው ገላዬ እሾህ ያበቅላል።

_ ይህን ያህል ?

_ እንዳይደብርህ ብዬ እንጂ ከዚህም ይከፋል። አስበው እስቲ ራሷ ደውላ ጠርታህ... ቤቷ ውስጥ... አልጋ አንጥፋ... ላዩ ላይ የፅጌሬዳ አበባ ቅጠሎች ጣል ጣል አርጋ... መሬት ላይ በበርካታ ሻማ ግብዳ ልብ ቅርፅ ሰርታ... ሰውነቷን አራቁታ... ወዘተ..ወ.ዘ.ተ... ከብዙ ወሬዎችና መሽኮርመሞች በኋላ ጠፍጣፋ ጣውላ ቂጥ ስታይ አታስተውክም? እውነቱን ልንገርህ ሴት የፈለገ romantic ብትሆን ቂጥ ከሌላት ምንም ናት...!

_ ቆይ ቆይ ሲጀመር ዋናው በፊት ያለው እንጂ ምን አገባህ የኋላው... አትከትበት.. አለበዛኸውም እንዴ ?

_ ያልገባህ ነገር አለ Man

_ ምን ?`_ የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ !?

2 months ago

እህ......ብለሽ ነግረሽኝ....
ጭንቅሽን ልጋራ..ልሰማሽ..ፈራለሁ..
እሱ አስተያየትሽ....ብዙ...ይናገራል..
ዝምታሽን ልቤ... በአቅሙ ያዳምጣል...
....እርጋታሽ ይጮሀል..
(ኡኡ...አንሶት... ፀጥታውን መርጧል..)
ካይኖችሽ:ከውብ ፊትሽ...ጥልቅ ሀዘን ይረጫል...
በፈገግታሽ መሀል ጥርሶችሽን አልፎ...
ትካዜሽ ይጋባል...
(ሳቅሽ ለቅሶን አዝሏል..መፍካት አያውቀውም..
በቅፅበት ይከስማል..)

......ራስን ዘንግቶ ለሌው መንሰፍሰፍ:
(ምነኛ ከባድ ነው ለዚ ሁሉ ማሠብ...)
በቦታቸው መሳል...
የብዙ ራስ ሸክም...በአንድ አንቺ ላይ ሲካብ..

...ያለ መሰልቸት...ፈገግታሽ ሳይነጥፍ..
..መከፈታ ....ብሶትን ደብቆ..
...ይህን ይዞ መቆም.
.....ባህሪሽ...እንደ መሬት...
.. መረገጡን ስሱ ልብሽ ችሏል..
መገፋት...መታመም..ውበትሽን ሳይነሳሽ..
ለሌላ መኖርን..ካላንቺ ማን ያውቃል...
.....ለፍቶ የወዙን 'ማይጠይቅ..
...ተጎድቶ ካሣውን ማይጠብቅ..
....ካላንቺ....ይኖር ይሆን..?!..
.....እንግዲ..እኔ አላውቅ...

2 months ago

ቀን ሲከፋ እንኳን ሚበሉት የሚያበሉት ይቸግራል።

_ የጎንደር ሰዉ
`ሰዉ እንዴት ለራሱ ሚጎርሰው አጥቶ ለሰው ሚያጎርሰው ይተርፈዋል ?... ይህን ጥያቄ ለመመለስ ሁነኛ ሰዉ ጎንደር ነበረች (ከተማዋን "ሰዉ " ያልኩትም " ናት " በማለት ፈንታ " ነበረች " ያልኩትም በምክንያት ነው )... አሁን ላይ ግን ልታጎርስ የሰደደችው እጅ ተነከሰባት መሰል እጇን ወደ ጉያዋ መሰብሰብ ጀምራለች።
ጎንደር በዚህ ሰዓት ለመኖር ድካም ተጭኗት ለመሞት አልሰንፍ ብላለች።
አንዳንዴ እኔ ያለሁባት ጎንደር ሙታ በኔ ውስጥ ያላቸው ቀድማ ሞታለች የተባለቸው ጎንደር ለትንሳኤ ብትበቃ ስል እመኛለሁ... ልቤ ውስጥ ያላቸው ጎንደር በእውን ካለችው የተሻለ ትክክለኛዋና እውነተኛዋ መሆኗን አውቃለሁ...
... ዓለማየሁ ገላጋይ ዘመኔን ሙሉ አየሁ የነበረ ህልም መቼቱ ጎንደር ናት። ጎንደር ስመጣ የተለየ ስሜት ይሰማኛል። ይላል... ጎንደር ውስጥ fake personality የለም ሁሉም ሌጣ እውነቱን ይዞ ነው አደባባይ ሚወጣው... ጎንደር ክሯም እምነቷም እዉነት ናት...
ዓለማየሁ ጎንደር ውስጥ ያለውን መንፈስና Vibe ወደሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ማዛመት ብንችል አብዛኛው ችግራችን ይፈታል... ይላል... ለዓለማየሁ ገላጋይ የኢትዮጵያ በተላይም የአዲስ አበባ የኢ-ሰብዓዊነት በሽታ መድሀኒቷ ጎንደር ናት...
(ይቺ ጎንደር እንግዲህ ከጥቂት ዓመታት ጎን ያደረችው ማለት ናት... አሁን ላይ ያላቸው የዚያችኛው Shadow እንጂ real እሷ አይደለችም...)

አቡነ ሓራን አሁን ላይ እንደ ጎንደር የናፈቀኝ ምፅአትም ሆነ ገነት የለም?`

2 months, 1 week ago

*፨ ፠ ፨ ፠

ምነው አፈርሽ ?
ምነው ከፋሽ ?
{ ያልለበ'ሺው ቀሚስ ሰፋሽ!}
ስላንቺ ቀና ባለ ፊት አንገትሽን ስለ ምን ደፋሽ ?
ለምን... ?

እርቃኑን ፊትሽ ከቆመ
እቅፍሽን ጠባቂ ወንዴ
እርቃንሽን ፊቱ መቆምሽ
ለሀፍረት ይሰጣል እንዴ ?

{ ስለምን ሀዘን ተሰማሽ?
ስለምን ራ'ሽን አማሽ ?}

ሰዉ መሆን አንዱ ላንዱ ነው
ሰውነት የጋራ ድፍድፍ
ህይወቱን ፆሞ ማያውቅ ፊት
ምን አላት ላንዲት ቀን መግደፍ ?

{ ስለምን ሰላምሽን አጣሽ?
ስለምን ራ' ሽን ቀጣሽ?}

(የሰዉ ሰውነቱ....)
አብሮ አንድ ላይ መንቃት
አልያ አብሮ ማሸለብ
ጻድቅ አያሰኝም
ባልንጀራን ቀድሞ ራስን መለብለብ ።

ራቁቱን ላለ ራቁት ገላሽን ኑሮ ለሚማጠን
እርፍና እኮ አይደለም
እሺ ብሎ መጦ እንዳ' ዲስ ማውጠንጠን
(ስሜት ክር መጠንጠን
ባልጋ ቤቱ እጣን ቤተ መቅደስ ማጠን)

ታዲያ ለምን ዝም አልሽ ?
እጅሽ ሀፍረትሽ ላይ አሁን ምን ያረጋል ?
ችላ ሲሉት እኮ
አይደለም ይህ ምሽት የሰዉ ሌ'ት ይነጋል ?

ተይ ነጋብን ሌቱ
" ዝሙት ሀጢያት" አትበይ ሌላ ነው እውነቱ
(አንዴ እቀፊኝ እንጂ
አይደለም ያንቺ ልብ ይደሰታል ቤቱ )

{ምነው ማፈር ነካሽ ?
ሀፍረቱን ለሸጠ
በግልብ ድፍረቱ ለጠየቀሽ ወጣት
መከልከል አይደለም መመኘት ነው ቅጣት። }

ምኞት ነክቶን ነበር
ምኞት ደርሶን ነበር...

(ይሄውልሽ...)
በሌለ እሳት ላይ
ምድጃ ማራገብ ቤቱን አያሞቅም
ምኞት ተነካክቶ
በግብር ላይ ማፈር ፍፁም አያፀድቅም።

ምነው ከፋሽ..........................?

፦ ግዑዝኤል*

2 months, 1 week ago

"Birth is suffering, aging is suffering, sickness is suffering, death is suffering... The struggle to maintain existence is suffering."

:-Buddha (Dhammacakkappavattana Sutta)

2 months, 1 week ago

**ከ ኢየሱስ ቀጥሎ ማን ሊመጣ ይችላል?... ጥበብ ሁሉ በ ኢየሱስ ይፈጠማል!!

ምናልባት ቀጥሎ እኛ ነን!!
እስካሁን አብረውን የሰው ልጆችን ለማንቃት ለተጓዙት በሙሉ ስማቸውን ዘርዝረን ባንጨርስም ከላይ ያሉት እንደ መታሰቢያ ይሁንልን።

ዝክር እንደመዘከር ያህል ስማቸውን ባናከብርም ባለን ተሰጥኦ ልክ በትምህርቶቻቸው ራሳችንን ልናገኝ በጀመርነው መንገድ መሪዎችችን ናቸውና _ ሰላም ለክሙ!!! ልንላቸው እንወዳለን።**

2 months, 1 week ago

*ያዲስ አመት ምኞት

"መጭው አዲስ ዓመት
የሰላም የደስታ
እንዲሆንላችሁ
ምናምን ምናምን
ሌላ ቃል የለህም፥እኔን የሚያሳምን?

ዐርባ ዘመን ሞላው
መጭው አዲስ ዓመት፤ካምናው እየባሰ ምድር በጠቅላላው
የፈንጅ ወረዳ ነው፤ሰርዶ የለበሰ

ትናንት ያልተገኘ፥ ነገም አይገኝም
ሰላም አልመኝም
አልመኝም ተድላ
እኔ እምጠይቀው
በሐሩር መካከል ፥ ትንሽ የዛፍ ጥላ
በዳገት ወገብ ላይ፥ እማርፍበት ኬላ በድብልቅልቅ መሀል፥ ብልጭ የሚል ስርአት
በውጊያ መካከል ፥አጭር የሻይ ሰአት
በዘንድሮ መቅሰፍት ፥ በከርሞ መከራ
ባለው ፋታ መሀል
ትንሽ መተቃቀፍ፥ጥቃቅን ዳንኪራ።*

:- በውቀቱ ስዩም

2 months, 2 weeks ago

" እኔ ምልህ 2016 እንዴት ነበር? "

"ከ 2ዐ17 ይሻላል! ''?****

2 months, 2 weeks ago
*"እውነቱን ለመናገር ቀን በበቀን ዓመትባ'ል ነው

"እውነቱን ለመናገር ቀን በበቀን ዓመትባ'ል ነው
ፀሐይ በምስራቅ ወጣ በምዕራብ እስከምትገባ... ."

፦ Pamfalone ቀዳማዊ

2 months, 2 weeks ago

" እግዜርም እንደ ሰው - ባ'ሰት እየማለ
አንድ እንጀራ ብለው - "ሙት የለኝም " አለ
?* "

:- አራሽ አንደፋራሽ*

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 4 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 11 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 day, 10 hours ago