NEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC

Description
ውድ ተከታዮቻችን
ይህ ነብዩ ስነ አእምሮ E-CLINIC በተለይ ሁኔታ በአካል ፣ በonline እና በመድዎል በማነኛዉም የስነ አእምሮ ህመም ላይ የማማከር አገልግሎት ይሰጣል...

ስልክ📞: +251922077637
ቴሌግራም: @Mentalhealth_NJ
E-mail: [email protected]
Address: Addis ababa
ነብዩ ጃግሶ(ስነ አእምሮ ባለሙያ)
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад

2 weeks, 4 days ago
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ***🙏***

እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ 🙏

ሰላም ይብዛላችሁ ውድ የሀገሬ ልጆች እንኳን  ለNEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC ቴሌግራም ቻናል ሁለተኛ ዓመት ክብር በዓል አደረሰን አደረሳችሁ🙏 ይህን አስመልክቶ በተለያዩ የስነ አእምሮ ርዕሰ ጉዳዮች በተለያዩ ባለሙያዎች በየሳምንቱ ቅዳሜ ከምሽቱ 3:00 ላይ ነፃ የOnline live stream ትምህርት አዘጋጅቷል።

የዚህን ሳምንት የፊታችን ቅዳሜ ማለትም ታህሳስ 19 Overcoming Depression በሚል ርዕሰ የተሰናዳ ትምህርት በነፃ ተጋብዛችኋል።

ማጋራት አይረሳ

እናመሰግናለን

ቦታው : https://t.me/psychiatry1

ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)

2 weeks, 5 days ago

ሰዎች በስሜትህ እንዲጫወቱ አትፍቀድ!!

👉 አንድ ሰው አንተ ላይ እና ሕይወትህ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ሲኖረው፣ ስሜትህንም እንዲቆጣጠር ኃይል እየሰጠኸው ነው—ያ ደግሞ አንተን ወደ ኋላ ይጎትትሃል! ከዛ ይልቅ በዙሪያህ ካሉ ሰዎች ጋር ጤናማ ወሰኖችን ፍጠር— ለእነሱ ሳይሆን ለራስህ ስሜትም ኃላፊነት ውሰድ!

👉 መርሆችህን ተከተል! ሁልጊዜም ምርጫዎችህን ራስህ እየመረጥክ መሆኑን እርግጠኛ ሁን— የራስህን ነገሮች ራስህ አድርግ!

👉 ጊዜህን በማማረርና መጥፎ ግንኙነቶችን በማሰብ አታሳልፍ!

⛔️የሚከተሉትን 7 እርምጃዎች በመውሰድ ደግሞ ሰዎች አንተ ላይ ኃይልን በመጎናጸፍ በስሜትህ እንዳይጫወቱ ለማድረግ ያግዙሃል!

  1. ለስሜቶችህ ኃላፊነትን ውሰድ

ስለራስህ በሚኖርህ ስሜት ማንንም ተወቃሽ አታድርግ! ለራስህ ስሜት ሙሉ ኃላፊነትን ውሰድ።

አንድ ሰው ስሜትህን አጋዥ ባልሆነ መንገድ ተጽእኖ እያደረገበት ከሆነ አዎንታዊ እርምጃን ውሰድ። ሁኔታውን ለመቀየር ሞክር ካልቻልክ ደግሞ ለሁኔታው የምትሰጠውን ምላሽ ለውጥ።

  1. ጤናማ ወሰኖችን አብጅ

አንዳንድ ሰዎች ከፈቀድክላቸው ጊዜህን፣ ገንዘብህንና ቦታህን ከልክ በላይ ከመውሰድ አይመለሱም። ስለዚህ ለራስህ ስትል ጤናማ ወሰን ማበጀት አለብህ።

አይሆንም በል፣ ተናገር፣ ሲያስፈልግህ እርዳታ ጠይቅ።

  1. ከመርሆችህ አንጻር ኑር

ስለመርሆችህ ግልጽ መረዳት ሲኖርህ ከመንጋው ጋር አብሮ ስለመጓዝ አትጨነቅም። ላንተ ጠቃሚ የሆኑ ነገሮችን ለይተህ እወቅ፤ ከዚያ አንጻርም ኑር።

  1. ሰዎች እንደተሳሳቱ ለማረጋገጥ መሞከርህን ተው

ምናልባት "አሳያቸዋለሁ!" ብለህ ስትዝት ለጊዜውም ቢሆን ትነቃቃ ይሆናል። እንደተሳሳቱ ለማረጋገጥ የምታደርገው ሙከራ ግን አንተ ላይ ስልጣን እንዲኖራቸው ያደርጋልና ተጠንቀቅ!

  1. የግል ዋጋህ በሌሎች ሰዎች አስተያየት እንዲወሰን አትፍቀድ

በቂ እንደሆንክ ለማረጋገጥ የሆኑ ሰዎችን ሐሳብ ከፈለግክ እነዛ ሰዎች አንተ ላይ ስልጣን አላቸው ማለት ነው። የግል ዋጋህ በሌሎች ጥገኛ እንዲሆን አትፍቀድ።

  1. በማማረር ጉልበትህን አታባክን!

ስለሰዎች በማማረር ጊዜህን ባጠፋህ ቁጥር ሕይወትህ ውስጥ የበለጠ ቦታ እንዲይዙ እየፈቀድክ ነው። ስለዚህ ስለ አለቃህ ወይም ስለ ሆነ ሰው ጊዜህን ሰጥተህ ከማለቃቀስህ በፊት እየሰጠሃቸው ያለውን ቦታ መርምር።

ጊዜህንና ጉልበትህን አዎንታዊ ነገሮች ላይ ማዋል የበለጠ ጠቃሚ እንደሚሆንልህ አስታውስ!

  1. ራስህን አትበድል!

ከአንድ ሰው ጋር ያደረግከውን መጥፎ ንግግር ተመልሶ ማስታወስና ማሰብ ሳታውቀው ብዙውን የአእምሮህን ኃይል እንዲወስዱ እያደረግ ነው። ከስህተት ለመማር ብታስብ እንኳ ተመልሰህ የአንድን ሰው አስከፊ ድርጊትና ንግግር ደጋግሞ በማሰብ አይሁን።

አእምሮህን ለሰዎች አታከራይ!!!

ተክሉ ጥላሁን

ነብዩ ስነ አእምሮ E-CLINIC

በዩቲዩብ የአእምሮ ጤና መረጃ ለማግኘት https://www.youtube.com/@nebiyujagiso

የባለሞያ እርዳታ ለማግኘት 👇👇👇
📞 +251922077637 ይደዉሉልን
ቴሌግራም👉 @Mentalhealth_NJ

ከውደዱት ይቀላቀሉን 👇👇
@Psychiatry1 @Psychiatry1
@Psychiatry1 @Psychiatry1

3 weeks, 1 day ago

የመርሳት ችግር-Dementia

Dementia(የመርሳት ችግር) ከእድሜ ጋር ተያይዞ ከሚከሰቱ አእምሮ ህመሞች አንዱ ሲሆን ዋና መገለጫው 🤔የማስታወስ ችሎታ ማጣት ቢሆንም የማሰብ፣ የመረዳት፣ የማገናዘብ፣ የማቀድ እና ውሳኔ የመስጠት ክህሎት ማሽቆልቆልን ያካትታል።

በተጨማሪም   ሀሳባቸውን በንግግር ለመግለጽ ይቸገራሉ/የባህርይ ለውጥ ይታይባቸዋል::  የመርሳት ችግር በማንኛውም እድሜ ክልል ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ። ነገር ግን በዋናነት የሚከሰተው እድሜያቸው 65 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ነው።

የመርሳት በሽታ መንስኤዎች፡-

አልዛይመር (Alzheimer's disease)

አካላዊ የህመም አይነቶች

✍️ የደም ግፊት/የልብ ህመም እና ተያያዥ እክል / ወይም መርጋት ህመም
✍️ የHIV/AIDS ህመም
✍️ የአንጎል እጢዎች
✍️ አንጎላችን ተደጋጋሚ አካላዊ ጥቃት ሲደርስበት ለምሳሌ ጭንቅላታቸው በተደጋጋሚ የተመቱ ሰዎች
✍️  የቫይታሚን ምግብ እጥረቶች፣ የእንቅርት

የአእምሮ ህመሞች

✍️ የድብርት ህመም
✍️ ለረጅም ጊዜ ማጨስና የአልኮል መጠጥ ማዘውተር

እንዲሁም በዘር የመጋለጥ ሁኔታ እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች የመርሳት ችግር ሊያመጡ ይችላሉ።

Derebe M(senior mental health specialist)

@PSYCHIATRIY1

3 weeks, 3 days ago
NEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC
3 weeks, 3 days ago
NEBIYU PSYCHIATRY E-CLINIC
3 weeks, 3 days ago

HAPPY 2ND YEAR ANNIVERSARY

ሁለት ዓመት ሆነን ቤትሰብቦቼ

በሳምንት አንዴ የነፃ Online live ቅዳሜ በ 3:00 ስዓት ሆኗል በአብላጫ ደምፅ። የሚጀምረው የNEBIYU PSYCHIATRIY E-CLINIC 2ኛ ዓመት አከባበር ጋር ሲሆን ቀኑም 19-04-2017 EC.

እንኳን አደረሳችሁ 🙏

እናመሰግናለን

ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)

1 month ago
ማህበራዊ ጭንቀት እክል-Social Anxiety Disorder

ማህበራዊ ጭንቀት እክል-Social Anxiety Disorder

በሌሎች እንዳይፈረድብህ በጣም ትፈራለህ?
አዳዲስ ሰዎችን ከመገናኘት ትቆጠባለህ?

እንደዚህ አይነት ስሜት ቢያንስ ለ6 ወራት ከተሰማዎት እና እነዚህ ስሜቶች የእለት ተእለት ተግባሮችን ለምሳሌ በስራ ቦታ ወይም በትምህርት ቤት ከሰዎች ጋር መነጋገርን ከባድ ያደርጉዎታል?

የማህበራዊ ጭንቀት እክል አብዛኛው ሰው ላይ የሚታይ አንዱ የአእምሮ ህመም ሲሆን በሌሎች ሰዎች የመታየት እና የመፈረድ ከባድ፣ የማያቋርጥ ፍርሃት ነው።
ይህ ፍርሃት በስራ፣ በትምህርት ቤት እና በሌሎች የእለት ተእለት እንቅስቃሴዎችዎ ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።

ጓደኛ ማፍራት እና ማቆየት እንዲሁም አቅማችንን እንዳንገልጥ ያደርገናል።

በእነዝህ ቦታዎች በሌሎች እንዳይፈረድብህ በጣም ትፈራለህ?

👉በተለያየ ቦታ ሃሳብ መስጠት፣
👉አዳዲስ ሰዎችን መገናኘት/ማዎራት፣
👉በሰዎች ፊት መሥራት፣
👉ክፍል ውስጥ Presentation ማቅረብ፣
👉ምግብ ቤት፣ ሱቅ፣ አምልኮ ቦታ ወይም ሌላ የህዝብ ቦታ ላይ እርዳታ መጠየቅ፣
👉የፍቅር ጓደኛ ማግኘት/መተዋወቅ ፣
👉በሰዎች ፊት ለጥያቄ መልስ መስጠት፣
👉በሰዎች ፊት መብላት፣
👉በቃለ መጠይቅ ውስጥ መሳተፍ፣ እና ወዘተ...

ማህበራዊ ጭንቀት እክል ውጤታማ ሕክምና አለው።

የንግግር ሕክምና-የስነ ልቦና ድጋፍ እንዲሁም የመደኃኒት ሕክምና አለው

ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)

Source: DSM 5

ይቀላቀሉን : https://t.me/psychiatry1

1 month ago

ውረድ!

በተሳሳተ ባቡር ውስጥ ከገባህ. . .

በመጀመሪያው ፌርማታ ላይ መውረድ አለብህ!

ካልሆነ ባቡር ላይ በቆይህ ቁጥር፣

የመመለሻ ዋጋ የበለጠ ውድ ይሆናል።

የማወራው ስለ ባቡር አይደለም!

መልካም ቀን

@PSYCHIATRIY1

1 month ago

ልቀቋቸው!!!

ምንም ነገር ብታደርጉ መለወጥ የማትችሏቸውን ነገሮች ልቀቋቸው!

ምንም ብትታገሉ የራሳችሁ ልታደርጓቸው የማትችሏቸውን ሰዎች ልቀቋቸው!

ምንም ብታሰላስሏቸው እንደገና የማትመልሷቸውን ያለፉ ሁኔታዎች ልቀቋቸው!

በቃ ልቀቋቸው! ለፈጣሪ ስጧቸው!

መልካም ምሽትና የእረፍት እንቅልፍ ለሃገሬ ሰዎች!!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ

@PSYCHIATRY1

1 month, 1 week ago

ጥሩ የእንቅልፍ ንፅህናን ለመጠበቅ በራስችን ማድረግ ያለብን ነግሮች

የእንቅልፍ ንጽህናን(sleep hygiene) መለማመድ የተሻለ የእንቅልፍ ጥራት እንዲኖር ያስችላል።

  1. ወጥ የሆነ የእንቅልፍ ሰዓት ይኑርዎት፡

በየቀኑ በተመሳሳይ ሰዓት ለመተኛት እና ለመነሳት ይሞክሩ ቅዳሜና እሁድ እንኳን ጨምሮ። ይህ የሰውነትዎ ውስጣዊ ሰዓት እንዲስተካከል እና የተሻለ እንቅልፍ እንዲኖር ይረዳል።

  1. ለእንቅልፍ ምቹ የሆነ አካባቢ ይፍጠሩ፡

መኝታ ቤትዎ ቀዝቃዛ፣ ጨለማ እና ጸጥ ያለ መሆኑን ያረጋግጡ።

  1. ከመተኛቶ በፊት ለኤሌክትሮኒካዊ መሳሪያዎች መጋለጥን ይገድቡ፡-

በስክሪኖች የሚወጣው ሰማያዊ መብራት በሰውነትዎ ተፈጥሯዊ የእንቅልፍ ማነቃቂያ ዑደት ላይ ጣልቃ ሊገባ ይችላል። ከመተኛቱ በፊት ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ያህል እንደ ስማርትፎኖች፣ ታብሌቶች ወይም ኮምፒተሮች ያሉ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን ከመጠቀም ይቆጠቡ።

  1. ዘና የሚያደርግ የመኝታ ጊዜን ያዘጋጁ

ከመተኛትዎ በፊት እንዲዝናኑ በሚረዱ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ይሳተፉ። ይህም መጽሐፍ ማንበብን፣ ሙቅ መታጠብን፣ እንደ ጥልቅ መተንፈስ ወይም ማሰላሰል የመሳሰሉ የመዝናኛ ዘዴዎችን መለማመድ ወይም የሚያረጋጋ ሙዚቃ ማዳመጥን ሊያካትት ይችላል።

  1. አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን ያስወግዱ፡-

ቡና፣ ኒኮቲን እና አልኮሆል የሚወስዱትን መጠን ይገድቡ ምክንያቱም እነዚህ የእንቅልፍ ሁኔታዎችን ሊያበላሹ ይችላሉ። ከመተኛቱ በፊት እነዚህን ንጥረ ነገሮች ከመጠቀም መቆጠብ ጥሩ ነው።

  1. አዘውትረህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርግ፡

አዘውትረህ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የተሻለ እንቅልፍ እንዲተኛ ሊያደርግ ይችላል ነገርግን ቢያንስ ከመተኛቱ በፊት ጥቂት ሰአታት በፊት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ለመጨረስ ሞክር።

  1. ከመተኛቱ በፊት ከበድ ያለ ምግብ እና ከመጠን በላይ ፈሳሽ ከመውሰድ መቆጠብ፡-

ትልቅ ምግብ መመገብ ወይም ከመተኛቱ በፊት ብዙ ፈሳሽ መጠጣት ምቾት ማጣት እና እንቅልፍን ሊያስተጓጉል ይችላል።

እነዚህን ልምዶች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ውስጥ በማካተት የእንቅልፍዎን ጥራት እና የቆይታ ጊዜ ማሻሻል ይችላሉ።

NB. ለብዙ ሰዎች ሊጠቅም ስለሚችል ማጋራት አይርሱ🙏

**ነብዩ ጃግሶ (ስነ አእምሮ ባለሙያ)

ነብዩ ስነ አእምሮ** እ-ክሊኒክ

በዩቲዩብ የአእምሮ ጤና መረጃ ለማግኘት https://www.youtube.com/@nebiyujagiso

የባለሞያ እርዳታ ለማግኘት 👇👇👇
📞 +251922077637 ይደዉሉልን
ቴሌግራም👉 @Mentalhealth_NJ

ከውደዱት ይቀላቀሉን 👇👇
@Psychiatry1 @Psychiatry1
@Psychiatry1 @Psychiatry1

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 год, 6 месяцев назад

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 1 месяц назад

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች

🔴 ውጤቶች

🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች

🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 2 недели, 1 день назад