የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

Description
ይህ ቻናል በላፍቶ ቢላል መስጂድ የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ሲሆን ሊንኩን በመጠቀም ለራሳችንም ሌሎችም እንዲጠቀሙ እናድርግ

https://t.me/lafto_qirat
Advertising
We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago

5 days, 7 hours ago

#ኢብኑ_ቁዳማህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«አብዛሃኛዎቹ ሰዎች የጠፉት የሰዎችን ወቀሳ በመፍራትና ሙገሳቸውን በመሻት መሆኑን አውቃለሁ። ሁሉም እንቅስቃሴያቸው የሰዎችን ውደታ በሚገጥም መልኩ ሆነ፤ ሙገሳቸውን መሻትና ወቀሳቸውን መፍራት! ይህ ከአጥፊ ነገሮች መካከል ነው። መታከም ይገባዋል።»

5 days, 20 hours ago

ታላቅ መሪ
እውነተኛ አፍቃሪ!

ብዙ ምላሶች ስለ ነብዩ ፍቅር አነብንበዋል ፤ እልፍ ብዕሮች ስለዚህ ታላቅ መሪ ውዴታ ከትበዋል! ገሚሱ በተግባር ውዴታውን ለመግለፅ ሲፍጨረጨር ገሚሱ ውዴታው ከተከሸኑ ቃላት ባለፈ ከላንቃው አልወርድ ብሎት ምላሱና ጣቶቹ ጫፍ ተንጠልጥሎ በተግባሩ እጅጉን ርቆ ይባስ ብሎ በተግባሩ አስተባብሏቸዋል!

ከተለያዩ የቃላት ጋጋዎች ይልቅ ግን የዚህ እውነተኛ አፍቃሪ ሰሐቢይ ውዴታውን በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባር የገለፀበት አጋጣሚ እስከመጨረሻው ቀልቤን ገዝቶታል!

ኹበይብ በመካ ጣዖታዊያን እጅ ከገባ በኃላ! ይህ ተከሰተ!

አቡ ሱፍያን (ከመስለሙ በፊት) እንዲህ አለው ፦

«ሙሐመድ ﷺ ባንተ ቦታ ሆኖ እሱን ብንገድለውና አንተ ከቤተሰቦችህ ጋር ብትሆን ትፈልጋለህን?» ብሎ ጠየቀው

ኹበይብም ፦

«በፍፁም በአላህ እምላለሁ እኔ ከቤተሰቦቼ ጋር  ሆኜ ሙሐመድ ﷺ አሁን ባለበት ቦታ እሾህ እንዲነካው እንኳ አልፈቅድም»  ሲል መለሰ! ከዚያም ሰቀሉት! ረዲየላሁ ዐንሁ!

ማብራሪያ አይሻም!

ጁምዓ ነው እርሳቸውን ማውሳት እናብዛ !!!

ሁሌ የሚወሱ ድንቅ ነብይ!  እንዴታ ጌታቸውስ

"መወሳትህን ላንተ ከፍ አድርገንልሃል።" (95:4)

ብሏቸው የለ!

اللــــــــهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد .اللـــــــهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد
❁ ❁❁ ❁

6 days, 7 hours ago

ከሞትን በኋላ ሰዎች እንዴት በፍጥነት እንደሚረሱን ብናውቅ ኖሮ፤ አላህን አምፀን ፍጡራንን ለማስደሰት አንለፋም ነበር፡፡
አላማችን የአላህን ውዴታ ማግኘት ግባችን ጀነት ይሁን!

1 week, 2 days ago

"ለወደፊቱ አስተካክል ያለፈው ይማርልሀል❗️"

{እናንተ በነፍሳቹ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ ከአላህ እዝነት በፍፁም ተስፋ አትቁረጡ አላህ ወንጀሎችን በሙሉ ይቅር ይላል እነሆ እሱ መሀሪ እና አዛኝ ነው።} (ሱረቱ አዝ ዙመር:53)

1 week, 3 days ago


     ቀና በል ቀን አለ!!

መንገድ ሁሉ እንቅፋት  በሆነበት ዐለም
መነሳት ነው እንጂ   መውደቅ ብርቅ አይደለም።*

ሰው ብታጣ ዛሬ   አትዘን ወንድሜ
አግኝቶ ማጣትን   ያስተምራል እድሜ።

ሲኖርህ የኖረ   ስታጣ ብታጣው
አለኝ ያልከው ወዳጅ   ከፊት ባታገኘው።

የዛሬው ውድቀትህ መማሪያህ ነውና
ባጣኸው ሳይጨንቅህ ባለህ ላይ ተፅናና።

መሙላት ቢቸግርህ  ቀን እየጎደለ
አታቀርቅር ተነስ   ቀና በል ቀን አለ!!
*

منقول

1 week, 3 days ago

"እግርህ ጀነትን እሰከሚረግጥ እለት ድረስ ትፈተናለህ አሁንም ዳግም ትፈተናለህ! ከዚያም ጀነት ውስጥ ለአንዳፍታ ትነከርና "ወላሂ ችግር ፍፁም ቀምሼ አላውቅም" ትላለህ።
ይህንን እድል ከታጋሾች ሌላ ማንም አይጎናፀፈውም።
"

1 week, 4 days ago

እንዴት እንደሚኖሩ እንጂ ለምን እንደሚኖሩ ከማያውቁትን ሰዎች እንዳንሆን እንጠንቀቅ ፤ 
የተፈጠረልን ነገር የተፈጠርንለትን ዓላማ እንዳያስተን እናስተውል!
ለምንድን ነው የተፈጠርነው?

1 week, 5 days ago

"እውነተኛው የአላህ ባሪያ ማለት  የአካሉ ሞት ሳይሆን የልቡ ሞት የሚያስፈራው ነው፡፡  ሆኖም ብዙ ሰዎች የአካላቸውን ሞት ይፈራሉ ስለ ልባቸው ሞት ግን ግድ የላቸውም ፡፡"

(ኢማሙ ኢብኑል ቀይዩም)

1 week, 6 days ago

ነጋዴ ወደ ማምሻ ላይ ሱቁን ይዘጋል ፣ ስለ ዕለት ውሎውም ሒሳብ ይሠራል ፤ መክሰር ማትረፉን ይገመግማል፣ ዕዳና ብድሩን ያወራርዳል …
እስኪ ሁላችንም ውሏችንን እናወራርድ **፣ ዛሬ ለአኼራችን ምን ሠርተን ዋልን?

ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ**

2 weeks ago

☑️ እናታችን አኢሻ (رضي الله عنها) እንዳስተላለፈችው የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል።

«እናንተ ሰዎች ሆይ! (ከመልካም) ስራ የምትችሉትን ያክል ብቻ ያዙ። እናንተ እስካልተሰላቻችሁ አላህ አይሰለችም። አላህ ዘንድ ተወዳጅ ስራ ትንሽ እንኳ ብትሆን ዘውታሪነት ያለውን ነው።»

[ 📖 صحيح البخاري (٥٨٦١) ]

We recommend to visit

Welcome To Amharic films

Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 year, 5 months ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 4 days, 15 hours ago

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 week, 5 days ago