Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад
.
.
ከተማዋ የዕለት እንጀራቸዉን ፍለጋ ወዲያ ወዲህ በሚዳክሩ ሰዎች የእግር ኮቴ እና ጫጫታ ታምሳለች።የአይጥ መርዝ ሻጮች እስፒከር ፣ የወያላዎች የሞላ የሞላ የሚል ጥሪ ፣ ሸራ ዘርግተዉ ቲሸርቷን በሀምሳ ሚሞሪ ሚሞሪ....የሚሉ ድምጾች ጎልተዉ ይሰማሉ።
የመንግሥት ሠራተኛው አቶ አበራ ከታናሽ ወንድማቸዉ ከአጎናፍር ጋር መንገድ ዳር ካለ የባስ እስቴሽን ወንበር ላይ ተቀምጠዉ ግራ ቀኙን ይታዘባሉ።አጎናፍር ነብሱ እስክትወጣ የሚወዳት ማሕደር ጋር እዚሁ ቦታ ነዉ የተቀጣጠሩት ። አቶ አበራም ማሕደር እስክትመጣ ወንድማቸዉን ብቻዉን ሊተዉት ስላልፈቀዱ እንጂ እሳቸዉም የሚሄዱበት አንገብጋቢ ጉዳይ እንዳላቸዉ አስቀድመዉ ለአጎናፍር ነግረዉታል።
አቶ አበራ ስለ ፍቅር ማራኪ ቃላትን እያሽሞነሞኑ መደስኮር አብዝተዉ ይወዳሉ።ዛሬ ደግሞ አፍቃሪ ወንድማቸዉን በግላጭ አግኝተዋልና እድሉን በፍፁም ማሳለፍ አልፈቀዱም።
የእናቴ ማስታወሻ ብቸኛ ወንድሜ አጎናፍር.... ብለዉ ይህንኑ ዲስኩራቸዉን መደስኮር እንደጀመሩ ማህደር ከሩቅ ስትመጣ ተመለከቷት።
ነገሩ ምቹ አጋጣሚን የፈጠረላቸዉ በሚመስል ንግግራቸዉን ቀጠሉ....እነሆ ልብህ የፈቀዳት ሴት መጥታለችና ወደርሷ ቅረብ!
....በል ሂድ....ነብስህን ለፍቅር አስገዛት!
....በል ሂድ.....
ናፍቆት ያዘሉ አይኖቿን በሐሴት ብርሀን ሙላቸዉ!
...........
የምትባዝን ነብሷ ካንተዉ ተጋምዳ እፎይ ብላ ትደላደል!
........
ትደሳብህ ዘንድ አለሜ በላት።
ትመካብህ ዘንድ አለሁሽ በላት።እያሉ ሲነግሩት..........
.......ማህደር መሐሉ አካፋይ ካለዉ ሰፊ አስፓልት ባሻገር የእግረኛ መንገዱ ላይ ቁማ እጇን አዉለበለበች።....
....በል ሂድ አታስጠብቃት አንተን ብላ የመጣች ፍቅርህ ደርሳለችና እ..ቅ..ፍ አድርግህ በጆሮዎቿ የፍቅርን ዜማ አንቆርቁርላት.......ብለዉት ፈጣሪ ካንተዉ ጋር ይሁን በሚመስል ትከሻዉን ሦሥት ጊዜ መታ...መታ አድርገዉት ተነስተዉ ሽቅብ መጓዝ ጀመሩ።
..... መቶ ሜትር አካባቢ በእግራቸዉ ከተጓዙ በሗላ ከአንድ ሱቅ ፊት ለፊት የቆመች ኮሮላ መኪናቸውን አስነስተዉ መጓዝ ጀመሩ።
በመሀል ስልካቸዉን ከኪሳቸዉ አውጥተዉ የልጆቻቸዉ እናት ወደሆነችዉ የሰማንያ ሚስታቸዉ ደዉለዉ ዛሬ ስራ እንደሚያድሩ እና እንዳትጠብቃቸዉ ካሳወቋት በሗላ መኪናቸውን ዳር አሲዘው አቆሟት።
በሩን ከፍተዉ ከወረዱ በሗላም መንገድ ዳር ፈንጠር ፈንጠር ብለዉ ከቆሙ ሴተኛ አዳሪዎች አንዷን መርጠዉ ዋጋ ከተነጋገሩ በሗላ የተሳፋሪ በሩን ከፍተዉ ወደ መኪናዉ አስገብተዋት የሴቷ ተራ እስኪደርስ መኪናቸዉን እየጋለቡ አልጋ ወደያዙበት ሆቴል ገሰገሱ።
Fu--ad
ለዉዲቷ****
እንዴት ነሽ አለሜ - ደልቶሽ ያላደርሽዉ፣
ለዘመኔ ማማር - ወዝሽን የገበርሽዉ፤
እንቁ ዘመንሽን - በአፍላዉ የጋገርሽዉ፤
አለኝ ያልከፈልኩት - ለኔ ያበደርሽዉ...
.... አንቺ ያልቆጠርሽዉ።
እንዴት ነዉ መዳፍሽ - ሳለቅስ የዳበሰኝ፣
አባብሎ እሚያስተኛኝ - ስራብ የሚያጎርሰኝ።
ናፈቀኝ እቅፍሽ - ዉየ የማድርበት፣
ስፈራ ሲጨንቀኝ - የምሸሸግበት፤
እናት አለሚቱ አመለ ሸጋዋ የኔ አንጀተ እንስፍስፍ፤
አለ ወይ በአለሙ አለም የሚያስረሳ እንዳቺ ያለ እቅፍ?
......እናት አለሚቱ......
የፍቅር መፍለቂያ - የመዉደድ ባልተቤት፣
አንጀተ ስፍስፏ - የልብ አዉቃ እመቤት፤
ካለሽ ሁሉ ሙሉ - ምን ጠፍቶ ካንቺ ቤት..
......እናት አለሚቱ......
ህመም ካንቺ ይራቅ - እንባ ከዐይንሽ ይድረቅ፣
ጥርስሽ ከሽፋኑ - እንደ ጥጥ ይፈልቀቅ፤
አለም አብራሽ ትፍካ - ሐዘን ይበል ፈቀቅ።
ጥርስሽ እዉነት እንጂ - ዉሸትን መች ያዉቃል፣
ፈገግታሽ ጉድ አለዉ - አድማሱን ያደምቃል፤
ሀዘን ጭንቀት ከስሞ - የትም ይደበቃል፤
አንዴ የሳቅሽዉ ሳቅ እንኳን ለኔ ቀርቶ ለዘመን ይበቃል።
......እናት አለሚቱ......
ፈጣሪም ሲያልቀዉ - የእናትነትሽን ገድ፤
ያከበረሽ እንዲያልፍ ከእግርሽ ስር አኖረዉ የጀነትን መንገድ።
✍Fu--ad
.
.
.
አለም ነበር ፍቅርሽ - ያልገለጡት ሚስጥር፣
ኮከብ ነበር ፍቅርሽ - ሚያስቸግር ለቁጥር።
ስላለሽኝ ነበር - ያማረዉ ህይወቴ፣
ስላለሽኝ ነበር - የፀናዉ ጉልበቴ።
.
.
ነበር ምን ይጠቅማል?
በይቅርታ ታምኖ - ፍቅር ካልዘለቀ፣
...እ ን ደ ተ ዋ ደ ድ ን...
...እ ን ደ ተ ፋ ቀ ር ን...
...የእድሜያችን ጀንበሩ ካላዘቀዘቀ።
✍Fu--ad
Join & share
? ? ?
@FuadPoems
@FuadPoems
@FuadPoems
.............ነይ በሏት ግድ የለም........
ከነጎደችበት - ከሩቁ ሀገሯ፣
ተለማመኑልኝ፣ይሁንብሽ በሏት በሁለ ነገሯ።
በመንደር በአድባሩ - በቦረቅነዉ ጊዜያት፣
በወዲያ በወዲህ ባሰባጠርናቸዉ የፍቅር ሆሄያት።
በአመሻሹ ድባብ - ባለፍንበት መንገድ፣
ባንቀጠቀጥነዉ ዛፍ - በፍቅራችን ሞገድ።
.............ነይ በሏት ግድ የለም......
በበአሉ መፅሀፍ - አብረን በገለጥነዉ፣
በድሮዉ ፍቅራችን - ከአድማስ ባሻገርነዉ።
በጥላሁን ዜማ - በእኩል አፍ ባዜምነዉ፣
ነይ በሏት ትምጣልኝ - መለያየት ሞት ነዉ።
.............ነይ በሏት ግድ የለም......
በታች ቆላይቱ - በአስያ ጨብራሪት፤
በልብ ወዳጅቱ - በአያ ሙሌ ክብሪት።
በሎሬት ፀጋየ - በሰላዉ ብዕሩ፣
በፃፋቸዉ ግጥሞች-
ባነበነብናቸዉ ቁጭ ብለን ከአድባሩ፣
አብረን ዝም ባልነዉ - ዝም ሲል መንደሩ።
.............ነይ በሏት ግድ የለም......
ናፍቆቴን ንገሯት - መክሰም መገርጣቴን፣
በመሄዷ ማግስት - ከመኖር መዉጣቴን፤
ነይ በሏት ግድ የለም - ትምጣ ትፈዉሰኝ፤
ትቢያየን አራግፋ - በፍቅሯ ታንግሰኝ።
......ነይ በሏት.........
✍Fu--ad
Join and share
???
@FuadPoems
@FuadPoems
@FuadPoems
ፍትህ እንድትነግስ - በደል እንዲቀበር፣
እኛዉ በምርጫችን - ዳኛ ሹመን ነበር።
ግን....
ማን ፍትህ አገኘ - ማን ተክሶ ተኛ?
ታዛቢዉ አድር ባይ - ዳኛዉ ሀሰተኛ!!!
✍Fu--ad
ለዛ ገፅ አምላኪ - ልብ ለማይደንቀዉ፣
ከመፅሀፍ በላይ - ሽፋን ላስጨነቀዉ፤
ይህንን ንገረዉ.....
የጥፍጥና ልኩ - በዉበት ቢ'ሰላ፣
እንቧይ ተዘንግቶ - ሎሚ ባልተበላ!!!
✍Fu--ad
.
.
ያየሽኝ እንደሆን - በጊዜዉ መነፀር፤
በዳ'ዮ ወፍራም ነዉ - ከኔ ሲነፃፀር፤
እጄም የኔ ያንሳል - ከሱ እሩብ አይደርስም፤
አፍ የሚይዝ ጉርሻ - ጠቅልሎ አያጎርስም።
እናልሽ ወዳጄ...
በደሌን አስረዳሁ - ዳኛዉ ፊት ቀርቤ፤
ደም እንባ እያነባሁ - ፍትህን ተርቤ።
ዳሩ ምን ያደርጋል....
መክሳቴ ነዉ መሰል - አላግባብ አስቀጣኝ፣
በዳዮ ቢወፍር ዳኛዉ - ፍርድ አሳጣኝ።
✍Fu--ad
Join and share
????
@FuadPoems
@FuadPoems
.
.
ትዝ ይልሻል ትላንታችን - እኔና አንቺ ያሳለፍነዉ?
ምድርን ትተን ከፍ ብለን-በፍቅር አክናፍ የከነፍነዉ፤
ትዝ ይልሻል ያረፍንበት? አረንጓዴዉ ድልድል ሜዳ፤
እንዳልፈታዉ ያሰርሽበት - ያስገባሽኝ የቃል እዳ!
.
.
እኔ ለአፍታም አይ'ረሳኝ - ፊቴ መጥቶ ይደቀናል፤
ቁጭት ሆዴን እየበላኝ - እንባ ከአይኔ ይከደናል፤
ያዘነ አይኔን ስጨፍነዉ - ቃል ይረግፋል ከእንባየ እኩል፤
የኔን ካልሽኝ ታምሜያለሁ - ግን እንዴት ነዉ ባንቺ በኩል?
✍Fu--ad
.
.
.
ሀዘኗ በዝቶ እንባ ስታፈስ ሲሸሿት ከርመዉ፤
ለአፍታ ብት'ስቅ
ከበዋት ቆሙ ከላይ ባደላት ዉበት ተገርመዉ።
ሳቋን ብቻ አይተዉ የተሰለፉት ከበር እስከበር፤
ቀርበዉ የልቧን አይተዉት ቢሆን ምን ሊሉ ነበር?
✍Fu--ad
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 год, 6 месяцев назад
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 месяц назад
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 недели, 1 день назад