አል ፉርቃን የፈትዋ ቻናል

Description
?السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
?️ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ የተለያዩ የአህለል ሱናህ ወል ጀምዓ ዑለማዎች እና ዱዓቶች ፈትዋ የሚለቀቅበት ነው።
?ቀደምት ዑለማዎች የሰጧቸው እና በዘመናችን የሚገኙ ዑለማዎችና ዱዓቶች የሚሰጧቸው ፈትዋዎች፣
↪️ወደ አማርኛ ተተርጉመው ይለቀቃሉ‼
"አል_ፉርቃን የፈትዋ ቻናል"
https://t.me/Al_furqan_fetwa_chanal
We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 Jahr, 7 Monate her

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 Monate her

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 1 Monat, 2 Wochen her

hace 3 semanas, 4 días
ስትቀኚ በልኩ ይሁን !

ስትቀኚ በልኩ ይሁን !

نصيحة ابن عثيمين رحمه الله للمرأة الغيورة

‌‌‌‌‏قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله تعالى :

من طبيعة المرأة أن تغار على زوجها ، وهذا دليل على محبتها له ..

ولكني أقول : الغيرة إذا زادت صارت غبرة وليست غيرة ، وتتعب المرأة تعباً شديداً  !!

لذلك أشير على المرأة أن تخفف من غيرتها ..

{ اللقاء الشهري [ ٣١ ] / ‎فتاوى_المرأة }

? ከሴት ልጅ ተፈጥሯዊ ከሆነው ባህሪዋ ውስጥ በባለቤቷ ላይ የምትቀና መሆኗ ነው። ይህ ለባለቤቷ ያላትን ውዴታ አመላካች ነው።

ነገር ግን እንዲህ እላለሁ ፦

? ቅናት ከልኩ ካለፈ አቧራ ይሆናል እንጂ ቅናት አይሆንም ! ሴቲቱም (በዚህ ሁኔታ ላይ ስትሆን) እጅግ በጣም መድከምን ትደክማለች !!!

? ለዚህም ሲባል ሴት ልጅ “የምትቀናውን ቅናት” ቀለል ያለ እንድታደርገው አመላክታታለሁ።

((አል-ሊቃኣ አሽ-ሸህሪ 31 አል-ፈታዋ ሊል-መርዓት ))

((ኢማም ኢብን ዑሰይሚን))

https://telegram.me/Al_furqan_fetwa_chanal

... ኢስማኤል ወርቁ...

#قناة_أبي_خالد_الدعوية
https://t.me/AbuKhlid3320/54066

hace 3 semanas, 6 días
በካፊሮች መከራ መደሰት...

በካፊሮች መከራ መደሰት...

فتاوى الدروس

السؤال:

هل للمسلم أن يفرح بالمصيبة في بلد الكفار؟

ጥያቄ ፦

አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው በ"ካፊር" ሀገር ላይ የሚደርስ በሆነ "ሙሲባ" መከራ መደሰት ይቻልለታልን ?

الجواب:

يفرح لها، إذا كان فيها نفعٌ للمسلمين يفرح لها: قُلْ بِفَضْلِ اللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَ خَيْرٌ مِمَّا يَجْمَعُونَ 
[يونس:58]،

إذا كان شيء ينفع المسلمين: انهزم جيشهم، هداهم الله للإسلام؛ يفرح.

س: إذا كانت زلزلة مثلًا في بلدٍ كافرٍ؟

ج: يفرح؛ لأنها قد تكون موعظةً، قد تكون فيها هداية.

فتاوى الدروس

لسماحة الشيخ الشيخ عبد العزيز بن باز

መልስ ፦

በዚህ ነገር ይደሰታል። በዚህ ነገር ውስጥ ለሙስሊሞች ጥቅም ካለው ይደሰታል።

(( قُلْ بِفَضْلِ اللَّهِ وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَ خَيْرٌ مِّمَّا يَجْمَعُونَ ))

«በአላህ ችሮታና በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡

(አል-ዩኑስ(58))

አላህ ወደ “ ኢስላም ” ይምራቸውና የከሃዲያን ሰራዊት መሸነፉን የመሰለ ሙስሊሞችን የሚጠቅም ነገር ሲሆን መደሰት ይቻላል።

ጥያቄ ፦

ለምሳሌ ፦ በካፊሮች ሀገር የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት መደሰትስ...?

መልስ ፦

አዎ ! ይደሰታል። ምክንያቱም ፦ በእርግጥም ይህ ነገር መከሰቱ ለእነሱ (ለከሃዲያኖች) መገሰጫ (ምክር) ሊሆናቸው ይችላል።እንዲሁም ምራቻም ሊሆናቸው ይችላል።

( ፈታዋ ወዱሩስ )

(( ኢማም ኢብን ባዝ ))

https://telegram.me/Al_furqan_fetwa_chanal

... ኢስማኤል ወርቁ...

hace 4 semanas, 1 día
ረጀብ የተለየ ነገር የለውም !

ረጀብ የተለየ ነገር የለውም !

قال الإمام ابن العثيمين رحمه الله ‼️

#ليس لشهر رجب ميزة عن سواه من الأشهر الحرم، ولا #يخص، لا بعمرة، ولا بصيام، ولا بصلاة، ولا بقراءة قرآن، بل هو #كغيره من الأشهر الحرم، وكل الأحاديث الواردة في فضل الصلاة فيه، أو الصوم فيه، فإنها #ضعيفة، لا يبنى عليها حكم #شرعي.

المصدر: اللقاء الشهري [32]

የረጀብ ወር ከተቀሩት "ሸህሩል ሑሩም" (የተከበሩት  ወራቶች) የሚለይበት ነገር የለውም ! በዑምራ ፣ በፆም ፣ በሶላት ፣ ቁርኣን በማንበብ አይለይም። እንደሁም "ረጀብ" እንደሌሎቹ (የተከበሩ ወራቶች) ናቸው።

ሁሉም በረጀብ ወር ውስጥ የሚሰገድ ሶላትና የሚፆም ፆምን ብልጫ አስመልክቶ የመጡ ሐዲሶች “ደዒፍ” ናቸው።

? በእነዚህ ሐዲሶች ሸሪዓዊ ሑክም አይገነባም !!!

((አል-ሊቃኣ አሽ-ሸህሪ 32))

((ኢማም ኢብን ዑሰይሚን))

https://telegram.me/Al_furqan_fetwa_chanal

... ኢስማኤል ወርቁ...

#قناة_أبي_خالد_الدعوية
https://t.me/AbuKhlid3320/54000

hace 4 semanas, 1 día
"ጁምዓ" "ጀምዓ" እና "ዒድ ሶላት" ለሴቶች...

"ጁምዓ" "ጀምዓ" እና "ዒድ ሶላት" ለሴቶች...

وقال شيخ الإسلام ابن تيمية في [المجموع] (6|458، 459) : فقد أخبر المؤمنات أن صلاتهن في البيوت أفضل لهن من شهود الجمعة والجماعة إلا العيد، فإنه أمرهن بالخروج فيه - ولعله والله أعلم.

- لأسباب: الأول: أنه في السنة مرتين، فقبل بخلاف الجمعة والجماعة. الثاني: أنه ليس له بدل، بخلاف الجمعة والجماعة فإن صلاتها في بيتها الظهر هو جمعتها. الثالث: أنه خروج إلى الصحراء لذكر الله، فهو شبيه بالحج من بعض الوجوه؛ ولهذا كان العيد الأكبر في موسم الحج موافقة للحجيج. انتهى

? ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ መጅሙዓ አል-ፈታዋ 6ኛው ጥራዝ ገፅ 458-459 ላይ እንዲህ ይላሉ ፦ “ ነብዩ ﷺ ሙእሚን ሴቶች ጁምዓ እና ጀመዓ (የህብረት ሶላት) መስጅድ ከመሳተፍ እቤታቸው መስገዳቸ በላጭ እንደሆነ አጠንክረው ተናግረዋል። ነገር ግን የዒድ ቀን ሴቶች እንዲወጡ አዘዋል ፤ (ትክክለኛውን የሚያውቀው አላህ ሲሆን) ይህንን ያሉበት ምክንያት እንደሚከተለው ሊሆኑ ይችላል በሚል አውስተዋል ፦

1️⃣ በጁምዓ እና በጀመዓ ተቃራኒ "ዒድ" በዓመት ሁለት ጊዜ ስለሆነ መውጣታቸው ተቀባይነት አገኘ።

2️⃣ በጁምዓ እና በጀመዓ ተቃራኒ "ዒድ" ተለዋጭ የለውም። እቤቷ ዝሁር መስገዷ ለእርሷ ጁምዓን እና ጀመዓን ይተካላታል።

3️⃣ በአንዳንድ ሁኔታዎች አላህን ለማስታወስ ወደ ሜዳ መውጣት ከሐጅ ጋር ያመሳስለዋል። ለዚህም ነው ታላቁ ዒድ ሐጃጆችን በመግጠም በሐጅ ሰዓት እንዲሆን የሆነው።

(( ሸይኸል ኢስላም ኢብን ተሚያ ))

https://telegram.me/Al_furqan_fetwa_chanal

... ኢስማኤል ወርቁ...

hace 3 meses, 1 semana
***⛓***ባሏ እንደማይፈልጋት አወቀች !

ባሏ እንደማይፈልጋት አወቀች !

س: إذا رأت المرأة من زوجها عدم رغبة فيها وهي ترغب البقاء معه، فكيف تعالج الموقف؟ 

ጥያቄ ፦

? ሴት ልጅ ባሏ እንደማይፈልጋት ካወቀችና እርሷ ከእሱ ጋር መቆየትን ብትፈልግ ምን አይነት ዘዴን ትጠቀማለች ?

ج: يقول الله تعالى: {وَإِنِ امْرَأَةٌ خَافَتْ مِنْ بَعْلِهَا نُشُوزًا أَوْ إِعْرَاضًا فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا أَنْ يُصْلِحَا بَيْنَهُمَا صُلْحًا وَالصُّلْحُ خَيْرٌ} [النساء: 128]

قال الحافظ ابن كثير: إذا خافت المرأة من زوجها أن ينفر عنها، أو يعرض عنها فلها أن تسقط عنه حقها أو بعضه من نفقة أو كسوة أو مبيت أو غير ذلك من حقوقها عليه، وله أن يقبل ذلك منها، فلا حرج عليها في بذلها ذلك له، ولا حرج عليه في قبوله منها؛ 
ولهذا قال: {فَلَا جُنَاحَ عَلَيْهِمَا أَنْ يُصْلِحَا بَيْنَهُمَا صُلْحًا وَالصُّلْحُ خَيْرٌ} [النساء: 128]
 أي: خير من الفراق...ثم ذكر
قصة سودة بنت زمعة رضي الله عنها، وأنها لما كبرت وعزم رسول الله صلى الله عليه وسلم على فراقها صالحته على أن يمسكها، وتترك يومها لعائشة، فقبل ذلك منها، وأبقاها على ذلك. انظر [تفسير ابن كثير] 
(2 / 406) الطبعة الأخيرة. 

تنبيهات على أحكام تختص بالمؤمنات.

መልስ ፦

አላህ እንዲህ ይላል፦

(( “ ሴትም ከባልዋ ጥላቻን ወይም ፊቱን ማዞርን ብታውቅ በመካከላቸው መስማማትን ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኀጢአት የለም። መታረቅም መልካም ነው። ” )) (አን-ኒሳእ፡ 128)

አል ሐፊዝ ኢብኑ ከሲር እንዲህ ይላሉ ፦ « ሴት ልጅ የባሏን መኮብለል ወይም ፊቱን ማዞሩን የምትፈራ ከሆነ በእርሱ ላይ ያለበትን እንደ ማልበስ ፣ መቀለብ እና እርሷ ጋር ማደርን (የመሳሰሉ) ሐቆች በሙሉ ወይም በከፊል መተው ትችላለች። እሱም ይህን መቀበል ይችላል። በሁለቱም ላይ ችግር የለባቸውም ለዚህም አላህ እንዲህ ይላል ፦

(( “ በመካከላቸው መስማማትን ቢስማሙ በሁለቱ ላይ ኀጢአት የለም። መታረቅም መልካም ነው። ” )) (አን-ኒሳእ፡ 128)

ይህም ማለት ከመለያየት የተሻለ ነው። በተጨማሪም የሰውዳ ቢንቱ ዘምዓተ (ረዲየላሁ ዓንሃ) ታሪክን ጠቀሰ ፦ « እድሜዋ ገፍቶ ትልቅ ሴት ሆና የአላህ መልክተኛ ﷺ ከእርሷ መለያየት ሲፈልጉ እርሷ ግን ከእርሳቸው ጋር መቆየት እንደምትፈልግ እና እርሷ ስለ (ደከመች) የእርሷን ቀን ለዓኢሻ በስጦታ መልክ እንደለቀቀች ስትነግራቸው የአላህ መልክተኛም ﷺ 
የእርሷን መብት በመጠበቅ (ቢደክማትም) ከእሳቸው ጋር እንድትቆይ አድርገዋል። ይህን ታሪክ ኢብኑ ከሲር ጥራዝ 2 ገፅ 406 ላይ አስፍሮታል።

(ተንቢሃቱ ዓላ አሕካሚ ተኽተሱ ቢል ሙእሚናት)

((( ታላቁ ዓሊም መዓሊ ሼይኽ ሷሊሕ ቢን ፈውዛን ቢን ዐብደላ አል-ፈውዛን  )))

https://t.me/Al_furqan_fetwa_chanal

...ኢስማኤል ወርቁ...

hace 3 meses, 2 semanas
***⚠️*** ተፈጥሮን መቃረን ነው !!

⚠️ ተፈጥሮን መቃረን ነው !!

«‏المرأة صناعتها بيتها، تبقى في بيتها تصلح أحوال زوجها، و أحوال أولادها و أحوال البيت هذه وظيفتها، أمّا أن تشارك الرِّجال بالكسب و طلب ‏الرزق فهذا خلاف الفِطرة و خلاف الشَريعة».

? ~ #‏شَرح رياض الصّالحين للشيخ محمد بن صالح العثيمين رحمه الله ١٤٠/٣

⚠️ « ሴት ልጅ ተግባሯ በቤቷ ነው። በቤቷ ትቆያለች ! የባለቤቷን ሁኔታ ታስተካክላለች። የልጆቿንም ሁኔታ ታስተካክላለች። በቤቷ ውስጥ ያለውን የስራ ድርሻዋን ትወጣለች።

? ወንድ ልጅን በገቢ ምንጭና ሲሳይን ፈልጎ በማምጣት ላይ መጋራት ከሆነ ይህ ተግባር የተፈጥሮን መቃረንና የእስልምና ሸሪዓን መፃረር ነው‼️

((( ታላቁ ኢማም መሐመድ ሷሊሕ ኢብን ዑሰይሚን)))

https://t.me/Al_furqan_fetwa_chanal

... ኢስማኤል ወርቁ ...

hace 3 meses, 2 semanas
***?*** የጎረቤት ሐቅ...

? የጎረቤት ሐቅ...

ለጎረቤት ሐቅ አለው !

? ወደ እርሱ መልካም መዋል ግዴታ ነው !

? (ጎረቤትን) ከማስቸገር መቆጠብ ግዴታ ነው !

? በእርግጥም ከቤቱ ፊት ለፊት የቆሻሻ መሰብሰቢያ ዕቃ ማስቀመጥ (ጎረቤትን) ከማስቸገር ውስጥ ይገባል። እንዲሁም በተለያዩ የሚድያ ማሰራጪያ ድምፆችን መልቀቅ ጎረቤት ከማስቸገር ውስጥ ይካተታል።

? ባጠቃላይ ሁኔታ ጎረቤትን ከማስቸገር መቆጠብ ግዴታ ነው !

? ይህ ከመሆኑ ጋር ስጦታን በማበርከት ፣ በመምከር ፣ በመልካም በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከል እንዲሁም በሌሎችም የመልካምነት መገለጫ በሆኑ ነገሮች መጎራበት ተገቢ ይሆናል !!!

((ኢማም ኢብን ባዝ))

https://telegram.me/Al_furqan_fetwa_chanal

… ኢስማኤል ወርቁ …

We recommend to visit

Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies

አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films

ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249

Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films

Last updated 1 Jahr, 7 Monate her

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @Aymu_xo

Last updated 2 Monate her

╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች

? ውጤቶች

? የጨዋታ ፕሮግራሞች

? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ

? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

Owner:- @hackersolo0⭐️

Last updated 1 Monat, 2 Wochen her