Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 9 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 2 months ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 3 months, 3 weeks ago
"እየጠሉ ማግኘት"
አለ ወዶ ማጣት ፣ አለ ጠልቶ ማግኘት
የሚሆን አልሆን ሲል ፣ የማይሆን መመኘት
ቀጥ ያለ ሲታጣ
መመልመል ጎባጣ
አለ ጠልቶ ያገኘ ፣ አለ አፍቅሮ ያጣ፡፡
አለ ቡዙ ብዙ .. .
ምንም ብርቄ አይደለም !
ኖሬ ያለፍኩት ነው ፣ ስንኖር ያየሽኝ
ወድጄሽ አጣሁሽ ፣ ጠልተሽ አገኘሽኝ፡፡
ብኖር የለሁሽም ፣ ባትኖሪም አለሽኝ!!!
✍በላይ በቀለ ወያ
አህያ ሁን አለኝ፡አህያ ሆንኩለት
አሰሱን ገሰሱ ፡ እንድሸከምለት፡፡
መጋዣ ሁን ብሎ፡ ፈረሱ አደረገኝ
በየዳገቱ ላይ፡ ወስዶ እሚጋልበኝ፡፡
እንጃ ግን ሰሞኑን፡ በግ ነህ ተብያለሁ
ሊያርደኝ ነው መሰለኝ፡ አሁን ፈርቻለሁ
✍ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
እንደአለመኝነታችን መድኀኒታችንን በግርግም ተቀበልነው ነገር ግን በሽተኞችም ነን እና ከእልፍኝ ሰገነታችን ተጉዘን ወደ ግርግሙም አመራን የመረጥነው በማይበጀን አለም ላይ ብንኖርም መድኀኒታችን ግን እኛን መርጦ አምላካችን ሰው ሆነ
ረቂቁ ቃል ከንጽህት ድንግል ማርያም ግዘፈ ስጋን ነስቶ ሰው ሆነ ??????????????
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረስዎ
"ወንበሩ ሰው አለው?"
እሷ
"ወንበሩ ሰው አለው?"
እኔ
"ነበረው"
(የለም የለም ውሸቴን ነው)
እመጣለሁ ካለች
ዘመን ያስቆጠረች፡፡
ደርሻለሁ ብላኝ
መጠበቅ የበላኝ
አይሃለሁ ያለች
ልክ ነሽ ሰው አለች፡፡
(ነበረች)
እሷ
"ወንበሩ ሰው አለው?"
እኔ
"ነበረው" እንዳልል
"አለውም" እንዳልል
ቁጭ በይ እንዳልል
ያንገበግበኛል ቃሏን እንደመጣስ
ግራ ገባኝ እኮ ግን ደሞ ብትመጣስ
ግን ደግሞ የለችም
መጣለሁ በላኝ ይኸው አልመጣችም....
ወንበሩ ሰው አለው
እንጃ
ቀርታለች እላለው
እንጃ
መንገድ ሰነከላት
እንጃ
ወይ ሌላ ከጀላት
እንጃ
መስከረሟ ጠባ
እንጃ
እግዜር መሀል ገባ
እንጃ
ብቻ ወንበሩ ሰው...አለው
ብቻ ወንበሩ ሰው...የለው፡፡
መቀመጥ
ያውም ወንበር ይዞ
ትመጣለች ብሎ
ሽንት እንኳ ቀዝቅዞ
መናፈቅ
ሳቅን ሲጠብቁ ስትቀር መነፍረቅ
መጎለት
ለመጣ ሰው ሁሉ ትመጣለች ማለት
መጠበቅ
እንደድሮ ፅሁፍ ላይታዩ መድመቅ
ነብዝዞ
ደብዝዞ
መገኘት
ሰውን ለመቀበል ራስን መሸኘት...
"ወንበሩ ሰው አለው?"
እንጃ..
✍ ኤልያስ ሽታኹን
ሀሳቤን ተጋርተሽ እኔ ተቃውሜ
በሀዘኔ ስቀሽ ሀዘንሽን ታድሜ
በለቅሶሽ ታክሜ
ሲያሻሽ መንዝረሽኝ
ፈልገሽ ሽጠሽኝ ያንች ባርያ ሁኜ
በደስታዬ ታመሽ በፍቅርሽ ታምሜ
ሁነሽ በሽታዬ ሁኜ መድሀኒትሽ
ደስታ ስትሰጭኝ ሁኜብሽ ጭንቀትሽ
በፍቅሬ ሲኦል ውስጥ በልብሽ ገነት ላይ
ከብረሽ ትኖሪ ዘንድ በሀሳቤ ሲሳይ
ውሰጅ ህሊናዬን ልሾም በሀሳብሽ
ንገሺ በልቤ ልንገስ በእንቁ ልብሽ
ድክመትሽ ሁኜብሽ
ከለላዬ ሁነሽ ሁኜልሽ ከለላ
ግራ ብቻ ሳይሆን ቀኝም ፊትም ኋላ
እንዲገባኝ አርጊ
ባምሮዬ አዳራሽ በቀንና ሌሊት ሁሌ እንድታበሪ
አንደ የኖህ ርግብ
የፍቅሬን ለምለም ሳር በልቤ ሰማይ ላይ ይዘሽ እንድትበሪ
የፍቅራችን ገመድ ፊትሽ ተንበርክኬ ላድርገው ጣትሽ ላይ
እንድታስታግሽልኝ የስትንፋሴን ስቃይ
አብረን እንድንኖር የሰው ሆነች ብሎ ሆዴም እንዳይባባ
እባክሽን አግቢኝ ቀኝ ብቻም ሳይሆን ግራም እንጋባ
አግባኝ እንጋባ ግራ እንጋባ
✍ Ŧəđđ¥ ቡዜ
ታላቅ የምሥራች ለግእዝ ቋንቋ አፍቃርያን በሙሉ።
እንሆ ታላቅ ስጦታ "ሙዳየ ግእዝ ቍጥር ኹለት" በአራት ምዕራፍ የተሰናዳች ድንቅ የግእዝ ሙዳይ በኅትመት ላይ የምትገኝ ስትኾን በቅርብ ቀን በገበያ ላይ እንደምትውል ስናበሥራችኹ በታላቅ ደስታ ነው። ስለዚኽ 'ንዑ ኀቤየ ኦ ፍቍራነ ግእዝ' እያለች አንባብያንን ትጣራለችና "እመት" እንድንላት ትሻለች።
የመጽሐፏ ደራሲ/ጸሓፊ፦
ግዛቸው ደጀኑ መኰንን (በግእዝ ቋንቋ የኹለተኛ ድግሪ ምሩቅ እና ግእዝን በርቀት የልሳነ ግእዝ መምህር)
@geezachew12
የመጽሐፏ ዋና አከፋፋይ፦
ኤልያስ
@EliasSourcing
☎️ +251978109058
እኔ መጽሐፏ በእጄ እስክትገባ ጓጉቻለኹ። እናንተስ⁉️****
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 9 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 2 months ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 3 months, 3 weeks ago