Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago
"መስጂዱ በመኖሩ የውሃ ችግራችንን ቀርፎልናል"
▪ በለገጣፎ ለገዳዲ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮች
- የክርስትና እምነት ተከታዮች የመሰከሩለት በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ የሚገኘው ሱመያ መስጂድ
- ሀሩን ሚድያ ሕዳር 19/2017
በለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ ህጋዊ ካርታ ያለው ሱመያ መስጂድ በፍርድ ቤት መስጂዱ እንዲነሳ ያለአግባብ ውሳኔ መሰጠቱን አስመልክቶ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ዘገባ መስራታችን ይታወሳል።
ሀሩን ሚድያ በለገጣፎ ለገዳዲ የሚኖሩ የክርስትና እምነት ተከታዮች ከመስጂዱ ምን አገልግሎት እያገኙ እንደሚገኝ ጠይቀን በምላሻቸው ሱመያ መስጂድ አካባቢው ላይ ውሃ ባለመኖሩ የከርሰ ምድር ውሃ በማውጣት ያለምንም ክፍያ ከግቢው ውጪ ባንቧ በመዘርጋት የአካባቢው ነዋሪዎችን የውሃ ችግር እየቀረፈ ይገኛል ብለዋል።
በለገጣፎ ለገዳዲ የሚገኘው ከ2014 ዓ.ል ጀምሮ ህጋዊ ካርታ ያለው ሱመያ መስጂድ ያለምንም የእምነት ልዩነት በደንበል ጣፎ ወረዳ ሮዚታ ሪል ስቴት አካባቢ ለሚገኙ ነዋሪዎች የነፃ ውሃ በማቅረብ የአካባቢውን የውሃ ችግር እየፈታ እንደሚገኝ ነዋሪዎቹ የገለፁ ሲሆን ይበልጥ ተጠቃሚዎቹ ደግሞ የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ሱመያ መስጂድ አስመልክቶ አንዳንድ የመስጂዱ መኖር ያላስደሰታቸው አካላት መስጂዱ እንዲነሳ ጥያቄ አቅርበው የነበረ ቢሆንም መስጂዱ ህጋዊ ነው አይነሳም በሚል ከተማ አስተዳደሩ ገልፆ አንደነበር ኮሚቴዎቹ ገልጸዋል።
በ2001 ዓ.ል ካሳ የወሰደ አርሶአደር መስጂዱ 1000 ካሬ ሜትር ወስዶብኛል በሚል ክስ መስርቷል።
ፍርድ ቤት በነበረው ክርክርም የመስጂዱ ካርታ ህጋዊ መሆኑንና ለገበሬው ካሳ መከፈሉን በማስረጃ ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ መስጂዱ እንዲነሳ በሚል ያለአግባብ ውሳኔ መወሰኑን የመስጂዱ ኮሚቴዎች ተናግረዋል።
የመስጂዱ ኮሚቴዎች የመስጂድ ጉዳይ የህዝብ ስለሆነ ለሸገር ከተማ አስተዳደርና ለለገጣፎ ለገዳዲ ክፍለከተማ አስተዳደር መስጂዱን በተመለከተ አስተዳደራዊ ዉሳኔ እንዲሰጡ መጠየቃቸውን ለሀሩን ሚድያ ገልፀዋል።
© ሀሩን ሚድያ
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አመራሮች የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት በመገኘት የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መርሀግብር አከናወኑ!
_ሀሩን ሚድያ ሕዳር 19/2017፤አዲስ አበባ
በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዘጋጅነት “ትብብርና አብሮነትን ማጎልበት ለዘላቂ ሰላም" በሚል መሪ ቃል የጉባኤው የቦርድ አመራሮች በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በመገኘት የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መረሃ ግብር አከናውኗል።
የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዝደንት እና የጉባኤው ም/የቦርድ ሰብሳቢ ሼህ ሱልጣን ሀጂ አማን ኤባ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር እንደዚህ አይነት ጉብኝት እና የልምድ ልውውጥ መድረክ ያለንን ግንኙነት የበለጠ ያጠነክረዋል ብለዋል።
የመረሃ ግብሩን ዋና አላማ ያብራሩት የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ የአዲስ አበባ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ በሃይማኖት ተቋማት መከካል የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቶቻቻንን ማጠናከር በመሆኑ የጉባኤው የቦርድ አባላት በየእምነት ተቋማት በመገኘት የጉብኝትና ልምድ ልውውጥ መርሀግብር እያካሄዱ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የጉባኤው የቦርድ ሰብሳቢ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ በበኩላቸው አሁን ያለው ትውልድ መገፋፋትን በመተው አንድነቱን እንዲያጠናክር ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
በመረሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ዋና ፀሐፊ ሼህ ሁሴን በሽር ም/ቤቱ ከተመሰረተበት ጀምሮ በመዲናችን አዲስ አበባ ያከናወናቸውን እና እያከናወናቸው ያሏቸውን መንፈሳዊ እና ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን በተመለከተ የም/ቤቱን ልምድ ለአባቶች አቅርበዋል።
የልምድ ልውውጡ ተሳታፊ የሆኑ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤን ወክለው የተገኙ አባቶች በአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባዩት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው ለትውልዱ ይሄን ሰላማዊ ግንኙነት አጠናክሮ ማስተላለፍ እንደሚያስፈልግ በመጥቀስ እስከታችኛው መዋቅሮች ድረስ በመውረድ ሥራዎችን ለትውልድ ማስተላልፍ እንደሚገባ ተናግረዋል።
“ትብብርና አብሮነትን ማጎልበት ለዘላቂ ሰላም በሚል መሪ ቃል” በሃይማኖት ተቋማት መከካል የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቶችን ለማጠናከር የሚደረገው ጉብኝት እና ልምድ ልውውጥ የዛሬው ለሁለተኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን ከዚህ ከቀደም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉብኝት እና ልምድ ልውውጥ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን በቀጣይም በሌሎች የጉባኤው አባል ቤተ ዕምነት የሚከወናወን መሆኑ ተገልጷል።
_ሀሩን ሚድያ በዝግጅቱ በመገኘት ያጠናቀርነውን የቪድዮ ዝግጅት በአላህ ፍቃድ ወደናንተ ሚያደርስ ይሆናል።
©ሀሩን ሚድያ
ለሀላባ ዘመናዊ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም ግንባታ ፈረሱን ለሰጠው አርሶ አደር ነዋሪነቱን ዱባዩ ካደረገ ባለሀብት ሌላ ከፍ ያለ የፈረስ በስጦታ ተበረከተለት!
- ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ ፣13/2017
ለሀላባ ዘመናዊ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም ግንባታ ፈረሱን ለሰጠው አርሶ አደር በዱባዩ ዲያስፖራ አ/ሹኩር ናስር ሌላ ከፍ ያለ ፈረስ በስጦታ ተበረከተለት።
ነዋሪነቱ በዱባይ ያደረገው ወጣት አብዱሽኩር ናስር በክልሉ ርዕስ መስተዳደርና አቶ እንዳሻው ጣሰውና በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሂዲን ሁሴን የተመራው ልዑክ ለስቴዲየሙ ገቢ ማሰባሰቢ ዱባይ በሄዱበት ወቅት ይሄን ታሪክ በመስማቱና ህዝቡ ለልማቱ ያለው ቁርጠኝነት ውስጤን ስለነካኝ በራሴ ለስቴዲየሙ ቃል ከገባሁት ገንዘብ በተጨማሪ ለዚህ የልማት አርበኛ አርሶ አደር በክብር ለመሸለም ቃል ገብቼ ቃሌን በዛሬው እለት የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሂዲን ሁሴንና ሌሎች አስተባባሪ አካላት በተገኙበት ፈርሱን አስረክቢያለው በማለት ገልጿል።
አያይዞም ወጣቱ በዚህ ፕሮጀክት ላይ ሁሉም ልማት የሀላባ ወዳጅና ተወላጅ ፕሮጀክቱ እስኪጠናቀቅ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።
የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሂዲን ሁሴን በበኩላቸው ይህ ወጣት ዲያስፖራ ያደረገውን ድጋፍ አድንቀው በሀላባ ህዝብ ስም አመስግነዋል አስተዳዳሪው ሁሉም ህዝብ ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ንቁ ተሳትፎ ማድረጉን አውስተው አሁንም እስከመጨረሻው ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
- ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ ስፍራው ተገኝቶ ያጠናቀረውን የቪዲዮ ዘገባ በተከታይ ወደናንተ የሚያደርስ ይሆናል።
© ሀሩን ሚዲያ
የሊባኖስ ጋዜጠኛ የሆነችው ሶኪያና መንሱር እስራኤል በፈፀመችው የአየር ድብደባ ከነ ቤተሰብዋ መገደሏ ተገለፀ
- ሀሩን ሚድያ ህዳር 6/2017
የሊባኖስ ጋዜጠኛ ሶኪያና መንሱር ካውታራኒ በደቡብ ሊባኖስ ውስጥ በሲዶን አቅራቢያ በሚገኘው ባለ ሶስት ፎቅ የመኖሪያ ሕንፃ ላይ እስራኤል በፈፀመችው የአየር ድብደባ ከሁለት ልጆቿ እና ከሌሎች የቤተሰቧ አባላት ጋር መገደላቸው ተገልጿል።
የሊባኖስ ፕሬስ አርታኢዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ኮሴፊ ጥቃቱን በማውገዝ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ነው በማለት አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችን፣ የአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት፣ የአረብ ጋዜጠኞች አጠቃላይ ፌዴሬሽን እና ዩኔስኮ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስበዋል።
ጆሴፍ ኮሴፊ በይፋዊው ብሔራዊ የዜና ወኪል በኩል በሰጠው መግለጫ “እስራኤል እየፈፀመች ያለው የቦምብ ድብደባ በሰላማዊ ሰዎች እና በታጋዮች መካከል ምንም ልዩነት የሌለው ነው ያለ ሲሆን፣ ሁሉንም ህግ፣ ቻርተር እና ስምምነት ይጥሳል እንዲሁም የሚነገረው የእሳት እና የደም ቋንቋ ብቻ ነው” ብሏል።
እንደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃ ህንፃው የብራዚል ተወላጅ የሆኑትና በሊባኖስ በአቶሞቲቭ ስራ ላይ የተሰማሩቱ የጎሰን ቤተሰቦች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በአየር ድብደባው ህንፃው ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን ስምንት ሴቶች እና አራት ህፃናትን ጨምሮ 15 ሰዎች ሲሞቱ 12 ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።
የሊባኖስ ፕሬስ አርታኢዎች ማህበር እንደገለጸው የሶኪያና መንሱር ሞት ተከትሎ የእስራኤል-ሃማስ ግጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተገደሉትን የሊባኖስ ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሰራተኞች ቁጥር ወደ 12 መድረሳቸውን ነው የገለፀው።
© ሀሩን ሚድያ
በመስጅድ እጦት ምክንያት ሰላት በጀመዓ ለመስገድ እንዲሁም ልጆቻችን ቁርአን ለማስቀራት ተቸግረናል ሲሉ በኮዬ ፌጨ የገንዳ ጡሬ አካባቢ ሙስሊሞች ገለፁ
- ሀሩን ሚዲያ፥ ሕዳር 5/2017
በሸገር ከተማ አስተዳደር ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ በዴሳ ወረዳ ገንዳ ጡሬ የሚኖሩ ሙስሊሞች ለአመታት የዘለቀ የመስጂድ ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም ምላሽ ባለማግኘታቸው የጀመዐ ሰላት የሚሰግዱበትም ሆኖ ልጆቻቸውን ኢስላማዊ ትምህርት ለማስተማር እንደተቸገሩ ለሀሩን ሚዲያ ገልፀዋል።
የኮዬ ፈጩ ክፍለ ከተማ በርካታ ሙስሊሞች የሚኖርበት በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ምክንያቶች በአካባቢው የሚኖሩ ሙስሊሞች ብዙ ቢሆንም ያለው መስጂድ እንደ ክፍለ ከተማ አንድ ብቻ በመሆኑ በመስጅድ እጦት እተሰቃዩ እንደሚገኙ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
በጊዜያዊነት የግለሰብ ቤት ተከራይተው ከ200 በላይ የሚሆኑ ልጆች ቁርአን እንዲማሩ የተደረገ ቢሆንም ከዛም ቢሆን ልቀቁ በመባላችን ልጆቻችን ሊበተኑብን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ከወረዳ እስከ ክልል የመስጅድ ጥያቄ አቅርበናል የሚሉት ነዋሪዎቹ ነግር ግን ምላሽ አላገኘንም በዚህ ምክንያት ባሳለፍነው ረመዳን በመኪና ማቆሚያ ፓርክ ሰግደን አሳልፈናል ሲሉ ገልፀዋል።
ነዋሪዎቹ ከግለሰብ ቦታ ለመግዛት ከዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ መጠየቃቸውን አንስተው ሙስሊሙ ማህበረሰብ በመረባረብ ልጆቻችን ከመበተን ይታደግልን ሲሉ ተማፅነዋል።
- ሀሩን ሚዲያ በቦታው በመገኘት ያጠናቀረውን የቪዲዮ ዘገባ በቅርቡ ወደናንተ ያደርሳል!
(ለአካባቢው ሙስሊም ቦታ ለመግዛት ድጋፍ ለማድረግ ከታች ያለውን አካውንት ይጠቀሙ
ንግድ ባንክ 1000620816756
የአካውንት ስም አርቀም መስጅድ
ስልክ ፦+251911274383
© ሀሩን ሚዲያ
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 5 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @MKHI7
Last updated 4 days, 15 hours ago
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
#ኢትዮጵያ
ያግኙን +251913134524
Last updated 1 week, 5 days ago