Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Abu Mahira- ንጽጽራዊ አስተምህሮ መድረክ

Description
«ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ መጠየቅ ትችላላላችሁ። ምላሹን በቻናል ይከታተሉ። 👇👇👇

@AbuMahira5


«ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡፡ (12:108)

Facebook ፦https://www.facebook.com/HarunYahya6/
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago

1 year, 1 month ago

{ وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ }
«እኔ ለእናንተ በእርግጥ መልካም መካሪያችሁ ነኝ» ሲልም አማለላቸው፡፡ (7/21)

«ለአንተ አዛኝ እና ጥሩ መካሪ መስሎ ለቀረበህ ሁሉ ሙሉ እምነትህን አትስጠው ምንም ማረጋገጫ የለህም።

«የምክርን ተንኮል ልባስማ ኢብሊስም ተላብሶታል። አደምን" ያሳሳተውና ከጀነት ያስባረረው ጥሩ አዛኝ መካሪ መስሎ ነውና።

«ኢብሊስ ለማታለል ሲመክር «የአመጽዋን ዛፍ» «የዘላለምን ሕይወት የምታኖር» ብሎ ስያሜዋን ቀየራት። ዛሬም በአታላዩ ምክሩ ሲያታልለን የነገሮችን ትክክለኛ ስያሜ ቀይሯቸዋል።

«አስካሪ መጠጥን፦ የነፍስ እርካታ የደስታ ምንጭ ሕሴት አድርጎ ሰይሞታል።

«ዝሙትና እርቃንነትን፦ ዘመናዊነትና የሥልጣኔ አርማ አድርጎ ሰይሞልናል።

«ጥሩ መካሪ የመሰለህ ሁሉ የጥሩ ልብ ባለቤት መሆን አይችልም። የነገሮች ስያሜና አቀራረብ የቱንም ያክል ቢለወጥም ትክክለኛ ባሕሪያቸውን ግን በፍጹም አይቀይርም።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago

«{ عَسَىٰ رَبُّنَآ أَن يُبۡدِلَنَا خَيۡرٗا مِّنۡهَآ}
«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን ነገር ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ (68/32)

«በሕይወትህ ባመለጡህ መልካም አጋጣሚዎች ሁሉ በቁጭት የተቃጠለችዋን ቀልብህን በዚህች በጌታህ ቅዱስ ቃል አፅናናት።

«የምትወደውን መልካም ሥራህን ባጣህ ጊዜ፣ የልበ-እምነት ወዳጅ ጓደኛህን መካከል መንገድ ላይ ከእጅህ ባመለጠህ ጊዜ፣ የንፍቅና ፊትን ሰጥቶህ ክቡር ደግ ሰው ነው ብለህ ባመንከውና ከጠበቅከው ተቃርኖ ባዶነቱን አሳይቶህ ባረጋገጥክም ጊዜ፣ በትርፍ ምኞት ተስፋ ሰንቀህ ባዶ በቀረህ ጊዜ.........

«ሁሉም አላህ ካንተ የወሰደው ነገር ሁሉ ሒክማ አለው ለሱ ብቻ ተወው። ለአንተ የተወልህ ነገር ሁሉ ደግሞ እዝነቱ ነው። በወሰደብህ ነገር ሒክማው ከተገለጸልህና ከደረስክበት አመስግን። ሒክማውን ካልደረስክበት ደግሞ መልካም ትግስትን ታገሥ።

«ነገሩ ሲከሰት የቱንም ያክል ልብህን ቢያቆስልህ እንኳ አብሽር የአላህ ቀደር ሁሉም ለአንተ ኸይር ብቻ ነው።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago

«አንዴ ኢማሙ ማሊክ ሙጥሪፍ ቢን አብዲላህን ጠየቁት፦ ሰዎች ስለ እኔ ምን ይላሉ? አሉት።

እሱም፦«ወዳጅ ያሞግስሃል የጠላ ደግሞ ያንኳስስሃል» አላቸው። እሳቸውም፦ ይህማ ችግር የለውም የሰው ልጆች ባሕሪ ነው። ነገር ግን ሁሉም ሰዎች ምላሳቸው በአንድ ቃል ላይ እንዳይስማማ አላህ ይጠብቀን» አሉት።

«ሁሉም ሰው እንዳያሞግሳቸው በአላህ ተጠበቁ። ነፍሳቸው ድንበር እንዳታልፍና እንዳትሸነግላቸው ፈሩ። ሁሉም ሰው በአንድነት እንዳይወቅሳቸውም በአላህ ተጠበቁ። ምናልባትም ሰዎች ካሏቸው ነገር በነፍሳቸው ውስጥ የሆነ ነገር እንዳይገኝባቸው ስለፈሩ ነበር።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago

«ዱኒያ ራሷ ሳትተውህ በፊት አንተ ራስህ ተዋት፣

«ቀብርህን በሕይወት እያለህ በኸይር ገንባ፣

«ጌታህን ከመገናኘትህ በፊት የእሱን ውዴታ አግኝ፣

« በራስህ ላይ ሳይሰገድብህ በፊት ቀድመህ ስገድ፤
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago

®፦-------
{ بَلِ ٱلۡإِنسَٰنُ عَلَىٰ نَفۡسِهِۦ بَصِيرَةٞ }
«በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል)፡፡ (75/14)

«ሰው በሌለህ ነገር የቱንም ያክል ቢያወድስህና ብትሞገስ ነገ በአኺራህ ሚዛን ላይ ምንም ታክል አይጠቅምህም።

«ሰው ደግሞ በሌለህበትና በማታውቀው ጉዳይ የቱንም ያክል ቢያነውርህና ቢተችህ፣ ቢያንቋሽሽህ ሐሰናትህን ምንም አይጎዳብህም።

«የሰው ልጅ የቱንም ያክል ደግ እና መልካም ጨዋ ቢሆንም እንኳ እሱን የሚጠላው ሰው መኖሩ አይቀሬ ነው። እነዚያ የአሏህ ውድ ነቢያቶች እንኳን ጥቂት ሰዎች ብቻ እንጂ ብዙው ሰው አልወደዳቸውም።

«ሰው ደሞ የቱንም ያክል የክፋትና ጭካኔን ጥግ ቢደርስ እንኳን ከዚሁ ክፋቱ ጋር የሚወደው ሰው አይጠፋም። ፊርዓውን እና ኑምሩድ እንኳን ብዙ ተከታዮችና ወዳጆች ነበራቸው።

«ስለዚህ ሰው በነፍሱ ላይ ብቻ መስካሪ ነው። ነገ አካሎችህ በአንተ ላይ ሲመሰክሩብህ ለምታፍርበት ጉዳይ ብቻ ስለ ራስህ ተጨነቅ እንጂ ዛሬ ሰዎች ስለ አንተ ጉዳይ በሚያወሩት እና ነገ ራሳቸው ሰለሚያፍሩበት ጉዳይ አታስብ።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago

«ጥያቄው ለሸይኽ ሷሊሕ አል ፈውዛን ነው»

«ጠያቂ»፦ ያ ሸይክ ዛሬ ላይ ኩፋሮች ጨረቃ ላይ ወጣን እያሉ ነው እና ይህን ጉዳይ አሕለል-ኪታቦችን «እውነት ብላችሁ አታረጋግጡ አታስተባብሏቸውም ከተባለው ሐዲስ ይካተታልን?

«ሸይኹ»፦ «ምን አለ እንደዚህ ያለውን ጉዳይ ለእነሱ ብትተዋቸው ከቻሉ ይውጡ ምን ይጎዳችኋል? እንዲያውም ሲወጡ ካያችሁ አትመልሷቸው ይውጡ ምድርን ለእኛ ብቻ ቢለቁልን ጥሩ ነው።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago

ረመዷን ⅓ ኛው አበቃ ⅔ኛው ይቀርሃል። ⅓ኛውን በመልካም ዒባዳ ካሳለፍክ በዚሁ ቀጥልበት በከንቱ ካለፈብህና ሐቁን ካጎደልክ ደሞ ጊዜ አለህ ወደ ራስህ ተመለስ። ምክንያቱም ረመዳን በጣት የሚቆጠሩ ትቂት ቀናት ብቻ ናቸው።
{ أَیَّامࣰا مَّعۡدُودَ ٰ⁠تࣲۚ} 2/184
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago

«{إِنَّ ٱلۡحَسَنَٰتِ يُذۡهِبۡنَ ٱلسَّيِّـَٔاتِۚ ذَٰلِكَ ذِكۡرَىٰ لِلذَّٰكِرِينَ }
«መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወግዳሉና፡፡ (11/114)

«ሁሌም ቢኾን ወንጀል ላይ በወደቅክ ጊዜ ጦርነቱን መሸነፍህን እንጂ ከትግል ሜዳው ግን አሁንም እንዳልተባረርክ ለነፍስህ ንገራት። ተስፋ አትቁረጥ! ለድጋሚ ትግል ነፍስህን በውዱዕ እና በረከዓተይን አዘጋጃት።

«ከዚያ በእነዚያው ወንጀል በፈፀሙት ጣቶችህ እስቲግፋርን አድርግባቸው። በዚያችው አሸንፋህ ሐራምን በተመለከተችው ዓይንህ ቁርኣንን ቅራባት። የጌታህንም በር በተውበት እምባ ቆርቁር። ጌታህ ራሱን «መሓሪ" ብሎ የሰየመው ወደ ራሱ መልሶህ ሊምርህ ከጃይ ነውና።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago
« ቁርኣን ውስጥ "አፈላ ተኽቲሙን» የሚል …

« ቁርኣን ውስጥ "አፈላ ተኽቲሙን» የሚል የለም። ይልቁንስ «አፈላ የተደበሩን» «አፈላ ተዕቂሉን» ነው የሚለው።

«ስንቀራ ቶሎ ለማኽተም በሚል ኒያ ብቻ መሯሯጥና የቂርኣቱን ለዛ ማበላሸት ተገቢ አይደለም። ተፍሲሩ ገብቶን ባናስተነትነው እንኳ የቂርኣቱን ሐቅ በአግባቡ ልንጠብቅ ይገባል።

«አንዳንዱ ሰው ቁርኣን ሲቀራ ከመፍጠኑ የተነሳ ለዐረብኛ ተናጋሪ እንኳን ምን እንዳነበበ ለማወቅ በጣም ያዳግታል።

«አሥር ጊዜ በሩጫ ከማኽተም አንድ ጊዜ በተደቡር ማኽተም በላጭ ነው።
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

1 year, 1 month ago

{ مِنۡهُم مَّن قَصَصۡنَا عَلَيۡكَ وَمِنۡهُم مَّن لَّمۡ نَقۡصُصۡ عَلَيۡكَۗ
«ከነቢያትም መካከል ታሪካቸውን ባንተ ላይ የተረክንልህ አልለ፡፡ ከእነርሱም ባንተ ላይ ያልተረክነው አልለ፡፡ (40/78)

«ሰዎች ያንተን ውለታና ችሮታ የደግነትህን ማንነት ሚዛን ቢዘነጉት እንኳ አትዘን! ያንተን ደግነት ጌታህ ብቻ ማወቁ ከማንም በላይ በቂህ ነው።

«ኑሕ"ﷺ" እኛ ስላወቅነው ሚዛኑ ላይ የሚጨምርለት የጤፍ ፍሬ የምታክል ክብደት የለችም።

«እነዚያም አላህ ታሪኮቻቸውን ያልነገረን ነቢያቶችም እኛ ስላላወቅናቸው ከሚዛናቸው ምንም የሚጎድል ቅንጣት ነገር የለም።

«ማንነትህን በአንተና በጌታህ መካከል ብቻ አሳምር። አንተ ማን እንደሆነክ ጌታህ ብቻ ማወቁ በቂህ ነው!
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
https://t.me/AbuMahira55

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ ነው። ሰውነትን አስቀድመው ግለሰብን፣ ህዝብና ሀገርን የሚያከብሩ፣ ሚዛናዊ አመለካከትን ያዳበሩ፣ ከጥላቻ አመለካከት የነፁ ኢትዮጵያውያን ቤት ነው።

ያግኙን +251913134524

Last updated 1 month, 2 weeks ago

ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም

- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት

ለማስታወቂያ ስራ  --> @MKHI7

Last updated 1 month, 2 weeks ago

BoA Social media links
@ https://www.facebook.com/BoAeth
@ https://www.instagram.com/abyssinia_bank
@ https://www.linkedin.com/company/bankofabyssinia/
@ https://twitter.com/abyssiniabank
@BOA_ATM_bot

Last updated 3 weeks, 5 days ago