Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago
¶"የረሱል"ﷺ" ልጆች"¶
1} አል ቃሲም፦ በዚህ ልጃቸው ኩኒያ አበል- ቃሲም ተብለው ይጠሩ ነበር። ከነብይነት በፊት የተወለደ ነው። የሁለት አመት ልጅ ሲሆን ወደ ማይቀረው አኺራ ሂዷል።
2} ዐብደሏህ፦ አጥ-ጠይብ አጥ-ጧሒርም ይባላል። ምክንያቱ ከነብዩ ﷺ የነብይነት ማዕረግ በኋላ ስለተወለደ ነው። አጥ-ጠይብ አጥ-ጧሒር የተባለው ከዐብደላህ ሌላ ነውም ተብሏል። { ትክክለኛው የመጀመሪያው ነው}
3) ኢብራሒም፦ በስምንተኛው አመት በመዲና ነው የተወለደው። በአስረኛው አመት ሞቷል። የዱኒያ ቆይታው የ17 ወይም የ18 ወር ብቻ ነበር።
®"ረሱል"ﷺ" የነበራቸው ሴት ልጆች አራት ናቸው።
1} ዘይነብ(ረ.ዓ) ፦ የአክስቷ ልጅ የሆነው አቡል ዓስ ኢብኑ ረቢዓ ያገባት ናት።
2} ፋጢማ(ረ.ዓ)፦ የታላቁ ሰሓብይ ዓሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረ.ዓ) ባለቤት ናት።
3} ሩቅያ (ረ.ዓ)፦ የዑስማን ኢብኑ አፋን ሚስት ናት።
4} ኡሙ ኩልሱም (ረ.ዓ) ፦ እሷም የዑስማን ኢብኑ አፋን (ረዓ) ሚስት ናት። መጀመሪያ ሩቅያን አገቡ። ከዚያ ሩቅያ ስትሞትባቸው ኡሙ ኩልሱምን አገቡ። ለዚህም ነው ዑስማን ዛ ኑረይን የተባሉት።
©"የረሱል"ﷺ" ሴት ልጆች ያለ ኺላፍ አራት ናቸው። ወንዶቹ ደግሞ በሶሒሕ ሦስት ናቸው።
¶ተሕዚብ ሢራህ ኢብኑ ሒሻም¶
«ዛሬ ላይ ስግብግብነት ሁሉን ነገር እንድናመልክ አድርጎናል። "አላህን"ﷻ" ዱኒያን እንዲሰጣችሁ ብቻ በማሰብ አታምልኩት። ይልቅ! እናንተንም ስራችሁንም እንዲወድላችሁ ብቻ በኢኽላስ አምልኩት። እሱ ከወደዳችሁ ቸር ነው ሁሉንም ነገር ሳትጠይቁት ይሰጣችኋል።
አላህን"ﷻ"*ስትለምኑ ሁሉም ነገር ገር እና ቀላል የሆነ ሕይወት እንዲሰጣችሁ አትለምኑት። ዱኒያ የፈተና መድረክ ናትና መቃረኑ አይቀርም። ይልቅ! የዱኒያን ጣጣዋን የምትጋፈጡበትን ብርታት እና ኃይል እንዲሰጣችሁ ለምኑት።*
https://t.me/AbuMahira55
«"እስኪ አሁን ያለህበትን ሁኔታ በደንብ ተመልከት!! ለሞትና ቀብርህ ተስማሚ የሆነ ጥሩ ሁኔታ ላይ ከሆንክ በዚያው ቀጥልበት። ነገር ግን ለሞትና ቀብር ዝግጁ ካልሆነ በመጥፎ ሁኔታ ላይ ከሆንክ ከዚህ ካለህበት አሕዋል ወደ አሏህ ተመለስ። ለሞትህና ለቀብርህ ወደ መዘጋጀትህ ተመለስ"» {ኢብኑል ጀውዚይ ረሒ)https://t.me/AbuMahira55
”ጀልባ በግዙፍ ባሕር ላይ ስትንሳፈፍ በዙሪያዋ ውሃ ስለ አካበባት ብቻ አትሰምጥም። ነገር ግን ውሃው ወደ ውስጥ ከገባ ትሰጥማለች። በዙሪያህ የሚከናወኑ ነገሮች ሁሉ ወደ ውስጥህ እንዲገቡ አትፍቀድ። ጓዝህ በዝቶ ትሰጥማለህ”።
https://t.me/AbuMahira55
"ሶሻል ሚዲያ አሁን ላይ ጃሂሉ ዓሊሙን የሚከራከርበትና የሚዘልፍበት ዶክተሩን በሽተኛው የሚያናንቅበትና የሚያዋርድበትን መድረክ የፈጠረ ነው። ዒልምና ዓሊም ቦታ አጥተው ዋልጌና አላዋቂዎች ነግሰው ዓለም ሁሉ ተከታያቸው ሆነ። ይህ የመጨረሻው ዘመን ፍፃሜ ምልክት ነው።
https://t.me/AbuMahira55
®፦ "ተዝኪራ"፦..........
*"{ هَـٰذَا مَا تُوعَدُونَ لِكُلِّ أَوَّابٍ حَفِیظࣲ }
[Surah Qāf: 32]
«ይህ ወደ አላህ "ተመላሽና" (ሕግጋቱን) ጠባቂ ለኾነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡
"አዋብ" "ተመላሽ" ማለት "ወደ አሏህ አብዝቶ ተውበት የሚያደርግ ማለት ነው። ኢማሙል- በገዊ ረሒመሁሏህ እንደሚሉት "አዋብ" ማለት ፦- ኃጢያት ላይ የሚወድቅ ከዚያም ወደ ጌታው በተውባ የሚመለስ አሁንም ኃጢያት ላይ የሚወድቅ እንደገና ከአላህ እዝነት ተስፋ ሳይቆርጥ ወደ ጌታው በተውባ የሚመለስ..... ማለት ነው።
"የአንቀፁ አውደ ፍሰትም የሚያስረዳን፦
"ብዙ ወንጀል ባይኖር ኖሮ ብዙ ተውበትም ባልነበረ ነበር" ነው።
"ወንጀልህን ከጌታህ እዝነት ጋር አነጻጽረህ አታግዝፈው! እሱ አር-ረሕማን ነው። እንዲሁም በተቃራኒው ወንጀልህን ከቅጣቱ የሚድን ቀላል ነገር አድርገህ አትመልከተው። እርሱ ቅጣተ- ብርቱ አሸናፊና የብርቱ ኃይል ባለቤት ነው።
"ሐያትህን "ቅጣቱን በመፍራት እና እዝነቱን በመከጀል መካከለኛ ሁን።
"ሰይጣንም በወንጀልህ ግዝፈትና ክፋት በሀፍረት ከጌታህ እዝነት ተስፋ አስቆርጦህ ወደ ጌታህ እንዳትመለስ አያድርግህ።
"ራሱን "መኃሪ ይቅር ባይ" ብሎ የሰየመው ጌታህ እኛ ሲበዛ ወንጀለኞች ስለሆንና እሱም ሲበዛም አብዝቶም ይቅር በማለቱ ነው።
"በቀን ሺ ጊዜ እንኳ በኃጥያት ነፍስህን ብትበድል በቀን ሺ ጊዜ የጌታህን ምህረት ከጅለህ ወደ እርሱ ከመመለስ አትቦዝን።
https://t.me/AbuMahira55
{ وَقَاسَمَهُمَآ إِنِّي لَكُمَا لَمِنَ ٱلنَّٰصِحِينَ }
«እኔ ለእናንተ በእርግጥ መልካም መካሪያችሁ ነኝ» ሲልም አማለላቸው፡፡ (7/21)
«ለአንተ አዛኝ እና ጥሩ መካሪ መስሎ ለቀረበህ ሁሉ ሙሉ እምነትህን አትስጠው ምንም ማረጋገጫ የለህም።
«የምክርን ተንኮል ልባስማ ኢብሊስም ተላብሶታል። አደምን" ያሳሳተውና ከጀነት ያስባረረው ጥሩ አዛኝ መካሪ መስሎ ነውና።
«ኢብሊስ ለማታለል ሲመክር «የአመጽዋን ዛፍ» «የዘላለምን ሕይወት የምታኖር» ብሎ ስያሜዋን ቀየራት። ዛሬም በአታላዩ ምክሩ ሲያታልለን የነገሮችን ትክክለኛ ስያሜ ቀይሯቸዋል።
«አስካሪ መጠጥን፦ የነፍስ እርካታ የደስታ ምንጭ ሕሴት አድርጎ ሰይሞታል።
«ዝሙትና እርቃንነትን፦ ዘመናዊነትና የሥልጣኔ አርማ አድርጎ ሰይሞልናል።
«ጥሩ መካሪ የመሰለህ ሁሉ የጥሩ ልብ ባለቤት መሆን አይችልም። የነገሮች ስያሜና አቀራረብ የቱንም ያክል ቢለወጥም ትክክለኛ ባሕሪያቸውን ግን በፍጹም አይቀይርም።
?????????
https://t.me/AbuMahira55
«{ عَسَىٰ رَبُّنَآ أَن يُبۡدِلَنَا خَيۡرٗا مِّنۡهَآ}
«ጌታችን ከእርሷ የተሻለን ነገር ሊለውጠን ይከጀላል፡፡ (68/32)
«በሕይወትህ ባመለጡህ መልካም አጋጣሚዎች ሁሉ በቁጭት የተቃጠለችዋን ቀልብህን በዚህች በጌታህ ቅዱስ ቃል አፅናናት።
«የምትወደውን መልካም ሥራህን ባጣህ ጊዜ፣ የልበ-እምነት ወዳጅ ጓደኛህን መካከል መንገድ ላይ ከእጅህ ባመለጠህ ጊዜ፣ የንፍቅና ፊትን ሰጥቶህ ክቡር ደግ ሰው ነው ብለህ ባመንከውና ከጠበቅከው ተቃርኖ ባዶነቱን አሳይቶህ ባረጋገጥክም ጊዜ፣ በትርፍ ምኞት ተስፋ ሰንቀህ ባዶ በቀረህ ጊዜ.........
«ሁሉም አላህ ካንተ የወሰደው ነገር ሁሉ ሒክማ አለው ለሱ ብቻ ተወው። ለአንተ የተወልህ ነገር ሁሉ ደግሞ እዝነቱ ነው። በወሰደብህ ነገር ሒክማው ከተገለጸልህና ከደረስክበት አመስግን። ሒክማውን ካልደረስክበት ደግሞ መልካም ትግስትን ታገሥ።
«ነገሩ ሲከሰት የቱንም ያክል ልብህን ቢያቆስልህ እንኳ አብሽር የአላህ ቀደር ሁሉም ለአንተ ኸይር ብቻ ነው።
?????????
https://t.me/AbuMahira55
Welcome To Amharic films Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 8 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 3 weeks, 1 day ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
? ዝውውሮች
? ውጤቶች
? የጨዋታ ፕሮግራሞች
? እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
? ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 months, 2 weeks ago