Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ወድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ባለፉት የተወሰኑ ወራት ውስጥ ትንሽ ከበድ ያለ ሕመም ገጥሞኝ ስታከም ነበር። በዚህም አንዳንድ ሥራዎች ላይ መደራረብ ፈጥሮብኝ እንደማስበው ትምህርቶች በሥዕላት ዙርያ መልቀቅ አልቻልኩም።
እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ በቀጣይ ከተለያዩ ወንድምና እህቶች በቪድዮም ትምህርት ይሁን አስተያየቶች ስለቀረቡልኝ ከጽሑፍ በተጨማሪ በቪድዮ በቲክቶክ እና ዩቲዩብ ላይ እመጣለሁ።
ከዚህ በፊት በነበረው መጠይቅ ላይም በስልክ እና በሜሴጅ እንደመረጣችሁት እነዚያን ርእሶች ይዤ የምመጣ ይሆናል።
ከወዲሁ ላሳውቅ የምፈልገው በቀጣይ የሚቀርቡ ትምህርቶች ላይ በመረጃ ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ እንጂ ግለሰብ ወይም ተቋም ላይ ያለነጣጠረ መሆኑ ነው።
ይሁን እንጂ ሰው እንዳይከፋው እያልኩኝ ላለፉት 10 ዓመታት ጀምሮ ዝም ያለኩትና ሳዝንባቸው የነበሩ ጉዳዮችን በይፋ የሚወጡ ይሆናል። ለቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ቀኖና ብናደላ ይገባናል።
ስለዚህ ወገባችን ታጥቀን ለመማርና ለውጥ ለማምጣት እንዘጋጅ። አስተያየትም በጨዋነት የምንለዋወጥ ይሆናል።
መልካም የሠሩ ይመሰገናሉ የሚያበላሹ እንዲያስተካከሉ በመረጃ ተደግፈን እናግዛለን።
እምቢ ብለው ግን በማናለብኝነት የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለሚንዱ ግን በመረጃ የሳሉት ሥዕል ስህተትነት ምእመናን እንዲያውቁና እንዳይጠቀሙ እናስተምራለን።
ተሐድሶን የምንከላከለው በመሞዳሞድ ሳይሆን ፊት ለፊት ተጋፍጦ ለቤተ ክርስቲያን ትውፊት በመቆም ነው።
የቅዱስ ዮሐንስ፣ የቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊና የአቡነ መብዓ ጽዮን በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።
በሠዓሊ ኃይለማርያም ሽመልስ (@ethioicons @shihaile)
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን፡፡
እንኳን ለቅድስት አርሴማና ለተከታዮቿ ሰማዕታት የፍልሰትና የቅዳሴ ቤት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የቅድስት አርሴማ ገድልና ታሪኳን ጠብቆ ጥንታዊ የተሳሉ ሥዕሎችን መሠረት በማድረግ የተሣለ ሥዕል ትርጉም ከአጭር የሰማዕቷ ተጋድሎ ጋር ከስር ቀርቧል።
ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::
ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::
ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::
ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::
*ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::
ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ ክርስቲያኖችን ወደ አርማንያ ተሰደዱ። በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ።
ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው። ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት።
ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::
አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::
+ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው። የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ።
የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን-ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::
ቅዱስ ጎርጎርዮስም ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ፈወሳቸው:: በዚህም ድርጣድስም አምኖ እህቱን ጨምሮ ከነቤተሰቡ ክርስቲያን ሆነ።
ቅዱስ ድርጣድስም አርማንያም በ301 ዓ.ም. የመጀመሪያዋ የክርስቲያን ሀገር እንድትሆን በአዋጅ አስነገረ። ቅዱስ ጎርጎርዮስንም የአርመን ፓትርያርክ እንዲሆን ፈቀደ። አብያተ ጣዖታትንም አዘግቶ በምትካቸው አብያተ ክርስቲያናትን አሳነጸ።
ቅዱስ ጎርጎርዮስም ተበትኖ የነበረውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ ቤተ ክርስቲያን አሳንጾ በታኅሳስ 6 በክብር አፈለሰው። ያሳረፈበት ስፍራም በራዕይ እግዚአብሔር ገልጦለት ነበር።
ከዚህም በኋላ በአርማንያ እየተዟዟረ ወንጌልን እየሰበከ ክርስቲያኖችን ወደ ጌታ በረት ጨመረ። በዚህም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ከሳቴ ብርሃን በማለት በአርመኖች ዘንድ ይጠራል።
ቅዱስ ድርጣድስም ስለ እምነትም ከጣዖት አምላኪዎች ጋር ከፍተኛ ትግል አድርጓል። በዚህም በ11ኛው ሰዓት የመጣው ንጉሥ በአርመን ቤተ ክርስቲያን <<ታላቁ ቅዱስ ድርጣድስ ሣልሳዊ|Tiridates III of Armenia >> በማለት የቅድስና ማእረግ ተሰጥቶ በታላቅ ክብር ይዘከራል። የሚታሰበውም በበዓለ ሃምሳ ከአምስተኛ እሑድ ቀጥሎ ባለው ቅዳሜ ላይ ነው።
ዳግመኛም በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች።
ከላይ የተጠቀሱትን ታሪኮች መሠረት በማድረግ የሰማዕቷን ቅድስት አርሴማ ሥዕል በሠዓሊ ኃይለማርያም ሽመልስ (@ethioicons @shihaile) ተስሏል።
የተሣለው ለደብረ ወርቅ ዋዱ ቅድስት ቁስቋም ቤተ ክርስቲያን በ2017ዓ.ም. ነው። አሣሣሉንም ስንመለከት ከቅድስት አርሴማ ጋር በአንድነት ቅድስት አጋታ እመ ምኔት(ጋያኔ)፣ ማኅበረ ደናግላን ሰማዕት፣ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ፓትርያርክ፣ ቅዱስ ድርጣድስ እና ቅዱስ ራጉኤልን በመጨመር ነው። የሥዕሉ ምስጢር ከስር ቀርቧል።
መልአኩ ከላይ መሆኑ ከፍ ያለና ሰማያዊ የሰማዕትነት አክሊልን እንደተቀበለች ለማመልከት ነው። ይህ ደግሞ በጣና ገዳማት መልአኩ ባለበት ስፍራ አክሊል ሲወርድላት ከተሳለው ሥዕል መነሻ በማድረግ የተሣለ ነው።
በስተግራ እመ ምኔት ቅድስት አጋታ ክብሯን እንድትጠብቅ ስትነግራት ይታያል። በስንክሳር ላይም የተመዘገበውን ምክሯን በመልእክት መልኩ ይዛ ትታያለች።
ከቅድስት አጋታ አጠገብ የእጅ ስራ አብራ የነበረች ደንግል ተስላለች። ይህንን የእጅ ስራ እየሸጡ ለእለት ምግብ ይውሉ እንደነበር ስንክሳሩ እንደሚገልጸው። ይህንንም ለመጠቆም በእጇ ብልቃጥ ይዛ ትታያለች።
በተጨማሪ ሌሎች ደናግል ሰማዕታት አብረው ይታያሉ።
በስተቀኝ በኩል ደግሞ ቅዱስ ጎርገርዮስ የፓትርያርክ ቆብ አድርጎና ልብሰ ተክህኖ ለብሶ እና ወንጌልን ይዞ ይታያል። ይህም ወንጌል በሀገረ አርማንያ ያዳረሰ መሆኑን ያጠይቃል።
ቅዱስ ድርጣድስ ደግሞ ዘውድ አድርጎ በእጁ ዓለምን ይዞ ይታያል። ይህም ንግሥናውን እና በግዛቱ ወንጌል እንዲስፋፋ ማድረጉን ያመለክታል።
ከእርሱ አጠገብ ያሉት ደግሞ ከአርሴማ ጋር አብረው የነበሩ ወንድ ሰማዕታት ይወክላሉ።
ከጀርባ ደግሞ የምንመለከተው ቤተ ክርስቲያን በንጉሥ ድርጣድስ ፈቃድና በቅዱስ ጎርጎርዮስ አማካኝነት የታነጸው ሕንጻን ይወክላል። ይህች ቤተክርስቲያን ደግሞ የቅድስት አርሴማ፣ ቅድስት አጋታና የደናግል ሰማዕታት ቅዱስ አጽም ማረፊያን ትወክላለች።
በአጠቃላይ በስተግራ ሰማዕትነቷን በስተቀኝ ደግሞ ቅዳሴ ቤቷን በማሰብ ተሥሏል። ይህንንም ለመግለጽ አርኬ በቀኝ እና በግራ ተጽፎ ይነበባል።
ምንጭ
Welcome To Amharic films
Best Place To find Amharic Movies
አዳዲስ እና የድሮ አማርኛ ፊልሞችን እና አማርኛ ተከታታይ ድራማዎችን ለማግኝት ቻናላችንን Join ይበሉ ።
Share:- @Amharic_Films
ለማስታወቂያ - @Abusheymc & @Alpha6249
Buy ads: https://telega.io/c/Amharic_films
Last updated 1 year, 6 months ago
ስለ መድፈኞቹ የሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የትም መሄድ አያስፈልግም
- የዝዉዉር ዜና
- የአሰልጣኞች አስተያየት
- የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
- ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት
ለማስታወቂያ ስራ --> @Aymu_xo
Last updated 1 month ago
╔╦╦═╦╔╦═╦═╦═╗
║ እንኳን ደህና መጡ | |
╚══╩═╩═╩╩╩╩═╝
➟ እንኳን ወደ ትልቁ የሊቨርፑል ( መርሲሳይድ) ቻናል በደህና መጡ ።
◉ ስለ ሊቨርፑል ◉
🔴 ዝውውሮች
🔴 ውጤቶች
🔴 የጨዋታ ፕሮግራሞች
🔴 እንዲሁም የተጨዋቾች ግለ ታሪክ
🔴 ጨዋታዎችን በቀጥታ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።
Owner:- @hackersolo0⭐️
Last updated 2 weeks ago